Translate

Tuesday, January 14, 2014

ማገዶ!

ማገዶ!


… አንተ ምን አለብህ ሁልጊዜም ነዲድ ነህ
ለኋላህ ተከታይ ቋያና ሀዲድ ነህ።
ትኩስነት ዕዳ ….
የማገዶ ፍዳ ….
 ከሥርጉተ ሥላሴ
‹‹ከእስረኞች ሁሉ ህገ-መንግስታዊ መብቴ ተጥሶ ዘመድ አዝማድ እና ጓደኛ እንዳይጠይቀኝ የተደረኩት እኔ ነኝ››እውነት ለመናገር ከዬካቲት በፊት በአጭር ጊዜ ላልመለስ ወስኜ ነበር። ብቻ እንዲህ ሆነላችሁ … ተክዤ ቆዬሁ። አፍጥጬም አዬሁት። ባለፉት ሳምንታት ዘሀበሻ ላይ የአንድነት ልዩ ጉባኤ ውጤትን ጀመርኩት። መጀመር ነበረብኝና ውስጤን አናጋርኩት – የግድ። የአዲሱን የአንድነት ልዩ ጉባኤ ተመራጮችን ዝርዝር አዬሁት። አቶ ሸፍጠኛው ሂደት …. አንተ ምን አለብህ ቀልድ። ዬደላህ! መለስህ መላስህ ግራጫ ያሰኛኃል …. ዛሬም አዲስ ትወና ይዘህ ከች … አታካች።
እርግጥ በሂደቱ  የቀድሞ የአንድነትምክትል ሊቀመንበር እሩቅ አሳቢውእስረኛው አቶ አንዱአለም አራጌ በጣም እንደ ተደሰተ ዘሀበሻ ላይም አንብቢያለሁ። በሌላ በኩልም ትናንትና በ07.01.2014 ዝርዝር መረጃ ስለመርጫው ሂደት „ከቃሌ ሩም“ አዳምጫለሁ።
የቃሌ ሩም ከአቶ ሃብታሙ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ እንደ አዳመጥኩት ከሆነ ምርጫው ዲሞክራሲ እንደ ነበረ ብቻ ሳይሆን አዲሱ አመራር በቃሊቲ እስር ቤት ከአቶ አንዱአለም አራጌ ጋር የነበረውን ቆይታ ምን ይመስል እንደነበርም በዝርዝር ተገንዝቤያለሁ። ያንገበገበኝ ጥቄ ይነሳል በማለት ጓጉቼም ነበር። የሆነ ሆኖ „አቶ አንዱአለም አራጌ  ዘግይቶ ሊታይ የሚገባው የአማራሩ ጥንካሬ ከ15 ዓመት በፊት መቅደሙ እንደ አስደሰተው ከደቡብ አፍሪካ የነፃነት ትግል ጋር በንጽጽር ሲያው በጣምም እንደተደነቀ ተስፋም እንደጣለበት“ ነበር አቶ ሃብታሙ የገለጹት። መልካም ነው …
ይህ የበለጠ የገለጸልኝ ነገር ቢኖር የአቶ አንዱአለምን ቅንነትና አውንታዊ ዕይታአመላክቶኛል። በሌላ በኩል ግን ይህ አዲስ መዋቅር ብቻውን የጥንካሬ መግለጫ ሊሆን ከቻላ ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ እስር ቤት እያለች መሰሉ ተከነውኖ ስለነበር እኔ እመደነቀብት ምንም ጉዳይ የለም።  …. ለአድናቆት ወይንም ተስፋን በሙሉ ጥግ ለመስጠት ነገን መጠበቄ ግን ግድ ይላል።
በነገራችን ላይ በትናንቱ ቃለ ምልለስ የተደስትኩበት አቶ ኃብታሙ ከወያኔ ጋር በነበረቸው አጭር የቤተኝነት የቆይታ ጊዜ „ በድዬ ከሆነ ይቅርታ የመጠዬቅ ሞራል አለኝ“ ማለታቸው አስተማሪ ነበር። ወጣትነት ሁሉንም ሞክሮ ማዬት በመሆኑ፤ ወጣቱ  በአጭር ጊዜ ውስጥ የወያኔን መሰሪ ሀገርና ህዝብን የመግደል ሴራ መርምረው ይህን መሰል እርምጃ መውስዳቸው አብነት ነው ለእኔ። በቀጣይ የትግል ሂደትም በሚያሳዩት የነቃ ጉልህ ተሳትፎ ውስጣቸውን አንጥሮ ማሳዬት የሚችሉ ከሆነ መልካም ነው። እንዲህ ከወያኔ እጅ እያመለጡ የሚመጡትን ወጣቶች  በአግባቡ ይዞ ሞራላቸውንም ጠብቆ የነፃነት ትግሉ ጽኑ ቤተኛ ማደረግ የሁላችንም ግዴታ ነው። ወጣትነት ብዙ ባህሪያት በህብር የሚገኝበት በመሆኑ በጥንቃቄ የአያዛዝ ጥበብን ይጠይቃል።
