Translate

Tuesday, October 11, 2016

ኢንጂነር ይልቃል ታሰሩ

(ዘ-ሐበሻ) የሰማያዊ ፓርቲን እስከባለፈው ሳምንት ድረስ ሲመሩ የቆዩት ኢንጂነር ይልቃል መታሰራቸው ተሰማ:: ከርሳቸው ጋር አብረው ሌሎች የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች መታሰራቸው ተሰምቷል::
መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አውጥቻለሁ; እየታደስኩኝም ነው ባለ ማግስት ተቃዋሚዎችን እየጠራረገ ማሰሩን ተያይዞታል::
hiber-radio-interview-with-eng-yilkal-getnet.jpg
ከኢንጂነር ይልቃል በተጨማሪ አቶ ወረታው ዋሴ; ወይንሸት ሞላ እና ብሌን መስፍን እንዲሁም እያስጴድ ተስፋዬ በተለያዩ ቦታዎች በደህንነቶች ተይዘው መታሰራቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል::
ሰማያዊ ፓርቲ ባለፈው ሳምንት ባደረገው ጉባኤ ኢንጂነር ይልቃልን ከሊቀመንበርነት ማንሳቱ ይታወሳል::

No comments:

Post a Comment