Translate

Sunday, October 13, 2013

ስብሃት ነጋ ወንጀል ፈፀሙ፤ በአሁን ሰአት በፖሊስ እየታደኑ ነው

ስብሃት ነጋ ወንጀል ፈፀሙ፤ በአሁን ሰአት በፖሊስ እየታደኑ ነው

ከኢየሩሳሌም አርአያ
በአሌክሳንደሪያ ቨርጂኒያ ከአንድ ሰአት በፊት ስብሃት ነጋና አብሯቸው የነበረ ግለሰብ በአንድ ኢትዮጲያዊ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ፈፅመው ማምለጣቸውን ማረጋገጥ ተችሏል። መስፍንsebehat nega one of the founders of TPLF የተባለው ኢትዮጲያዊ በአሁኑ ሰአት በሆስፒታል የሚገኝ ሲሆን የሲቪሊቲ ሩም ፓልቶክ አዘጋጅ አባ መላ በስልክ አግኝቶት ስለሁኔታው ያነጋገረው ሲሆን፤ መስፍን እንደገለፀው በድብደባው ጅርባው እንደተጎዳና ብዙ ደም እንደፈሰሰው ገፆዋል። እነስብሃት ድብደባውን ሲፈፅሙ በቅርብ ርቀት ቪዲዮ እየተቀረፁ እንደነበረና ይህኑን ማስረጃ ለፖሊስ መስጠታቸው ታውቋል። ድርጊቱ ከተፈፀመ በኋላ ፖሊስ በአካባቢው ፈጥኖ የደረሰ ሲሆን፣ በአሁን ሰአት እነስብሃትን ለመያዝ ፖሊስ መሰማራቱ ታውቋል።

Friday, October 11, 2013

እስክንድር ነጋ በአራት ጎብኚዎች ብቻ እንዲጎበኝ ተደረገ

1394241_527514827333456_269824761_n
ታዋቂው የፖለቲካ ተንታኝና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በሚገኝበት የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር በተላለፈ ትዕዛዝ መሰረት የጎብኚዎቹ ቅጥር መወሰኑን የማረሚያ ቤቱ ምንጮች ለፍኖተ ነጻነት ገለጹ፡፡ የመስከረም 19/2006 ሰላማዊ ሰልፍ ብስጭት ከፈጠረባቸው አካላት መካከል አንዱ የሆነው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ብስጭቱን አደባባይ ያወጡበትን እርምጃዎች መውሰድ መጀመሩ እያነጋገረ ነው፡፡ለአንዷለም አራጌ የጎብኚዎቹን ስም እንዲሰጥ ካልሆነ ግን በማንም እንደማይጎበኝ የነገረው አስተዳደሩ የእስክንድርን ጠያቂዎች ቁጥር በአራት መወሰኑ ታውቋል፡፡

አያ ጅቦ ሳታመካኝ ብላኝ !!!

ኃይለማሪያም ደሳለኝ በአንድ ወቅት ዉሸትን የማያዉቅ ጠንካራ ክርሰቲያን ነዉ ተብሎ ሲነገርለት ሰምተን ነበር፤ ታድያ ይህ ሰዉ መለስን ሲተካ ብዙዎች በጥርስ የለሽ አንበሳነቱ ቢስማሙም ዉሸት እንደ ንጉስ በነገሰባት ኢትዮጵያ ዉስጥ ዉሸት የማያዉቅ መሪ መጣ መባሉ ብዙዎቻችንን ነጻነት የተገኘ ያክል አስደስቶን ነበር። ሆኖም ከወያኔ ጋር የዋለ ሰዉ እራሱን ሆኖ መክረም አይችልምና ኃይለማሪያምም ባስቀመጡት ቦታ የማይገኝ የሌላ መንደር ሰዉ ሆኖ ተገኘ። በዚህም የዜጎችን ተሰፋ አመከነ፤ ደስታቸውንም ወደ ኃዘንና ትካዜ ለወጠው።
ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ላይ በመገናኛ ብዙኋን ፊት ያየዉን አላየሁም፤ የሰማዉን አልሰማሁም፤ ያልሆነዉን ሆነ የሆነዉን ደግሞ አልሆነም እያለ ሽምጥጥ አደርጎ የካደዉ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፤ በእርግጥም ጎበዝ የመለስ ዜናዊ ተማሪ መሆኑን በተግባር አስመስክሯል። ኃይለማሪያም ባለፈዉ ዓርብ አንድ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶ ነበር። ይህ ግለሰብ በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫዉ ኢትዮጵያን ያክል ትልቅ አገር ከሚመራ ሰዉ ቀርቶ ከአንድ ተራ የቢሮ ተላላኪ እንኳን የማይጠበቅ መልስ ሲመልስ ተስተዉሏል።

ግንቦት 7 ለአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ንግግር ምላሽ ሰጠ – “ኃ/ማሪያምንና ጌቶቹን እንዲህ ያቃዣቸዋል?”

