Translate

Saturday, October 31, 2015

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የለሊቱ የቪኦኤ ሚስጥራዊ ጉባኤ (በአበበ ገላው)

በአበበ ገላው (ትርጉም በታኬ)
Tedros Adhanom and Ambassador Girma Birruበቅርቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም እና አምባሳደር ግርማ ብሩ በዩናይትድ ሰቴትስ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲ.ሲ በሚገኘው የቪኦኤ ሬዲዮ ጣቢያ በሌሊት በድብቅ በመግባት ሕጋዊ ስልጣኑ ሳይኖራቸው ስለስርጭቱ ለጥቂት የድርጅቱ ሠራተኞች የኢዲቶሪያል መመሪያ ከሰጡ በኋላ በአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት (ቪኦኤ) እና በህወሀት የበላይነት በሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት መካከል ያለው የሻከረ ግንኙነት ያልተጠበቀ አቅጣጫ ይዟል፡፡ ስብሰባው በሚስጥር በተካሄደበት ጊዜ የአምባገነኑ አገዛዝ ባለስልጣኖች ለሬዲዮ ስርጭቱ ሰራተኞች ስለዜና አዘጋገብ፣ እንደዚሁም ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ስለሚተላለፈው የስርጭት ጥራት ሁኔታ መመሪያ የመስጠት ሙከራ ያደረጉ ለመሆናቸው ከታመኑ ምንጮች በተገኙ መረጃዎች ተረጋግጧል፡፡

አይኔ አያየ እዚህ ዉስጥ አልገባም – መሠረት ሙሌ (ኤፍሬም ማዴቦ ከአርበኞች መንደር)

ኤፍሬም ማዴቦ ከአርበኞች መንደር
Patriotic Ginbot7 fighters
መብራቱን አጥፍቼዉ አልጋዬ ላይ የወጣሁት በግዜ ነዉ። አለወትሮዬ እንቅልፍ የሚባል ነገር በአይኔ አልዞር ብሎኝ ከጨለማዉ ጋር ፊት ለፊት ተፋጥጠናል። የነፋስ ሸዉታ እንኳን የማይሰማበት ደረቅ ሌሊት ነዉ። ጨላማዉ አይን ይበሳል። እቤቱ ዉስጥ ያለዉ ሰዉ ሁሉ ተኝቷል። ቀኑን በሠላም ላዋለኝ አምላክ ምስጋና ሰጥቼ ሌሊቱንም አደራ ብዬዉ ፀሎቴን ጨረስኩ። ያ ምቀኛ እንቅልፍ ግን አሁንም እንደከዳኝ ነዉ። ትንሿ አልጋዬ ላይ ግራ ቀኝ እያልኩ ተገለባበጥኩ። እንቅልፍ ተጎትቶ የሚመጣ ይመስል አሁንም አሁንም ላይ ታች እያልኩ አልጋዉ ላይ እራሴን ጎተትኩት . . . እንኳን እንቅልፍ ሊወስደኝ ጭራሽ አይኖቼ መርገብገባቸዉን ያቆሙ ይመስል ቀጥ ብለዉ ቀሩ። ከተጋደምኩበት ብድግ ብዬ መብራቱን አበራሁና ለመንገድ ከያዝኳቸዉ ሁለት መጻህፍት አንዱን አዉጥቼ ማንበብ ጀመርኩ። እኔ ላንብበዉ ወይ መጽሀፉ ያንብበኝ አላዉቅም። ጧት ስነሳ ግን “The Architecture of Democracy” የሚል መጽሐፍ ደረቴ ላይ ተለጥፎ ነበር።

Thursday, October 29, 2015

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ) በላንድ ክሩዘር መኪና ተሳፍረው ወደ አርባ ምንጭ ከተማ በፍጥነት ያመሩ የነበሩ 10 የፌደራል ፖሊስ አባላት ኮንሶ እና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ከነመኪናቸው ሙሉ በሙሉ ተደመሰሱ፡፡


የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)
በላንድ ክሩዘር መኪና ተሳፍረው ወደ አርባ ምንጭ ከተማ በፍጥነት ያመሩ የነበሩ 10 የፌደራል ፖሊስ አባላት ኮንሶ እና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ከነመኪናቸው ሙሉ በሙሉ ተደመሰሱ፡፡
====================================================
በትናንትናው ዕለት አመሻሽ ላይ አስሩ የፌደራል ፖሊሶች መጀመሪያ አንድ አይሱዙ የጭነት መኪና በኃይል በማስገደድ አስቁመው የተሳፈሩ ሲሆን መኪናው መንቀሳቀስ ሲጀምር "የጫንካቸውን ፖሊሶች አራግፍ አለያ ከነንብረትህ አብረህ ትጋያለህ!" የሚል የስልክ ማስጠንቀቂያ መልዕክት ለአሽከርካሪው በመድረሱ አሽከርካሪው መኪናውን አቁሞ ፖሊሶቹን "አልሄድም" ይላቸዋል፡፡ ቀጥሎም ፌደራል ፖሊሶቹ ሾፌሩን ለማንገራገር ሞክረው ትዕዛዛቸውን በቀላሉ ሊቀበል ባለመቻሉ ስልክ ተደዋውለው ሌላ ላንድ ክሩዘር መኪና እንዲመጣላቸው በማድረግ ተሳፍረው ጉዟቸውን ቀጥለው ኮንሶ እና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ሲደርሱ ቅፅበታዊ ጥቃት ተከፍቶባቸው ከነተሳፈሩበት መኪና ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል፡፡
በተያያዘ ዜና ሙሉጌታ አባ፣ ፀጋዬ ገብረ ፃድቅ እና በኃይሉ ሲሳይ የተባሉ የህወሓት ጆሮ ጠቢዎችና የአካባቢው ቆራጭ ፈላጮች ፎቶግራፋቸው በማህበራዊ ሚዲያው መሰራጨቱን ተከትሎ ከትናንት ምሽት ጀምሮ አርባ ምንጭ ከተማ ከከዚህ ቀደሙ በባሰ ሁኔታ በፌደራል ፖሊስ ተጥለቅልቃ እየታመሰች ትገኛለች፡፡ 

Wednesday, October 28, 2015

(ሰበር ዜና) መምህር ግርማ ታሰሩ

Memeher-Girma
(ዘ-ሐበሻ) በአውሮፓ የተለያዩ ሃገራት በማጥመቅ ላይ ቆይተው ወደ ሃገራቸው የተመለሱት መምህር ግርማ ወንድሙ በአዲስ አበባ ፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የመምህሩ ቅርብ ሰዎች የሆኑ ታማኝ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ:: እንደ ዘ-ሐበሻ ምንጮች ዘገባ ከሆነ መምህር ግርማ ወንድሙ ፈቃድ ሳይኖራቸው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስም ተጠቅመው በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሃገር በማስተማር እና በማጥመቅ ሥራ ላይ ተሰማርተዋል በሚል በቤተክህነት በቀረበባቸው ክስ ነው የታሰሩት:: በአገልግሎታቸው የተነሳ በወንጀል እንደሚጠየቁ በፖሊስ እንደተነገራቸው የተገለጸው መምህር ግርማ በአዲስ አበባ ፖሊስ ቁጥጥር ሥር ላይ ውለው ምርመራቸው እንደቀጠለ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል:: ምንጮቻችን የሚያደርሱንን መረጃዎች ይዘን እንቀርባለን::

ዘ-ህወሀት በኢትዮጵያ የተከሰተውን ረሀብ ማቆም ይችላልን? (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በአውዳሚ ረሀብ መካከል ተሰንጋ መያዟ ታላቅ ዓለም አቀፍ ሚስጥር ሆኖ ይገኛል፡፡Can the T-TPLF Stop the Famine in Ethiopia?
.. 1984-85 ወዲህ ለሁለተኛ ጊዜ የተከሰተ ታላቅረሀብ!
ባለፈው ሳምንት ግሎባል ፖስት/Global Post የተባለው የዜና ወኪል በርዕሰ አንቀጹ የመጀመሪያ ርዕስ በማድረግ እንዲህ የሚል ጥያቄ አቅርቧል፡
“ኢትዮጵያ ባለፉት 30 ዓመታት ጊዜ ውስጥ በአስከፊነቱ የመጀመሪያ የሆነውን ድርቅ ተጋፍጣ ትገኛለች፡፡ መንግስት በአሁኑ ጊዜ የተከሰተውን ረሀብ ማስቆም ይችላልን?”
ግሎባል ፖስት መንግስት ረሀቡን ማስቆም ይችላል ወይ የሚል ጥያቄ ያቀረበለት እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ ለሚጠራው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ-ህወሀት) ነው፡፡

