Translate

Saturday, July 27, 2013

*ዶ/ር ነጋሶ ለአትሌት ኃይሌ ሃሳብ አቀረቡ -“ አንድነት ፓርቲ ይሻልሃል!”

*ዶ/ር ነጋሶ ለአትሌት ኃይሌ ሃሳብ አቀረቡ -“ አንድነት ፓርቲ ይሻልሃል!”
ፖለቲካዊ ወጋችንን የምንጀምረው ሰሞኑን የተፈጠረች አንድ “ህዝባዊ ቀልድ” በመጋራት ነው፡፡ ምን ሆነ መሰላችሁ? ባለፈው ሳምንት የኦሮምያ ክልል ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ሃላፊዎች በሙስና ተጠርጥረው መያዛቸውን ተከትሎ በአካባቢው ውሃ ጠፍቶ ነበር አሉ፡፡ ህዝቡ ምንም ምርጫ ሲያጣ ነገሩን ለበላይ ሃላፊዎች ለማመልከት ተገደደ (ካለመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል አሉ!) የተሰጠው ምላሽ ግን ከእስከዛሬው ለየት ያለ ነው፡፡ “ውሃ የጠፋው በኤግዚቢትነት ተይዞ ነው” ተባለ፡፡ ይሄን እንደሰማው ምን ትዝ እንዳለኝ ታውቃላችሁ? በሙስና ተጠርጥረው የተያዙት ዘጠኙ የኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን ሃላፊዎችና ሲጠፋብን የነበረው መብራት! ከዚያማ የሞኝ ነገር በዚያው ቀጠልኩ፡፡ የዚያን ሰሞን የተከሰተውን የወርቅ መወደድና የዶላር መጥፋት ከታሰሩ የባንክ ሃላፊዎች ጋር አገናኝቼው ቁጭ አልኩ፡፡ (እቺን እቺንማ ማን ብሎኝ!) ከ97 ምርጫ ቀውስ ጋር ተያይዞ የቅንጅት አመራሮች ከታሰሩ በኋላ የፖለቲካ ድርቀት ተከስቶ እንደነበረ ትዝ አይላችሁም ? እኛ ግን በጣም ትዝ ይለናል (በእንጀራችም መጥቶብን ነበራ!) እንዴ ጋዜጣ የሚገዛ እኮ አልነበረም (ፖለቲካ ጠፍቶ ነበራ!) እና ያኔ ፖለቲካው የት ገብቶ ነበር ብዬ አሰብኩ፡፡ ወዲያው መልሱ ብልጭ አለልኝ “ፖሊስ በኤግዚቢትነት ይዞት ነበር!” (ከፖሊስ ማረጋገጫ ባይገኝም) በኋላ ሲፈቱ እኮ በኤግዚቢትነት የተያዘውም ተፈታ፡፡ እኛም እንጀራ መብላት ጀመርን – የአንባቢን የፖለቲካ ጥማት ለማርካት እየሞከርን፡፡ (በኤግዚቢትነት የተያዘው ውሃ አልተለቀቀ ይሆን?)

የነጀማነሽ ማህበር ከነብዩ ኤልያስ ለፓትርያርኩ አመጣን ያሉትን መልእክት ይፋ አደረጉ

አርቲስት ጀማነሽ ሰሎሞንን ያካተተው የማህበረ ሥላሴ ዘደቂቀ ኤልያስ አባላት፣ ለፓትርያርኩ ያመጣነውን “የቅዱስ ኤልያስ” መልእክት የሚቀበለን አጥተናል በማለት ለመገናኛ ብዙሃን ይፋ አደረጉ፡፡ በብሔረ ሕያዋን ይኖራል ከተባለው ነብዩ ኤልያስ ተልከን መልእክታችንን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስ እንዳናደርስ የጥበቃ አባላት ከልክለውናል ያሉት የማህበሩ አባላት፤ ከመልዕክቶቹ መካከል ትክክለኛው ሰንበት ቅዳሜ ስለሆነ በእሁድ ፋንታ በብሔራዊ ደረጃ ታውጆ መከበር ይገባዋል የሚል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ “ኦርቶዶክስ” የሚለውን ስያሜ የሚቃወሙት የማህበሩ አባላት፤ “ተዋህዶ” የተሰኘው እምነት ጥንታዊ የጉባኤ እለታትን ጨምሮ አራት የቅዱሳን መታሰቢያ ቀናት በብሔራዊ በዓልነት ለማስከበር ፓትሪያርኩ ከፌደራል መንግስቱ ጋር መነጋገር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

በሙስና የተጠረጠሩ ዋና ሃላፊዎች እየተፈለጉ ነው

በማሽኖች ግዢና ኪራይ ከፍተኛ ሙስና ፈጽመዋል ተብለው ከሚፈለጉ 25 የኦሮሚያ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ባለስልጣናት መካከል 13ቱ የተያዙ ሲሆን፤ የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅና ምክትላቸውን ጨምሮ ዋና ዋና ሃላፊዎች እስካሁን አልተያዙም፡፡ ዘንድሮ አንድ ሺህ የሚጠጉ ጥቆማዎች እንደቀረቡ የኦሮሚያ ፀረ ሙስና ኮሚሽን የኮሙኒኬሽንና የትምህርት ክፍል ሃላፊ አቶ ጠይብ አባፎጊ፤ ጥቅሞች መነሻነት ከ250 በላይ የምርመራ መዝገቦች ተከፍተዋል፤ የውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ሃላፊዎች ላይ የተከፈተው የምርመራ መዝገቡም ከእነዚህ አንዱ ነው ብለዋል፡፡
የድርጅቱ ቦርድ ዋና ፀሐፊ፣ ዋና ስራአስኪያጅና ምክትላቸው፣ እንዲሁም የፋይናንስና የማሽነሪ ግዢ ሃላፊዎች በፖሊስ እየተፈለጉ ሲሆን፤ መጀመሪያ ላይ የተያዙትን ጨምሮ እስካሁን 13 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተገልጿል፡፡ ተጨማሪ ተጠርጣሪዎች ይኖሩ እንደሆነ የተጠየቁት አቶ ጠይብ፣ ጉዳዩ ከእቃ ግዢና ኪራይ ጋር በተያያዘ ስለሆነ አንዳንድ ባለሀብቶችንም ሊመለከት ይችላል ካሉ በኋላ፣ እስካሁን ግን እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ የኦሮሚያ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዘንድሮ ከከፈታቸው 250 መዝገቦች መካከል፣ 150 ያክሉ ላይ ውሳኔ እንደተሰጠባቸው አቶ ጠይብ ጠቅሰው፣ ተከሳሾች ከ4 ወር እስከ 18 ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣቶችና ተጨማሪ የገንዘብ መቀጮ ተፈርዶባቸዋል ብለዋል፡፡ ኮሚሽኑ በፍ/ቤት ውሳኔ አማካኝነት ከለአራት አመታት ባደረገው ግምገማና በደረሰው ጥቆማበኦሮሚያ ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ወደ መንግስት ካዝና እንዲገባ መደረጉን የገለፁት አቶ ጠይብ በሌሎች የክልሉ መስሪያ ቤቶች ላይ ምርመራው እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
addis admas

ትዝታ ዘ ባንዲራ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዘቀዘቁት ባንዲራ


2012-03-02t171851z_319859376_gm1e83303nh01_rtrmadp_3_kenyaትዝታ ዘ ባንዲራ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዘቀዘቁት ባንዲራ
ትላንት በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ላይ ኢቲቪ አንድ ግለሰብ የሆነ ነገር ሲያውለበልብ አሳየንናተቃዋሚዎቹ  ለባንዲራ የሚሰጠውን ክብር በማንቋሸሽ የተቀዳደደ ባንዲራ ሲያውለበልቡ ነበር ብሎ አሳየን… 1ኛ … ያ ሰውዬ የተቃዋሚዎቹ ተወካይ ስለመሆኑ ምንም ማስረጃ የለም፡፡ 2ኛ የያዘው ነገር ባንዲራ ስለመሆኑም መለየት አልተቻለኝም… የሆነ ሆኖ… ይቺ ዜና ወሬ ከየት ትዝ እንዳለችኝ እንጃላቷ…  ድጋሚ አትሜያታለሁ….

