Translate

Thursday, February 8, 2018

ህወሓትና ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዓላማው!

የአዘጋጆቹ ማስታወሻ፤ ባለፉት ዓመታት ከህወሓት እየኮበለሉ የወጡ የቀድሞ አባላት በርካታ ናቸው። እንዳንዳቸው የሚወጡበት ምክንያት ቢኖራቸውም ህወሃትን በማጋለጥና ማንነቱን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በማሳወቅ የአቶ ገብረመድኅን አርአያን ያህል ታላቅ ሥራ የሠራና መስዋዕትነት የከፈለ አለ ለማለት ያስቸግራል። አብዛኛዎቹ የቀድሞው አባላቱ የህወሓትን ምሥጢራዊ አሠራር እና እጅግ አረመኔያዊ ግፍ፤ ኤፈርት በኢትዮጵያ ሐብት ላይ የፈጸመውንና እስካሁንም እየፈጸመ ያለውን የኢኮኖሚ ግፍ፣ ዝርፊያ፣ ሌብነት፣ … የመሳሰሉ ጉዳዮች በአደባባይ ከመናገር ሲቆጠቡ ተስተውለዋል። አንዳንዶቹም በህወሓት ከፍተኛ አመራር ላይ የነበሩ የቀድሞ አባላት ቢሆኑም፤ ኤፈርትም ሲያስተዳድሩ የቆዩ ቢሆኑም ስለጉዳዩ ሲጠየቁ የሚሰጡት ምላሽ አባይ ጸሐዬ ወይም ስብሃት ነጋ ከሚሰጡት ምላሽ ያልተለየ ሆኖ ተገኝቷል።
አቶ ገብረመድኅን አርአያ “ዝሆን ላይ የሚጮህ እብድ ውሻ ብቻ ነው” በሚል ርዕስ ያቀናበሩትን ዳጎስ ያለ ሠነድ በድረገጻችን ላይ እንድናትመው በላኩልን መሠረት ከጥቂት ወራት በፊት ክፍል አንድን አቅርበን ነበር። (ይህንን ዕትም ለመረዳት ክፍል አንድን ማንበብ አስፈላጊ በመሆኑ እዚህ ላይ በመጫን እንዲያነቡ እናሳስባለን)። ስማቸው የግድ መገለጽ ስላለበት ስማቸው የወጣ ለዚህ ጽሁፍ ምላሽ መስጠት ለሚፈልጉ በራችን ክፍት ነው። የዝግጅት ክፍላችን ለአቶ ገብረመድኅን ምስጋናውን እያቀረበ ሌሎችም የህወሓት የቀድሞ አባላት ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱና በዚህ መልኩ ከሕዝብ ጋር እንዲታረቁ ሃሳብ እንሰጣለን። ያለ እውነት ዕርቅ የለም፤ ያለ ዕርቅ አብሮ መኖር የለም።

ዝሆን ላይ የሚጮህ እብድ ውሻ ብቻ ነው!

ወያኔዎች በትግራይ ህዝብ የጥቃት ዘመቻ የከፈቱበት ምክንያት የትግራይ ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ እምነቱ ከፋፋይና ዘረኛው ወያኔ ፤ በእውቅና አለመቀበሉ ቀጥሎ ያለውን ዋና ምክንያቶች እንመልከት።
1. አማራ ደመኛ ጠላትህ ሲሉት አይደለም ወንድሜ ወገኔ ኢትዮጵያዊ ነው በማለቱ፣
2. ተሓህት የትግራይን ሕዝብ አይወክልም አናውቃችሁም በማለቱ፣
3. ተሓህት የነጠቀውን የሰሜን ጎንደርና የሰሜን ወሎ ለም መሬቶች አንቀበልም፣ የሰሜን ጎንደሩ የጎንደር ጠ/ግዛት ነው፣ የሰሜን ወሎ የወሎ ጠ/ግዛት ነው፣ ከትግራይ ግንኙነት የላቸውም፤ በጎንደር በኩል የሚያዋስነን ተከዜ ወንዝ ነው። በወሎ በኩል ማይጨው ችንኮማጂ ነው፤ ሲሆን በምን መልኩ ነው የትግራይ የሚሆነው በማለቱ፣ ከወንድሞቻችን ጥላቻና ቅራኔ አትፍጠሩብን ብሎ ጮሆ በመናገሩ፤ ሸዋዊ የትግራይ አማራ ተብሎ የግድያ ኖህ የወረደበት።
4. የተሓህትን ፕሮግራም አንቀበልም 1ኛ ትግራይ የኢትዮጵያ የታሪክ አስኳል የትግራይ ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ የሚመካ ነው፤ ትግራይ የኢትዮጵያ አካል ግዛት እንጂ ቅኝ ተገዢ አይደለችም፤ አማራው ኢትዮጵያዊ፤ ትግራይም ኢትዮጵያዊ ፤ ምንም ልዩነት የለንም በማለት ጮሆ በመናገሩ።
5. በጣሊያን ጊዜ የተዋጉና በኢትዮጵያዊነታቸው የሚኮሩ የትግራይ ልጆችን የህ.ወ.ሓ.ት.ን መርህ የሚያጨናግፉ ናቸው ብሎ በማሰብ ህ.ወ.ሓ.ት አጥፍትዋቸዋል። በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የታሪክ አዋቂዎች አዛውንት ሊቃውንት የአምስት ዓመት ከወራሪው ጣልያን የተዋጉ አርበኞች በመብራት እየፈለገ የወያኔው መሪዎች የገደልዋችው ያጠፍዋችው፤ ተገድለውም ሃብት ንብረታቸው ህ.ወ.ሓ.ት ወርሶታል። እነዚህ የሃገርና የህዝብ አለኝታዋች ሙሉ በሙሉ በትግሉ ጊዜ አጠፉዋቸው፤ ገደልዋቸው። ዛሬ ስለ ትግራይም ሆነ አጠቃላይ ስለ ነበረው ጥንታዊ ታሪክ በትግራይ ውስጥ የሚያውቅ ተፈልጎ አንድም አይገኝም።