Tuesday, October 27, 2015

አይ ስብሐት ነጋ – ከፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

በኢትዮጵያ ውስጥ ሥልጣን ሳይኖረው ባለሙሉ ሥልጣን፣ እውቀት ሳይኖረው ባለሙሉ እውቀት የሆነ ሰው ስብሐት ነጋ ብቻ ነው፤ እንዲያውም ከዚያም አልፎ ራሱን የቻለ ሉዓላዊ ነጻነት ያለው ግለሰብ ነው ለማለት የሚቻል ይመስለኛል፤ በዚህ ግለሰብ ላይ የማደንቃቸው ሁለት ነገሮች ናቸው፤ በሉዓላዊነቱ የተጎናጸፈውን ሥልጣን ሙሉ በሙሉ ይጠቀምበታል፤ ይቆጣኛል ወይም ይቀጣኛል ብሎ የሚፈራው የለም፤ ስብሐት ነጋ የሚፈራው ምንም ነገር የለም፤ ሁለተኛ በሉዓላዊነቱ ያለውን ሙሉ ነጻነት በሙሉ ልብ ይጠቀምበታል፤ ናስ በላይ ከበደ እንዳለው ‹‹የቅብጠት መዘላበድ›› ሊሆን ይችላል፤ ስብሐት ነጋ የተናገረው ነገር ትክክል ይሁን አይሁን ጉዳዩ አይደለም፤ ዋናው ነገር መናገሩ ነው።

በቅርቡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከጋዜጠኛነት ተማሪዎች ጋር ባደረገው ውይይት ላይ ሁለት ሰዎች ጽፈው አይቻለሁ፤ ዶር. በድሉ ዋቅጅራ በፋክት ላይ፣ ናስ በላይ አበበ በኢትዮ-ምኅዳር ላይ፤ ሁለቱም ሰዎች አልወደዱለትም ማለት ያንሳል፤ የሚወዱለትና የሚያጨበጭቡለት መኖራቸውም ሳይታለም የተፈታ ነው፤ ነገር ግን ስብሐት ነጋም ሆነ ደጋፊዎቹ አደባባይ ወጥተው ለመከራከር አይችሉም፤ ናስ በላይ አበበ እንደሚነግረን ‹‹አቶ ስብሐት ነጋ የውጭ ሰው እንዳይገባ ከተማሪዎቹ ጋር ተደራድረው ነበር የመጡት፤ ስለሆነም ነበር ከፍተኛ ጥበቃ አልፈን የገባነው፤›› ብቻውን ተናግሮ በጭብጨባ የሚሸኝበት መድረክ በመፈለጉ በከባድ ጥያቄም ቢሆን የሚያጣድፉት ሰዎች እንዳይኖሩ ማረጋገጡ በተማሪዎቹም ቢሆን ውሎ አድሮ ትዝብት ላይ ይጥለዋል።

የተቦርነ የፈራረሱ ቅኝቶች (ከአርአያ ተስፋማርያም)

