Translate

Thursday, January 28, 2016

ር'ዮት አለሙ እንደ ክርስቶስ ደሞ እንደ በላይ ( ሄኖክ የሺጥላ )

ር'ዮት አለሙ እንደ ክርስቶስ ደሞ እንደ በላይ ( ሄኖክ የሺጥላ )

ጋዜጠኛ 'ና መምህርት ር'ዮት ዓለሙ ከጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ጋ ታሪኳን ( ያሳለፈችውን መከራ ፣ እንግልት ፣ ስቃይ እና አስር ) በቅንጭብ ካካፈለችበ የኢሳት ማህደር ውስጥ ገብቼ ቃለ ምልልሷን አደመጥኩ ። እኔ በግሌ ቃለ ምልልሱ ፥ ስለ ወያኔ ( ወይም የ ዘንድሮ ትግሬ ምንነት) ስላለኝ እምነት ( ኣቋም ) ማረጋገጫ ከመሆን ውጪ ሌላ ነገር አላገኘሁበትም ። እንደ ሰው ፣ እንዲሁ አንዳንዴ "እስኪ እኔ ትግሬ ብሆን ኖሮ ሄኖክ የሺጥላ የሚጽፈውን "ትግሬ ተኮር" ጽሑፎች እንዴት ነበር የማያቸው?" ብዬ ራሴን ደግሜ ደጋግሜ ጠይቄ ላገኘሁት መልስ የ ር'ዮት ቃለ ምልልስ ስጋ ለበስ ባለ እስትንፋስ ማስረጃ በመሆን ለወያኔ -ትግሬ ሊኖረኝ የሚችለውን ቅንጣት "ምናልባችን" ጠራርጎ የወሰደ ፣ የማንነታቸው ፍጹም ማረጋገጫ ሆኖም አግኝቼዋለሁ ።