ዘንድሮ ከቀረቡት የሙስና ጥቆማዎች መካከል ከግማሽ በላይ ኮምሽኑን የሚመለከቱ አይደሉም

በጋዜጣው ሪፖርተር
ለፌዴራል የሥነምግባርና የጸረ ሙስና ኮምሽን በ2005 በጀት ዓመት ከቀረቡት የሙስና ጥቆማዎች መካከል በኮምሽኑ ሥልጣን ሥር የሚወድቁት ከግማሽ በታች መሆናቸው ተጠቆመ።
ከኮምሽኑ የተገኘ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እንዳመለከተው በበጀት ዓመቱ ለኮሚሽኑ የቀረቡት 3ሺ710 ጥቆማዎች ሲሆኑ ጥቆማዎቹን የመመዝገብና የመለየት ስራ ተከናውኗል። ከቀረቡት ጥቆማዎች 1ሺ670 (45 በመቶ)በኮሚሽኑ ሥልጣን ሥር የሚወድቁ ሲሆኑ 2ሺ40 (55 በመቶ) ከኮሚሽኑ ስልጣን ክልል ውጪ ሆነዋል። በተጨማሪም ከቀረቡት ጥቆማዎች 42ቱ የከለላ አቤቱታዎች የነበሩ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 21ቹ የመጀመሪያ ከለላ ሲሰጣቸው 16ቱ ከለላ የማያሰጣቸው ሆነው ተገኝተዋል፤ ቀሪዎቹ 5ቱ በመጣራት ላይ ይገኛሉ። ከቀረቡት ጥቆማዎች መካከል ከግማሽ በላይ ኮምሽኑን የሚመለከቱ ሊሆኑ ስላልቻሉበት ምክንያት በሪፖርቱ የተጠቀሰ ነገር የለም።
በበጀት ዓመቱ 508 የምርመራ መዝገቦችን በራስ ኃይል መርምሮ ለማጠናቀቅ ታቅዶ 449 ተመርምረው ተጠናቀዋል። ክንውኑ ዝቅ ሊል የቻለው የበጀት ዓመቱ የአዲስ ሰራተኞች ቅጥር በወቅቱ ባለመፈጸሙ ምክንያት ነው ብሏል።

Friday, July 26, 2013

House of Commons - Dr Wondimu Mekonnen

 የመለስ ዜናዊ የመጀመሪያ ልጅ ሰመሃል መለስ ኒው ዮርክ ውስጥ በሚገኝ አንድ ባንክ ውስጥ 5 ቢሊዮን ዶላር በ2011 ኣስገብታለች። ይህን ያሉት እንግሊዝ አገር እሚገኙት ምሁር እና የመንግስት ተቃዋሚ የሆኑት ዶክተር ወንድሙ መኮንን ናቸው። ዶክተር ወንድሙ የቼኩን ኮፒ አያይዘው ለእንግሊዝ ፓርላማ ሃውስ ኦፍ ኮመንስ አቅርበዋል። ሙሉውን እዚህ ያገኛሉ
A cheque of $5 Billion lodged  by Semhal Meles in New York, Image Courtesy of Dr. Wondimu
De Birhan

Semehal Meles Zenawi, the daughter of the late Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi, has deposited $5 billion in one of the banks in New York.

ImageSemehal Meles Zenawi, the daughter of the late Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi, has deposited $5 billion in one of the banks in New York, said Dr. Wondimu Mekonnen, an academic and opposition figure, said during a recent presentation at the House of Commons in the U.K. The date on the cheque that Wondimu distributed states the money was lodged on October, 2011.

Wondimu also showed and distributed a copy of the cheque of the money she lodged to the members of the House that attended his presentation.

Celebrity Net Worth site said Meles Zenawi got a net worth of $3 billion. What a shame! That is wrong guys. Absolutely wrong. I have got a copy of a cheque signed by Semhal Meles Zenawi, the daughter of Meles Zenawi himself, depositing in one of the New York banks $5 billion. I have got and I will give you the copy. Don’t ask me how it came into our possession but that is a fact.

የመንግሥትን ስም ማጥፋት ማለት የክቡርነታቸውን…? (ፕ/ር መሰፍን ወልደማርያም)

ስም ምንድን ነው? መታወቂያ ነው፤ መጠሪያ ነው፤ ስም ማጥፋት ሲባል ስም አለ ማለት ነው፤ ከስምም አልፎ የገነነ ስም አለ ማለት ነው፤ ስለዚህም ሊጠፋ የሚችለው የገነነ ስም ሲኖር ብቻ ነው ማለት ነው፤ ደራርቱ ቱሉ፣ ፋጡማ ሮባ፣ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ የገነኑ ስሞች ናቸው፤ አንድ ሰው እነዚህን የገነኑ ስሞች አጠፋህ ቢባል ሊገባን ይችላል፤ ዘለቀ ወርዶፋ፣ አየለ ተከስተ ስማቸው ጠፋ ቢባል፣ መጀመሪያ የሚቀርበው ጥያቄ እነማን ናቸው? ዱሮስ የገነነ ስም ነበራቸው ወይ? የሚል ይሆናል፤ ስለዚህ መሰላሉን ያልወጣውን ሰው ውረድ ቢሉት ትርጉም የለውም።

Prof. Mesfin Woldemariam
ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ስም ነው፤ ዘርፈሽዋል ማናለብህ ስም ነው፤ ክቡር ፕሬዚደንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ስም ነው፤ ታደሰ ክፍሎም ስም ነው፤ ደራርቱ ቱሉ ስም ነው፤ ውቢቱ ማስረሻ ስም ነው፤ አዜብ መስፍን ስም ነው፤ ቴዎድሮስ ካሣሁን ስም ነው፤ አበበ ቶላ ስም ነው፤ ሚካኤል በላይነህ ስም ነው፤ ሐጎስ በየነ ስም ነው፤ … እነዚህ ሁሉ ስሞች በመሆናቸው አንድ ቢሆኑም ከእያንዳንዳችን ጋር ባላቸው ግንኙነት ይለያያሉ፤ አንዳንዶቹን እናውቃቸዋለን፤ በተለያዩ መንገዶችም ቢሆን ከኑሮአችን ጋር የተያያዙ ስለሆኑ፣ ያስደስቱናል ወይም ያስከፉናል፤ ስለዚህም ሲያስደስቱን እናወድሳቸዋለን፤ ሲያስስከፉን እንወቅሳቸዋለን፤ ዋናው ጥያቄ የሚመጣው እዚህ ላይ ነው፤

የሰማያዊ ፓርቲ እንቅስቃሴ የወያኔን ቁንጮዎች ስጋት ላይ ጥሏል

ህዝብን ለማስፈራራት በታቀደ መለኩ እንደተለመደው የወያኔ ባለስልጣናት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ እጅግ ስላሰጋቸው የሰማያዊ ፓርቲ እንቅስቃሴ የሚከተለውን አስፍረዋል፣

የሰማያዊው ፓርቲ ጥቁር ተግባራት
ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሕዝባዊ ሰልፍ ላይ ያቀረባቸው ጥያቄዎች የተሰላፊዎች ጥንቅርና መሰረታዊ ዓላማ በእጅጉ አነጋጋሪ ለሆኑ ጉዳዮች መነሻና መንደርደሪያ ሆነውኛል።

ስለተፈናቀሉ ሰዎች ሰማያዊ ፓረቲና መኢአድ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ አስገቡ

ከቤንሻንጉል-ጉምዝና ከደቡብ ክልሎች ለተፈናቀሉ አርሶ አደሮች ጉዳይ መፍትሔ እንዲሰጡ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ የፃፉት ደብዳቤ ምላሽ አለማግኘቱን ሁለት ተቃዋሚ ፓርቲዎች አስታወቁ፡፡

Amhara Ethnic group members Ethiopia
የአርሶ አደሮቹ ጉዳይ መፍትሔ የሚያገኝ ከሆነ መንግሥትን ለመክሰስ በጀመሩት ሂደት እንደሚገፉበትም ተቃዋሚዎቹ መኢአድ እና ሰማያዊ ፓርቲ ጠቁመዋል፡፡