ትግራይ በ17ቱ የህ.ወ.ሓ.ት. የትግሉ ዘመን ወድማለች። የታሪክ አዋቂ በኢትዮጵያዊነቱ የሚቆረቆር በትግሉ ዘመን ተመልሶ እንዳያንሰራራ ተመልሶ እንዳይፈጠር አድርገው በመምታት አጥፍተዉታል። በጣም የሚያስገርም ሁኔታም የተፈፀመው በወልቃይት፤ ጠለምት፤ ጠገዴ ብቻ በሰሜን ጎንደር አማራው በተመሳሳይ ሁኔታ አዛውንቶች እየተፈለጉ በስውር እየታፈኑ፣ የት እንደገቡ የማይታወቁ ማን ተያዘ ማን ተገደለ የሚለው በግልጽ ለማወቅ አስቸጋሪ ቢሆንም ብዙ የሰሜን ጎንደር አዋቂ ሽማግሌዎች የውሃ ሽታ ሆነው የቀሩ አሉ፤ ይህን ለማወቅ የሚችሉት የየአካባቢው ነዋሪዎች ናቸው። የታሪክ አዋቂ ሲጠፋም ተተኪው ትውልድ ይቸገራል። የህ.ወ.ሓ.ት. መሪዎች ይህ እንደፖሊያሳቸው የሚጠቀሙበትም የቆየው ታሪክ ለማጥፋትና ለማክሰም ነው።
በእነዚህ ንጹሃን የትግራይ እና የሰሜን ጎንደር ኢትዮጵያውያን የፈሰሰሰው ደም ተጠያቂው ማነው? ማነውስ ሃላፊነቱ የሚቀበለው? ምንስ አጥፍተው ነው? ወደ ትግራይ ስንመለስ፤ የተናገሩት እውነት ነው፤ ትግራይ የአማራው ቅኝ ተገዢ አይደለችም፤ ሰሜን ጎንደር፤ ወልቃይት፤ ጠገዴ ጠለምት፤ ቃፍታ (ሰቲት) ሁመራ  የሰሜን ወሎን መሬቶች የትግራይ አይደሉም፤ አልነበሩም፤ ይህም ታሪክ የሚያውቀው ሃቅ ነው። የትግራይ ህዝብ ምን አጠፋ ህ.ወ.ሓ.ት የገደለው የረሸነው ያጠፋው። ማንኛውም ህዝብ አስተዋይና አርቆም ሃሳቢ እንደሆነ ሁሉ የትግራይ ህዝብም ከዚሁ ተነስቶ ነበር እውነቱን የተናገረው። ይህ ህ.ወ.ሓ.ት. የጀመረው በትግራይ ህብረተሰብ ማጥቃትና መግደል የንጹሃን ዜጎችን ደም በከንቱ የፈሰሰው ይህ ደም አሁንም በእግዚአብሔር ፊት እየጮኸ ይኖራል። መሬትና ሰማይ የፈጠረ ጌታም ፍርዱን ይሰጣል፤ የማይቀር ነው። የህ.ወ.ሓ.ት. መሪዎች የአማራው ጎንደሬው ለምና ሰፊ መሬት በሕገ ወጥ በጉልበት ለመንጠቅ፤ የአማራው ደም የንጹሁን ኢትዮጵያውያን ዜጎች ደማቸው በትውልድ መንደራቸው እንደጎርፍ ካለምንም ጥፋትና ሃጥያት ፈሰዋል፤  ዘራቸው አጥፍተዋል፤ ህፃን፣ አራስ፣ እርጉዝ፣ ሽማግሌ፣ ወጣት፣ ተገድለዋል፣ በስዉር ጠፍተዋል። የእነዚህ ንጹሃን ኢትዮጵያዊ ዜጎችም ፈጣሪ አምላክ ፊት ደማቸው እየጮኸ ነው። ቀሪዎቹ በሂወት ያመለጡም በስደት እየተንከራተቱ ይኖራሉ።
ይህን አሳዛኝ ታሪክ ያነሳሁት የትግራይ ሕዝብ ነፃአውጪ ህ.ወ.ሓ.ት.፤ ማ.ገ.ብ.ት ተብሎ ሲፈጠር ቀጥሎም ደደቢት በርሃ ወርዶ ተ.ሓ.ህ.ት. (ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ) ከዛም ስሙን ለውጦ ህ.ወ.ሓ.ት. (ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ) ቢልም እውቅና ያልሰጠው በአንጻሩ ግን የትግራይ ሕብረተስብ ፀረ ወያኔ አምርሮ የታገለው ህዝብ ነበር። ፀረ ወያኔ ሆኖ መታገሉ ከባድ መስዋእትነት በሂወቱ በንብረቱ በሃብቱ ከፍሎ ነው ያለፈው። ሁሉ ኢትዮጵያዊም ይህን በእምነት ሁሉ ኢትዮጵያዊ  ያምንበታል። ለዚሁም ተጠያቂዎቹ አረጋዊ በርሄ፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየ፣ ግደይ ዘርአጽዮን፣ ስዩም መስፍን፤ መለስ ዜናዊ ሲሆኑ፣ እነዚህ በዋና የንፁሃን ደም በሰሜን ጎንደር በትግራይ በኢትዮጵያውያን ንፁህ ደም በፈጸሙት ወንጀል ግንባር ቀደም ተጠያቂ ናቸው። ቀጥሎ ደግሞ፣ ስየ አብርሃ፣ አውአሎም ወልዱ አርከበ ዕቁባይ ገብሩ አስራት በዋናነት ግንባር ቀደም ይጠቀሳሉ።የኢትዮጵያ ህዝብ ክስ ሲመሰርትም መነሻው ከዚሁ ነው። የህ.ወ.ሓ.ት. ፋሺስት ድርጅት ለብዙ ዓመታት የመሩትም እነዚህ፤ ተከታትለው ወደ ሥልጣን የመጡ እንደሆነ እንመለክታለን።
ይህ የትግራይ ሕዝብ በማጥፋት የተሰማራው የህወሓት አመራር ሕዝብ በመግደሉ በተሰማራበት ወቅት በተሓህት ውስጥ የነበርው ታጋይ በዝምታ አልተመለከተውም ነበር። ከዲሞክራሲያዊ ጥያቄዎችእና በህዝቡ እየተፈጽሙት ያሉትን ግፍን ሰቆቃ ድርጅቱ ከምን ተነስቶ በምን ምክንያት ሰላማዊ ህዝብ እያሰረና እያሰቃየ ሽማግሌዎች ወጣቱን ወንድ ሴት ይፈጃል የሚሉና ተዛማች ብዙ ጥያቄዎች ተነሱ። አመራሩ በታጋዩ የተነሱ የዲሞክራሲ ጥያቄዎች ተቀብሎ በሰላም ከመፍታት ይልቅ ታጋዩን በመወንጀል፤ ይህ ፀረ ተ.ሓ.ህ.ት እንቅስቃሴ  ነው በማለት ራሱ አመራሩ ለተነሱ የዲሞክራሲ ጥያቄ በመወንጀል ሕንፍሽፍሽ የሚል ስም በመስጠት፣ በበዙ ታጋዮችና ሰላማዊ ዜጋውም በሕንፍሽፍሽ ተመርዘዋል ተብሎ ሰላማዊ ዜጋው ከየቤቱ እየተለቀመ፤ ታጋዩ ከትግል ሜዳው እየተለቀመ፣ እየታፈነ፣ በቶርቸርና በእሳት እየተቃጠለ፣ በእሳት የጋለ ፍም ሳንጃ ሆድ እቃው እየገባ ተገደል፣ ጠፋ፣ የተገደሉት ሰላማዊ ዜጎችም ሙሉ ንብትና ሃብታቸው በህወሓት ተወረሰ። የብዙዎች ቤት ፈረሰ።