ሰሞኑን ስተኛ መገላበጥ አበዛሁ። ለምን? … ቀኑን አላስታውስም ብቻ „ጠርዝ ላይ ያለ ስጋቴ“ የሚል አንድ ጹሑፍ በአደራ ተርጓሚው፤ በቀጥተኛው፤ በግልጹና በግንባር ሥጋው ….  በወጠት አንዱአለም አራጌ ዙሪያ የሆነ ነገር ብዬ ዘሃበሻም አውጥቶልኝ ነበር። ጹሑፌ አጭር ቆይታ ብቻ ነበር የነበረው። የፈራሁት እንሆ ደረሰ።
እኔ እንደሚገባኝ በአደራ ጠበቂው  በአቶ አንዱዓለም አራጌ ውስጥ በፍጹም ሁኔታ  አንድነት ፓርቲው አለ። በአንድነት ማዕከላዊ አመራር ውስጥ አቶ አንዱአለም ግን……. ቀደም ባለው ጊዜም በክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ ውስጥ በፍጹም ሁኔታ አንድነት ነበር።  በአንድነት ማዕከላዊ አመራር ውስጥ  ወ/ት ብርቱካን ሜዴቅሳ ግን  … በተመሳሳይ ብቃት፤ በሙሉዑ ተቀባይነት፤ የህዝብ ፍቅር የነበራቸው ሁለቱም የአንድነት ወጣቶች የነፃነት ቀንበጦች ላይ አንድነት የወስደው ተመሳሳይ እርምጃ ግን አልተመቸኝም።- አንጀቴንም አቃጠለው። ይህቺ እናት ሀገር ኢትዮጵያ ወጣቶቻና ሴት ልጆቿ መቼ ይሆንቦታቸውን አግኝተው በብቃታቸው፤ በእርግጠኝነታቸው፤ በመሆን መቻላቸው፤ በሙቅና ትኩስ ፍላጎታቸው ትራስነት ከዚህ የመከራ ፍዳ የሚታደጉዋት።ወጣትነት እኮ ገዢ መሬት ላይ ያለ አጥቂ ሰራዊት ማለት ነበር። ወኔውም ልቡም ላለው። ማሸነፍ ማለት ወጣትነት ነው ለ እኔ። በመንፈስም በአካልም።
…. ዘመኑም ይሄዳል
እየለቀሙ ማፈስስ … እያፈሰሱ መልቀም …
ዕጣውም ይፈሳል – ጣጣው ይጎፍራል …..
ወጣቶቹ ለሚከፍሉት መስዋዕትን መታጋያ መድረካቸውን የሚያፈናቅል ተግባር ፊታውራሪ ሂደት እስር ላይ እያሉ ይፈጸማል። ይህ ጥቁር የታሪካችን ጠበሳ በወጣት የፖለቲካ መሪዎቻችን ላይ የተሰነዘረ የተስፋችን ጥቃት ነው። ያማል።  የሚጎረበጥ – የጓጎለ ጎብዳዳ – ገጠመኝ። ዛሬ ላይ ሆነን የሰሞኑን ጉሽ ነገር ስንለካ፤ ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ ከኃላፊነቷ ላይ ሆና ብትሆን ኖሮ፤ ሚዛን ያለው ምላሽ በተሰጠው ነበር። ኢትዮጵያዊነትን በፈተነው ጠቀራማ ዘመቻ ላይ የግንባር ቀደም ተዋናይ በመሆን የድርሻዋን ትውጣ እንደ ነበረ አልጠራጠረም። ግልጽ አቋምም ትወስድ ነበር። የጌጣችን ፈርጥ ሚስጢር እሷ ውስጥ ነበርና።  ምክንያቱም ከነፃነት በላይ ትርጉም ያለው መንፈስ ሊኖር ከቶ አይችልም። የሰብዕናና የማንነት ምንዛሬ ህልውና ነጻነት!። ነፃነት ያለው ህዝብ በራስ የመተማመን መንፈሱ ሙሉዑ ነው። የትም ቦታ፤ በዬትኛውም ጊዜ፤ ማናቸውንም ፈተና የሞቋቋምና በእራስ እንደ ራስ ሆኖ የሚያቆም ዓውራ እሴቱ ነፃነት ብቻ ነውና። ስለሆነም  ለአንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ማናቸውም ፈተና ከሀገሩ ሉዕላዊነት በታች እንጂ በላይ ሊሆን ከቶ አይችልም። ሀገር አለኝ ማለት የግጥምጥሞሽ ቃል አይደለም። የመኖር አለመኖር ህግ እንጂ ….
