Translate

Thursday, January 28, 2016

ኢትዮጵያ “ነፃነት የሌለባት”፤ ኤርትራ “ከክፉዎች የከፋች” ተባሉ

በዓለም ዙሪያ የሚሰማው የምጣኔ ኃብት ድቀት እና የማኅበራዊ ነውጥ ፍራቻ አምባገነን መንግሥታት በአውሮፓ አቆጣጠር ባለፈው 2015 ዓ.ም ይበልጥ አፋኝና ጨቋኝ እንዲሆኑ ሰበብ ሳይሰጣቸው እንዳልቀረ ዛሬ የወጣ የዓለም የነፃነት ሁኔታ ሪፖርት አስታውቋል፡፡
ፍሪደም ሃውስ የሚባለው ነፃ ቡድን በዚህ ሪፖርቱ የሃገሮችን የዴሞክራሲያዊ የነፃነት ይዞታዎች ገምግሞ በደረጃ አስቀምጧቸዋል፡፡ አምባገነን አገዛዞች ባለፈው የአውሮፓ ዓመት በ2015 ዓ.ም ይበልጥ የከፉ መሆናቸውን ይህ ዛሬ የወጣ የዓለም የነፃነት ይዞታ ሪፖርት ይናገራል፡፡

መንግሥታቱ የሚጠቀሙባቸው እጅግ የከፉ የአፈና ዘዴዎች፣ የሽብር ፈጠራ ጥቃቶች መብዛት እና የምጣኔ ኃብት መላሸቅ፣ ነፃነት በዓለም ዙሪያ እየተጉላላች፣ ይዞታዋ ወደ አስፈሪ ሁኔታ እያዘገመ መምጣቱ እያሰጋ መሆኑን ሪፖርቱ ይጠቁማል፡፡
ተቀማጭነቱ ዋሺንግተን ዲሲ ዩናይትድ ስቴትስ የሆነው ፍሪደም ሃውስ የሚባለው የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ተሟጋች ቡድን ባለፈው የአውሮፓ 2015 ዓ.ም የዓለም የነፃነት ይዞታ ለአሥረኛ ተከታታይ ዓመት እያሽቆለቆለ የመጣበት ዓመት እንደነበረ አስታውቋል፡፡
የፍሪደም ሃውስን ሪፖርት ለማግኘት ይኽንን ይጫኑና ይከተሉ፤ የሂዩማን ራይትስ ዋችን ሪፖርት ለማግኘት ይኽንን ይጫኑ

No comments:

Post a Comment