Translate

Tuesday, August 23, 2016

በቂሊንጦ ወህኒ ቤት ታስረው የሚገኙ እስረኞች የሶስት ቀን ብሄራዊ ሃዘን እንዲታወጅ ጠየቁ


ኢሳት (ነሃሴ 17 ፥ 2008) 
በተለያዩ ክልሎች ለዴሞክራሲ፣ ፍትህና ነጻነት ሲሉ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖችን ለማስታወስ ኢትዮጵያውያን ከነሃሴ 19 እስከ 21 ፣ 2008 የሚቆይ የሶስት ቀን ብሄራዊ ሃዘን እንዲታወጅ በቂሊንጦ ወህኒ ቤት ታስረው የሚገኙ እስረኞች ጠየቁ። 
በአቶ በቀለ ገርባ፣ ደጀኔ ጣፋ፣ አዲሱ ቡላላ፣ ጉርሜሳ አያኖ፣ ዮናታን ተስፋዬ፣ ፍቅረማሪያም አስማማው፣ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ እና ብርሃኑ ተክለ ያሬድ በጋራ ተጽፎ ለኢሳት የደረሰው ደብዳቤ፣ “ብሄራዊ የሃዘን ቀን የሚታወጀው የዲሞክራሲና የፍትህ ጥያቄ አንግበው የተሰው ወገኖቻችንን በልባችን ውስጥ ህያው ሆነው እንደሚኖሩ ለማረጋገጥና እነሱም የወደቁለትን አላማ በትግላችን እንደምናሳካው ቃል ለመግባት እንዲሁም ለቤተሰቦቻቸውም አጋርነታችንን ለማሳየት ነው” ሲል ያስረዳል። 

Sunday, August 21, 2016

ህወሃት በሕዝብ ላይ የደገሰው በዶ/ር ደብረጽዮን አንደበት

ህወሃት በሕዝብ ላይ የደገሰው በዶ/ር ደብረጽዮን አንደበት

(ክንፉ አሰፋ)
haile tplf debretsion
ባለፈው ሳምንት ጌታቸው ረዳ ከአልጃዚራ ቴሌቭዥን ጋዜጠኛ ጋር ተጋፍጦ ነበር። አንድ ጥያቄ ቀረበለት። “በራሳችሁ የምትተማማኑ ከሆነ ለምን የተባበሩት መንግስታት ታዛቢዎች እንዳይገቡ ከለከላችሁ?”
ሚኒስትር ጌታቸውም። “የተባበሩት መንግስታት አያስፈልገንም። እኛው ራሳችን ከህዝቡ ጋር እንነጋገራለን።” ሲል ነበር የድፍረት መልስ የሰጠው።

አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ቃለምልልስ ሰጠ “ከባለፉት 9 ወራት ብቻ ከ1 ሺህ በላይ ኦሮሞዎች በኢትዮጵያ ተገድለዋል – ወደዚያ አልመለስም”

 አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በሪዮ ኦሎምፒክ በማራቶን ውድድር የብር ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ ካመጣ በኋላ እጁን ወደላይ በማጣመር መንግስትን የተቃወመው ባለፉት 9 ወራት ብቻ ከ1 ሺህ በላይ ኦሮሞዎች በመንግስት ጸጥታ ኃይሎች በመገደላቸውና በርካቶችም በመታሰራቸው ነው አለ:: አትሌቱ በቃለምልልሱ ላይ እንዳለው ወደ ኢትዮጵያ ቢመለስ ለህይወቱ አስጊ በመሆኑ ወደ ኢትዮጵያ እንደማይመለስ አስታውቋል:: ቃለምልልሱን በቭዲዮ ይመልከቱት::

Saturday, August 13, 2016

ስለ ወያኔ መውደቅ ሳስብ(ሄኖክ የሺጥላ)

ስለ ወያኔ መውደቅ ሳስብ ፥ አይኖቼ በደስታ እንባ ይሞላሉ ። እንባውን የፈጠረው ይቺን ቀን ማየት ያልቻሉትን ብዙዎች ስለማስብ ነው ። ዛሬ ጎንደር ላይም ሆነ ኦሮሚያ ላይ የተነሳው ትግል ፥ ባንድም ይሁን በሌላ መልኩ የዛሬው ደረጃ ላይ ከመድረሱ በፊት አእላፋት ህይወታቸውን ገብረውበታል ። እልፎች ታስረዋል ፥ ህልቆዎች ከስራ ፥ ከሃገር ተባረዋል ፥ ቆጥረን የማንጨርሳቸው ሊህቃኖች ተንገላተዋል ፥ ታድርደዋል ። ህፃናቶች ተገለዋል ፥ እናቶች ፀጉራቸውን ተላጭተው አሸባሪ ተብለው ታስረዋል ። ብዙዎች በርሃ ወርደዋል ፥ እጅግ ብዙዎች ሞተውለታል ፥ ብዙዎችም ሞተውበታል!

በደብረማርቆስ ንግድ ቆሟል | አልሞ ተኳሾች ብዙ ሰው አቁስለዋል

በደብረማርቆስ ንግድ ቆሟል | አልሞ ተኳሾች ብዙ ሰው አቁስለዋል
(ዘ-ሐበሻ) በጎጃም ደብረማርቆስ የተነሳውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር አልሞ ተኳሽ (ስናይፐር) ፖሊሶችን መጠቀሙ ተሰማ:: እነዚህ አልሞ ተኳሾችም ያቆሰሏቸው ስዎች ቁጥር ከ20 እንደሚበልጥ ዘ-ሐበሻ በስልክ ያነጋገረቻቸው የደብረማርቆስ ነዋሪዎች ገልጸዋል::

በወልቃይት ጠገዴና ቃብቲያ ሁመራ ህዝብ ላይ የታቀደው ድቡቁ የህወሓት ሴራ ሲጋለጥ

A Quest for Identity and Geographic Restoration of Wolkait-Tegede, Gondar, Amhara, Ethiopia.
በቅድሚያ ይህንን ድብቅ የወያኔ ሴራ የሚያጋልጠውን ሰነድ ከነትርጉሙ የላኩልንን ወገኖች ከልብ እናመሰግናለን።

Friday, August 12, 2016

በጎጃም መንግስት ፈረሰ እየተባለ ነው

Alemnew Mekonnen
የአማራውን ሕዝብ “ልፋጫም” ብሎ የተሳደበዉና ሕወሃት ጉልበት ብቻ አመራር ላይ የተቀመጠው አለምነህ መኮንን ባረፈበት ሆቴል ድብደባ እንደተፈጸመበት መረጃዎች ይጠቁማሉ። አለመነህ በሕወሃት ታጣቂዎች ታጅቦ ሾልኮ ከአካባቢው ያመለጠ ሲሆን፣ ብዙዎች ሰዉዬው አይኑን በጨው አጥቦ በዚህ ወቅት ሕዝብ ፊት ለመቅረብ መድፈሩ አስገርሟቸዋል።
በጎጃም እነብሴ ሳር ምድር፣ቋሪት እና ሌሎች ደጋማ ቦታወች ያሉ አርሶ አደሮች መንግስት ፈርሷል የሚል ወሬ በመስማታቸው የቀበሌ ሊቀመንበር እና ፀሃፊወችን ቤታቸውን በድንጋይ እና በጥይት እንደደበደቡ እየተነገረ ነው። እስካሁን አራት የገጠር ሚሊሻወች የተገደሉ ሲሆን አቶ ቢያድጌ አለሙ የሚባል ሊቀመንበር መገደሉ ታውቋል።