Translate

Sunday, January 31, 2016

የኃይለማርያም ደሳለኝ ስድስተኛው አማካሪ ከትግራይ – ብርሃነ ገ/ ክርስቶስ (የአርከበ እቁባይ አማች)

arekebe
ከኤርሚያስ ለገሰ
እነሆ! ዛሬ ደግሞ ” በሚኒስትር ማእረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ መልእክተኛ ” የሚል ሹመት ሰማን። የአዲሱ ቦታ ስልጣን እና ሃላፊነቱ ባይገለጵም ሹመቱ ከተሰጠው ሰው ማንነት ተነስቶ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም። ቢያንስ ቢያንስ ” የዶሮ ወጥ መልእክተኛ” እንደማይሆን ይጠበቃል።

ባይሆን በዚያን ሰሞን በደረሰባቸው መደናገጥ የተነሳ ” ህውሀት ትግራይን ብቻ ነው የሚያስተዳድረው” ያሉት ሰውዬ ትክክል ሳይሆኑ አይቀርም። እንደምናየው ከሆነ ህውሀት ከአማካሪነት( ልዩ) ማለፍ የቻለ አይመስልም። ለምሳሌ፣
1• አርከበ እቁባይ… በሚኒስትር ማእረግ የጠቅላያችን ልዩ አማካሪ (በመሬት ጉዳይ፣ በኢንዱስትሪና ከተሞች ጉዳይ እንደሚያማክር ልብ ይሏል)
2• አለቃ ፀጋዬ በርሔ( የስብሀት ነጋ አማች) … በሚኒስትር ማእረግ የፀጥታ ልዩ አማካሪ ( የደህንነት ሐላፊ እና ምክትሉ፣ እንዲሁም የኢታማዦር ሹሙ የሕውሐት አባላት መሆናቸውን ልብ ይሏል)
3• ብርሃነ ገ/ ክርስቶስ ( የአርከበ እቁባይ አማች) …በሚኒስትር ማእረግ የጠቅላያችን ልዩ መልእክተኛ ( የውጭ ጉዳይ የበላይ ሃላፊው ህውሀት መሆኑን ልብ ይሏል)
4• አባይ ፀሐዬ… ( የፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሔር የቀድሞ ባል) በሚኒስትር ማእረግ የፓሊሲ ጥናት ልዩ አማካሪ (ዴሬክተር)
5• ፋሲል ናሆም… በሚኒስትር ማእረግ የጠቅላያችን የህግ አማካሪ
6• ንዋይ ገብረአብ… በሚኒስትር ማእረግ የጠቅላያችን የኢኮኖሚ አማካሪ (የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ ደብረፂዮን መሆኑን ልብ ይሏል)

1 comment:

  1. እንኳን ሊያማክር ራሱንም የሚመራ አይመስልም ነብራራ ቢጤ !!

    ReplyDelete