ግንቦት 7 የፍትህና የዴሞክራሲ ንቅናቄ በወቅታዊ ርዕሰ አንቀጹ ከቀናት በፊት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ለጋዜጠኞች ለሰጡት ቃለ ምልልስና በተቃዋሚዎች ላይ ላቀረቡት ክስ ምላሽ ሰጠ። የግንቦት 7 ምላሽ ሙሉ ቃል እንደወረደ የሚከተለው ነው፦
ኃይለማሪያም ደሳለኝ በአንድ ወቅት ዉሸትን የማያዉቅ ጠንካራ ክርሰቲያን ነዉ ተብሎ ሲነገርለት ሰምተን ነበር፤ ታድያ ይህ ሰዉ መለስን ሲተካ ብዙዎች በጥርስ የለሽ አንበሳነቱ ቢስማሙም ዉሸት እንደ ንጉስ በነገሰባት ኢትዮጵያ ዉስጥ ዉሸት የማያዉቅ መሪ መጣ መባሉ ብዙዎቻችንን ነጻነት የተገኘ ያክል አስደስቶን ነበር። ሆኖም ከወያኔ ጋር የዋለ ሰዉ እራሱን ሆኖ መክረም አይችልምና ኃይለማሪያምም ባስቀመጡት ቦታ የማይገኝ የሌላ መንደር ሰዉ ሆኖ ተገኘ። በዚህም የዜጎችን ተሰፋ አመከነ፤ ደስታቸውንም ወደ ኃዘንና ትካዜ ለወጠው።

“የይሉኝታ ፖለቲካ ይገድላል”

“የይሉኝታ ፖለቲካ ይገድላል”

mitmitta1

“ሙሉ ኢትዮጵያዊ ነኝ” ትላለች። የተወለደችው ዱከም ነው። በቀድሞው አጠራር በኢትዮጵያ የተለያዩ ጠቅላይ ግዛቶች ኖራለች። ሐረር፣ ባህርዳር፣ አስመራ፣ አዲስ አበባን በመጥቀስ ልዩ ትዝታዎች እንዳሏት ትናገራለች። ከዛሬ ሃያ ዓመት በፊት አሜሪካ ከትማለች።

Thursday, October 10, 2013

ትንሽ ስለ ተስፋዬ ገብረአብ

Abraha Desta the facebook
አብረሃ ደስታ
‘የተስፋዬ ገብረአብ ማንነት አጋለጠ’ የተባለውን ፅሑፍ አነበብኩት። ገረመኝም። ረዥም ነው። የአንድ ሰው ማንነት ለማጋለጥ አርባ ምናምን ገፅ? ተስፋዬ ገብረአብን ‘ያጋለጠ’ ፅሑፍ ለኔ ምንም ዓይነት ተጨማሪ መረጃ አልሰጠኝም።
ስለ ተስፋዬ ገብረአብ ትንሽ ለመፃፍ የተገደድኩት ምክንያት አንዳንድ የህወሓት ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች ‘የተስፋዬን መጋለጥ’ ምክንያት በማድረግ እኔ አንድ ነገር እንድልላቸው ስለወተወቱኝ ነው። አንዳንዴ’ኮ ጎበዞች ናቸው። ተፎካካሪያቸውን ማኖ ማስነካት ይችላሉ። እኔ ደግሞ ማኖ መንካት እወዳለሁ፤ (ማኖ ካልነካንላቸው ከስድብ ዉጭ ሌላ የሚያውቁት ነገር የላቸው)።

የተሞሉትን የሚተነፍሱ ጠቅላይ ሚኒሰትር

JONAS TAMERU  ( OSLO NORWAY )

Ethiopian PM Hailemariam Desalegn on Al Jazeeraለሁለት  አስርተ አመታት በኢትዮጲያና  በህዝቦቿ ላይ ነግሶ በማን አለብኝነት አድራጊ ፈጣሪ ሆኖ በሁሉም ያገሪቱ አቅጣጫዎች ሰላማዊውን ህዝብ ለሞትና ለስደት እንዲሁም ለእስር ሲዳርግ የነበረው አምባገነኑ የህውሃት ዘረኛ ቡድን የመለስ ዜናዊ  ሞት ተከትሎ በይስሙላ ምርጫ ያስቀመጠው አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የዚሁ ዘረኛ ቡድን ደቀ መዝሙር ሆኖ በነሱ በመቃኘት ተፈጥሮአዊ ባህሬያቸውን ወርሶ አሁንም በሃገራችን  ስርዓቱ ካለው እኩይ ተፈጥሯዊ  ባህሪ አንፃር የናፈቅነውንና የተመኘነውን ነፃነትም ሆነ ለውጥ ሳይመጣ እነሆ ሌሎች ንፁሃን ሲገደሉና ሲሰደዱ እንዲሁም ሲታሰሩ አየን ሰማን፡፡