ለሰነበተ የዶ/ር ፈቃደ አዘዘ ጥያቄ መልስ

በክፍሉ ሁሴን  

The Ethiopian Air Force is the air arm of the Ethiopian National Defense Forcesአፍቃሪ ወያኔ የፌስቡክ ወዳጄ “ሰላማዊት ስዮም”በጣለችልኝ የፍልሚያ ሸማ መሰረት ምላሹን ልሰጥ ለዛሬ ቃል ገብቼ ነበር።ሰላማዊት “እስቲ ስለዘንድሮ ፓይለቶች (ወያኔ የአየር ሃይል ፓይለት ይሁኑልኝ ብሎ በትዕዛዝ ወይም በአብዮታዊ ዴሞክራሲ አግባብ “ፓይለት” የሆኑትን ማለቷ ነው) አውቃለሁ የምትለውን ያህል ስለድሮዎቹ በሐውዜንና በመሳሰሉ ቦታዎች በገበያ ላይ ቦምብ እየጣሉ ሰላማዊ ሕዝብ ስለፈጁት ፓይለቶች ደም ከውሃ ይወፍራል በሚለው አይነት ሳትደብቅ ንገረን፤ለልጆችህም ንገራቸው (አባቴ የኢትዮጲያ ንጉሰ ነገሥት መንግስት አየር ሃይል ቆፍጣና መኮንንና ፓይለት የነበረ መሆኑን ዘወትር በኩራት የማነሳውን ተሸማቅቆ ሁለተኛ አያነሳውም በሚል የተወረወረ ወያኔያዊ አሽሙር መሆኑ ነው) ስትል “ተፈታተነችኝ።” ለእሷም ሆነ የታሪክን ሚዛን ለመጠበቅ ሲባል ምላሹን ለዛሬ ይዤ ለመቅረብ ቃል ስገባ እስከዚያው የዶ/ር ፈቃደ አዘዘን “ዲሞክራት ፓይለቶች”የሚለውን ግጥሙን ‘አያ ጎሽሜ’በሚል ርዕስ ካሰተመው መድብሉ እያነበባችሁ ጠብቁኝ ማለትን ዘነጋሁ።ግድየለም ይህ ምላሽ ካልተንዛዛ እዚሁ ላነሳው እሞክራለሁ።አሁን ወደ ጭብጡ።

‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ በወባ ከሚሞተው ይልቅ በፖለቲካ ጦስ እና ችግር የሚጎዳው በቁጥር ይልቃል›› ተመስገን ደሳለኝ – [ጋዜጠኛ]

ኢትዮጵያን ማን ይታደጋትበተሰኘውና በቅርቡ ኢትዮጵያ ውስጥ ታትሞ በገበያ ላይ በዋለው መፅሀፍ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ  የሰጠው ቃለ – ምልልስ የሚከተለውን ይመስላል፡፡ ዘ-ሐበሻ ድረገጽ ለግንዛቤ በሚል ለአንባቢዎቹ እንደወረደ አቅርቦታል
‹‹ተመስገን ደሳለኝ ጋዜጠኛ ሳይሆን የፀረ-ኢሕአዴግ ፖለቲካ አቀንቃኝ ነው›› ሲሉ ጋዜጠኛነቱ ላይ ጥያቄ የሚያቀርቡ ወገኖች የመኖራቸውን ያህል ከብዙ ፓርቲዎች በተሻለ ገዢው ፓርቲን በብዕሩ የታገለ፣ ጋዜጣ አንባቢው ኅብረተሰብ ከፖለቲካዊ ፍርሃት እንዲላቀቅ በጽናት የጣረ፣ የቁርጥ ቀን ጋዜጠኛ መሆኑን ምስክርነት የሚሰጡለትም አሉ። አራት ዓመት ገበያ ላይ በቆየችው ፍትሕ ጋዜጣ፣ ታይተው በጠፉት አዲስ ታይምስ መጽሔትና ልዕልና ጋዜጣ ላይ ባሰፈራቸው መጣጥፎቹ የመነጋገሪያ ርዕስ የነበረው ተመስገን ለእሱ በተሰጡ ቀጣይዎቹ ገጾች ላይ ከእዚህ መጽሐፍ አዘጋጆች የቀረቡለትን ሞጋች ጥያቄዎች በመመለስ የ‹‹ኢትዮጵያን ማን ይታደጋት?›› አካል ሆኗል።
በልጅነትህ ምን መሆን ትፈልጋለህ ስትባል ምላሽህ ምን ነበር?
ያደግኩት ፊት በር አካባቢ ነው። ይህ ሰፈር ደግሞ በአዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙ በርካታ የደሀ ሰፈሮች አንደኛው ነው።

የናሳ ተመራማሪ የዶክተር ጥላዬ የህይወት ጉዞ – “ከእረኝነት ወደ ናሳ ተመራማሪነት”


source – shegarmedia

ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ በኢትዮጵያ ታሪክ የት-መጣነት(origin) ጉዳይ ባደረጉት ጥናት ላይ የተደረገ ቃለ መጠይቅ (ኦድዮ)

”እኛ ኢትዮጵያውያን ታላቅ ሕዝብ ነን።እራሳችንን ዝቅ ማድረግ አይገባንም።ለምን ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አለች አሁን? ይህ ማለት ኢትዮጵያን ያስጠሩ ሰዎች ቀድመው ነበሩ ማለት ነው።……ቀድሞ ‘ኢትዮጵ’ የሚባል ሰው ስለነበረ ነው።ለሀገር ሲሆን ‘ኢትዮጵያ’ አሰኛት እናም ከእርሱ ዘር የተወለድነው ሁሉ ኢትዮጵያውያን እንባላለን።እኔ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ጃማይካ ነኝ ወዘተ ብልም ሃቁ እንዳፈጠጠ አለ።ይህ ሰው የኢትዮጵ ልጅ ስለሆንኩ እኔ ሁላችንም ብታምኑም ባታምኑም፣ብትክዱትም ባትክዱትም  ሁላችንም የእርሱ ልጅ ነን።እርሱ ከየት መጣ ለሚለው በሚወጣው መፅሐፌ ላይ ተዘርዝሯል። እኛ ኢትዮጵያውያን ከየት እንደመጣን ከስር መሠረታችን የሚታወቅ እንጂ ሜዳ ላይ የተጠልን አይደለንም።ማንነታችን በትክክል የተመዘገበ እና የታወቀ ከማንም በላይ በእዚህ ምድር ላይ ከአይሁዳውያንም ቀዳሚ ነን።”

የሰማያዊ ፓርቲ ጥያቄ እና የመንግስት ምላሽ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ገፅ 3 (አጀንዳ)

የሰማያዊው ፓርቲ ጥቁር ተግባራት ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሕዝባዊ ሰልፍ ላይ ያቀረባቸው ጥያቄዎች የተሰላፊዎች ጥንቅርና መሰረታዊ ዓላማ በእጅጉ አነጋጋሪ ለሆኑ ጉዳዮች መነሻና መንደርደሪያ ሆነውኛል። ሰማያዊ ፓርቲ ከአንድነት ፓርቲ ባለመስማማትና በልዩነት ራሳቸውን ያገለሉ፣ መርህ ይከበር በሚል ተሰባስበው የነበሩ ግለሰቦች የመሰረቱት ፓርቲ ነው፡፡ ወደ ኋላ ስንመለስም በ1997 ዓ.ም ቅንጅትን ከመሰረቱትና የከሸፈውን አመጽ በማስተባበርና በመምራት ከፊትና ከኋላ የነበሩ፤ ዛሬ ደግሞ የቀድሞውን ማንነታቸውን ሳይለቁ በአዲስ መልክና በአዲስ ኮፍያ ለመንቀሳቀስ እየሞከሩ ያሉ ናቸው፡፡ አንድ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ሕገ መንግስቱ በሰጠው መብት በሰላምና በሕጋዊ መንገድ ሕጉንና ስርዓቱን አሟልቶ መንቀሳቀስ ይጠበቅበታል፡፡ ሰማያዊም ፓርቲ ሆነ ሌሎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በውጭ ከሚገኘው ጽንፈኛና አክራሪ ኃይል ጋር በመቀናጀት በአረቡ ዓለም የታየውን አብዮት ወደ ኢትዮጵያ እናመጣለን በሚል ለረዥም ጊዜያት ውስጥ ውስጡን ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል፡፡