የትግራይ ሕብረተሰብ ለዚሁ ሁሉ መጥፎ ጥቃት የተዳረገበት ዋና ምክንያት ከላይ የተጠቀሱ ሲሆኑ ሌላው ደግሞ ጣልያን ኢትዮጵያ በ1928 በወረረበት ጊዜ በአርበኝነት የተዋጉ ሁሉ የተሓህት-ህወሓት አመራርን በመኮነናቸው ነበር። ይህ ሲሆን አረጋዊ በርሄ፣ ግደይ ዘርአጽዮን፣ አባይ ፀሃየ፣ ስብሃት ነጋ፣ ስዩም መስፍን፣ መለስ ዜናዊ ያሳለፉት መመሪያ እነዚህ የትግራይ ሸዋ አማራ በአጭሩ አነጋገር ሸዋዊ ትግራዋይ በሙሉ በየትም ትግራይ መሬት የሚኖሩ በሕዝብ ግንኙነት እየተለቀሙ ታስረው ሃለዋ ወያኔ (06) በሚስጢር እንዲገቡ በማለት በሰጡት የትእዛዝ መመሪያ ሁሉም ከያሉበት ተለቅመው ሃለዋ ወያኔ እየገቡ ተገድለዋል፣ ንብረታቸውን ተወርሰዋል። ዛሬ በትግራይ እንኳንስ ከጣልያን የተዋጋ በወቅቱ ሕጻናት የነበሩትም አንድም ሰው አይገኝም፣ ተገድለዋል። ዋና የተገደሉበት ምክንያት፤
  1. የህ.ወ.ሓ.ት የፖለቲካ አቋም ወይም ፕሮግራም አንቀበልም ብለው በማውገዛቸው
  2. አማራ የትግራይ ህዝብ ደመኛ ጠላት ስለሆነ አብረን እንምታው እናጥቃው ሲባሉ፤ አማራ የትግራይ ህዝብ ጠላት አይደለም፤ ሁላችን አንድ ኢትዮጵያ ወንድማሞች ነን፤ አማራ የፈጸመብን በደል ጥቃት የለም፤ አማራው የኛ፤ እኛም የሱ ነን በማለታቸው፤
  3. የሰሜን ጎንደር፣ የሰሜን ወሎ መሬት የትግራይ ነው የምትሉን የትግራይ አይደለም፤ በታሪክም አልነበረም፤ የወንድሞቻችን በጉልበት የምትወሩት ያላችሁ ርስተ መሬት አንቀበልም በማለቱ
  4. ጣልያን ጣልያን የምትሉት በየቦታ ከጣልያን የተዋጋነው ሃገራችን ኢትዮጵያ ለመውረር በቅኝ አገዛዝ ስርአቱ ሊገዛን የመጣው፤ ወራሪ ቅኝ ገዢ ጠላት ነው፤ የሃገራችን ኢትዮጵያ አንድነትና ሏላዊነት አሳልፈን አንሰጥም በማለት ጣልያን መታነው አሸነፍነው፤ ኢትዮጵያን ነፃ አወጣን፤ በማለት ፀረ ወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት አቅዋም በመያዛቸው ነበር።
ሆኖም ይህንን መቀበል ያቃታቸውና ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑት ከላይ በተጠቀሱ የወያኔ መሪዎች ከባድ ጥቃት በመሰንዘር ህዝቡን ጨረሱት፤ ህጻናትም ሳይቀሩ አብረው ተጨፈጨፉ። ዛሬ ታሪክ ነጋሪ በትግራይ ፈጽሞ አይገኝም። የታሪክ ፈላስፋዎች የታሪክ አዋቂዎች የሆኑት የወያኔው መስራቶችና አሁንም በሥልጣን  ያሉት ደንቆሮች የወያኔ መሪዎች በሥልጣን ኮረቻ የተንጠለጠሉ ቅኝ ገዢዎች የህ.ወ.ሓ.ት. ባንዳዎች ናቸው።
ይህ በዚሁ እንዳለ፣ የትሓህት-ህወሓት መሪዎች በትግራይ ሕብረተሰብ የጀመሩትን ጥቃት እንደቀጠለ ሁኖ የወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ጠለምት፤ ሰቲት ሁመራን፤ በጉልበትና በማንአለብኝነት በካርታቸው የተካተተው በፕሮግራማቸው ውስጥ የትግራይ መሬት ነው በማለት ሰፊዉን የጎንደር ክፍለ ሃገር መሬት የሰሜን ወሎ መሬት በማካተት (ፀሃፊና አዘጋጅ አረጋዊ በርሄ ነው) ሕገ ወጥ የለም ሰፊ መሬት ወረራ ፈጽመዋል። ይህን ወረራ ለማስፈጸም የተካሄድ ቅድመ ዝግጅት በሰሜን ቤገምድር (ሰሜን ጎንደር)፤ ንን ዘለለው የተባለው ነገር ግን አካባቢውን የማያውቀው በስመ ተወላጅ በአባቱ በኩል ተወላጅ የሆነውን ታጋይና በህዝብ ግኑኝነት ክፍል የተመደበ በሱ የሚመራ ቡድን በወልቃይት፤ በጠገዴ፤ በጠለምት ጥናት እንዲያካሂድ በ1969 ዓ.ም ውስጥ ተላከ። ይህ ከሃዲ ግለሰብ ከግለሰው እስከ ቡድን ከቡድን በየበአላቱ እሁድ ወ.ዘ.ተ. በየቤተክርስትያኑ እየተንቀሳቀሰ ወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ጠለምት፤ ቃፍታ ሁመራ የትግራይ መሬት መሆኑ የሰሜን ጎንደር ህዝብም ሁሉ ትግራዋይ መሆኑ የታሪክ ሃቅነት በጎደለው ለማሳመን ባካሄደው መፍጨርጨር ሳይሳካለት በሙሉ የሰሜን ጎንደር ህዝብ በልበ ሙሉነት ወድቅ አደረገው። በግልጽም እናንተ ወራሪ የጣልያን አሽከሮች ውላጅ ናችሁ በማለት አሸማቀቃችው። ይህ የጎንደር ግዛት በማንም ያልተደፈረ በእናንተ ከሃዲዎች እይፈፈርም ብሎ ህዝቡ በግልጽ የተናገረበት ጊዜም ነው። ከዚያም ተዋርዶ ተደብዶቦ፤ ህዝቡም ወደ ማንም ቤት ዝር እንዳይሉ በማስጠንቀቅ በርሃብ ጠውልገው ወደመጡበት እንዲመለሱ አደረጋቸው። ነገር ግን መኮንን ዘለለውና ቡድኑ ሲያደርጉት የነበረው ሤራ ህዝቡ ሁሉ ቢቃወምም ትልልቅ ሰዎች የታሪክ አዋቂዎች የበሰሉ ጠንካራ ሰዎች በብዛት በሚስጢር እየመዘገቡ፤ እነዚህ ሰዎች በሂወት ካሉ ነገሩ አይሳካም በማለት በድብቅ ስማቸው ወደ ወያኔ መሪዎች በየእለቱ በማስተላለፍ ለክፉ ሞት ዳረጉዋቸው።
