Translate

Tuesday, October 3, 2017

ክህደትና ድጋፍ መንሳት – የፖለቲከኞች መሰሪ ስልት (ይገረም አለሙ)

Birtukan Mideksa
Birtukan Mideksa is an Ethiopian politician and former judge who was the founder and leader of the opposition party, the Unity for Democracy and Justice (UDJ).
ይገረም አለሙ
ተዋከበና
ወዲህ ዘወር ቢል ሰው የለምና
ገብርዬ ሲሞት ቀኙ ዛለና
አረሩን ስቦ ጠጣው ያ ጀግና

ብላቴናው ቴዎድሮስ ካሳሁን አያሌ  አመታትን ወደ ኋላ በምናብ ተጉዞ ስለ ንጉስ ቴዎድሮስ የዘፈነው ዘፈን መቅደላ በአይነ ህሊናችን እንድናይ  የማድረግ አቅም አለው፡፡  በምስል የምናውቀው ሽጉጥ የጎረሰው ቴዎድሮስ ፈጥኖ ከህሊና ድቅን ይላል፡እንዲህ በትውስታ የቴዎድሮስን ምስል እያየሁ በስሜት አንድነት አጥተን በወያኔ በባርነት የመገዛታችን ቁጭት እያንገበገበኝ ከግጥሞቹ መካከል ወዲህ ዘወር ሲል ሰው የለምና የምትለዋ ደግሞ ከመቅጽበት 16 ዓመታታ ወደ ኋላ አንደርድራ 2001 ዓ.ም ላይ ትወስደኝና ሌላ ትውስታ፣ ሌላ ቁጭት፣ ሌላ ወይ ነዶ ውስጥ እያስገባችኝ ተቸግሬአለሁ፡፡ ዝግባ የሚያሳቅፍን አንድ ፍቅር አጥተን ሲልማ፣ምን ብዬ ልግለጸው፡፡ ዘፈኑን ማዳማጥ ማቆም ሳይኖርብኝ አይቀርም፡፡
ቴዲ በዘፈኑ ወዲህ ዘወር ሲል ሰው የለምና ሲል በዛች ሰአት በንጉስ ቴዎድሮስ ዙሪያ አንድም ሰው ሳይኖር ቀርቶ አይደለም፡እንደ ገብርዬ የሚታመን፣ ጠላት የሚመክት አለኝታ የሚሆን ሰው ማለቱ እንጂ፡፡ታሪክ እንደሚነግረን ያለ ግዜያቸው የተወለዱት ካሳ አርቆ አሳቢ ሆነው ህልማቸውን በዙሪያቸው ያሉ እንኳን አልረዳላቸው ብለው አንድም ድጋፍ በመነሳት ሁለትም በክህደት ጎድተዋቸዋል፡፡ክህደት የከፋና የገዘፈ ቢሆንም ሁለቱም ጀርባን  ባዶ የሚያስቀሩ በመሆናቸው ጉዳታቸው ተመሳሳይ ነው፡፡ ለፈጻሚው ነው እንጂ ልዩነታቸው ለሚፈጸምበት ሰው ዘወር ሲል ከጀርባው ሰው የሚያጣባቸው ተመሳሳይ ነው ውጤታቸው፡፡
ስለ ሌሎች እውቀቱ ባይኖረኝም ኢትዮጵውያን ግን በተለይ ደግሞ ፖለቲኮቹ በሁለቱም ተክነናል፡፡ባህሩን የሚያሻግር ሙሴ ማግኘት ያልቻልነው በትረ ሙሴ የመጨበጥ አቅም ያላቸው ሰዎች ሳይወለዱ፣ ወደ መድረኩም ሳይወጡ ቀርተው ሳይሆን በዙሪያቸው የሚኮለኮሉ ሰዎች አፈ ቅቤ ልበ ጩቤ እየሆኑ፣ ታማኝ መስለው እየካዱ፣ አለኝታ መስለው ድጋፍ እየነሱ ሲመች ሲያመቻቸውም እየገፈተሩ በአጭር ለመቀጨት እያበቁዋቸው እንጂ፡፡