በሌላ ሀገር ቅኛ አለመገዛት እኮ ቃላት ሊገልጸው – ሊተነትነው – ሊፈትሽው የማይችል ረቂቅ መንፈስ ነው። አብነቱ አይደለም ለእኛ ዓለምን የናኘ ብቻ ሳይሆን አፍሪካን ለነፃነት ያበቃ በኽረ ጉዳይ ነውና። ከዚህ አንፃር የክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ ከፖለቲካ መድረክነት መገለል ጉዳቱ ለዛሬም – ለነገም ነው …. ሚስጢሩ ለሚገለጽላቸው …. በሌላ በኩል ትውልድ ከቶውንም ሊተካው የማይችለው የአፍሪካ የቅኔ ልዑሉ፣ ፓን እፍሪካኒስቱ፣ የሃያሲው፤ የመምህሩ፤ የጸሐፊው፤ የገጣሚው  የብላቴ ጌታ ሎሬት  ጸጋዬ ገ/መድህን በህይወት አለመኖርም … ሌላው የልባችን ውጋት ነው።  አጅሬ ቢኖር፣ እሱ ቢኖር እንዲህ ያለ ታሪክን ጨለመ የሚያለብስ ዘመቻ፤ ሆነ ድፍረትም ፈጽሞ አይታሰብም ነበር። በአንዲት ዘላላ ቅኔዊ ስንኝ አመጣጥኖ፤ አቻችሎ ቀጥ ያደርገው ነበር።የብዕሩ ደም ፈውስና መዳህኒት ነበርና … እሱም  እንደ ብርቴ የኢትዮጵዊነት ልዩ ፈርጥ ቅመም ነበረውና አምላከ – ቅብዕ።
አሁን ወደ ቀደመው እንደ አቨው … አዎን! ወያኔ በህዝባዊ ፍቅር ተወዳድረው ያሸንፉኛል የሚላቸውን ወጣት የነፃነት አርበኞችን በነፃነት ትግሉ ማዕዶት አስርጎ ባስገባቸው አባሎቹ አማካኝነት እዬለቀመ ያሰራል፤ አቶ ሂደት ደግሞ መንገዱን ተከትሎ መስዋዕትነታቸውን አፈር ድሜ አስግጦ፤ ለዘር ሳያበቃ  የበሬ ግንባር የምታክል የጉልማ መሬት ሳያስቀር ለሌላ አዲስ ሂደት አዲስ አመራር ይመርጣል፤ ይሾማል …. ይሸልማል፤ የድርጅቱ ዋነኛ ዓላማ ተስፋ — ቆራጭነትን ሰንቆ እሱን ያዬ፤ እሷን ያያ እያለ መቀጣጫ ያደርጋል … ቲያትሩ … ድራማው ይሄው ነው የፍታውራሪ ሂደት  … ቁስለት!
„አንዱአለም የሰላም ታጋይ እንጂ አሸባሪ አይደለም“ በዬሀገሮች የተካሄዱ ሰላማዊ ሰልፎች መሪ መፈክር ነበር። „መንገድ በስሙ ይሰዬም“ ሌላው የህዝበ – ጉባኤ ድምጽ ነበር …. በቃ ይሄው ነው?  …  ማገዶነት ብቻ። የሰላማዊ ትግልን የሚያስከፍለውን መስዋዕትነት የሚከፍሉ ጀግኖች አሉን፤“ እያሉ በመሰዋዕትነቱ እምነት ጥለው ትግሉን የሚያግዙ፣ የሚረዱም ወንድሞችና እህቶች በርካታ ናቸው። ምልክታቸውን አንዱአለምን አድርገው።  … ከአዲሱ መጸሐፉ ውስጥም ጥቅሶችን እያወጡ መንገዳችን ይሄ ነው የሚሉም ወገኖች አሉ። አሁን ይህን መርዶ ሲሰሙ ከቶ ምን ብለው ይሆን?  አቶ ሂደት ካስመረጠው አዲሱ ዝርዝር ውስጥ እስረኛው፣ የሰላም መርህ አራማጁ እሩቅ አሳቢው አቶ አንዱአለም የለም። አይገርምም?! በውስጡ እያለ በሩን አቶ ሂደት ቀረቀረበት። ….  እና ይሄው ነው በቃ?! … ድራማው ይህ ነው … ማለት ነው። አቶ ሂደት በቦታው ሌላ ሰው አስመርጦበታል።ቢፈታ የተሰዋለትን ፓርቲውን ትቶ ከቶ ዬት እንዲሄድ ነው የተፈረደበት …ስቃይ – የመንፈስ!