የህ.ወ.ሓ.ት . መሪዎች አሁን የገጠማቸው ክሽፈትና ወርደት አጸፋውን ለመመለስ ዝግጅታቸውአሰቀመጡ። ቀደም በማለት በትግራይ ሕብረተሰብ የአፈና ዘዴ በመጠቀም አነስተኛ ሀይል አፋኝ ጉጅሌ በማደራጀት ክፉና አረመኔው ጨካኞች አፋኝ ቡድን ሶስት አቅጥጫ ተሰማራ። ይህ ጊዜም በ1969 ዓ.ም. ወደ መጨረሻው አካባቢ  በሶስት አቅጣጫ በማሰማራት
  1. ወልቃይት፣
  2. ጠለምት፣
  3. ጠገዴ
ውስጥ ሲገቡ ጉጅሌያቸውን ይዘው በሶስቱ ቦታዎች ተሰማርተው ቀደም ሲል ከመኮነን ዘለለው የነበሩ የህዝብ ግኑኝነት መሪነት በድብቅ በዘዴ የተቃወሙት የሰሜን ጎንደር አማሮች አንድ በአንድ በተናጠል እያፈኑ ሰውን በመልቀም ያፈኑዋቸውን ሓለዋ ወያኔ በማስገባት ወንድ፣ ሴት ሳይሉ ገደሉዋቸው። ሃብት ንብረታቸውም  እየተወረሰ ዝርፍያው ቀጠለ ቀስ በቀስም የጀመሩት ጥቃት እየተስፋፋ ሄደ።
ተ.ሓ.ህ.ት. ለ1ኛው ጉባኤ ይዘጋጅም ስለነበረ 1ኛ ጉባኤው የካቲት 5 ቀን 1971 ዓ.ም. ዓዲ ዳዕሮ አካባቢ ማይ አባይ በተባለው ቦታ ተካሂዶ የአመራር ቦታ ለውጥም ተደረገ። በዚሁ መሰረት እንደሚከተለው ተደላደሉ።በዚሁ ጉባኤ የተመረጡ አመራሮች አምስቱ የቆዩ ፖሊት ቢሮ (ሥራ አስፈጻሚ) እንዳሉ ተመልሰው ሥልጣናቸው ሲይዙ ቀሪዎቹም ዝርዝር የሚከተለው ነው፤
1ኛ. አረጋዊ በርሄ፤ ወታደራዊ አዛዥ፤ ፖሊት ቢሮ
2ኛ. ስብሃት ነጋ፤ የህ.ወ.ሓት ሊቀ መንበር፤ ፖሊት ቢሮ
3ኛ. ግደይ ዘራፅዮን፤ የህ.ወ.ሓ.ት ም/ሊቀመንበር፤ ፖሊት ቢሮ
4ኛ. አባይ ፀሃየ፤ የፕሮፓጋንዳ ክፍል ዋና ሃላፊ፤ ፖሊት ቢሮ
5ኛ. ስዩም መስፍን፤ የውጭ ጉዳይ ዋና ሃላፊ፤ ፖሊት ቢሮ
6ኛ. ገብሩ አስራት፤ ማዕከላዊ  ኮሚቴ
7ኛ. መለስ ዜናዊ፤ የፕሮፓጋንዳ ጽ/ቤት ም/ሃላፊ፤ ማዕከላዊ  ኮሚቴ
8ኛ. አስፍሃ ሓጎስ፤፤ ማዕከላዊ  ኮሚቴ
9ኛ. አርከበ (ዮሓንስ) እቁባይ፤ ማዕከላዊ  ኮሚቴ
10ኛ. ፃድቃን ገብረተንሳይ፤ ማዕከላዊ  ኮሚቴ
11ኛ. ስየ አብርሃ፤ ማዕከላዊ  ኮሚቴ
12ኛ. አታክልት ቀፀላ፤ ማዕከላዊ  ኮሚቴ፤ ግንቦት ወር 1971 ዓ.ም በስብሃት ነጋና በአባይ ፀሃየ እንዲሁም በመለስ ዜናዊ  የተገደለ። ገዳይ ሳሞራ (መሓመድ) የኑስ በሲሞኖቭ ባልር መነጽር ጠመንጃ።
13ኛ. ዘርአይ አስገዶም፤ ማዕከላዊ  ኮሚቴ
14ኛ. አውዓሎም ወልዱ፤ ማዕከላዊ  ኮሚቴ
15ኛ. ተወልደ ወ/ማርያም፤ ማዕከላዊ  ኮሚቴ ብዙም ሳይቆይ በህመም ምክንያት ሱዳን ሂዶ 1975 ዓ.ም የተመለሰ ነው።
የነዚህን ስም ዝርዝር ያስቀመጥኩበት ካለ ምክንያት አይደለም፤ በተለይ በአማራው ላይ የዘር ማፅዳት ከባድ ወንጀል በመፈጸማቸው ነው። አማራው ያፈራው ሃብት ንብረት ወ.ዘ.ተ. መርፌም ሳትቀር ለህ.ወ.ሓ.ት. ውርስ እንዲሆን ብለው የህዝብ ሃብት ንብረት የዘረፉ፤ የአማራው ህዝብ  የገደሉ፤ የግድያውም ቀንደኛ ተባባሪዎችና ፈፃሚዎች የነበሩ ናቸው። እነዚህ ተሰባስበው ነው በንጹሃን ዜጎች ላይ እልቂትና ሰቆቃ እያደረሱ የመጡ፤ ከአምስቱ ፖሊት ቢሮ ስድስተኛው መለስ ዜናዊ አብረው ሊጠየቁና ሊከሰሱ የሚገባቸውናቸው። የሰሜን ጎንደር ህዝብ በአረጋዊ በርሄ የሚመራው የህ.ወ.ሓ.ት ሰራዊት ቀሪው አራቱ ፖሊት ቢሮ በየቦታው ተሰማርተው ትዕዛዝና አመራር በመስጠት ማእከላዊ ኮሚቴውም ይበልጥ በዘር ማጥፋቱ ተሰማርተው የነበሩ፤
1. አዋአሎም ወልዱ፤ 2. ስየ አብርሃ፤ 3. መለስ ዜናዊ ከስየ አብርሃ ተደራቢ በመሆን፤ 4. ዘራይ አስገዶም፤ 5. ፃድቃን ገብረ ተንሳይ፤ 6. ገብሩ አስራት፤ 7. አርከብ እቁባይ፤ 8. አስፍሃ ሓጎስ ናቸው።
ከዚህ ቀጥሎ ያሉት ደግሞ በየተዋጊው ሰራዊት ተመድበው ትእዛዝ በመስጠት በአማራው ላይ ጥቃት በመክፈት የአማራ ዘር ማጥፋት ከባድ እርምጃ በመውሰድ፤ አማራው ሊቋቋመው በማይችል ሁኔታ ሰላማዊው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ዘሩን ለማጥፋት ያለው የሌው ሃይላቸው አጠናክረው ግፍ የፈጸሙ የህ.ወ.ሓ.ት. መሪዎች፤ 1. አረጋዊ በርሄ፤  2. ግደይ ዘራጽዮን፤ 3. ስብሃት ነጋ፤ 4. አባይ ጸሃየ፤ 5. ሥዩም መስፍን፤ 6. መለስ ዜናዊ፤ በሰሜን ጎንደር አማራ በትንሹ ከ1969ዓ.ም. የጀመረው ጥቃት በክፉ መልኩ ተጠናክሮ ከታህሣስ ወር 1972 ዓ. ም. የተጀመረው የአማራ ዘር ማጥፋት ዘመቻ እስከ 1977 ዓ .ም. በቀጠለበት ጊዜ በዋናነት የዘር ማጥፋት ወንጀሉን በአማራው ላይ የፈጸሙ ዋናዎቹ እነዚህ ናቸው። በዚሁ የወያኔ ጥቃት ከ2 ሚልዮን በላይ ነብሰ ጡር አራስ ህፃናት ሽማግሌዎች ወጣቶች ወንድ ሴት ልዩነት በሌለው በወያኔ እጅ ተገድለዋል። አገዳደሉም በተለያየ ስልትና ዘዴ ተፈጽሞባቸውል። ቀሪው ለስደት ተዳርጓል፤ የመጣ ይምጣ ከቤቴ ወጥቸ አልንገላታም ያለም አለ።
