Translate

Tuesday, April 2, 2013

አዲስ አበባ በነዋሪነት የማታውቃቸው ድምጽ ሊሰጧት ነው


ከእሁድ እስከ እሁድ

(የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች)
map of eritrea


በኤርትራ “ውስጣዊ ትርምስ” ያሰጋል ተባለ
በኤርትራ እየጎላ የሄደው ያለመረጋጋት፣ እየተገለለች የሄደችውን አነስተኛ ሀገር በውስጣዊ ትርምስ ውስጥ ሊከት ይችላል እንደሚችል የዓለም አቀፍ የቀውስ ቡድን International Crisis Group የተባለው ድርጅት ባወጣው ዘገባ ገለጸ። ለሰላማዊ የስልጣን ሽግግር የሚያመች ስርአት ባለመኖሩም ወታደራዊው ሀይል የመሪነት ሚና ሊጫወት እንደሚችል ስጋቱን አስታውቋል። ጎልጉል በኤርትራ መፈንቅለ መንግስት ይገመታል ሲል መዘገቡ ይታወሳል።

ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ በቃሊቲዎች ክስ ቀረበባት!


ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ በቃሊቲዎች ክስ ቀረበባት!

አቤ ቶኪቻው
መምህርት እና ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ በቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙትን የአስተዳደር እና የጥበቃ ሰራተኞች ትንቂያለሽ፣ትሰደቢያለሽ እንዲሁም “የምትሰሩትን በሚዲያ እና ድረ ገፆችReeyot Alemu, the 31 year-2012 Courage in Journalism Award winner. አጋልጣለሁ” ብለሽ ትዝቺያለሽ በሚል ክስ ቀርቦባት መጋቢት 25 /2005 ዓ.ም ቃሏን መስጠቷ ተሰማ፡፡
ጋዜጠኛይቱ ክሱን አስመልክቶ ቃሏን እንድተሰጥ የተጠየቀቸችው መጋቢት 19 /2005 ዓ.ም ምሽት ከመኝታዋ ተቀስቅሳ የነበረ ቢሆንም ከጠበቃዬ ጋር ሳልነጋገር ምንም የምሰጠው ቃል የለኝም በማለቷ እስከ መጋቢት 25 ሊዘገይላት ችሏል፡፡
ርዮት የተከሰሰችው በፌደራል ታራሚዎች አያያዝ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 139/1999 አንቀፅ 36 መ እና ሠ ላይ በተቀመጠው መሰረት ሲሆን ይህ አንቀፅ “ከባድ የዲሲፒሊን ቅጣት የሚያስከትሉ ድርጊቶች” ተብሎ የተዘረዘረ ነው፡፡

ለዜጎች መሞት፣ መፈናቀልና መሰደድ ተጠያቂው መንግስት ነው!!!


አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)
ወንጀለኞች በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን
በተደጋጋሚ ፓርቲያችን እንደሚገልፀው አምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት የሚከተለው ቋንቋን መሰረት ያደረገ ፌደራሊዝምና የስርዓቱ አራማጆች ካላቸው የስልጣን እድሜን የማራዘም ጉጉት ተደማምረው ለሃገራችን እንዲሁም ተቻችሎ፣ ተዋልዶ፣ ተዛምዶና ተዋድዶ ለዘመናት ይኖር ለነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ግልፅና አስፈሪ አደጋ ወደ መሆን እንደደረሱ በግላጭ እየታየ ነው፡፡ለዜጎች መሞት፣ መፈናቀልና መሰደድ ተጠያቂው መንግስት ነው!!!
ያ ለዘመናት አብሮን የቆየው በጋራ የመኖር ዕሴት እየተደመሰሰ በምትኩ የሚያጋጩ ስልቶች እየተፈጠሩና እየተተገበሩ ወደ ሰቆቃ ተለውጠው ይገኛሉ፡፡ የዜጎች ሰዋዊና ህጋዊ መብት እየተጣሰም ነው፡፡ በኢትዮጵያችን ውስጥ አብሮ የመኖር፣ ከቦታ ቦታ የመዘዋወርና በፈለጉት ቦታ ሃብት የማፍራት ህልውና እያከተመ መጥቷል፡፡ ለዚህ ክፉ ድርጊት ተጠያቂ የሚሆነው ደግሞ የዜጎችን መዘዋወር መብትና ሃብት የማፍራት መብት ማረጋገጥ የተሳነው መንግስትና መንግስት ብቻ ነው፡፡

Monday, April 1, 2013

አዜብ እርግጫሽ አልበዛም?


