‹‹ጠ/ሚ/ር መለስን በማጣቱ ሰው ተደናግጦ ነበር፤ … እኔንም ገለውኝ ነበር፤ ግን አልሞትኩም እስከአሁን ከእናንተው ጋር ነኝ›› ሲሉ መናገራቸውን ሼክ ሙሐመድ ሁሴን አል-አሙዲ መናገራቸውን ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው ኢትዮቻናል ጋዜጣ ዘገበ። ዘገባው ለግንዛቤ ይጠቅማል በሚል ሳንጨምር ሳንቀንስ አቅርበነዋል – ያንብቡት። በአሁኑ ወቅት በሥሩ 20 ግዙፍ ኩባኒያዎችን የሚያስተዳድረው የሜድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ባለፈው እሁድ 10ኛውን የደምበኞች፣ የሠራተኞችና የቤተሰቦች ቀን በዓል አከበረ፡፡ የቴክኖሎጂ ግሩፑ ቺፍ ኤግዚክዩቲቭ ኦፊሰር ዶ/ር አረጋ ይርዳው በበዓሉ ላይ እንደገለፁት ‹‹የሜድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ውስጥ መሪዎችም ሆንን ተመሪዎች ሁላችንም እኔንም ጨምሮ ሠራተኞች ነን፤ አሠሪ ቢኖር አንድ ሰው ብቻ ነው›› ነበር ያሉት፡ ፡ ዶ/ር አረጋ ‹‹ አንድ አሠሪ ብቻ ነው ያለን›› ያሏቸው ክቡር ዶ/ር ሼክ አል- አሙዲ በበዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግርም ‹‹ለአንድ ሀገር መመስረቻው ቤተሰብ ነው፡ ፡ ከዚያ ቀጥሎ ቤተሰብ ወልዶ ተዋልዶ ሠራተኛ ይፈጥራል፤ ሠራተኛውም ለሚያመርተውም ደምበኛ ያመጣል፡፡ ከምወዳቸው ነገሮችና መገኘት የምፈልገው ይህንን ቀን ነው›› ብለዋል፡፡