ከማ.ገ.ብ.ት ምስረታ እስከ የካቲት ወር 1967 ዓ.ም. የማገብት ሊቀ መንበር፤ ቀጥሎም በትግሉ ሜዳ ከየካቲት ወር 11ቀን 1967 ዓ.ም እስከ የካቲት ወር 1971 ዓ፣ም ሊቀ መንበርና ወታደራዊ አዛዥ የነበረው አረጋዊ በርሄ ነው። በምን ምክንያት ሊቀ መንበርነቱን ለቀቀ ለሚል ጥያቄ አጭር መልስ።
አረጋዊ በርሄ፤ ስብሃት ነጋ፤ መለስ ዜናዊ ስብሰባዎች በሚካሄዱባቸው ጊዜያት ገና ወደ ጉባኤው ሳይገባ ሶስቱ እየተደበቁ የሚያደርጉት ስምምነት ነበራቸው። ድርጅቱን በሞኖፖል ለመቆጣጠር የሚያስችላቸው ሶስቱን የተስማሙበት አረጋዊ ሊቀመንበርነቱን ለስብሃት ነጋ ሊሰጠው አረጋዊ በወታደራዊ አዛዥነቱ እንዲወሰን መለስ ዜናዊ የማርክሲስት ሌኒንስት፤ በሌኒናዊ መርሀግብር የካድሬዎች አሰልጣኝና አደራጅ ኮሚሽን እንዲሆን በተስማሙት መሰረት ነበር። 1ኛው ጉባኤው ተካሂዶ 15 አመራር ተመርጠው የሥራ አስፈፃሚው ምርጫ በሚመረጥበት ጊዜ በሁሉም ተሰብሳቢ በሙሉ ድምጽ የተመረጠው አረጋዊ በርሄ የህ.ወ.ሓ.ት. ሊቀመንበር ቢመረጥም ብሞትም አልቀበልም ስብሃት ነጋ ነው ብቁ ለሱ ይስጠው ብሎ አንገቴን ለካራ አለ። የተመረጡ  አመራር ስብሃት ለዚሁ ብቃት የለውም እባክህ ተቀበለን ቢሉቱም በፍፁም አልቀበልም በማለቱ ለስብሃት ነጋ ሰጡት። መለስ የተሰጠውን ቦታ አደላድሎ ያዘ፤ አረጋዊም ድሮም የራሱ የነበረው ወታደራዊ አዛዥነቱን ያዘ፤ቀሪው በየቦታው ተደላደለ። በአጭሩ ነው የገለፅኩት እንጂ ብዙ ታሪክ አለው፤ ለወደፊቱ ራሱን በቻለ ርዕስ ለህዝብ አሳውቃለሁ፤ ለአሁኑ ይህ ይበቃል። አረጋዊ በርሄ ደግሞ በታጋዩ እንዲጠላ እንዲናቅ ያደረገው ዋናው ይህ ነው። ስብሃት ነጋ ማለት አእምሮው የዞሮበት ደፍድፍ ደንቆሮ ገዳይ ጨካኝ አውሬ ነው።
አረጋዊ በርሄ
ህወሓት ከኢህአፓ ጦርነት ስለአጋጠመው ደፍሮ ሰሜን ጎንደር ሕዝብ ለማጥቃት ሁኔታውና ጊዜው አልፈቀደለትም ነበር። ከኢህአፓ ጋር በተካሄደው ጦርነት ኢህአፓ ጥቃት ደርሶበት ሰሜን ጎንደርን ለቆ በመውጣቱ ምክንያት በአረጋዊ በርሄ ወታደራዊ አዛዥ የሚመራው የወያኔ ሰራዊት ጠቅላላ ወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምት(‘ሰሜን ጎንደር’) በመውረር ከፍተኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጸመ። ስብሃት ነጋ፣ ግደይ ዘርአጽዮን፣ አባይ ፀህየ፣ ስየ አብርሃ፣ ስዩም መስፍን መለስ ዜናዊ የወያኔውን ሰራዊት ተከፋፍለው በመያዝ ሰሜን ጎንደር የንጹሃን ዜጎች አማራ የሬሳ ክምር መሬት አደረጉት። እነዚህ ሁሉ አመራር በቀጥታ ትእዛዝ የሚቀበሉት፣ የሚንቀሳቀሱት፣ ጥቃት የሚፈጽሙበት ቦታዎች ከአረጋዊ በርሄ በሚሰጣቸው መመሪያ ነበር። በዚሁ ጊዜም ተጨማሪ (06) ሃለዋ ወያነ በስፋት እንዲዘጋጁ አመራሩ ስላመነበት በምክትል ሊቀመንበሩ ግደይ ዘርአጽዮን ቁጥጥር ተጨማሪ ሃለዋ ወያን እንዲዘጋጅ በታዘዘው መሠረት በርሱ ኃላፊነት ተጨማሪ ከመሬት በታች 12 ሜትር ጥልቀት ትንሽ ጠባብ መስኮት 150 እስከ 200 እስረኞች የሚይዙ ሆነው እንዲሰሩ ወስኖ የነበሩትም እንዲሰፉ አድርጎ አሰራው። የሚሰሩበትም ቦታዎቹም፣ ግህነብ (ቃሌማ)፣ ፍየል ውሃ፣ ባኽላ ሳምረ፣ ሱር እስር ቤት ሲሆን፣ እንዲሰፋ የተደረጉባቸው ቦታዎች ደግሞ አዲ በቅሎ፣ ወርዒን ፃኢ ጨምሮ በስፋትና በብዛት ከመሬት በታች ሃለዋ ወያኔ ተሰሩ። በዚሁ ጊዜ አማራዎች፣ ሽማግሌ፣ ወጣት፣ ህፃን፣ ሴት፣ ወንድ ሳይለዩ ወደነዚህ ሃለዋ ወያኔ እየታፈሱ ታጋዙ። እዛው እንደገቡም በተለያዩ የጭካኔ ግፍ ተገደሉ። በጢስ እየታፈኑ የሞቱት አማራዎች ብዙ ናቸው። በጅምላ ጉድጓድ በጥይት እየተደበደበ ያለቀው አማራ ብዙ ነው። ወህኒ ቤት ውስጥ በገባው ተላላፊ በሽታ ምክንያት ኮሌራን ሌላ በሽታዎች በመተላለፍ ሕዝብ አለቀ። በቶርቸር፣ በመርዝ፣  በእሳት፣ የጋለ ብረት ወደ ሆዱ በመክተት አሰቃይተው ንጹህ ኢትዮጵያዊ ዜጋ አጠፉት። የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች በአማራው ያልፈጸሙት ግፍ የለም ። እነዚህ አረመኔ ግፈኞች በአንድ ህዝብ ላይ አማራ ጠላታች ብለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ አካሂደዋል። የሞተም በሂወት ያሉትና የሞቱትም እንደነ መለስ ዜናዊ በከባድ ወንጀል
1. ዘር በማጥፋት፤
2. ሃገር ለባእዳን መሸጥ (ለሱዳን)፤