ውጤት አልባው ፀረ ሽብር ትግል በሶማሊያ የኬንያ፣ የታንዛኒያና የብሩንዲ አክራሪዎችም ከአልሸባብ ጐን ቆመዋል

ውጤት አልባው ፀረ ሽብር ትግል በሶማሊያ
-    ኤርትራ የጦር መሣሪያ ድጋፏን ቀጥላለች
-    የኬንያ፣ የታንዛኒያና የብሩንዲ አክራሪዎችም ከአልሸባብ ጐን ቆመዋል
-    ቻይናን ያቋረጡ ፈንጂዎች አልሸባብ እጅ ደርሰዋል

ለመለስ ሙት አመት ማስታወሻ (ከፋሲል የኔአለም) ጋዜጠኛ

ከመለስ ሞት በሁዋላ ያለው የኢትዮጵያ ሁኔታ ከሌኒን ሞት በሁዋላ የነበረውን የሩስያ ሁኔታ ያስታውሰኛል። ሌኒን በቦልሼቪክ ፓርቲ ውስጥ የገዘፈ ስም ነበረው፣ በፓርቲው ውስጥ ያሰፈነው የዲሞክራሲያዊ ማእከላዊነት አሰራር የምእራቡን ዲሞክራሲን ለማይቀበለው የኮሚኒስት ታጋይ ሁሉ የሚመች ነበር ፤ በዲሞክራሲያዊ ማእከላዊነት መርህ መሰረት ማንም የድርጅቱ አባል የሆነ ሰው እንደልቡ መናገር ይፈቀድለታል፣ ውሳኔ ከተላለፈ በሁዋላ ግና ውሳኔውን ያለምንም ማቅማማት ይተገብራል። ሌኒን ሲሞት የሌኒንን ቦታ ለመያዝ ይቋምጥ የነበረው ስታሊን የመጀመሪያ እቅዱ ይህን የዲሞክራሲያዊ ማእከላዊነትን አሰራር ማፍረስ ነበር። ስታሊን ተናግሮ የማሳመን ወይም አዳዲስ ሃሳቦችን የማፍለቅ ስጦታ ወይም ችሎታ አልነበረውም። ትሮትስኪን የመሳሰሉ፣ ከስታሊን የተሻለ አስተሳሰብ እና ብቃት የነበራቸው፣ ሰዎች የዲሞክራሲያዊ ማእከላዊነትን አሰራር ተጠቅመው ወደ ስልጣን የሚመጡበት እድል ከፍተኛ ነበር፤ ስታሊን ይህንን አሰራር ካላስቆመው በስተቀር በክርክር የመሪነቱን ስልጣን ሊይዝ የሚችልበት እድል አልነበረውም፣ አፈረሰው።

Wednesday, July 24, 2013

የኃይሌ ወደ ፖለቲካው መድረክ መምጣት እያነጋገረ ነው

haile_flag

“ኃይሌ ወደ ፖለቲካ መግባቱ መብቱ ቢሆንም እንደስፖርቱ በፖለቲካውም የሚያንጸባርቅ አይመስለኝም” ዶ/ር መረራ

እስቲ እረጋ ብለን ደግሞ እንነጋገር… “ጭርቁምፈምቶታ ኡመታ ኢትዮጵያ”

1057430_650235654989038_1014715955_n
Abe Tokchaw
እስቲ እረጋ ብለን ደግሞ እንነጋገር…  ”ጭርቁምፈምቶታ ኡመታ ኢትዮጵያ” ወንድማችን
ጃዋር መሀመድ እኔን ጨምሮ በርካቶች የሚያደንቁት ወጣት ነው፡፡ ሀሳቦቹ አንጀት ላይ ጠብ የሚሉ ገዢ ሀሳቦች ናቸው፡፡ የሚገዙት ታድያ እንደ ገዢው ፓርቲ አስገድደው አይደለም፡፡ ጃዋር ወደው ፈቅደው የሚገዙላቸው ሀሳቦች ባለቤት ነው፡፡ እኔ ከጃዋር ሀሳቦች ጋር በቅጡ የተዋወቅሁት የቱኒዚያ አብዮት የተቀሰቀሰ ሰሞን ነበር፡፡ ስለ ቱኒዚያ እና ግብፅ አብዮቶች መንስኤ፤ አስፈላጊነታቸው  እና ውጤታማነታቸው ጃዋር ከፃፈው በተሸለ ገብቶኝ እና ተመችቶኝ ያነበብኩት መኖሩን እንጃ…
ከዛም በኋላ ጃዋር የሚሰጣቸውን ትንታኔዎች ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ እሰማለሁ፡፡ ሰምቼም እስማማለሁ፡፡ ምን መስማማት ብቻ፤ የሆነ ቀን ጃዋር ምርጫ
ቢወዳደር ይምራኝ ብዬ የምመርጠው ሁሉ እስኪሆን ድረስ አክባሪው ሆኛለሁ…!
ከእለታት በአንዱ ቀን እኛ “በፌስ ቡክ አስተዳደር የኢህአዴግ ዋና የስራ ሂደት ባለቤት” የምንለው ዳንኤል በርሄ በአሁኑ ሰዓት በአልጀዚራ የሚተላለፈውን እባክችሁ ቅዱልኝ ብሎ ተማፅኖ ሲያሰማ “እኔ እንደ እናንተ አይደለሁም” በሚል “ሙድ” ልቀዳለት ወደ አልጀዚራ ጎራ አልኩ… የማከብረው ጃዋር በአልጀዚራ ስቱዲዮ ጉብ ብሏል፡፡ እውነቱን ለመናገር ጃዋርን ባየሁት ጊዜ ኖራ…  ብዬ አባቴ የሚያከብረው ሰው ሲመጣ እንደሚያደርገው በአክብሮት ከመቀመጫዬ ተነስቻለሁ…

Tuesday, July 23, 2013

ሰበር ዜና: ኢህአዴግ አንድነት ፓርቲን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ

በደቡብ ወሎ ዞን በሚገኘው ኩታበር ወረዳ አንድነት ፓርቲ ሐምሌ 7 ቀን 2005ዓ.ም. በደሴ ያካሄደውን ህዝባዊ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በመቃወም ህዝቡ ሰላማዊ እንዲወጣ ኢህአዴግ እያስገደደ መሆኑን ምንጮቻችን በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡
የኩታበር ወረዳ ነዋሪ ሰልፍ እንዲወጣ የተደረገው ነገ ረቡዕ ሐምሌ 17 ቀን 2005 ዓ.ም. ጠዋት መሆኑም ታውቋል፡፡ በተለይ ሰፊ የማስፈረሳሪያና የቅስቀሳ ስራ እየተካሄደ ያለው በወረዳው ቀበሌ 05፣06 እና 07 መሆኑንም ምንጮቻችን ጨምረው ገልፀዋል፡፡EPRDF-logo
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢህአዴግ ካድሬዎች ገበሬውን በግድ ከአቅሙ በላይ የዘር ማዳበሪያ ውሰዱ እያሉ ከፍተኛ ገንዘብ ከማስከፈላቸው በተጨማሪ ለአልማ(ለአማራ ልማት ማኀበር)፣ለአባይ፣ ለመሬት ግብር እየተባሉ ከፍተኛ ዋጋ በመጠየቃቸው እና ነዋሪዎቹ አቅማቸው እንደማይፈቅድ ሲናገሩ ወደ እስር ቤት እየተወሰዱ በመሆኑ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ከአካባቢው እየተሰደዱ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡ ማዳበሪያና ዘር አንወስድም ያሉ ገበሬዎችንም መሬታችሁ ይነጠቃል በሚል የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ደምሴን ጨምሮ የወረዳው ሹማምንት እያስገደዱ እንደሆነ ነዋሪዎቹ በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡
ስለጉዳዩ የዝግጅቱ ክፍሉ የወረዳውን አስተዳደር አቶ ደምሴን እና የወረዳውን ግብርና ጽህፈት ቤትና የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችን ለማናገር ጥረት ቢደረግም አልተሳካም፡፡
#milloinsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ
- See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=5069#sthash.gOzowTbJ.dpuf

