Translate

Wednesday, October 4, 2017

“ታፍኜ እቤት ውስጥ እንድቀመጥ ከተደረኩ በኋላ ተረስቻለሁ” – የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ፓርቲ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋ

በጽዮን ግርማ (VOA Amharic)
በፓርቲያቸው ስም ምንም ዓይነት መግለጫ እንዳይሰጡ፣ ከቤት እንዳይወጡና ሥራ እንዳይሠሩ ከተደረጉ አንድ ዓመት ከዘጠኝ ወር እንደተቆጠረ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ፓርቲ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።
Bekele Nega of Oromo Federalist Congress
አቶ በቀለ ነጋ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሀፊ
“ከዚህ በላይ መብቴ ሊነካ አይገባም፣ ታፍኜ እቤት ውስጥ እንድቀመጥ ከተደረኩ በኋላ ተረስቻለሁ” ብለዋል።
ፓርቲያቸው አባል የሆነበት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የሚገኙበትን ሁኔታ ጠቅሶ ደብዳቤ ጽፎ ቢጠይቅም አጥጋቢ ምላሽ የሚሰጥ አካል መታጣቱን ጨምረው ተናግረዋል።
የፓርቲው ጠበቃ አቶ ወንድሙ ኢብሳ በበኩላቸው “ይህን ትዕዛዝ አስተላልፌያለሁ” የሚል አካል መታጣቱን ተናግረዋል። ሁኔታውን ከፖሊሰ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

No comments:

Post a Comment