3. የመሬት ወረራ መፈጸም (ሰሜን ጎንደር፤ ሰሜን ወሎ) የታላቅዋን ዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ የትግራይ መንግሥት ማስፋት የሌላው ክፍለ ሃገር ለምና ሰፊ መሬት በመንጠቅ  የህዝቡ ማንነት፣ ባህሉን፣ ወጉን፣ ፀረ ዲሞክራሲ፣ ፀረ ህልውና፣ በመሆነ መልኩ የፈጸሙት ከባድ የወንጀል ተግባር ነው። አሁንም ህ.ወ.ሓ.ት በዚሁ እየቀጠለበት ሲሆን እንዲያውም በከፋ መልኩ በግማሹ ወደ ትግራይ በማካለል ግማሹ ለሱዳን መንግሥት በመሸጥ በአማራው ላይ የሚፈጸመው ግፍ አባብሶታል።
በአማራው እየተፈጸመ ያለው ግፍ አማራን ብቻ የሚመለክት አይደለም፤ የሁሉ ኢትዮጵያዊ ጥቃት ነው፤ አማራው ዘሩ ሲጠፋ አማራው ብቻ አይደለም ዘሩ የሚጠፋው ያለ ሁሉ ኢትዮጵያው ነው ዘሩ የሚጠፋ ያለው፤ የጎንደር ለምና ሰፊ መሬት ለሱዳን እየተሸጠ ያለው የጎንደር ብቻ አይደለም የሁሉ ኢትዮጵያዊ ነው፤ የኢትዮጵያ የታሪክ ቦታዎች፤ ቴዎድሮስ በመቅደላ፤ ዮሃንስ በመተማ እምቢ ለጠላት ብለው የተሰዉበት መሬት ወያኔ ለኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ለሆነው የሱዳን መንግሥት አሳልፎ መሸጥ ታሪካችንም አሳልፎ እየሸጠው ይገኛል።ስለሆነም የጎንደር ህዝባዊ ትግል የሁሉ ኢትዮጵያዊ ትግልም ነው። የምንታገልበትም ጊዜው አሁን ነው። ጎንደርና ትግራይ፤ ጎንደርና ሲዳሞ፤ ጎንደርና ሓረር፤ ጎንደርና አፋር፤ ጎንደርና ኦጋዴን፤ ጎንደርና ጋምቤላ፤ ወ.ዘ.ተ ምንም ልዩነት የለንም! ሁላችን የኢትዮጵያ ልጆች ነን፤ ኢትዮጵያ የሁላችን ሃገር መመክያ ናት፤ ሁላችን ሃገራችን ከወያኔው ፋሽሽት ስርአት ከሃዲ ባንዳ ተባብረን ኢትዮጵያን እናድን።
የወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ጠለምት፤ ሌላውም አማራ በህ.ወ.ሓ.ት.፤ የወረደበት ከባድ የጥቃት ዘመቻ በዝምታ ወይም እየተገደለ አልቀረም። ተወልዶ ያደገበት የትውልድ ቦታው ስለሆነ መግቢያው መውጫው ስለሚያውቀው፤መሳሪያ ያለው ታጥቆ፤ የሌለው በቤቱ ያገኘው ጎራዴ፤ ፋስ፤ ገጀራ፤ ወ.ዘ.ተ. እናቶች ወጣት ሴቶች ወንድም ሳይቀር በርበሬ በመያዝ ወያኔን በሚገባ በሁሉ አቅማቸው ገድለዉታል፤ አጥቅተዋል። በአንዳንድ ቦታዎችም ሙሉ በሙሉ ለማለት የሚቻለው የወያኔ ሠራዊት ደምሠዉታል። የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በታሪክ የተመሰከረለት አርበኛ ተዋጊ፤ ሙሉ ወኔ ያለው ህዝብ ከመሆኑ የተነሳ ከ1972 ዓ.ም. ጀምሮ ወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት. እንደፈለገው ኢትዮጵያን እንዲያፈርስ ህዝብ ሊበታትን በደም ሊያቃባ እድል አልሰጠዉም። የወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ጠለምት ህዝብ ቆለኛም ደገኛም ህዝብ ነው። የመሬቱ ነፋስ የተስማማ ከመሆኑ የተነሳ ወያኔ ይህ ህዝብ በቀላሉ ሊያጠቃው ጠራርጎ ሊያባርረው አልቻለም። ሌላው አማራ ቶሎ ብሎ በመቻኮል ወደ በቀል አርምጃ አይሸጋገርም፤ ከተነሳ ግን ወደ ኋላ አይታጠፍም፤ በአማራ ጥርስ የገባ ጠላት የመጨረሻ እጣ ፈንታው ውድቀት ምርኮ ናት። አማራ ለኢትዮጵያ አንድነት ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ዋልታና ማገር፤ የሃገሩ ድንበር በመጠበቅ፤የእስልምና፤ የክርስትና ሃይማናት ባለቤት በመሆኑም እነዚህ ሁሉ ተዳምረው በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ ህዝብ፤በባንዴራው አረንጓዴ፤ ብጫ፤ ቀይ የሚኮራ ህዝብ ነው። ይህ አማራ የሚባለው ህዝብ ዘሩን ካልጠፋ ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር በአፄ ምኒሊክ የተፈጠረች ናት፤ ከተፈጠረችም ከ100 ዓመት ያነሰ ዕድሜ ያላት ታሪክ-አልባ ሃገር ናት፤ ከዓለም ካርታ ለመፋቅ ይቻላል፤ ብሎ የተነሳው የባእዳን ቅጥረኛ ባንዳ ወያኔ፤ የአማራው ወኔ ጥንካሬ ጀግንነት አይቶታል፤ አሁን እያየው ነው።