ሰበር ዜና፣ አዲስ አበባ ከተማ በግድግዳ ጽሁፎች (ግራፊቲ) ተሸፍና አደረች

ድምፃችን ይሰማ

ሰኞ ሐምሌ 15/2005
እሁድ ምሽት ለሰኞ አጥቢያ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ቦታዎች የሙስሊሙን ህብረተሰብ ጥያቄዎች በሚያንጸባርቁ ጥቅሶች ተጽፎባቸው አደሩ፡፡ በከተማዋ የተለያዩ መንገዶች፣ የመንገድ አካፋዮች እና አጥሮች ላይ መንግስት ሕገ መንግሰቱን እንዲያከብርና በእምነት ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆም የሚጠይቁ ጽሁፎች በትላልቅ ቁመት ለህዝብ በሚታይ መልኩ ተጽፈው የተገኙ ሲሆን ይህ በተጻፈባቸው ቦታዎችም ሰዎች ሁኔታውን በትኩረትና በግርምት ሲመለከቱ እንደነበር ታውቋል፡፡Ethiopian Muslims protest, Addis Ababa1
በካዛንቺስ፣ በጦርሀይሎች በውንጌት አስኮ መንገድ እንዲሁም ገና በውል ባልታወቁ ቦታዎች ደምጻችን ይሰማ፣ ኮሚቴው ይፈታ፣ ሕገ መንግስቱ ይከበር፣ ጥያቄያችን ይመለስ፣ በእምነታችን ጣልቃ አትግቡብን የሚሉ ጽሁፎች ተጽፈው የታዩ ሲሆን በካባቢው የሚገኙ የወረዳ አስተዳደሮችም በተፈጠረው ነገር በመደናገጥ ጽሁፎቹን ለማጥፋት ጥረት እያደረጉ ይገኛል፡፡ የጎዳና እና የግድግዳ ጽሁፎች በአለም የታወቁ የመቃወሚያ ዘዴዎች በመሆናቸው ህብረተሰቡ መልእክቱን ለሚመለከተው አካል ለማድረስ የሚጠቀምባቸው ናቸው፡፡

Friday, July 19, 2013

በአንድ ሳምንት ሁለተኛ አደጋ!

“አውሮፕላኑ አየር ላይ እያለ ሊፈነዳ ይችል ነበር”


ethiopian
ከአዲስ አበባ ወደ አክሱም ይጓዝ የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ረቡዕ ለት በጭንቅ እንዲያርፍ መደረጉ ተገለጸ፡፡ አደጋው ከአምስት ደቂቃ በፊት ቢከሰት ኖሮ አውሮፕላኑ አየር ላይ እያለ ሊፈነዳ ይችል እንደነበር ባለሥልጣናት አስታወቁ፡፡

ፍልስፍና አልባ የሆነ ፖለቲካ የአንድን ህብረተሰብ አስተሳሰብ ያዘበራርቃል

የመጨረሻ መጨረሻም አገርን ያወድማል!

political philosophy

የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ ግብረ ኃይል ቀጣይ እቅዱን ይፋ አደረገ

Millions of voices for freedom - UDJየአንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ ግብረ ኃይል ዛሬ ሐምሌ 11,2005 ዓ.ም ከረፋዱ 4 ሰዓት ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ቀጣይ የህዝባው ንቅናቄ ዕቅዱን አፅድቋል፡፡

በዚሁም መሰረት በሚቀጥሉት የሀገራችን ከተሞች ህዝባዊ ስብሰባዎችንና ታላላቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎችን ጠርቷል፡፡ በየክልሉ ያሉ የአንድነት ፓርቲ ድርጅታዊ መዋቅሮችለፓርቲው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ግብረኃይሉ ያቀዳቸው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች ከአዲስ አበባ አስቀድሞ በክልል ከተሞች ለማድረግ የተወሰነ ሲሆን የህዝባዊ ንቅናቄው ማጠቃለያ የሚሆነው መስከረም አምስት ቀን 2006ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚደረገው ታላቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ይሆናል፡፡ ግብረ ኃይሉ መስከረም 5, 2006 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ያቀደው ሰላማዊ ታጋዮቹ አንዱአለም አራጌና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የታሰሩበትን ሁለተኛ አመት ለመዘከር እንደሆነ ታውቋል፡፡

“ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የምናደርገው ትግል በስም ማጥፋትና በፍረጃ አይገታም!” ሰማያዊ ፓርቲ

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
Statement from Semayawi party of Ethiopia, regarding Nile issue.ሰማያዊ ፓርቲ በሃገራችን የሚፈፀሙ የሰብአዊ መብት ጥሰትና የአስተዳደር ብልሹነት እንዲስተካከል የመንግሥት አካላት አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ በተደጋጋሚ ሲጠይቅ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ነገርግን እነዚህ ጥያቄዎቻችን በመንግሥት በኩል ምላሽ ስለተነፈጋቸው ጥያቄዎቹ ከፍ ባለደረጃ ትኩረት እንዲያገኙ ሆነው መቅረብ እንዳለባቸው ተገንዝበናል፡፡ በዚህም መሰረት ጥያቄዎቹን በሰላማዊ ሰልፍ መጠየቅ እንዳለበት ወስኖ ግንቦት 25 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም በአዲስ አበባ ባካሔደው ታላቅ ሠላማዊ ሠልፍ ጥያቄዎቹ እንዲመለሱ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡ በተጨማሪም ጥያቄዎቻችን ከመንግሥት በኩል በሦስት ወር ጊዜ ምላሽ የማያገኙ ከሆነ ሌላ የተቃውሞ ሠልፍ ከፍ ባለ ደረጃ የሚጠራ ስለመሆኑ ፓርቲው አቋሙን በሰልፉ ዕለት አሳውቋል፡፡

ከፍተኛ የሙስና ወንጀል ሲጋለጥ

(ከኢየሩሳሌም አርአያ)
ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከአቶ ገ/ዋህድ፣ አቶ ነጋና ምህረተአብ ጋር በመመሳጠር በሶስት መርከብ ስሚንቶ አስጭነው አገር ውስጥ በማስገባት ከፍተኛ የሙስና ወንጀል መፈፀማቸውን ምንጮች አጋለጡ። በተከለከለ ፍራንኮ ቫሉታ ፈቃድ አገር ቤት የገባው ስሚንቶ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ትርፍ አዜብና ግብረአበሮቻቸው እንደዛቁበት ያረጋገጡት ምንጮቹ፣ አያይዘውም ጉዳዩ በደህንነት ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ እጅ እንደገባ አስታውቀዋል። በሕገወጥ መንገድ የውጭ ምንዛሪ በከፍተኛ ደረጃ በመመደብና አስፈላጊውን ትእዛዝ በመስጠት እንዲሁም የጥቅም ተካፋይ በመሆን ግንባር ቀደም ሚና የተጫወቱት አዜብ መስፍን ከዚህ ድርጊታቸው በተጨማሪ ከዚህ ቀደም ከስሚንቶው ጋር በተያያዘ ተመስርቶ የነበረውን ክስ እንዲቋረጥ ማድረጋቸውን የጠቆሙት ምንጮች፣ ይህና ሌሎች ተያያዥ የወንጀል ድርጊቶችን የሚያስረዱ ማስረጃዎች በአቶ ጌታቸው እጅ እንደገቡ አረጋግጠዋል።

Thursday, July 18, 2013

ኢህአዴግ በሩን እንዲከፍት የዓለም ባንክ አዘዘ

የማነቂያው ገመድ ከርሯል፤ “ትግሉ ይቀጥላል” ኦባንግ ሜቶ

world-bank
ኢህአዴግ ለሚገዛት ኢትዮጵያ ከፍተኛ መጠን ያለው ዕርዳታ የሚሠጠው የዓለም ባንክ፤ ለዕርዳታና ልማት የሚልከው ገንዘብ ኢህአዴግ የሕዝቡን ሰብዓዊ መብት ለመጣስ ተጠቅሞበታል በሚል ሙሉ ምርመራ እንዲካሄድ አዘዘ፡፡ የባንኩ ውሳኔ ኢህአዴግን የማነቂያው ገመድ እንደሚያከረው ተገለጸ፡፡ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ በተለይ ለጎልጉል በሰጡት መግለጫ “ይህ በጥናት ከምናካሂደው ትግል አንዱ ውጤት ነው፤ ገና ጅማሬ ነው፤ ጠንክረን እንሠራለን” አሉ፡፡