ወዲህ ዘወር ሲል ሰው የለምና የሚለውን ቃል ስሰማ ከመቅጽበት በርሬ 2001 ዓ.ም ላይ አረፍኩ ብየ ለምን አንዴትና በምን ምክንያ እደሆነ ሳልነግራችሁ አንጠልጥዬ ሌላ ነገር መዘብዘብ ውስጥ ገባሁ አይደል፡፡ ወደ ገደለው ግባ ነው የሚሉት የሸገር ልጆች፤
አዎ 2001 ዓ.ም ወርሀ ታህሳስ፤ መሹዋለኪያ አካባቢ በነበረውና ኋላ የአቶ ስዬ አብርሀ ወንድም አሰፋ አብርሀ በገዙት አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ጽ/ቤት ውስጥ የፓርቲው ምክር ቤት አባላት ሰብሰባ ተቀምጠዋል፤ያ ሳምንት እጅግ ውጥረት የበዛበት፣ ጭንቀት የነገሰበት ይሄ ወይንም ያ ይሁን ብሎ አስተያየት ለመስጠትም ሆነ ምክር ለመለገስ አስቸጋሪ የነበረበት ወቅት ነው፡፡ ምክር ቤቱም ስብሰባ የተጠራውም በዚሁ ጉዳይ ላይ ሊመክር ነበር፡፡
በሴራ ፖለቲካ የተካኑትና በጥሎ ማለፉ ጨዋታ ተሸንፈው የማያውቁት በዚህም ቆመው አይደለም ሞተው ሳቀር የሚገዙን አቶ መለስ የፓርቲው ሊቀመንበር የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ አጀማመር ስላላማራቸው ይቺ ባቄላ ከአደረች አትቆረጠምም በማለት ተንኮል የተነኮሉበት ወቅት ነበር፡፡ ሰበብ ሲፈልጉ ሲያፈላልጉ ሰነባብተው ስውድን ሀገር ባደረግሽው ስብሰባ  ለደጋፊዎችሽ ይቅርታ አልጠየኩም ብለሻል የሚል ሰበብ ፈጥረው ብቅ አሉ፡፡ብርቱካንን ዳግም አስሮ አለም አቀፍ ውግዘት ከማስተናገድ ሞራሏን ገሎ ሰብእናዋን አዋርዶ ከፖለቲካው መድረክ ለማስወጣት ይሄ ጥሩ አጋጣሚ  መስሎ የታያቸው የተንኮሉ ሊቅ በአንዱ አሽከራቸውን በኩል አስተባብይ አለዛ ወደምታውቂው ቃሊቲ አልክሻለሁ የሚል መልእክት አደረሷት፡፡ በዚህ ወቅት የነበረው ሁኔታ አንዲህ ተቆንትሮ የሚጻፍ ኤዴሌምና አጉል አልነካካውም፡፡
በዛ ምንም ማድረግ ባይቻል አይዞሽ አብረንሽ አለን ማለት በራሱ ትልቅ ዋጋ ባለው ሰአት በአጠገቧ የነበሩ ሰዎች ነገረ ስራቸው አላማር በማለቱ ነበር አንዳንድ የምክር ቤት አባላት  ፊርማ አሰባስበው የሥራ አስፈጻሚው አያያዝ የሚያስተማምን አልመስላችሁ ስላለን  የበላይ ባለሥልጣኑ ምክር ቤት ተሰብስቦ አንድ ነገር ይበል በሚል ስብሰባው የተጠራው፡፡
