Translate

Friday, October 4, 2013

ከሙስና ተጠርጣሪው የአዳማ ጉምሩክ የህግ ማስከበር ሃላፊ ጋር በተያያዘ 7 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ተያዘ

ከሙስና ተጠርጣሪው የአዳማ ጉምሩክ የህግ ማስከበር ሃላፊ ጋር በተያያዘ 7 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ተያዘ

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት የአዳማ ጉምሩክ የህግ ማስከበር ሃላፊ ከነበሩት ተመስገን ስዩም ጋር በተያያዘ 7 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ጥሬ ገንዘብ ሲያዝ 7 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ዶዘር ደግሞ ማሳገዱን የፌዴራል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ገለፀ፡፡
የፌዴራል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በአቶ ተመስገን ስዩም ላይ ያካሄደው ተጨማሪ ምርመራ እንደሚያመለክተው ግለሰቡ በሃላፊነት ላይ በነበሩበት ወቅት 12 የነዳጅ ማመላለሻ ቦቴዎችን በሌላ ሰው ስም ገዝተው ለተገዙት መኪኖች ውክልና በመውሰድ መኪኖቹን ለሌሎች ሰዎች ሸጠዋል፡፡
ከሽያጩ በተገኘው ገንዘብ ደግሞ ሁለት ዶዘሮችን ለመግዛት ከ15 ሚሊዩን ብር በላይ ለአንድ ድርጅት ክፍያ ፈፅመዋል፡፡

Thursday, October 3, 2013

በጣሊያን ጀልባ ሰጥሞ ከ90 የሚበልጡ አፍሪካውያን ስደተኞች ህይወት አለፈ

በመቶዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ስደተኞችን ይዛ ወደ ላምቤዱሳ ደሴት በማቅናት ላይ የነበረች አንዲት ጀልባ  እሳት  ተቀስቅሶባት  በመስጠሟ 92 ሰዎች ሞቱ ።
በጀልባዋ ላይ የተቀሰቀሰውን እሳት ለማምለጥ ስደተኞቹ ወደ ባህር መዝለላቸውና  ጀልባዋም መስጠሟ  ተነግሯል ። 150 የሚጠጉ ሰዎችን ህይወት ማትረፍ  እንደተቻለ ፖሊስ አስታውቋል ።
200  የሚሆኑ  ስደቶች  ግን እስካሁን  የደረሱበት  ያልታወቀ ሲሆን ፥  የሟቾች ቁጥርም አሁን ከተጠቀሰው  በላይ  ሊሆን  እንደሚችል ተገምቷል ።
ከስደተኞቹ መካከል  የሚበዙት  ኤርትራውያንና  ሶማሊያውያን ሲሆኑ ፥ አንድ ህፃንና  አንድ ነፍሰ ጡር ሴትም  ይገኝተውበታል ።
በአሁኑ ወቅት  የሜዲትራኒያን ባህር የተረጋጋ ሁኔታ ያለው በመሆኑ  በየእለቱ አፍሪካውያን ስደተኞችን የያዙ ጀልባዎች በደቡባዊ የጣሊያን  የባህር ዳርቻ  እንደሚደርሱ  ነው የሚነገረው ።
ሆኖም ስደተኞቹን የሚጭኑት ጀልባዎች ጤንነት አሳሳቢ በመሆኑ  አሳዛኝ ክስተት በአከባቢው  እየተደጋገመ መጥቷል ።
የመንግስታቱ  ድርጅት  የስደተኞች ጉዳይ ደርጅት እንደሚለው  በዚያ  አከባቢ  ችግር ባለባቸው ጀልባዎች በመሰፈራቸው በየዓመቱ በተንሹ 1  ሺህ 500 የሚሆኑ  ስደተኞች ባህር ላይ  የቀራሉ ።

ምንጭ ፦  ቢቢሲ

ሰበር ዜና በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒተ ሊቀመንበር በሳውዲ ደህነቶች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ ዲፕሎማቱ ተደናገጡ !

ሰበር ዜና
በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒተ ሊቀመንበር በሳውዲ ደህነቶች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ ዲፕሎማቱ ተደናገጡ !

በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቀመንበር እና የአንባሳደር መሃመድ ሃሰን  የቅርብ ዘመድ እንደሆኑ የሚነገርላቸው አቶ ሙስጠፋ ሁሴን ሰሞኑንን በሳውዲ ጸጽታ አህይሎች በቁጥጥር ስራ መዋላቸውን ውስጥ አውቂ ምንጮች ገልጸዋል።
አቶ ሙስጠፋ ሁሴን ምንጩ ከየት እንዳልሆነ ያልታወቀ 2 ሚልዮን ሪያል « በኢትዮጵያ ምንዛሪ ከ10 ሚልዮን ብር በላይ በእጃቸው መገኘቱን ተከትሎ በሳውዲ የደህንነት ሃይሎች ለጥያቂ ይፈለጋሉ ተበለው እንደ ተያዙ  የሚናገሩት እነዚ ምንጮች ጉዳዩ በቀጥታ ከኢትዮጵያው አንባሳደር ክቡር መሃመድ ሃሰን ጋር ግንኙነት እንዳለው ይገልጻሉ  ። አቶ ሙስጠፋ ሁሴን ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ለረጅም አመታት ሲኖሩ ቀዋሚ የሆነ የገቢ ምንጭ እንዳልነበራቸው የሚጠቅሱት ታዛቢዎች  ከቅርብ ግዜ ውዲህ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሪያሎችን ማገላበጥ መጀመራቸው ጉዳዩ የሳውዲን የደህንነት ህይሎች ባቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ መንግስትንም የሚያሳስብ ጉዳይ ነው ብለዋል ።

