Translate

Wednesday, September 10, 2014

በወያኔ ስር የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት፣ የወያኔ አገልጋይ ኢሕአዴግ፣የአፋኞችና የነፍሰ ገዳዮች ምሽግ- የወያኔ ደህንነት

ነዓምን ዘለቀ,        

ዋና ጸሃፊያችንና  የትግል ዳችን  አንዳርጋቸው ጽጌ
g7-logo
የንቅናቄአችን ዋና ጸሃፊና የትግል ጓዳችን  አንዳርጋቸው ጽጌ  በየመን ትብብር በፋሽስታዊ ወያኔ አፋኞች  እጅ መውደቅ ያስቆጣው የኢትዮጵያ ሕዝብ ባሳየው ወገናዊነት ልባችን ተነክቷል። የአንዳርጋቸው መታሰር ይቆጨናል፤ እየደረሰበት ያለው ስቃይ ያንገበግበናል፤ የሱን አይነት ብርቱ፣ ቆራጥ፣ አስተዋይና ብቃት ያለው ታጋይ ትግሉ ማጣቱ ይጎዳናል:: አንዳርጋቸው በሳል የፖለቲካ ሰውና ቆራጥ የተግባር ታጋይ ብቻ አይደለም። በግል ለማታውቁት በበርካታ የእውቀት ዘርፎች በጥልቀት ያነበበ፤ ፍልስፍና፣ ሊትሬቸር፣ ሲኒማ የሚወድና ህሊናው በዕውቀት በከፍተኛ ደረጃ የበለፀገ ነው። የሰው ልጅ መከራ፣ በደልና ስቃይ እስከ አጥንቱ ይሰማዋል። ዱባይ ላይ ከአመት በፊት ስላገኛት ኢትዮያዊት የነገረኝ ሲቃ እየተናነቀው ነበር።ልጅቷ ሲያገኛት ያለማቋረጥ ታለቅሳለች፤ ምን እንደሆነች ቢጠይቃት ለመናገር ባትፈቅድም አጥበቆ ሲይዛት እንደተናገረችው፤ ተቀጥራ በምትሰራበት  የቤቱ ባለቤት ሽማግሌ አረብና አራት ወንድ ልጆቹ በየገዜው ተራ በተራ ደፍረዋታል። የሚያስነባት ይህ ነበር። አንዳርጋቸው “የኢትዮጵያውያን መከራና ውርደት መቼ ነው የሚያበቃው” በሚል ነበር ሲቃ እየተናነቀው ያጫወተኝ።

አንዳርጋቸው የንዋይና የስልጣን ፍቅር የለበትም። ፍላጎቱ ያ ቢሆን ኖሮ ዛሬ  ወያኔ ከሰበሰባቸውና ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኙ የወያኔ ሎሌዎች የተሻለ ደረጃ ላይ ባገኘነው ነበር። በምንም መለኪያ በሱ ደረጃ ብቃት፣ ምሁራዊ ብስለትና ስብዕና  የተላበሡ እንደሌሉባቸው ግልጽ ነው። አንዳርጋቸው የመረጠው የፍትሕ፣ የነጻነትና የእውነትን መንገድ ሲሆን እሱ የመረጠው ከህሊናው ጋር መኖርን ነው።  ለዚህም ነው ስልጣን እና ገንዘብን ገፍቶ፣ የአውሮፓን ምቾት ትቶ፣ በርሃ ወርዶ አፈር ላይ እየተኛ በርካታ ታጋዮችን አስተምሮ ትግሉን ጠንካራ መሰረት ላይ የተከለው – ትግሉን መስመር አስይዞ ዛሬ በፋሺስቶች እጅ ቢወድቅም።
ፋሽስቶቹ ወያኔዎች በተለመደው ድንቁርናቸው ያቀዱትና የአለም አቀፍ ህግን ጥሰው የሄዱበት የብልግናና የውንብድና  መንገድ እሱን በማፈን ነጻነትና  ፍትህ የጠማውን የኢትዮጵያ ህዝብ አንገት እናስደፋለን፣ ቅስም እንሰብራለን፣ ታጋዮችና ትግሉን እናዳክማለን፣እናመክነዋለን ከሚል ስሌት  ነበር። በተቃራኒው ኢትዮጵያውያን በሀገር ውስጥም በውጭው አለም ከዳር ዳር በከፍተኛ ቁጣና ቁጭት እንዲንቀሳቀሱ እያደረገ፤ ለመራራ ትግል እንዲዘጋጁና ለመስዕዋትነት እንዲቆርጡ እያነሳሳ ይገኛል። <<እኔም አንዳርጋርጋቸው ጽጌ ነኝ>> በሚል በሺህ የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን ትግሉንም ንቅናቄአችንንም እንዲቀላቀሉ እያደረገ ነው።  