Translate

Tuesday, March 14, 2017

የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ጋዜጣዊ መግለጫ

የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ

Sochii Biyyaa Itiyoophiyaa
 Ethiopian National Movement

 ዋሽንግተን ዲሲ – መጋቢት 13, 2017 

ለሃያ ስድስት አመታት የዘለቀው የህወሃት / ኢህአዴግ ጨቋኝ አገዛዝ በወገኖቻችን ላይ ያደረሰውና እያደረሰ ያለው ግፍና መከራ ቅጥ ያጣ መሆኑ ለሁላችንም ግልጽ ከሆነ ቆይቷል። ዕለት ተዕለት በወገኖቻቻን ላይ የሚደርሰው የማዋረድና የሰቃይ ገፈት በተለያየ መልኩ ለስርአቱ ታማኝ በሆኑ የጸጥታ የፖሊስና የሚሊሽያ ኃይሎች ይፈጸማል። ይህ ህዝብን ያለማቋረጥ የማሰቃየትና የመበደል ስራን ዋነኛ ሙያው ያደረገው ዘረኛ ስርአት በአደባባይ በጠራራ ጸሃይ ወገኖቻችንን በጥይት መቁላት አልበቃ ብሎት ዛሬ ደግሞ የሰርአቱ ግፈኞች ጠግበው በሚጥሉት የቆሻሻ ናዳ ህጻናት ሴቶች ወንዶች አዛውንትና ወጣቶች ለሞትና ለአካል ጉዳት እንዲዳረጉ እያደረገ ነው።
Ethiopian garbage dump landslide
 ወገኖቻቻን የሚልሱት የሚቀምሱት አጥተው በረሃብ ሰቆቃ በሚሰቃዩበት በዚህ ወቅት “ታላቅ የኢኮኖሚ እድገት”
አስመዝግቤአለሁ እያለ ያለማሰለስ የሚያቅራራው የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ለከፍተኛ የአመራር አባላቱና በሙስና ለተዘፈቁ ጥቂት አድርባዮቹ የቅንጦት ደሴት ፈጥሮ በወገኖቻቻን ላይ የበደልና የመከራ ቀንበር በመጫን በአገራችን ታሪክ ወደር የሌለው የግፍና የሙስና ስርአት ገንብቷል። ይህ የህወሃት/ኢህአዴግ የፖለቲካ የኢኮኖሚና ማሀበራዊ በደል ያስመረራቸው ወገኖቻችን ቀጣይነት ባለው ህዝባዊ እምቢተኝነት ለነጻነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ መከበር የሚያደርጉት ትግል በተፋፈመበት በዚህ ወቅት ስርአቱ የሚያደርሰው በደል እየከፋ እንደሄድ ብዙም የሚያከራክር አይደለም።

 የኢዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ በዚህ ባለፈው ሳምንት ከአዲስ አበባ ወጣ በሎ በሚገኘው የቆሻሻ መጣያ ዙሪያ የሚኖሩና ከዚያ ቆሻሻ በሚገኝ ልቅምቃሚ የአሳር ኑሮአቸውን በሚገፉ ወገኖቻቻን ላይ የደረሰው አሰቃቂ የሞትና የመቁሰል አደጋም የስር አቱ አምባገነናዊ የፖለቲካና የኢኮኖሚ መርህ ውጤት ነው ብሎ ያምናል። “የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ወገኖቻችን በህወሃት/ኢህአዴግ የተዋረደው ክብራቸውን አስመልሰው በክብርና በነጻነት ሊኖሩ የሚችሉት ይህ ስርአት በአስቸኳይ ተወግዶ በዲሞክራሲና በህግ የበላይነት ላይ የቆመ ስርአት ሲመሰረት ብቻ ነው ብሎ ያመናል።

 ለዚህ የነጻነት ትግል መሳካትም በአራቱ ማዕዘን ያሉ ወገኖቻችን የትግል ክንዳቸውን አስተባብረው ይህ የመከራ ዘመን እንዲያበቃ መታገል አማራጭ የሌለው ስልት መሆኑን ተረድተው በአዲስ መንፈስ እንዲነሳሱ ጥሪ እናቀርባለን።

 በእኛም በኩል ትግሉ የሚጠይቀውን መስዋእትነት ለመክፈልና ትግሉም ከታለመለት ግብ እንዲደርስ የድርሻችንን ለመወጣት ዝግጁ መሆናችንን ዳግም እናረጋግጣለን።” ሲሉ ዶክተር ዲማ ነጎ የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ገልጸዋል። በመጨረሻም ይህ አስቃቂ የሞትና የመቁሰል አደጋ ለደረሰባቸው ወገኖች መጽናናቱን እንዲሰጣቸው ክልብ እንመኛለን። 

ለተጨማሪ ማብራሪያ

 Email: ENMPR@protonmail.com

No comments:

Post a Comment