በርግጥም ስጋቱ ትክክል መሆኑ እዛው ሰብሰባው ላይ በግልጽ ታየ፡፡ ሌሎቹ ምን አሉ ምን ሰሩ የሚለውን ከላይ እንዳልኩት ላልጨርሰው ሳልነካካ ለግዜ ላቆየውና ብርቱካን የተናገረችውን ብቻ ብጠቅስ  የነበረውን ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ይመስለኛል፡፡ምክር ቤቱ ሰብሰባ የተጠራበት አግባብ ትክክል አይደለም ከሚለው አንስቶ በዚህ አጀንዳ ላይ መነጋገር አይችልም ሥልጣኑ አይደለም  እስከሚል የዘለቀ  ብዙ ህሊና ሊቀበላቸው የሚከብዱ ቃላት ከአንድ አቅጣጫ ሲነገሩ ብርቱካን እጇን አወጣች፤ ሰብሳቢው ዶ/ር ሽመልስ ተክለጻድቅ (ነብሳቸውን ይማረው )ሲፈቅዱላትም ከመቀመጫዋ ተነስታ ከፊት ለፊት ሆኜ አመራር ስሰጥ ጀነራሎቼን ከጀርባዬ አጣኋቸው አለች፡፡ ቴዲ አፍሮ ወዲህ ዘወር ሲል ሰው የለምና ሲል ከመቅጽበት የሚታወሰኝ ይሄ የብርቱካን ንግግር ነው፡ቴዲ አፍሮ ይህን ሲሰማ ምን እንደሚል ባላውቅም፡፡ ምን አልባት አንድ ቀን ያዜምላት ይሆናል፡፡
አበው ያመኑት ፈረስ ይጥላል በደንደስ እንደሚሉት መሆኑ ነው፡፡አይደለም የፓርቲ ሊቀመንበር ሲኮን ተራ አባልም ሲኮን ከወያኔ በኩል ብዙ ችግር ሊገጥም አንደሚችል ይገመታል ብቻ ሳይሆን ይታወቃል፡ ስለሆነም  አካልንም መንፈስንም አዘጋጅቶ ነው ወደ ፓርቲ የሚኬደው፡፡ በአንድ ዓላማ ተሳስሮ፣ እስከ ቀራንዮ አብሮ ለመዝለቅ ተማማሎ፣ በአንድ ህግ ለመገዛት ተስማምቶ ከተሰለፉት የትግል አጋር ግን አደጋ ይገጥመኛል ክህደት ይፈጸምብኛል ተብሎ አይሰጋም፣ ብቻ ሳይሆነን አይጠረጠርምና ሲከሰት የሚያደርሰው የመንፈስ ስብራት የሞራል ውድቀት ቀላል አይሆንም፡፡ ወያኔ ከሚያደርሰው ዘጠና ከመቶ ጉዳት ወገን በሚባሉት የሚደርስ አስር ከመቶ የሚሆን የክህደት ጉዳት ይበልጥ ያማል፣ይበልጥ ይጎዳል፡፡ በተቃውሞው ጎራ የትየለሌ አስተዋጽኦ ሊያደርጉ የሚችሉ በርካታ ወገኖች አምነዋቸው አብረዋቸው በተሰለፉ ሰዎች በግል በደረሰባቸው ወይንም በሌሎች ላይ ሲደርስ ባዩት ተማረውና ተስፋ ቆርጠው ከመድረኩ ለመወርዳቸው ምስክር ነኝ፡፡