ዛሬ ብዙ ሺዎች የአንዳርጋቸው ጽጌን ፈለግ ተከትለዋል፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሚሊዮኖች የነጻነት፣ የእኩልነት፣ የፍትህ ጠበቆችና ታጋዮች ሆነው የፋሽስታዊውን የወያኔን ስርዓት በሁሉም መንገዶች እንደሚፋለሙ አፍታም ጥርጥር የለንም። በግንቦት 7 በኩል  እልሃችን፣ ቁጭታችን፣ ጽናታችን፣ ቁርጠኝነታችን እጥፍ ድርብ እንዲሆን አድርጎናል። እኛም ግንባራችችንን ሳናጥፍ የተጀመረውን ትግል ከግብ ለማድረስ በቁርጠኝነት ተነስተናል። በዛሬው እለትና በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ንቅናቄያችን በመላው ዓለም በ27 ከተሞች ከሚያደርገው ህዝባዊ ስብስባዎች አንዱ በሆነው በአትላንታ ከተማ በመካከላችሁ የተገኘሁት ኢትዮጵያ ሀገራችንንና ህዝባችን የሚገኙበትን የምታውቁትን እጅግ አስከፊ ሁኔታ  ለመደጋገም አይደለም።
የዛሬው ስብሰባ ዋና አላማና ትኩረት ትግሉ ወደ አንድ ሌላ ወሳኝ ምዕራፍ መሸጋገሩን በተመለከተ የጋራ ግንዛቤና የትግል አቅጣጫ እንዲኖረን ለመመካከር ነው ሲሆን፤ ሁሉም የዚህ ትግል ንቁ ተሳታፊና አባል እንዲሁም ደጋፊ በመሆን ምን አይነት ተግባራዊ የትግል እንቅስቃሴዎችን ማድረግ እንደሚገባን ሁላችሁም ወስናችሁ እንድትንቀሳቀሱ ለማስገንዘብና ለልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎችም የንቅናቄአችንን ጥሪ ለማቅረብ ነው።
Andargachew-high
ዘረኛውና ዘራፊው የወያኔ አርነት ትግራይ ስርዓት
የኢሕአዴግ/ኦህዴድ ከፍተኛ ካድሬና የካድሬዎች አሰልጣኝ የነበረውና በልዩ ልዩ ከፍተኛ መንግስታዊ ሃላፊነቶች  ስርአቱን  ያገለገለው አቶ ኤርሚያስ ለገሰ ከጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ጋር በኢሳት ቴሌቪዥን እና ራዲዮ ያደርገውን ሰፊ ቃለ-ምልልስ  የተከታተላችሁ ይመስለኛል። አቶ ኤርሚያስ ለገሰ በርካታ ሃቆች፣ መረጃዎችና ቁም ነገሮችን በአካተተበት “የመለስ ትሩፋቶች” በሚል ርእስ ያሳተመው የመጀመሪያ መጽሐፉ በቨርጂንያ በተመረቀበት ወቅት በስፍራው ተገኝቼ  ኤርሚያስ ሲናገር የሰማሁዋቸውና ለዚህ ስብሰባ ፋይዳ አላቸው ብዬ የወስድኳቸውን እዚህ ለመጥቀስ እወዳለሁ፡፡
“ስርዓቱ የኔ ነው እንድትል፤ የኔነት ስሜት (Sense of Belongingness) እንዲሰማህ አያደርግም።  የወያኔ/ህወሃት ዋና ተግባሩ ዘረፋ ነው”።  “ኢህአዴግ  ጥራትም በጽናትም በብቃትም እዚህ ግባ የሚባል ድርጅት አይደለም” የሚሉ አስተያየቶችን ሰንዝሮ ነበር
የወያኔን አገዛዝ ምንነት አሁንም ድረስ በአግባቡ ላልተረዱ ብዙ መረጃዎችና ሃቆች ያካተተ መጽሀፍ ነው። ባለራዕይ ከሚሉት ከቀድሞ የወያኔ ቁንጮ ጀምሮ በቀለኞች፣ ቂመኞችና ዘረኞች መሆናቸውን ይበልጥ ተረድተንብታል። የአብዛኞቹን የወያኔ መሪዎችና አባላት እኩይነት፣ ዘራፊነት፣ አጭበርባሪነት፣ የስርዓቱን እጅግ የወረደና የዘቀጠ ምንነት፣የመሪዎቹን ርካሽነት፣ ጭካኔአቸውን፣ ለከት የሌለው ስግብግብነታቸውን፣ በስርዓቱ ውስጥ የነገሰውን አድርባይነት ገላልጦ አሳይቶናል። እጅግ የወረደ ስብዕና ባላቸው ጨካኝና ርካሽ ሰዎች እጅ ሀገራችን ኢትዮጵያ እንደወደቀችም ተገንዝበናል። ስርዓቱን ጥለው ከወጡት የቀድሞ ባለስልጣናት ያልሰማነውን በርካታ ውስጠ ድርጅታዊ ምስጢሮችን ያካተተ ትልቅ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ታሪካዊ ሰነድ ጭምር በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያነበው የሚገባ መጽሐፍ ነው የሚል እምነት አለኝ።
እነዚህን  ላለፉት በርካታ የትግል አመታት ካጠራቀምናቸው መረጃዎችና ሃቆች ጋር ስንደምራቸው የዚህ ዘረኛና  ለከት የለሽ ስግብግብ የወያኔ አገዛዝ ማንነት መፈተሽ የሚገባው በይፋ (officialy)  ባስቀመጠውና በብልጣ ብልጥነት በሚነግድባቸው – አብዮታዊ ዴሞክራሲ፣ ልማታዊ መንግስት፣ የትራንስፎርሜሽን እድገት ወዘተ – ርዕዮቱ ሳይሆን በተግባር በሚሰራበት (Operating) ርዕዮት ሊሆን ይገባዋል፤ ይህም ተግባራዊ ርዕዮት ዘረኝነትን መሰረት ያደረገ ወያኔዎች የተያያዙት መንግስታዊ ዘረፋ ነው። ወደ ስልጣን እስኪመጡ ከደርግ/ኢሰፓ ጋር በሚታገሉበት ወቅት በጠባብ ብሄረተኝነትና በዘረኝነት የታጀለ ቢሆንም፣ ቢያንስ በወቅቱ አንግበውት የነበረው ፍትህ፣ እኩልነት፣ የብሄር ብሄረሰቦች መብት ወዘተ የሚሉ ነበሩት። ዛሬ ግን ትርጉም አልባ መፈክሮች መሆናቸውን የወያኔዎች 23 ዓመታት ተግባሮቻቸውና አድራጎቶቻቸው በይፋ ይመሰክሩባቸዋል።
የፋሽስቱ ወያኔ ዘረኝነት ከህመም ወደ ነቀርሳ (Cancer) የተለወጠ መሆኑ ግልጽ ነው። ከ23 ዓመታት በኋላም የመከላከያ ሰራዊቱን ዕዝ ወሳኝና ቁልፍ ቦታዎች ከላይ እስከታች 95 በመቶ፤ የደህንነቱ መዋቅሩም 90 በመቶ እንዲሁም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ 50 በመቶ ኤፌርት የሚባለው የህወሃት ግዙፍ ኩባንያዎች ስብስብ (Conglomerate) ተቆጣጥሯል። የህወሃት አባላትም በቤተሰብ፣ በዘመድ-አዝማድ የተያያዙ  በሰፊው የትግራይ ህዝብ ስም የሚነግዱየትግኛ ቋንቋ ተናጋሪዎችሁሉንም በበላይት ይዘዋል። ይህ አዲስ ዘረናና ዘርራፊ ገዥ ቡድን (oligarchy)  የዳበረበት፣ ፍጹም የሆንር ኢፍትሃዊ  የስልጣን፣ የጥቅም፣ የስራ፣ የትምህርት፤ የኢኮኖሚ ወዘተ የነገሱበት፤  አድሎ  የተንሰራፋበት  መሆኑን  የምታውቁትና  የኢትዮጵያ ህዝብም  የሚኖርበት ሃቅ ነው ።