ግልጽ ደብዳቤ ለሃይሌ ገብረሥላሴ

Wednesday, July 17, 2013

የአውሮፓ ፓርላማ ልዑካን በኢትዮጵያ


ፀረ ሽብር የተባለውን ደንብ ነቅፈናል። አንቀጹ የሚያሻማ፣ ግልጽ ባልሆኑ አንቀጾች የተቀመጠ ነው። ሰዎች በዚህ ሳቢያ ራሥረዋል። ስለሆነም የህግ አውጪው ፣ ተርጓሚውና አስፈጻሚው ዘርፍ ፤ ነጻነት በተሃድሶ ለውጥ ሊቀየር ብለን እናስባለን ። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ እሥር ቤቶች የታሣሪዎች ይዞታ እንዲታይ የሚል አቋም ነው ያለው ።
ኢትዮጵያን ለ3 ቀናት የጎበኘው የአውሮፓ ፓርላማ የሰብዓዊ መብት ልዑካን ቡድን ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች የተያዙበትን እስርቤት እንዳይጎበኝ ተከለለ ። ከአዲስ አበባ የወጡ ዘገባዎች እንዳመለከቱት ቡድኑ እስር ቤቱን እንዲጎበኝ ፈቃድ አግኝቶ ነበር ። የልዑካን ቡድኑ የኢትዮጵያ መንግሥት የታሰሩትን ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች እንዲፈታ ጠይቋል ። 

Tuesday, July 16, 2013

ድል መሰዋትነት ይፈልጋል!

ከተስፋዬ ዘነበ (ኖርዌይ በርገን) Ethiocenter.blogspot.com

Author and writer Tesfaye Zenebe from Norway
ከተስፋዬ ዘነበ (ኖርዌይ በርገን)
ሃብትና ስልጣን አስክሮአቸው፣ በዚህች ደሃ ሃገርና ሕዝብ ላይ ተፈናጠው ሁለት አስርተ አመታት ያስቆጠሩ አምባገነን መሪዎቻችን የሃገርና የሕዝበ ፍቅር አጥተው  በምዝበራ ለመክበር ብቻ፣ ሕዝብንም በሃገሩ በሰላም የመኖር መብቱን ቀምተው ተደላድለው ለመቀመጥ ዘንድሮም እንደ አምናው በሽብር ስም በጫኑብን የአፈና መረብ ሸብበው ሕዝቡን ከዳር እዳር ማስጨነቃቸው ሳያንስ አሁን ደግሞ ለዚህ እኩይ ተልኳቸው ላሰለጠኑዋቸው  የስርዓቱ ሰዎች (ደህንነቶች) በዴሞክራሲና በመልካም አስተዳደር ችግር ከኑሮው ጋር ደፋ ቀና የሚለውን ሰላማዊ ሕዝብ  የሚያሰቃዩበትንና ባስም ሲል የሚገሉበትን ህጋዊ ፈቃድ ሰጥተዋቸዋል፡፡

ትንሽ ስለጃዋራዊያን

by Fasil Yenealem (facebook)

የጃዋር ንግግር ያበሳጫቸው ብዙ የፌስ ቡክ ወዳጆቻችን ቁጣቸውን በቻሉት መንገድ ሁሉ እየገለጹ ነው። ነገሩ ከቁጣ ወይም ከውግዘት ወይም ከይቅርታ መጠየቅ ወይም አቋምን ከመግለጽ ባለፈ በደንብ ተብላልቶ መታየት ያለበት ይመስለኛል። በመጀመሪያ ፣ ጃዋር የዚህ ትውልድ ( የህወሀት ዘመን ልጅ ነው)። እርሱ ቢክደውም ፣ የአብዮታዊ ዲሞክራሲን የብሄር ፖለቲካ ጡጦ እየተጋተ ያደገ ልጅ ነው። የብሄር ፖለቲካን ለመጋት የግድ የህወሀት አባል መሆን አይጠይቅም፤ በማርክስ አስተምህሮ መሰረት የገዢው ፓርቲ ርእዮትዓለም የተገዢዎች ርእዮትዓለም ሆኖ የሚያገለግልበት እድል ሰፊ ነው። በተለይ ነጻ አስተሳሰቦች እንደልባቸው በማይንሸራሸሩበት ወይም ፕሮፓጋንዳው ሁሉ ከአንድ ኩሬ በሚፈልቅበት አገር የገዢው ፓርቲ ርእዮትዓለም በተለይ በወጣቶች አስተሳሰብ ላይ ተጽእኖ ማሳደሩ አይቀሬ ነው።

Monday, July 15, 2013

ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በፖሊስ የታሰሩት የአንድነት አባላት ከ42 ደርሰዋል ከታሳሪዎቹ ውስጥ ሁለት ሴቶች ይገኙበታል

ሰበር ዜና

ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በፖሊስ የታሰሩት የአንድነት አባላት ከ42 ደርሰዋል ከታሳሪዎቹ ውስጥ ሁለት ሴቶች ይገኙበታል
Millions of voices for freedom - UDJዛሬ ሐምሌ 8 ቀን 2005 ዓ.ም መንግስት የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን የወረዳ አመራሮችንና አባላትን በዘመቻ ማሰር ጀምሯል፡፡ እስከአሁኗ ሰዓትም 42 የሚሆኑ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አባላት በፖሊሲ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ፡፡ የፍኖተ ነፃነት ጋዜጠኞች ተዘዋውረው እንደዘገቡት 42 የሚሆኑ የአንድነት ፓርቲ አባላት በፖሊስ እንዲታሰሩ ተደርጓል፡፡ የአንድነት ፓርቲ በአዲስ አበባ እያሰራጨ ያለውን ህጋዊ በራሪ ወረቀት ለህዝብ በማደላቸው የተያዙት አባላት ከአዲስ ከተማ 15፣ ከጉለሌ7 ፣ ከየካ 9 እንዲሁም ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ናቸው፡፡
የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው ህዝባዊ ንቅናቄ የተደናገጠ የሚመስለው ኢህአዴግ በየአካባቢው የአንድነት አባላትን ምክንያት እየፈለገ ማገትና ማሰሩን ገፍቶበታል፡፡

የሚወለዱበት፣ የሚሞቱለትና የሚሞቱበት መሬት

Prof. Mesfin Woldemariamየሚወለድበትን መሬት ማንም ሰው አይመርጥም፤ የዘመኑ ቅንጦት ኢትዮጵያ አርግዞ አሜሪካ መውለድ ቢሆንም፣ ልጁ ምርጫው ውስጥ የለበትም፤ አንኳን ልጁ አባትዬውም ምርጫው ውስጥ የሚገባ አይመስለኝም፤ በእንደዚህ ያለው ኢትዮጵያን አስጠልቶ-ሌላ-እንዲሆን በተፈጠረ ቅንጦት የሚወለድ ኢትዮጵያዊ ምን እንደሚሆን መተንበይ ያዳግታል፤ ልጁ ወይም ልጅቱ በራሳቸው ዝንባሌ፣ ፍላጎትና ጥረት ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው ግንኙነት በእልህ ከአልተለወጠ እናቶቻቸው የተለሙላቸው ማንነት ከኢትዮጵያዊነት ይገነጥላቸዋል፤ ነገር ግን የኢትዮጵያዊነት ስሜት እንዲህ በቀላሉ ተቀርፎ የሚወድቅ አይደለም፤ ሲደንቀኝ የቆየ ነገር ልናገር፤ አንድ ጊዜ በኢሰመጉ ተልእኮ ካናዳ ሄጄ አንድ ስብሰባ ላይ አንድ አርመን ወጣት ነበረ፤ ይህ ሰው ለኢትዮጵያ ያለው ስሜት በጣም የጋለ ነበር፤ በሌላ ዘመን ደግሞ ፋጡማ ሮባ በአትላንታ ማራቶን በአሸነፈች ጊዜ ደግሞ በቴክሳስ የሚኖር ከአንድ ግሪክ ገንፍሎ የወጣው ንግግር በጣም ልብን የሚነካ ነበር፤ ለዚህ አርመንና ለዚህ ግሪክ የኢትዮጵያዊነት ስሜት በዘር የተላለፈላቸው አይመስለኝም፤ ስለዚህም አሜሪካ የሚወለዱትም ኢትዮጵያውያን ልጆች እናቶቻቸው ሳያውቁ ከውስጣቸው የሚያስተላልፉላቸው ስሜት ኢትዮጵያዊነታቸውን ይገነባው ይሆናል፤

Sunday, July 14, 2013

ድሃው ሕዝብ ጉዳዩን ማስፈጸም አይችልም

"ጉቦኝነት 44% ሆኗል"

city“ዕድገት”፣ “ትራንስፎርሜሽን”፣ “ህዳሴ”፣ “የመለስ ውርስ (ሌጋሲ)”፣ … በሚመሯት ኢትዮጵያ ሙስና እየከፋ መሄዱ ታወቀ፤ ከመቶ ሰዎች ውስጥ ከ40 በላይ የሚሆኑት ጉቦ የሚሰጡ መሆናቸውን አስታወቁ፡፡

በቦንድ ሽያጭ ያልተሳካው የገንዘብ ዘረፋ በኮንደሚኒየም ሰበብ መሳካት የለበትም!