በርግጥ እንዲህ በቀላሉ ተስፋ ለመቁረጥ ከመነሻው ወደ ትግል መግባት አልነበረባቸውም የሚል ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ አይነት አስተያየት ሊሰጥ ይችላል፡፡ነገር ግን እንዲህ አይነት ቅን ሰዎች የሀገሬ ፖለቲከኞች አብዛኞቹ የተካኑበትን የሴራ ፖለቲካና  የጥሎ ማለፍ ጨዋታ የማያውቁ ሊለምዱትና ሊለማዱትም የማይችሉ እነርሱ ወደ ትግል የገቡት ከወያኔ ጋር ለመታገል በእውቀታቸው በገንዘባቸው ወዘተ የተቃውሞውን ጎራ ለማጠናከር እንጂ እርስ በእርስ ገመድ ለመጓተት አይደለምና እየተሻኮቱ መቀጠሉን እየተካካዱ አብሮ መዋሉን በየወንዙ መማማሉን አይመርጡትም አይለምዱትም፡፡
ብርቱካንም ፖለቲካ ማለት እንዲህ ነው እንዴ፣ፖለቲከኞቹስ እንዲህ ነው እንዴ ነገረ ስራቸው ያለችባቸውን ግዜያት አስታውሳለሁ፡ ለሁለተኛ ግዜ ወደ ቃሊቲ ከመላኳ ሁለት ቀናት በፊት “ቃሌ” በሚል ርዕስ ባሰራጨው ጽሁፍ  ውስጥ   “ሕገወጥነትንና ማናለብኝነትን መቼም አልለምደውም፤ አልተባበረውም” በማለት እምነቷን አቋሟን የህግ ሰውነቷን ወዘተ በግልጽ ተናግራለች፡፡ ይህ ደግሞ አንደ ብዙዎቹ ፖለቲከኞች ለማለት ብቻ ያለችው ሳይሆን በተግባር ትኖርበት የነበረ ለመሆኑ በቅርብ የሚያውቋት  ሁሉ የመሰክሩላታል፡፡ መነሻዬ የቴዲ አፍሮ ወዲህ ዘወር ሲል የምትለዋ ቃል የፈጠረችው ትውስታ በመሆኑ እንጂ ለዚህ የሚያውቋት ሁሉ ይመሰክሩላታል ላልኩት እኔም ብዙ ማስረጃዎችን ማቅረብ እችል ነበር፡፡ ቦታውም ግዜው የተነሳሁበት ምክንያትም ወደዛ የሚወስድ አይደለም እንጂ፡፡አንድ ነገር ግን በርግጠኝነት ማለት ይቻላል፡፡ አንደሌሎቹ ፖለቲከኞች ይህን መልመድና መለማመድ የሚያስችል ስብእና ቢኖራት ኖሮ እንዲህ ከመድረኩ አናጣትም ነበር፡፡
ብርቱካን ከፊት ሆኜ አመራር ስሰጥ ጀነራሎቼን ከጀርባዬ አጣኋቸው በማለት ፍርጥ አድርጋ  የቆሰለ ስሜቷን ነገረችን እንጂ አፈጻጸሙ ይለያይ እንጂ ክህደትና ድጋፍ መነሳት በብዙዎች ላይ ተፈጽሟል፡፡ፕ/ር አሥራት ወህኒ ሲወርዱ የአመራር አባላቱ ይበልጥ አልህ ይዞአቸው ተጠናክረው አሳሪውን መታገል፣ ለታሰሩት መሪያቸውም ድጋፍና አለኝታነታቸውን ማሳየት ሲገባቸው ተቀዳሚና  ምክትል ሊቀ መንበር ይባሉ የነበሩት ሳይቀሩ ከመቅጽበት ነው ፓርቲውን ጥለው የወጡት፣ አንዳንዶቹ ከሀገር ጭምር፡፡ የድርጅቱን መሪነት የተረከቡት ሰዎችም ቢሆኑ አንድም ቀን  ይፈቱ አይደለም ህክምና ያግኙ ብለው አልጠየቁላቸውም፡፡ ነብሳቸውን ይማርና እርሳቸውም ወደማይቀርበት አለም ሄዱ ኢ/ር ኃይሉ ሻውል ለ17 ዓመታት በአሥራት ወንበር ላይ ሲቀመጡ አንድ ቀን በደግ ይሁን በክፉ ስማቸውን አንስተው አያውቁም፡፡ ህይወቴና የፖለቲካ ርምጃዬ በሚል ርዕስ በጋዜጠኛ ባጻፉት መጽሀፍም እንደዚሁ፡፡ ለአመታት ወደ ኋላ ተጉዞ መተረኩ ቢያንስ ለዛሬ የሚፈይደው የለምና ዘልቄ መግባቴን ባልሻውም አስራት ላይ ክህደትና ድጋፍ መንሳት መፈጸሙን ግን እመሰክራለሁ፡፡ አሌ የሚል  ካለ ሜዳውም ፈረሱም ይሄው በአሉባለታ ሳይሆን በመረጃና ማስረጃ እንነጋገር፡፡
ክሀደትና ድጋፍ መንሳት ከተነሳ መታለፍ የሌለባቸው ሌላው ሰው ፕ/ር መረራ ናቸው፡፡ እኔ ቢራ እየጠጣሁ መታገል የምፈልግ ነኝ በማለት ሰላማዊ ታጋይነታቸውን በግልጽ ያሳወቁትና እኛ ሰዎችን በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ አናስርም የሚሉት የወያኔ ንጉሶች እንደ ማጣቀሻ  ሲጠቅሱዋቸው የነበሩት መረራ በወያኔ እስር ቤት ከተጣሉ ወዲህ እንደ ሙት ከሰልስትና ሰባት በኋላ ስማቸው ሲነሳ አልሰማሁም፡፡ ያለግብሩ ዋንኛ ተቀዋሚ የሚል ቅጥል የተለጠፈለት መድረክ አንዴ በሊቀመንበርነት ሌላ ግዜ በምክትል ሊቀመንበርነት እንዳልመሩት ሁሉ ሲታሰሩ አልባሌ መግለጫ ከማውጣት በዘለለ ያለው ነገር የለም፡፡ ለአመታት የትግል አጋራቸው የነበሩትና መድረክን በተሌዩ ድርጅቶች ስም  በአከስዮን የያዙት ፕ/ር በየነ ጴጥሮስማ ድጻቸውም አልተሰማ፡፡ የመድረክን ምንነት የፕ/ር በየነን ማንነት ለሚያውቅ ሰው በመረራ እስር የተፈጸመው ዝምታ ላይገርመው ይችላል፡፡ የኦፌኮ ዝምታ ግን እንቆቅልሽ ነው፡፡  እናስ ይሄ ክህደትና ድጋፍ መንሳት ሊሰኝ አይበቃም ትላላችሁ፡፡ መረራ ከእስር ተፈተው የሚሉትን ለመስማት ያብቃን፡፡
ወዲህ ዘወር ቢል ሰው የለምና  ቴዎድሮስ ለቲዎድሮስ
ከፊት ሆኜ አመራር ስሰጥ ዘወር ስል ጀነራሎቼን ከኋላዬ አጣኋቸው ብርቱካን በዛች ሰአት፡
ስለ ፕ/ር አሥራት  በቁጭት የሚናገሩ ሰዎች  ለፕሬዝዳንትነት ሲታጩ ከማን ጋር የምሰራው ብለው ነበር ይላሉ፡፡ ኋላ የተፈጸመባቸው ክህደትና ድጋፍ መንሳት አስቀድሞ ታይቷቸው ነበር እንበል!
“ይሄ እኮ የአካዳሚ ውይይት አይደለም፤ እንዲህ አይነቱን ጥያቄ ብትተይ ይሻላል” የሚል ነበር። ለእነርሱ ያስፈገጋቸው፣ ያስገረማቸው ጉዳይ ግን እኔን ሁሌም የምኖርለት፣ የምቆምለት፣ እንዳንዴም የምታሰርበት እና የምፈታለት ታላቅ ቁም ነገር ነው። የሕግ የበላይነት ወይም ሕገመንግሥታዊነት። 
ብርቱካን ሚደቅሳ
ታኅሣሥ 18/2001 ዓም

No comments:

Post a Comment