ባሪው የወያኔ አገዛዝ በመጠነ ሰፊ ቅራዎች ተቀስፎ የተያዘ፣ ደካማና ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ የገባ ስዓት ነው።መሪዎ እርስ በርስ የማይተማኑ፣ የጎጥ የሚተያዩ የሚናናቁ ስለመሆናቸው ንቅናቄያችን በርካታ መረጃዎች አሉት።ለስልጣን ያላቸው ስግብግብነትና ዘራፊነታቸው ስላስተሳሰራቸውና ስላያያዛቸው ብቻ በጉልበትበአፈና በሽብርየሚገዙ ናቸው። ራሱ ባወጣው ህገ መንግስት ውስጥ የደነገጋቸውን ዩንቨርሳል ዲክላሬችን ኦፍ ሁማን ራይትስና ሌሎች ህጎችን ሁሉ በየእለቱ እየረገጠ የቀጠለ ስርዓት ነው። በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት (Legitimacy) የሌለው መሆኑን የስርዓቱ መሪዎች ያውቁታል። የዚህን ስርዓት ደካማነትና የፈጠራቸውን ዘርፈ ብዙ ቅራኔዎች የሚመሰክሩት ስርዓቱን ጥለው የሚወጡት  ብቻ አይደሉም፤ በቅርብ ጊዜ አዲሱ ለገሰ የሚባለው መሪ ካድሬ የፃፈውንና በኢሳት የቀረበውን ብዙዎቻችሁ የሰማችሁ ይመስለኛል። ስርዓቱ ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደወደቀ ከፍተኛ የሆነ የአመራር እጦትና በርካታ ሌሎች ችግሮች እንዳሉበት፤ ከግንቦት 7ና ከኦነግ ጋር የሚሰሩ የብአዴንና የኦህዴድ አመራሮች እንዳሉ ወዘተ አዲሱ ለገሰ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪዎች ባቀረበው ሪፖርት ዘርዝሯል። ይህን ተከትሎም በመላው አገሪቱ የሚገኙ 350ሺህ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ኢህአዴግ  የሚባለው የወያኔ መገልገያ ድርጅት አባል ለማድረግ አስገዳጅ ስልጠና መጀመሩን ታውቃላችሁ፡፡
የወያኔ/ህወአት አገልጋይና መሳሪያ የሆነው  ኢሕአዴግ
Hailemriam the puppet
ወያኔዎች ኢህአዴግ በሚባለው ጭንብላቸውና መሳሪያቸው ከዚህ ቀደም እንዳደረጉት አሁንም ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን አስገድዶ የፓርቲ አባል የማድረጉ ሂደት  እድሜያቸውን የሚያራዝም የሚያድን እንደማይሆን እነሱን ከተኩት ከደርግ/ኢሰፓ ስርዓት ትምህርት ለመወስድ ያልቻሉ የአዕምሮ ስንኩላን ስብስብ መሆኑን ዳግም እያረጋገጡ ነው። እነሱ የተኩት ኢሰፓ ሁሉም የህብረተስብ  ክፍል ሁሉም ዜጋ  በግድ አባል ለማድረግ የሞከረ፣ በግለስብና በህዝብ ላይ ፍጹማዊ አገዛዝ (Totalitarian)  ለመዘርጋት ሞክሮ ያልተሳካለት፡ ለውድቀቱም አንዱ መንስኤ አሁን ወያኔ በማድረግ ላይ ያለውን በዜጎችና በህዝብ ላይ ፍላጎቱን በማስገደድ፤ በጉልበት መጫኑ ነበር። በኢሰፓ ርዕዮት አምነው ከልብም ተቀብለው ለፓርቲው ህልውና የታገሉና መስዋዕት የሆኑት ስንቶቹ እንደሆኑ በዚያች ቀውጢ ሰዓት የኢትዮጵያ ህዝብም ራሳቸው ወያኔዎችም የሚያውቁት ነው፡፡