ከአርአያ ተስፋማርያም
ወዳጄ ተቦርነ በተመለከተ ግልፅ ያልሆኑልኝ ነገሮችን አንስቼ በጥያቄ መልክ አቅርቤ ነበር። አንተም ለኔ ጥያቄ የሚሆን የመልስ ፅሑፍ ለጥፈህ አነበብኩት። የመለስክልኝ መልስ በጣም አስገርሞኛል፣ ግራም አጋብቶኛል። ያንተኑ ተረት በመዋስ “ማሞ ሌላ መታወቂያው ሌላ” ብየዋለሁ። ምክንያቱም ጥያቄዬን መመለስ ስላልቻልክ ወይም ስላልፈለክ እኔን በመሳደብ ጥያቄውን ለማድበስበስ ስትሞክር ነበር። ሃሳብን በሃሳብ መርታት ሲቃትህ ሃሳቡን ያቀረበውን ግለሰብ የማጥቃት የተባለ የክርክር ግድፈት ወይም ሎጂካል ፋለሲ ነው። ምን አልባት ጥያቄዬን ካልተረዳኸው ደጋሜ ላንሳው።
ዘረኛ፣ ኣምባገነንና ሙሰኛ የሆነው የኢህአዴግ መንግስት ህዝባችንን ከፍላጐቱ ውጭ በሀይል፣ በማስፈራራትና በዘር በመከፋፈል እየገዛ 24 አመታት አለፈ። ይህ መንግስት የስልጣን ዘመኑ እንዲቀጥል ህዝቡን በዘር መከፋፈል፣ በሀይል ማፈንና አዲሱ ትውልድ በተለያዩ የማይረቡ ጉዳዮች ማደንዘዝ ዋና አላማዬ ነው ብሎ እየሰራ ይገኛል። ለብዙ ኢትዮጵያዊያን ሞት፣ እስራት፣ ግርፋት፣ ድህነትና ስደት ተጠያቂ ከሆነው ከዚህ መንግስት ጋር የጥቅም ተካፋይ ሆነው ስልጣኑ እንዲረዝም በገንዘባቸውና በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ ከሚረዱት ሰዎች አንዱ ሼኽ አልሙዲ ናቸው። ሼኹ በኢትዮጵያ ፖለቲካ በፈፀሙት ደባ፣ የሀገሪቱን ሃብት በመበዝበዝ የሃገራችንን ባህልና ወግ የሚያናጋ የማህበራዊ ቀውስ በህብርተሰቡ ውስጥ በማምጣት የሚጠየቁ ሰው ናቸው።
ከላይ እንደጠቀስኩት የዚህ መንግስት ዋና አላማው ህዝቡን ከፋፍለህ መግዛት ብቻ ሳይሆን ትውልዱን ስለሃገሩ ታሪክ፣ ስለማንነቱ፣ ስለሰብዓዊና ዴሞክራሲ መብቶቹ እንዳያውቃና እንዳይጠይቅ ማደንዘዝ ነው። ለዚህ አላማ መሳካት የፖለቲካ፣ የታሪክ፣ የፍትህ፣ ፍልስፍናና የማንነት ጥያቄ የማያነሱትን እንዲሁም ህዝብ እንዲነቃ የሚያደርጉትን የመገናኛ ብዙሃን እየዘጋ፣ ሽብርተኛ እያለ ጋዜጠኞችንም እያሰረ፣ እያሸማቀቀ፣ ከሀገር ያሰድዳል። በተቃራኒው ደግሞ ህዝቡ ከሀገሩ ጉዳይ ጋር እንዲፋታ የፖለቲካም ሆነ የመብት ጥያቄ ሲያነሳ የተባለውን አድራጊ፣ የተጠየቀውን ፈፃሚ ይሆን ዘንድ እንደ ሰይፉ ፋንታሁን አይነት ትውልዱን የሚያደነዝዙ ዝግጅቶችንና መገናኛ ብዙሃንን “የመዝናኛ ፕሮግራም” በሚል ስም ይለፈልፋል።
አነተ ገለልተኛ እያልክ የምታወድሰው ጓደኛህ ሰይፉ ፋንታሁን ይህንን የኢህአዴግን አላማ ግንባር ቀደም አስፈፃሚ ከመሆኑ በተጨማሪ አሁን በስልጣን ላይ ያለውን አምባገነን መንግስት የሚደግፍ ካድሬ መሆኑን አገር ያውቃል። ከዚህ በተጨማሪ ሰይፉ የኢሃዴግ መንግስትን እድሜ ለማርዘም ሌት ተቀን የሚለፉትና የአገርን ሃብት ያለአግባብ የሚዘርፉት የሼኹ ሎሌ ነው። በቅርቡ በሸራተን ሆቴል ሲያገባ የሰርጉን ወጪ ሙሉ በሙሉ በሼኹ የተሸፈነለትም በዚሁ የኢህአዴግ ካድሬነቱና ታማኝነቱ የውለታ ምላሽ ነው። ከሼኹና ከገዢው ፓርቲ ጋር አልተባበርም ያሉና ከተፅዕኖ ውጭ የሆኑ አርቲስቶች ፈተና ሲገጥማቸው አይተናል። ህዝብ የጀግንነት ክብር ከሰጣቸው ታማኝ በየነና ቴዲ አፍሮ ይጠቀሳሉ።