ህ.ወ.ሓ.ት አማራውን ሲያጠቃ አብሮም የተጠቃው የኢትዮጵያ ተዋህዶ ክርስትናም ነው። ቀደም ሲል በ1971 ዓም በአክሱም አውራጃ እንዳባ ጴንጦሌን (ብዙ አክሱማዊም እንዳባ ፍሬሚናጦስ) እያለ የሚጠራው ከአክሱም ከተማ የ5 ኪሎሜትር ርቀት ያለው አካባቢው የሚጠራበት ስም ደግሞ እንዳየሱስ በተባለው ቦታ ጥንታዊው ገዳም እንዳ አባ ጴንጦለን ብዙ ጥንታዊ ቅርሶች፤ ብዙ ጥንታዊ የታሪክ መጻህፍት፤ ጥንታዊ የብራና ጽሁፎች የሚገኝበት ገዳም ለመዝረፍ ህ.ወ.ሓ.ት በሰነዘረው ጥቃት ሳይሳካለት ቀርቷል። ቀጥሎም በአድዋ ውስጥ የሚገኘው እንዳሥላሴ ገዳም ላይ ቢሞክርም አልተሳካለትም። ይህ ኦፐረሽን የተመራው በአረጋዊ በርሄ ነበር፤ቀጥሎ ወያኔ የዘመተው ወደ ዋልድባ ገዳም፤ በዚሁ ገዳም ተልእኮው ሙሉ ለሙሉ ተሳካለት፤ በህ.ወ..ሓ.ቱ ሊቀ መንበር ስብሃት ነጋና በህ.ወ.ሓ.ቱ ም/ሊቀመንበር ግደይ ዘራጽዮን መሪነት ዋልድባ ገዳም ሙሉ በሙሉ ተዘርፈዋል። ብዙ ብጹዓን ባህታውያን፤ ቀሳውስት፤ አባዎች ተገድለዋል፤ ታሪካዊ ቅርሶች መጻህፍት ብራናዎች ሃብቱ ንብረቱ ወ.ዘ.ተ. ተዘርፈዋል። አሁንም ዋልድባ ገዳም እየተጠቃ ይገኛል፤ ባለታሪክ ጥንታዊ ገዳም እየወደመ ለህልፈቱም ገደል አፋፍ ነው ያለው፤ ይህ ገዳም አማራን ብቻ አይመለከትም የሁሉ ኢትዮጵያዊነው፤ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይና ዋልድባ ገዳም በሚል ርእስ ለሁሉ ኢትዮጵያዊ ስለ አሰራጨሁት የዚሁ ቅዱስ ዋልድባ ገዳም በህ.ወ.ሓ.ት. የደረሰበትና እየደረሰበት ያለው ጥቃት በዝርዝር ስለፃፍኩት ጽሁፉ በየዌብ ሳይቱ ስለሚገኝ እዛው ፈልገን እንመልከት።
በአማራው የተፈጸመው አሰቃቂ ጥቃት ደግሞ ከሁሉ የከፋ በአርከበ እቁባይ፣ ዘርአይ አስገዶም፣ ሳሞራ የኑስ፣ ታደሰ ወረደ፣ ሃየሎም አርአያ ወዘተ የሚመሩ የገዳይ ቡድን ሕዝቡን እየሰበሰቡ በሳር ቤት ውስጥ በማስገብት ቤቱን በእሳት በማቃጠል ያለቅው ሰው ቁጥር ብዙ ነው። እኔ ራሴ ያየሁት አርከብ እቁባይ 12 ቤተሰቦችን ሰብስቦ በገዛ ቤታቸው፣ አባት፣ እናት፣ ልጆች፣ የተዳሩ ሴቶች ልጆቻቸውን ጨምሮ ከነህፃናቱ ሰብስቦ ሳር ቤት አዳራሽ አስገብቶና ቤቱን ዘግቶ እሳት ለቀቀባቸው። ሁሉም ቤተሰብ በእሳቱ አለቁ። በዚሁ በሰሜን ጎንደር የተካሄደው የዘር ማጥፋት ወንጀል በተጨማሪ ሁሉም ንብረታቸው ሃብታቸው፣ በሬ፣ ላም፣ ፍየል፣ በግ፣ አጋሰስ ጠቅላላ የቤት እንሣት ሁሉ በህወሓት ተዘርፈው ተወርሰው ተወሰደዋል።
ከ1972 ዓ.ም. ታህሳስ ወር ይህ ሁሉ ጥቃት የተጀመረው አጠቃላይ የጠገዴ፣ ጠለምት፣ ወልቃይት አማራ ዘሩ ሲጠፋ ቀሪው ደግሞ ወደ ሱዳን ተሰደደ፤ ጫካ ውስጥ ገብቶ ፀረ ወያኔ በሽምቅ ውጊያም የተሰማራ ጥቂት አልነበረም። ህዝብም ባገኘው መንገድ ሁሉ ወያኔን ከማጥቃት አላቆመም፤ የወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ጠለምት፤ ሴቶች በርበሬ በትንሽ ከረጢት ቋጥረው ከወገባቸው አትለይም በቤታቸው ውስጥም የተዘጋጀ አለ የወያኔ ታጋይ በመንገድ ሲገኙት አቁመው ለማነጋገር በመሰለ መልኩ ከያዝዋት በርበሬ ዘግነው በማውጣት አይኑ ላይ በመርጨት እዛው ሲደናበር መሣሪያ ማርከው ብዙ የወያኔ ታጋይ ገድለዋል። ወደ ቤታቸው የሚመጣ ታጋይም በርበሬ በውሃ በጥብጠው የሚበላ የሚጠጣ አቅርበው ደህና ነው ብሎ ሆዱን ሲሞላ፤ የበጠበጡት በርበሬ አይኑ ላይ በመድፋት የታጠቀው መሳሪያ ማርከው ታጋዩም በድምፅ አልባ መሳሪያ ይገድሉታ፤ በዚሁም ተገድሎ የጠፋ የወያኔ ታጋይ ብዙ ነው።
በ1973 ዓ.ም . በተለያየ መንገድ የተገደሉ ከማስታውሳቸው ውስጥ፤ በህዝብ ግንኙነት የነበሩት፤ አለማየሁ፤ብርሃነ፤ ፍስሃ፤ ገብረተንሳይ፤ ነጋሽ፤ አማረ፤ ደስታ የተባሉና ሌሎችም ብዙ ተገድለዋል። እነዚህን የጠቀስኩት ከማውቃቸው ነው። በወያኔ ታጋይ ሰራዊትም በተለያዩ መንገዶች በህዝቡ የተገደሉም ብዙ ናቸው ከማስታውሳቸው ለመጥቀስ ገብረ ሥላሴ፤ በላይ፤ ፍጹም፤ ካህሳይ፤ ነጋሽ፤ ገረግዚሄር፤ አባይ፤ አበበ፤ ጸጋይ፤ የሚባሉ ህዝቡን ለመግደል በቡድን በቡድን ተከፋፍለው ሲንቀሳቀሱ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብም በየጫካው  ተደብቆ በማድፈጥ የገደላቸው እነዚህን አስታውሳለሁ። የወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ጠለምት ህዝብ የሚቻለውን ሁሉ አቅሙ በፈቀደለት መጠን ህ.ወ.ሓ.ት. ወያኔን ከማጥቃት ባለው መሣሪያ እየተጠቀመ ወደ ኋላ ሳይል ጀግንነቱን ያስመሰከረና ያሳየ ህዝብ ነው። እኔ ባለኝ እምነት ይህ ኩሩ ጀግና ህዝብ ከወያኔ ፋሽሽት ቅኝ ገዢ አረመኔ ስርአት እየታገለ የመጣና ባለኝ እምነት መሠረት እውነትም የኢትዮጵያ መድህን ጠባቂም ነው። ተስፋ ሳይቆርጥ ከ1972 ዓ ም. አንስቶ እስከ ዛሬዋ ዕለት የማንነት ጥያቄው አድማሱን በማስፋት ወያኔ በማጥቃት ተሰማርቶ ይገኛል። በመሬቴ ላይ እሞታለሁ እንጂ ትወልድ ቦታየ አለቀም ያለው በ1969 ግንቦት ወር  የተጀመረው ጥቃት እስከ ዛሬ ድረስ ቀጥሏል። ይህ የሰሜን ጎንደር ህዝብ በወያኔ እየሞተ እየተገደለ ማንነቴን አሳልፌ አልሰጥም ብሎ 42 ዓመት ሙሉ ከተሓህት-ህወሓት ዘራችንም ብታጠፉ አንድ ሰወ እስኪቀር ማንነታችን አሳልፈን አንሰጥም እኛ አማራ ጎንደሬዎች እንጂ ትግሬዎች አይደለንም፤ ብሎ እስከ አሁን ድረስ በማንነቱ የማይደራደር ማንነቱን አሳልፎ የማይሰጥ ኩሩ ኢትዮጵያዊ አማራ ነው።