ዜጎችን  በማስገደድ የስልጣናቸውን እድሜ ለማራዘም የስርዓቱ አገልጋይና የአፈና  መሳሪያ ለማድረግ የሚደረገው ይህ ሂደት የፋሽስቱን የወያኔን ስርዓት እድሜ የሚያራዝም አይሆንም። ታሪክ አንዳንዴ ራሱን ስለሚደግም የዚህንም ሂደት ውጤት የምናየው ይሆናል፡፡ ከወደቁ በኋላ መንፈራገጥ ለመላላጥ ከመሆን እንደማያልፍ ጥርጥር የለንም፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የፓርቲ አባላት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰላዮችና አፋኞች አምባገነናዊ ስርዓቶችን – ከሆስኒሙባርክ እስከ ሙአመር ጋዳፊ – ሊያድኗቸው እንዳልቻሉ  የቅርብ ጊዜ ምሳሌዎች ናቸው።
በስርዓቱ ውስጥ የሚገኙ ኢህአዴግ የሚባለው  የህወሃት መሳሪያ የሆነው ድርጅት አባላት አብዛኞቹ ለኑሮ ዋስትና፣ለእለት ጉርስ፣ የስራና የትምህርት እድል ለማግኘት ወዘተ ሲሉ አባል እንደሆኑ እናውቃለን። በኢትዮጵያዊነታቸው በዜግነታቸው ማግኘትና መጎናጸፍ የሚገባቸውን መብቶቻቸውን ለማግኘት ባለመቻላቸውና በመገደዳቸው እንደሆነ  ግልጽ ነው። ለሆዳቸው ሳይሆን ለህሊናቸው ጭምር ተጨንቆ ማሰቢያው ግዜው አሁን ነው፤ ጊዜው ሳይመሽ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር መወገን እንላለን ።
ይህን ስርአት ከውስጡ እንዲታገሉት፤ የስርአቱ መናጆና ባይተዋር ለሆኑት ብዙሃኑ የኢሃአዴግ አባላት ጥሪያችንን እናቀርብላቸዋለን። የወያኔ ስርአት ዘረኛና ዘራፊ፤ የህዝብን መብቶች አፋኝ ስርዓት መሆኑን ከእነሱ በላይ እማኝ እንደሌለ ያውቁታል። ጥቂት ሺዎች የሚመዘብሯትና የሚንደላቀቁባት በአፈና በሽብር የሚገዟት ኢትዮጵያ እንደሆነች እነዚሁ ብዙሃን የኢህአዴግ አባላት ያዉቁታል። የፋሽስቱ ወያኔ ግብዓተ መሬት ሁሉንም ጠራርጎ ወደ ክፉኛ ወድቀትና አይቀሬው ግብዓተ መሬቱ ከመሄዱ በፊት ከህሊና  ጋር ተነጋግሮ ከአፋኞች፣ ገዳዮችና ዘራፊዎች ጋር አብሮ መቆም ሳይሆን በልዩ ልዩ መንገዶች የዚህን አሸባሪና የዘርኝነት ነቀርሳ የተጠናወተው ስርአት ወድቀት እንድታፋጥኑ፤ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንድትቆሙ ጥሪ እናቀርባለን። በታሪክ ሆነ በህግም ፊት ከተጠያቂነት ለመዳን የሚቻለው ለዚህ ስርዓት እድሜ የማራዘም ተግባራትን በመፈጸም ሳይሆን የስርዓቱን እድሜ የሚያሳጥር ተግባራትን በማድረግ ብቻ ነው እንላለን።
የኢህአዴግ የሚባለው የህወት መጠቀሚያ ድርጅትም ሆነ የራሱ የፋሽስቱ የወያኔ ከፍተኛ ባለስልጣኖችና ከፍተኛነራሎች ዛሬ የዘረፉትን የህዝብ ገንዘብበምራብሮችንብረት እየገዙበት ወደ ውጭ ባንኮች ገንብ እያሸሹ እንደሆነበየጊዜው የሚደርሱን በርካታ መረጃዎችአሉ። ቤተስቦቻቸውንም ወደ ውጭ የሚልኩ ጥቂቶች አይደሉም። እንድ እግራቸው አገር ውስጥ ሌላው ወደ ውጭ መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ ብሃኑየስአቱ ተከታዮችና ደጋፊዎች ሊያውቁት ይገባል።
ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ በወያኔ_ስር_የሚገኘው_የመከላከያ_ሰራዊትፍይናል

No comments:

Post a Comment