ኢ.ሴ.ኤፍ.ኤን ከኢህአዴግና ከሼኽ አልሙዲ ተፅዕኖ ራሱን አላቆ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመስራቱ ምን ያክል የህዝብ ድጋፍ እንደነበረውና ውጤታማ እንደነበረ አይተናል። እኔ ለአንተ የማቀርበው ጥያቄ የሚነሳው እዚህ ላይ ነው። እዚህ አሜሪካ አላሙዲ ከፈጠሩት የስፖርት ፌዴሬሽን ጋር የተባበሩትን አርቲስቶች እያወገዝክና ሌላ ስራ እንዳይሰሩ እያሳደምክ፣ በአንፃሩ ቀንደኛ የገዥው ፓርቲ ካድሬና የሼኹ ወዳጅ በመሆን ከኢትዮጵያ ህዝብ ከተዘርፈው ገንዘብ ተካፋይ የሆነው ሰይፉ ፋንታሁንን የአንተ ጋዷኛ በመሆኑ ብቻ አላሙዲ በሸራተን ደግሰው ሲድሩት ለምን ለማውገዝ ተሳነህ?..ማውገዝ እንኳ ቢቀር የሼኹ ሎሌ የሆነው ሰይፉን በምን መለኪያ ገለልተኛና በእመነቱ የሚፀና ለማለት ደፈርክ?.. ወይም ገለልተኛነትና በእምነት መፅናት ምን እንደሆኑ አታውቅም! አለበለዚያ ለአንተ ገለልተኛነትና በእምነት መፅናት ማለት ከአንተ ጋር የሚመሰረት ጓደኝነት ነው ማለት ነው። ሌላው ጥያቄ እዚህ አሜሪካ አገር ከአልሙዲ ጋር የተባበሩትን አርቲስቶች ከተቃወምክ አዲስ አበባ ላይ ከዚያው ግለሰብ (ሼኹ) ጋር የሚተባበሩትንና የቅርብ ወዳጅ የሆኑትን ሰዎች ማንቆለጳጰስ እንዴት ትችላለህ?..በተጨማሪ በአላሙዲ የሚረዳውን ፌዴሬሽንና ሸራተን ለየብቻ እንደሆኑ አድርገህ ለመግለፅ ሞክረሃል። እጅግ አስቂኝ ነው።ሁለቱም በሼኹ የሚዘወሩ ናቸው!
ከአምባገነኑ መንግስት ኢህአዴግና መንግስትን ከሚደግፉት እነሼኽ አላሙዲ ጋር መተባበር አይገባም ካልክ አቋምህ ወጥ ሊሆን ይገባል። አዲስ አበባም ሆነ አሜሪካ፣ ሰርግም ሆነ ስፖርት ጓደኝነት ኖረም አልኖረ፣ የግል ጥቅም ተገኘም አልተገኘ፣ አቋምህ ወጥ መሆን ይገባዋል። ስትቃወም፣ ስትደግፍ፣ ወጥ የሆነ አቋም ይኑርህ!
በእነኚህ ጉዳዮች ላይ የምታንፅባርቀው ወጥ ያለሆነ አቋም ሳስብ አንድ ጥንታዊ የቻይና ተረትን አስታወሰኝ። ሰውዬው በመንደሩ ውስጥ ሱቅ ከፍቶ ጦርና ጋሻ አንድ ላይ ይሸጣል። የሚገርመው ግን ጦሩን ሲያሻሽጥ “ሁሉንም ነገር ይበሳል” እያለ ሲሆን ጋሻውንም ሲያሻሽጥ “ምንም ነገር አይበሳውም” እያለ ነበር። አንተም፣ ያንተም ጓደኛም ሰይፉ ፋንታሁን ከአልሙዲ ተሻርኰ እየሰራና ሸራተን ሰርግ ሲደገስለት እያየህ ገለልተኛና በእመነቱ የሚፀና ብለህ ታወድሰዋለህ! አሜሪካ አገር ያሉ አርቲስቶች ከአልሙዲንና አላሙዲ ከፈጠሩት ፌዴሬሽን ዝግጅት ላይ ሲዘፍኑ ደግሞ “ባንዳና ከሃዲ” ብለህ ታወግዛለህ፤ እንዴት ነው ነገሩ?..የባንዳነትና የኢትዮጵያዊነት መለኪያው የአንተ ፍቃድና ጓደኝነት ሆነ እንዴ?..ለነገሩ የአንተን የአቋም መዘባረቅ በተመለከተ ግራ የሚያጋቡኝን አንድ ሁለት ነገሮች ልጠቃቅስልህና ወደ ዋናው ሃሳቤ ልመለስ። ድምፃዊ ቴዴ አፍሮ ከአልሙዲ ጋር ላለመስራት ወስኖ የኢትዮጵያ ህዝብ ጀግና እያለ ሲወድሰው ኢህአዴግ ደግሞ እንደጠላት ሲያዋክበው በነበረት ጊዜ አንተም ከሰይፉ ጋር ሆነህ ቴዲ አፍሮን በማዋከቡና የድምፃዊውን መልካም ስም በማጠልሸት ዘመቻ ላይ ከሰይፉ ጋር ተሳታፊ ነበርክ። ሁለተኛ የሰይፉን በመዝናኛ ስም ህዝብ የማደንዘዝ ተግባር ላይ አካልና አጋር ነበርክ። አንተ የእኔን የትላንት፣ የዛሬና የነገ አቋም ለመጠየቅ አንዳችም ማስረጃ ባይኖርህም እኔ ግን እነዚህንና ሌሎች ለጊዜው የማልገልፃቸውን ስህተቶችህን እያወቅኩ ኢትዮጵያዊነትህን አልተጠራጠርኩም።