በቃለ ምልልሱ ውስጥ ር'ዮት ስለ ፓስተር ዳንኤል ታነሳለች ። በይበልጥም ር'ዮት ፓስተር ዳንኤል "አንዳንድ ጥያቄዎች ( አምስት በቁጥር ) ልጠይቅሽ ነበር ፣ በመጀመሪያ ስለ ሁኔታሽ ወይም አያያዝሽ ለማወቅ እፈልጋለሁ እስቲ ንገሪኝ ሲላት፣ " < አምስቱንም በአንድ ላይ ጠይቀኝ!> " ብላ የመለስችለትን መልስ ደግሜ ደጋግሜ ነው የሰማሁት ። ይህ ብቻም አይደለም ፣ ለምሳሌ ማእከላዊ ስትሄድ ፣ መርፌ ወግተው እና ደንዝዘው መቀሌ /ትግራይ ያለች እስኪመስላት የስራ ( የማሰሪያ ቋንቋው) ትግረኛ መሆኑ ፣ በትግሬና ትግሬ ባልሆኑ ፖሊሶች ም ሆነ ታሳሪዎች መሃከል ስላለው አይን ያወጣ ልዩነት ( በተለምዶ ዘረኝነት የምንለው ማለት ነው ) ፣ እና ሌሎች መሰል ጉዳዮችን ትዳስሳለች ።
ከዚሁ ሁሉ መከራ እና በደል በሗላም ግን ር'ዮት ግማሽ እንደ ክርስቶስ ግማሽ ደሞ እንደ በለይ ዘለቀ እንደምታሰብ የተረዳሁ መሰለኝ ። ር'ዮት የምታስበው ነጻነት ትግሬንም ነጻ የሚያወጣ ፣ የምታቀነቅነው ፍትህ ለአማሮች የጎደለባቸውን ያህል ትግሬዎችም ያጡት ነው ብላ የምታስብ አይነትም ነች። ይህ ባህሪዋ ክርስቶሳዊ ሲያስመስላት ፣ ግራ-ጉንጯን አስረው " ሲያላጉት " ለነበሩት ጨካኞች ታጥባ የምትሰጠው ቀኝ- ጉንጭ ደሞ ያሌላት ሰው በመሆኗ ይሄኛው ባህሪዋ እና እምነቷ በላይን ያስመስላታል ።
እንደ አንድ ግለሰብ በ-ር'ዮት አለሙ ውስጥ ብዙ ነገርን ነው ያየሁት ። ር'ዮት የቀደሙ አባብቶቻችንን እና ጀግኖች እናቶቻችንን ደም የያዘች የትውልድ በረከት ናት ። ልብህን ከፍተህ ፣ ብዙ ሳትመሳጠር እና ራስህን ሳትዋሽ እቴጌ ጣይቱ ምን ትመስል እንደነበር ማወቅ ከፈለክ ፣ ር'ዮት አለሙ ጥሩ የጣይቱ መስታወት ስለመሆኗ ብዙ የሚያሻማ አይመስለኝም ። በ-ር'ዮት ውስጥ ፍቅርን ፣ ጀግንነትን ፣ አልበገርም ባይነትን ፣ የሀገር ፍቅርን ፣ ከምንም በላይ መሰረት ያለው ጠጣር ብልህነትን ታያለህ ። ር'ዮት ፍቅሯ ክርስቶሳዊ ሲያደርጋት ፣ ጽናቷ ደሞ ፍጹም ኢትዮጵያዊ ያደርጋታል ። ር'ዮት ወኔው ለተሰለበ ፣ ድፍረቱ ለዶለዶመ ፣ ቁጣው ለወየበ ፣ የወንድነት ሃሞቱ ለፈሰሰ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ( ወንድ ፣ ሴት ፣ ወጣት ፣ ሽማግሌ ፣ አረጋዊ ፣ ባልቴት ) እንደ ፈውስ ናት ! ር'ዮት ከጽናቷም ፣ ከፍቅሯም ፣ ከተጫነባት የታሪክ እዳም ባሻገር ፣ መድረሻዋን አርቃ መመልከት የምትችል ፣ ሕልሟን በጊዜ ( በቀናት እድሜ ) የማትመትር ፣በሁኔታዎች ከፍ ዝቅ የማይል ፣ በአለት ላይ የተቀረጸ አቋም ያላት እህት ስለመሆኗ ፣ ይቺ ቅንጭብ ታሪኳ በቂ ይመስለኛል ።
ስለ ር'ዮት ሳስብ ፣ "ከዋሻው ጫፍ ላይ የሚታየው ብርሃንን" የሚሉትን ትመስለኛለች ። ርዮት ተፈትና ያለፈች ነች ። አስካሁን በዘመኔ እንደ እሷ ፣በወያኔ እሳት ተፈትኖ ያለፈ ሰው ብዙ አላውቅም ። ምናልባት ዶ/ር ታዬ ወ/ሰማዕት ፣ እና በጣት የሚቆጠሩ ጥቂቶች ይኖሩ ይሆናል ። ይህም ማለት አሁንም በፈተና ላይ ያሉት እና ፈተናውን ያለ አንዳች ጥርጥር እንደሚያልፉ እርግጠኛ የሆንኩባቸውን አንዷለም አራጌን ፣ እስክንድር ነጋን ፣ ተመስገን ደሳለኝ እና ሌሎችንም መጥቀስ ሳያስፈልገኝ ማለት ነው ።
ር'ዮት የጥካሬያችን ተስፋ ብቻ ሳትሆን ፣ የ አልገዛም ባይነታችን መቅድም ናት ። ር'ዮት ዝቅ ከማይል ራስ ውስጥ ፣ ከማይጎነበስ ማንነት ውስጥ ፣ ከማይወላውል እና ከማይናወጥ ስብዕና ውስጥ እንደ እንጉዳይ ተፈልቅቃ የወጣች የኛ ፣ የዚህ ዘመን ትውልዶች ጸሐይ ነች ። ር'ዮት እና መንፈሷ ዛሬ በሀገሬ ሰማይ ላይ ያበራሉ ። የ ር'ዮት ደም ዛሬ በሀገሬ ጅረት፣ በዓልገዛም ባይነት በ- ፈረሰኛው ቀየውን ይጋልበዋል ። ር'ዮት ያሳለፈችው መከራ አንገት ቀና የማድረግ ፣ የሰውነት ፣ ነውና እንዲህ እንደዛሬ መለስ ብለው ሲያዩት ያኮራል ። ር'ዮት ባልተፈተነ ሕይወት ሃሴት ውስጥ ከመዋኘት ፣ በተፈተነ መራራ መከራ ውስጥ ማለፍን መርጦ ኄምሎኩን ተጎንጭቶ እንዳለፈው ሶቅራጥስ ኢትዮጵያዊቷ ሶቅራጥስ ነች ። በሕይወት እና በሞት መሀከል ሞትን ለአርነት ሲል የመረጠው ክርስቶስ እንኳ " ፍቃድህ ቢሆን ይህንን ጽዋ ከኔ ብታዞረው " ብሎ መጠየቁን ስናስታውስ ፣ ር'ዮት በዚህ ባህሪዋ ፍጹም በላይ ዘለቀን ትመስላለች ማለት እንችላለን ። ክብር ይገባሻል !
እንደ በግ ተነድተው ተገፍተው የሞቱ
አለሁ ባይ ጠፊዎች በሞሉባት ዓለም
እንቢ ብሎ መሞት ፣ ቁብ ታሪክ አይደለም !
ነብስ አውቆም መንበርከክ ፣ ዳዴን ያላቆመ
አያውቅም ነጻነት ቆሞ ካልታከመ !
ጀግና ከነጠፈው ፣ ሀሞት ከፈሰሰው
በዚህ በኛ ሀገር
በኩራዝ ፈልገህ ብታገኝ አንድ ሰው
ያንድ ጀግና መቆም ፣ ከእልፎች መንበርከክ
ጎልቶ ኣይታይም ፥ ሆኖ ኣያውቅም ታሪክ !
ግን ግን
የሆዳም ታሪክ
እዳሪ ነው
የጀግና ታሪክ ኣእማድ ነው
ይኸው ይታያል ከሩቁ
ፈርተው ከእግሩ ስር ሲወድቁ !
( ተገጠመ በሔኖክ የሺጥላ - ር'ዮት አለሙን በማሰብ ) !

No comments:

Post a Comment