Ginbot 7 weekly editorialወያኔ  በጠመንጃ ኃይል ሥልጣን ከተቆጣጠረበት 1983 ጀምሮ በከተሞች አካባቢ ምንም አይነት ሕዝባዊ ተቀባይነት ኖሮት አያውቅም :: ለዚህም የሚሰጠው  ምክንያት ከተሞች በጠላትነት በተፈረጀው አማራና የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂዎች የተሞሉ ስለሆነ ነው ይላል::  ዋና ከተማችን  አዲስ አበባ በዚህ ውንጀላ ዋጋ ከከፈሉት ከተሞች ግንባር ቀደሟ ናት :: በተለይ በመጀመሪያው የወያኔ 10 (አሥር) የሥልጣን አመታት የከተማዋን የነዋሪዎች አሰፋፈር ስብጥር ሆን ብሎ  ለመቀየር ከመሞከር ጀምሮ የተለያዩ የአገልግሎት መስጫ ተቋሞችን አቅም ለማዳከም በርካታ አሳዛኝ እርምጃዎች ተወስደዋል ::

ታሪክን ወደኋላ መለስ ብለን እንቃኝ። የፋሺስት ጣልያን ጦር በእንግሊዝ ጦር ትብብር በኢትዮጵያ አርበኞች  ከተደመሰሰ በኋላ በአሸናፊነው ወደከተሞች የገባው የእንግሊዝ ጦር ያገኘውን ንብረት በወቅቱ የቅኝ ግዛቶቹ ወደ ነበሩት ኬንያና ሱማሌ አሽሽቷል። ከብዙ ዓስርተ ዓመታት በኋላ ወያኔ ይህንኑ እኩይ ተግባር ደገመው።

አንድነት ፓርቲ በጎንደር እና ደሴ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በድምቀት ተካሄደ

(ECADF) – ሰሞኑን የአንድነት ፓርቲ አመራር አባላት በጎንደርና ደሴ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ሲያስተላልፉና ቅስቀሳ ሲያደርጉ ነው የከረሙት። ሂደቱ በራሱ ከፍተኛ ትግል የተካሄደበት ነበር፣ አባላቱ ሲታሰሩ ሲፈቱ ከርመዋል፣ በደሴ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ የአንድነት አመራር አባላት በቀን ውስጥ ሁለት ጊዜ ታስረው ተፈተዋል። ኢህአዴግ/ወያኔ ሰልፉን በቀጥታ ለማገድ ከሞሞከር አንስቶ መላ ካድሬዎቹን አሰማርቶ ህዝቡ አንድነት በጠራው ሰልፍ ላይ እንዳይገኝ ሲያግባባና ሲያስፈራራ ሰንብቶ ነው ሰልፉ የተጠራበት ቀን ሀምሌ 7 እንዳይደርስ የለም የደረሰው።

ፖሊሱና የፖለቲካ ካደሬው አንድ አካል ሆነው በሚኖሩበት ኢትዮጵያ ህዝብን ከአደጋ እንዲከላከል ከህዝብ በሚሰበሰብ ገንዘብ ደሞዝ ተቆርጦለት የተሰማራው የፖሊስ ሀይል ያለምንም እፍረት የካድሬ ስራ ያከናውናል።
በጎንደር ሰላማዊ ሰልፈኛው የሚጓዝባቸው ጎዳናዎች መጋቢ መንገዶች በፌደራል ፖሊሶች ተዘግተው ውለዋል፣ አላማቸው በተቻለ መጠን የሰላማዊ ሰልፈኛውን ቁጥር መቀነስ ነበር። ይሁንና የጎንደር ህዝብ መንገዶችን እያሳበረ፣ የሚጥለው ዝናብና መንገድ የዘጋው የፌደራል ፖሊስ ሳይበግረው ሰልፉን ተቀላቅሏል።

Friday, July 12, 2013

ዜና በጨዋታ፤ ድራማው ይብቃ… (ህዝበ ሙስሊሙ) ምን ሰርቼ ልብላ (አርቲስቱ መንግስት)

600540_589521871099173_1142193440_nዜና በጨዋታ፤ ድራማው ይብቃ… (ህዝበ ሙስሊሙ) ምን ሰርቼ ልብላ (“አርቲስቱ” መንግስት)
ዛሬ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በመላው ሀገሪቷ ታላቅ ተቃውሞ ሲያሰሙ ውለዋል፡፡ በተቃውሞው በይበልጥ ጎልቶ ከወጡ መፈክሮች መካከል “ድራማው ይብቃ!” የሚል ይገኝበታል… ድራማው… ድራማው… የቱ ድራማ… ሰው ለሰው…? ብለው የጠየቁ እንደሆነ መልሱ አዲስ መስመር ላይ ይገኛል…
መንግስታችን በአርቲስቶች ሽልማት ዘርፍ “የምንግዜም ኮመዲያን” በሚል ሽልማት ሊያገኝ ይገባል… ሲሉ አስተያየታቸውን የሚሰጡ ብዙሃን ናቸው፡፡ እንደ ብዙሃኑ ገለፃ ከሆነ፤ (ደግሞም መሆኑ አይቀርም) “መንግስት በተለያየ ጊዜ ህዝቡን በሳቅ እየገደለው ይገኛልና የሚደርስበት ኮመዲያን አልተገኘም” ስለዚህም ሽልማት ሲያንሰው ነው፡፡ ይህንን ሲያብራሩ የነበሩ ብዙሃን አሁን ደግሞ እያረሩ መንግስት በትራጄዲውም መስክ የሚደርስበት አልተገኘም እና “ኮመዲዮትራጀዲ” ተብሎ ይሸለም እያሉ እየተናገሩ ነው፡፡
ነገሩ ሲብራራ የሚከተለውን መልክ ይይዛል…

ሰበር ዜና – ደቀ መዛሙርቱ በመንበረ ፓትርያርኩ ቅጽር የተቃውሞ ትዕይንት እያካሄዱ ነው. በተቃውሞው የተበሳጩት ሊቀ ጳጳሱ ራሳቸውን ስተው እንደነበር ተጠቁሟል

MNN
Board members of the college
ፖሊስ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ዋና ሥራ አስኪያጅ አነጋግሯል
‹‹ከሣሾቼን እንዳታነጋግሩ›› ያሉት አቡነ ጢሞቴዎስ ቋሚ ሲኖዶሱ በጉዳዩ ላይ እንዳይወያይ ማከላከላቸው ተሰምቷል
በተቃውሞው የተበሳጩት ሊቀ ጳጳሱ ራሳቸውን ስተው እንደነበር ተጠቁሟል
‹‹አልፈው በመቃብራቸው ላይ መሣቅ እንፈልጋለን›› – የጥላቻው ምሬት
‹‹በተራዘመው መርሐ ግብር ሳቢያ የተጨመረው በጀት ለብክነት እየተዳረገ ነው›› /ደቀ መዛሙርቱ/
ዛሬ ጠዋት ወደ መንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ያመሩት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት በመንበረ ፓትርያሪኩ ቅጽር ላይ የተቃውሞ ትዕይንት እያካሄዱ ነው፡፡