መቼም ይህ ሂድት የሚባል አንጀተ ደንዳና ርህራሄ የለውም … ለሁለት ምክትል ቦታ ከነበረው ምን አለ አንዱ ቦታ እንኳን ለመንፈሱ ደህንነት፤ ለፈኖቹ ሲል እንኳን ክፍት አድርጎ ቢጠብቀው … ለምን ሁለት አስፈላጊ እንደሆነ ባይገባኝም …. መቼም አቶ ሂደት መተዛዘን ነግ ለእኔ ቢል ጥሩ ነበር።
ሌላው በአቶ ሂደት የተገረምኩት ደግሞ የአዲሱ የአንድነት አመራር አካላት ሙህራንና በእድሜያቸውም ከ60% በላይ በወጣቶች ተገነባ የሚባለው ጉድ ነው። …. የትኞቹ ናቸው ወጣቶች ፕሬዚዳንት የሆኑት? …. ቲያትር ነው … ። እርግጥ ነው እኔም እማምንበት አንድ መርህ አለ …. ወጣትና ነበር የፖለቲካ ተመራጮች የሂደት ተከታታይነት ማደረግ ይጠበቃል …. እርሾ።
… ይህም ቢሆን በኢጂነር ግዛቸው ከነባሩ አመራር ስላልነበሩ ክፍተት አለው። የሆነ ሆኖ አሁንም እዛው ከአዛውንታት ላይ ነው ያለው የመወሰን፤ የመምራት ቁልፉ …. የዛሬው ትውልድ እጅግ የቀደመና የሰለጠነ ሆኖ ሳለ ግን ተፈራ …. ለምን?! አባቴ መዳህኒተ ዓለም ይወቀው። ….ተከታዩ ካቴና የሚጠብቀው ደግሞ ማን ይሆን?  …. አቶ ሂደት  ልጆቹን ለካቴና እያመቻቸ ያቀብልና ለአዲስ ትወና ይዘጋጃል …. መስራች – ልዩ – ማሟያ እያለ …
ደጃችዝማች ሂደት  ካቴና ላይ ለሚገኙ አካሎቹ መንፈስ ቢያንስ ተቆርቋሪ ቢሆን መልካም ነው። ለቤተሰቦቹም ይሰብ። „ነግረንህ ነበር አስታውሰንህ ነበር“ የሚሉ አይጠፉም እንዲህ አይነት ተርጓሚ አጥብቆ የሚሻ ገጠመኝ ሲታይ። ኃላፊነት ያለው ተግባር ቢፈጽም መልካም ነው። የአሁኑ ሆናል። አይተናል ሰምተናል … ይብቃኝ መሰል የተቋጠረን መግል ለማፍሰስ፤
እርገት። የቀድሞው የአንድነት ሊቀመንበር ዶር/ ነጋሶ ጊዳዳ በቃኝ ማለታቸውን በአውንታዊነትና በቅንነት ማዬት ይገባል። በወያኔ ሥርዓት ውስጥ የነባራቸውን የሥም ቦታ በፈቃዳቸው ለቀቁ፤ በአንድ ወቅት የኢትዮጵያን ህዝብም ይቅርታ ጠዬቁ፤ ከጎጥ አስተሳሰብ ወጥትው የአንድነት ኃይሉ ቤተሰብ ሆኑ፤ እኔኑ እሰሩኝ ወጣቶቼን ልቀቁ ብለው የትክክለኛ እረኝነትን አብነትም አሳዩን። አሁንም ከዕድሚያቸው ጋር ሊመጥን የሚችል እርምጃ ወሰዱ። ስለሆነም የሚወስዷቸው እርምጃዎች ሁሉ በምሳሌነት ሊያሰመሰግናቸው ይገባል እላለሁ እኔ፡ እንዲያውም እንዲህ የሚል ጠፍቶ ነው ተተኪው አዲስ ወጣት ትውልድ አቅሙን የሚተረጉምበት መድረክ ያጣው – የዘመንም ግጭት ደልቶት የምናዬው።
ትንሽ ብትክትክ አልኩ መሰል፤ ያለተመቸኝንም የተመቸኝም አዘናንቄ የምለውን አልኩ።ቸር እንሰንብት።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

No comments:

Post a Comment