ይነጋል በላቸው

ABC es: Popular Spanish news paper that exposed Money spree of Hazeb Mesfen among other leader's wifes in Paris one of fashion cities 2 years ago  ''Azeb Mesfin Ethiopian, who used to squander in haute couture heritage of her husband: 1,200 million euros.''

http://www.abc.es/20110120/internacional/abci-primeras-damas-derrochan-201101201613.htmlከሰሞነኛ አስቂኝ ዜናዎችና ሀተታዎች አንዱ የወይዘሮ አዜብ ድህነት ነው፡፡ ‹ባለቤቴ መለስ የባንክ ደብተር ያልነበረው፣ ቤተሰቡን በአራት ሺህ ብር ገቢ ብቻ በችጋር የሚቆላ፣ መላ ሕይወቱን ለእናት ድርጅቱ ለሕወሓትና ለኢትዮጵያ ሲል መስዋዕት ያደረገ …› እያለች  ታወራለች አሉ፤ ‹ወጣ ብሎ በትርፍ ሰዓት እያስተማረ እንዳይደግፈን የፀጥታው ሁኔታ አላመቸውም› ብላ አለመጨመሯም እርሷው ሆና ነው – ‹የመለስ አንጎል በበማርኬት ጨረታ በሚሊዮን የሚገመት ሸያጭ ያወጣል› ስትል ቅንጣት ያላፈረች ወራዳ ሴት እኮ ናት፡፡ እኔም ሰው አገኘሁ ብዬ ስለርሷ ጊዜየን ማጥፋቴ እየከነከነኝ ነውአ- አሁን፤ ልፋ ያለው እንዲሉ ነው፡፡ ቀደም ሲልም ‹መለስ ጥሎብኝ የሄደውን የጋራ ልጆቻችንን በማሳደግ እፈተናለሁ› ብላ ነበር አሉ፡፡ የማትለው ነገር የለም ይባላል ይቺ የጉድ ተራራ – ሦስተኛይቱ ዮዲት ጉዲት፡፡

መንግስት አቀባባይ የሆነበት የእህቶቻችን ስቃይ


"እኛን ማገዝ ግድ ነው" ዶ/ር ማይገነት

ethiopian girl in arabia
“በግል ጥሪ የላከልኝ የለም። ያገባኛል የምትሉ እንድትገኙ የሚል መልዕክት ሰማሁና መጣሁ። የማውቀውንና ያየሁትን እውነት ተናገርኩ። ስቃዩ ከሚነገረው በላይ ነው። የሚነገረውና በተግባር የሚደርሰው በእጅጉ የተለያየ ነው …” በማለት ምስክርነቷን ችግሩን ለመፍታት መንቀሳቀስ ለጀመሩት ወገኖች ማካፈሏን የምትናገረው ወ/ት ዘቢባ ዘለቀ ናት። በንግግሯ ሁሉ መፍትሔ አንዲፈለግ አበክራ ትጠይቃለች።

የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዲግ) ማኒፌስቶ


የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዲግ) ማኒፌስቶ

እኛ የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር መስራቾች ለሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝቦች ፍትህ፣ ነጻነት፣ እኩልነትና የዲሞክራሲ መብት መከበር መታገልን መሰረታዊ ዓላማው ያደረገ አዲስ የኦሮሞ የፖለቲካ ንቅናቄ መመስረት በይፋ እናበስራለን። ይህ እርምጃችን በኦሮሞ የነጻነት ትግል ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ከመሆኑም በላይ የኢትዮጵያን መንግስት የጭቆና ባህሪ ከመሰረቱ በመለወጥ በትክክለኛ ዲሞክራሲያዊ የፌዴራል ስርዓት ለመተካት የሚያስችል ይሆናል ብለን እናምናለን። ይቀጥላል…

በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ አካል ነዉ!


በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ አካል ነዉ!


መግለጫ
በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ  ያለው ግፍ አካል ነዉ!
የወያኔ መሪዎች እነ መለስ ዜናዊና ስብሐት ነጋ በ1967 ዓም ለትግል ደደቢት በረሀ እንዲገቡ ያነሳሳቸዉና ያሰባሰባቸዉ በአማራዉ ህዝብ ላይ ያላቸው  ጥላቻና የበቀል ስሜት  እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ በደልና እሮሮ አንገፍግፏቸዉ እንዳልሆነ በተለያዩ ግዜዎች ለህዝብ ይፋ የሆኑት የወያኔ  መግለጫዎችና ለረጂም ግዜ ወያኔን የመሩት መለስ ዜናዊና ስብሐት ነጋ በየአደባባዩ ላይ ያደረጓቸዉ ንግግሮች በግልጽ ያሳያሉ።