በምሬት እየታገለ የሚገኝ የጎንደሩ ህዝብ ከቀን ወደ ቀን ጥንካሬው በግልጽ እየታየ ነው። በየትም ቦታ የተገኘ አማራ እንዲገደል ህ.ወ.ሓ.ት. ያወጀው በ1969 ሲሆን፣ በትግራይ ውስጥ የሚኖሩ አማራዎችም ከየቦታው እየተለቀሙ እንዲገደሉ አምስቱ የተሓህት አመራሮች፣ አረጋዊ በርሄ፣ ሊቀመንበር፣ ግደይ ዘርአጽዮን፣ የድርጅቱ ም/ሊቀመንበር፣ አባይ ፀሃየ፣ ስዩም መስፍን፣ ስብሃት ነጋ አድርገዋል። ትግራይ የትግራዮች እንጂ የሌላው መጤ ቦታ አይደለችም፣ ስለሆነም ማንም የትግራይ ተወላጅ ያልሆነ ከትግራይ ይውጣ ተብሎ እንዲታወጅም ያደረጉት እነዚሁ ናቸው። በአዋጁ መሰረትም አማራው በነቂስ እየተፈለገ ተገደለ፣ እነዚህ ይህ ውሳኔ የተላለፈባቸው ከትግራይ ተጋብተው ልጆች ወልደው ያሳደጉም ናቸው፤ ያመለጠውም ሂወቱና ቤተሰቦቹን ይዞ የሸሸም ብዙ ነው። ይህ የተመለከተና ያየ የትግራይ ህዝብም ወያኔን አወገዘ፤ መሬታቸው ነው አይወጡም፤ ይህ የኢትዮጵያ ቦታ ነው፤ ማነው ወጪ ማነውስ አስወጪ፤ ከፈለጋቹህ ወያኔዎች ውጡ እያለ ከአማራው ወንድሙ ጋር ቆመ። በየቦታው ፀረ ወያኔ እንቅስቃሴ ተነሳ፤ ወያኔም በየቦታው ይህ እንቅስቃሴ የታዩባቸው ቦታዎችን በህዝብ ግንኙነት ክፍል በኩል በፀረ ወያኔ ፖሊሲ ተንቀሳቅሰዋል ያላቸውን የትግራይ ሰዎች አንድ በአንድ እየለቀመ ሓለዋ ወያነ በማስገባት ደብዛቸው አጠፋቸው፤ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ።
ተሓህት-ህወሓት ይህን ሁሉ በሰሜን ጎንደር አማራው ኅብረተሰብ ላይ ይህን ሁሉ ግፍ ሲፈጽም እጃቸውን ለወያኔ የሰጡ የኢህአፓ አባላት የነበሩ፤ ታምራት ላይኔ፣ አዲሱ ለገሰ፣ ተፈራ ዋልዋ፣ በረከት ስምኦን፣ ዮሴፍ ረታ፣ መለሰ ጥላሁን፣ ህላዊ ዮሴፍ፣ ታደሰ ካሳ፣ ሙሉአለም አበበ፣ ወዘተ ይገኙበታል። ከወያኔ ህወሓት ጋር በመተባባር የሰሜን ጎንደር፣ ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት ወዘተ የቀድሞዎቹ ኢ.ህ.ዴ.ን. በህ.ወ.ሓ.ት. አምሳልና ቡራኬ ተጠፍጥፈው የተሰሩ ተላላኪዎች የዛሬዎቹ ብአዴን አካባቢው ለብዙ ጊዜ የቆዩበትና የሚመሩበት ስለነበሩ ሕዝቡን በነቂስ ስለሚያውቁት አካባቢ እየመሩ ለወያኔ ጥቃትና የዘር ማጥፋት ወንጀልም ተባባሪ ሆነዋል። ወያኔን እየመሩ የሰሜን ጎንደሬውን አማራ አጥቅተውታል። ስለሆነም በማራው ላይ የደረሰው የዘር ማጥፋት ወንጀል በተለያዩ የጥቃት ዘዴዎች በህወሓት የተፈጸመው እነዚህ የብአዴን አመራር ከህወሓት አመራር ጋር አብረው ተጠያቂ ናቸው።
በሕዝብ ላይ ለሚደርሰው ጥቃት፤ ሃብት ንብረት ዘረፋ፤ ለሚደርሰው ማንገላታት ሰላማዊ ዜጋው ተይዞ ለእስር የሚዳረገው በሕዝብ ግንኙነት በኩል ጥናትና ሪፖርት ነው። መኮንን ዘለለው ለመጀመሪያ ጊዜ በህ.ወ.ሓ.ት በኩል ወደ ወልቃይት ጠገዴ የተሰማራው እሱ ነበር፤ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ግን አልተቀበለውም። ሪፖርቱ ሲያስተላልፍም ሁሉም ፀረ ተ.ሓ.ህ.ት./ህ.ወ.ሓ.ት ናቸው በማለት ከነስም ዝርዝራቸው ለወያኔ ፖሊት ቢሮ (ከ100 በላይ ሰዎች ሴቶችም አሉበት) ቀስ በቀስ አንድ በአንድ ብስራት አማረ በሚመራው አፋኝ ቡድን ተለቅመው በቡምበትና ሱር ሓለዋ ወያነ ገብተው ጠፍተዋል፤ ንብረታቸውም ሙሉ በሙሉ በወያኔ ተዘርፎ ባዶ ቤት ቀርቶዋል። የዚህ ሁሉ ተጠያቂው ስንመለከት፣ መኮንን ዘለለው ነው። በዚህም ላይ የሚጠየቁ መረሳ ረዳ፣ አጽብሃ ሃይለማሪያም፣ ፀጋይ በርሄ (ሃለቃ)፣ መኮንን የአዲረመጽ ሕዝብ ግንኙነት፣ አርአያ ወርቅነህ፣ ቅዱሳን ነጋ፣ ቀሺ ታደሰ፣ መሃሪ ግብርገርግስ፤ ሃለቃ ታደለ አለምሰገድ፤ መብራት በየነ፤ ወዘተ ናቸው። እነዚህም አንኳር ተጠያቂ ናቸው።
ገብረመድህን አርአያ፣ ፐርዝ፣ አውስትራሊያ
በሚቀጥለው ዕትም “የህወሓት ፕሮግራም” በሚል ርዕስ ሃተታ እናቀርባለን።http://www.goolgule.com/tplfs-objective-of-destroying-ethiopia/

No comments:

Post a Comment