ክንፉ አሰፋ

ሕዝባዊ አመጹ ያመጣውን ቀውስ ተከትሎ በህወሃት ከፍተኛ አመራር ውስጥ ከፍተኛ መበጣበጥ እና የርስ-በርስ ፍጥጫ መከሰቱን ከታመነ የውስጥ አዋቂ ምንጭ መረጃ ደርሶናል።
“Whoever sows injustice will reap calamity.”
“አመራሩ ክፉኛ ከመከፋፈሉ የተነሳም የርስበርሱ ችግራቸው ላይ ተወጥረዋል።” ይላል መረጃው። ቀንደኞቹ የህወሃት አባላት ስርዓቱ እንዳበቃለት ስለተገነዘቡ ንብረት እና ልጆቻቸውን በማሸሽ ላይ ናቸው።
ሕዝቡ ሁሉ እንደተፋቸው በግልጽ እየነገራቸው ስለተገነዘቡ፤ የህወሃት የደህንነት አባላት ሕዝቡን ተተው የራሳቸውን ሰራዊት እና ፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሰልሉ ተነግሯቸዋል። “ተጠርጣሪ” የኦህዴድ እና ብአዴን አባላት በነዚህ ሰላዮች ስለተከበቡ በፍርሃት መወጠራቸውን ከራሳቸው አንደበት እየተሰማ ነው።