ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
(እ.ኤ.አ መጋቢት 27/2016 በማሪዮት ጆርጅታዎን ከተማ (ዋሺንንግቶን ድሲ ) ቪዥን ኢትዮጵያ በተባለው ድርጅት አስተባባሪነት “ስለወደፊቷ ኢትዮጵያ፡ ሽግግር፣ ዴሞክራሲ እና ብሄራዊ አንድነት ጉባኤ” በሚል ርዕስ በእንግሊዝኛው ቅጅ ከቀረበው ንግግር የተወሰደ ነው፡፡)

…
“ስለወዲፊቷ ኢትዮጵያ፡ ሽግግር፣ ዴሞክራሲ እና ብሄራዊ አንድነት ጉባኤ” በሚል ርዕስ ስለተዘጋጀው ጉባኤ ቪዥን ኢትዮጵያን እና የጉባኤውን አስተባባሪዎች በሙሉ ለማመስገን እፈልጋለሁ፡፡
ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው ከወራት በፊት በዚህ ጉባኤ ላይ እንድገኝ እና እንድሳተፍ ጥሪ ባቀረበልኝ ጊዜ ኢትዮጵያን ገጥመዋት ባሉት መሰረተ ሰፊ የተሳትፎ መድረክ፣ ውይይት እና ክርክር ጉዳዮች ሀሳብ እጅግ በጣም ነበር የተደሰትኩት፡፡ የቪዥን ኢትዮጵያን አርዓያ በመከተል ሌሎችም እንደዘሁ በርካታ የውይይት መድረኮችን ያዘጋጃሉ የሚል ተስፋ አለኝ፡፡