Wednesday, July 10, 2013

የአንድነት ፓርቲ አቤቱታና የተቃዉሞ ሠልፍ ዕቅድ

0,,5588468_4,00
የፓርቲዉ አባላትና ደጋፊዎች የታሠሩትም ፊርማ ለማሰባሰብ፥ ሠልፍና ስብሰባዉን ለማደራጀት ሲንቀሳቀሱ ነዉ።ከሰኔ ሃያ-ሁለት እስከ ሰላሳ በነበረዉ አንድ ሳምንት ብቻ ዘጠኝ የፓርቲዉ አባላት በፀጥታ አስከባሪዎች ታስረዋል።አብዛኞቹ የታሠሩት ሰሜን ጎንደር ነዉ።አንዱ ታስረዉ ተለቀዋል።አስራ-አንደኛዉ ከግድያ ሙከራ አምልጠዋል።
የኢትዮጵያ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የመንግሥት ፀጥታ አስከባሪዎች አሠረዋቸዋል ያላቸዉ አባላቱና ደጋፊዎቹ እንዲፈቱ በደብዳቤ ጠየቀ።የፓርቲዉ ሊቀመንበር ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ለሐገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ለአቶ ሐይለ ማርያም ደሳለኝ በፃፉት ደብዳቤ እንዳሉት ሠላማዊ ሠልፍ ለማደራጀት እና የአቤቱታ ፊርማ ለማሰባሰብ በሕጋዊ መንገድ ይንቀሳቀሱ የነበሩ የፓርቲዉ አባላት አላአግባብ ታስረዋል።አብዛኞቹ የታሠሩት ሰሜን ጎንደር ነዉ።አንድነት ፓርቲ የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት እንዲከበር፥የዜጎች መብት እንዲጠበቅ የፀረ-ሽብር ሕግ እንዲሠረዝ በመጠየቅ በመጪዉ ዕሁድ ጎንደርና ደሴ ከተሞች የአደባባይ ሠልፍ መጥራቱንም ሊቀመንበሩ አስታዉቀዋል።ነጋሽ መሐመድ ዶክተር ነጋሶን በስልክ አነጋግሯቸዋል።

የቃሊቲ ዉሎየ እና የእስክንድር ነጋ የሰላማዊ ትልግ ጥሪ

በበትረ ያዕቆብ

ትናንት በማለዳ ነበር ተነስቼ ከሰሚት ወደ ሳሪስ ያቀናሁት፡፡ የሐምሌን ቀዝቃዛ የጠዋት አየር እየተመገብኩ ከጓደኞቼ ጋር ከተቀጣጠርኩበት ሐበሻ ካፌ ስደርስ ሰዓቴ ከጥዋቱ 1፡30 ይል ነበር፡፡ ሁላችንም ከየአቅጣጫዉ በዚያች አነስተኛ ካፌ ከተሰባሰብን በኋላ ቁርስ ቢጤ እንደ ነገሩ ቀማምሰን የዕለቱን ዕቅዳችንን ለመፈፀም ተነሳን—በልባችን ስኬትን እየተመኘን፡፡ እናም ፍራፍሬ በየአይነቱ ሸማመትን ፤ ያስፈልጋሉ ያልናቸዉን ነገሮች ሁሉ አሟልተን ጉዞአችንን ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት (በርግጥ ማረሚያ ቤት የሚለዉ ቃል ፍፁም አይገባዉም) አደረግን ፤ ለኛ ሲሉ እራሳቸዉን አሳልፈዉ የሰጡ የጭንቅ ጊዜ ልጆች ማለትም አንዱአለም አራጌን ፣ እስክንድር ነጋን እና ርዕዮት አለሙን እንዲሁም ሌሎችን ለመጎብኘትና አይዞአችሁ ሁሌም ከጎናችሁ ነን ልንል፡፡
ይሁን እንጅ እዚያ ደርሶ እነዚያን ጀግኖቻችንን አይዟችሁ ማለት ዉጣ ዉረድ ነበረዉ፡፡ ምንም እንኳን ሁላችንም ከነርሱ ፊት ለመቆም በጣም ብንጓጓም ብዙ መሰናክሎችን ማለፍ ነበረብን፡፡

Monday, July 8, 2013

እዩልኝ ሲያቅመኝ፤ “አቤ ወደ ሙርሲ የላካቸው ጀቶች ግጭት” ጎንደር ዘ ኢትዮጵያ

 (Abe Tokichaw)

996816_481813375244363_822890382_n
እዩልኝ ሲያቅመኝ፤  ”አቤ ወደ ሙርሲ የላካቸው ጀቶች ግጭት”
አንድ አማርኛ መመህር ነበሩን ጺማቸው የጎፈረ ጸጉራቸው የተንጨበረረ ነበር፤ በአንዱ ቀን ታድያ ፊት ለፊታችሁ በምታዩት ነገር ግጥም ጻፉ አሉና አዘዙን፡፡ ሁላችንም አንገታችንን ደፍተን ስንንደፋደፍ አንዱ ሳተና ጨርሻለሁ… ሲል እጁ
ን አወጣ… በል እስቲ አጋራን… አሉና መድረኩን ሰጡት፡፡ እርሱም ጀመረ፤
ያጎፈረው ጢምዎ…
ዝንጀሮ አስመስልዎ…
አቤት የፀጉርዎ…. ብሎ ገና ከመጀመሩ ተማሪው ሳቁን መቆጣጠር አቅቶት ከት…ት ብሎ መሳቅ ጀመረ፡፡ ይሄን ጊዜ መምህሩ ተቆጡ…
ተዉ እንጂ ተማሪዎች… ገና እኮ ነው በደንብ ያቅመኝ እንጂ… አሉን፡፡ ሌላ ሳቅ…
አንድ ወዳጄ ባለፈው ግብጽን አስመልክቶ ያወጋሁትን በእንዲህ መልኩ ይዋጋዋል… ደህና አድርጎ አቅሞኛል፡፡ ለነገሩ እኔም የምለቀው አይመስለኝም…  ስለ ባዕድ ሀገር የማውራት ሞራሌ እስኪሰባሰብ ግን እስቲ እርሱ ያቃመኝን ላልደረሰው ላዳርሰው ብዬ በድረ ገፃችን ላይ ለጥፌዋለሁ፡፡

አቶ ብርሃነ መዋ ኢትዮጵያውያን በአንድነት እንጂ በተናጠል ትግል ውጤት ለማምጣት እንደሚቸገሩ ገለጹ

በሰሜን አሜሪካ የአንድነት ድጋፍ ማህበር፣ ጁላይ 5 ቀን ሕዝባዊ ስብሰባ በዋሺንገትን ዲሲ አካባቢ ባደረገው ሕዝባዊ ስብሰባ ከሕዝብ ጋር ተወያየ። በስብሰባዉ በአካል ተገኝነተዉ፣ አንጋፋዉ የቀድሞ የሰሜን አሜሪካ ቅንጅት ድጋፍ ማህበር አመራር አባል የነበሩት አቶ ብርሃን መዋ፣ እንዲሁም የአንድነት ፓርቲ የዉጭ ግንኙነት ክፍል ሃላፊው አቶ ተመስገን ዘዉዴ፣ ለሕዝቡ ንግግር አድርገዋል።
አቶ ተመስገን የአንድነት ፓርቲ ስለጀመረዉ የሶስት ወራት የሚሊዮኖች ድምጽ እንቅስቃሴ ገለጻ የሰጡ ሲሆን ኢትዮጵያዉያን የተዘጋጁ ፔትችኖችን በመፈረም የእንቅስቃሴው አካል እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል። በአገር ቤት የሰማያዊ ፓርቲ በጠራዉ ስብሰባ የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች እንደተባበሩ፣ የአመራር አባላቱን በሰልፉ እንደተገኙ የገለጹት አቶ ተመስገን፣ አንድነት ትግሉን እስከረዳ ድረስ፣ ማንም ጠራ ማንም፣ በማናቸዉም ሰላማዊ እንቅስቃሴዎች ጎን እንደሚቆም አስረድተዋል። ብዙዎች እየታሰሩ፣ እንግልትና መከራ እየደረሰባቸው እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ተመስገን፣ ትግሉ ከመቼዉም በበለጠ ወሳኝ ደረጃ ላይ እንዳለም ገልጸዋል።