አንባሳደር መሃመድ ሃሰን መንግስት ከጣለባቸው ሃላፊነት ውጭ፡  በማንኛውም ንግድ  ስራ ላይ እንደማይሰማሩ የሚመስክሩላቸው ወገኖች  በአቶ ሙስጠፋ ሁሴን አማካኝነት ከፍተኛ ሪያሎችን ህገወጥ፡በሆነ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ አሾልኮ በማስገባት  ከተጠቀሱት ግለስብ  ጋር ቀጥተኛ የሆነ የጥቅም ግንኙነት ሊኖራቸው እንደሚችል ጥርጣሬያቸውን ይገልጻሉ።  በተለይ ከቅርብ ግዜ ወዲህ የስራተኛ እና አሰሪ ኤጀንሲ ባለቤት በመሆን ሃላፊነት በጎደለው መልኩ አያሌ ኢትዮጵያውያን እህቶቻችንን  ወደ ሳውዲ አረቢያ በማስመጣት ንግድ ስራ ላይ ተሰማረተው እንደነብሩ የሚነገር ላቸው  አቶ ሙስጠፋ ሁሴን በሳቸው ኤንጄንሲ አማካኝነት የመጡ እህቶቻችን  በአሰሪዎቻቸው በተፈጸምባቸው አሰቃቂ  ግፍ እና በደል ለሞቱ 3 እህቶቻችን  ግባር ቀደም ተጠያቂ መሆናቸው ይነገራል።

አቶ ሙስጠፋ ሁሴን በኮሚኒቲ የሊቀመንበር ነት ዘመናቸው ከኮሚኒተው  ስራ አመራር ሳያማክሩ «ጌታውን የተማመነች በግ እንዲሉ » የአንባሳደር የቅርብ ዘምድ  በመሆናቸው ብቻ ከኮሚኔው መተዳዳሪያ  ደንብ ውጭ በግላቸው ውሳኔ የኮሚኒትውን ካፍቴሪያ  ካዝና  ጨምሮ ቀዋሚ እና ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን እንዳሻቸው ሲዘውሩ እንደ ነበር  ይታወቃል ። በሙስሊም  የሃይማኖት አባትነታቸው  ሽፋን  የህዝብን አመኔታ እና ፍቅርን  ለማግኘት  ያደረጉት ሙከራ  የተሳካላቸው አቶ ሙስጠፋ ሁሴን በሪያድ አስዳጊ በሌላቸው ህጻናት ስም አንባሳደር መሃመድ ሃሰን በሰጦቸው የድጋፍ ደብዳቤ  ከተለያዩ  የሳውዲ  በጎ አድራጊ ገለስቦች እና ተቋማት ከፍተኛ ሪያል በመሰብሰብ  ለግል ጥቅማቸው  አውለዋል በመባል ይታማሉ ።

ይህ በዚህ እንዳለ አቶ ሙስጠፋ ሁሴን ካዝና ውስጥ፡የተገኘው 2 ሚልዮን ሪያል  ከኮሚኒቲው ማህበር ካፍቴሪያ እና ከኢትዮጵያ አለም አቀፍ ት/ቤት የተዘረፈ ሊሆን እንደሚችል  አንዳንድ የኮሚኒተው አባላት ግምታቸውን ይገልጻሉ። አቶ ሙስጠፋን ሁሴን ከእስርቤት ለማስለቀ ኤንባሲው ያደረገው ሙከራ እሳክሁን እንዳልተሳካ የሚናገሩት  የኤንባሲው ምንጮቻችን ጉዳዩ አንባሳደሩን ጨምሮ በኮሚኒትው ዘረፋ የሚታሙትን ዲፕሎማቶች ቤት ሊያንኳኳ እንደሚችል ይናገራሉ ።
@[100005161082407:2048:Ethiopian Hagere] ሳውዲ አረቢያ ጅዳ በዋዲበሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቀመንበር እና የአንባሳደር መሃመድ ሃሰን የቅርብ ዘመድ እንደሆኑ የሚነገርላቸው አቶ ሙስጠፋ ሁሴን ሰሞኑንን በሳውዲ ጸጽታ አህይሎች በቁጥጥር ስራ መዋላቸውን ውስጥ አውቂ ምንጮች ገልጸዋል።
አቶ ሙስጠፋ ሁሴን ምንጩ ከየት እንዳልሆነ ያልታወቀ 2 ሚልዮን ሪያል « በኢትዮጵያ ምንዛሪ ከ10 ሚልዮን ብር በላይ በእጃቸው መገኘቱን ተከትሎ በሳውዲ የደህንነት ሃይሎች ለጥያቂ ይፈለጋሉ ተበለው እንደ ተያዙ የሚናገሩት እነዚ ምንጮች ጉዳዩ በቀጥታ ከኢትዮጵያው አንባሳደር ክቡር መሃመድ ሃሰን ጋር ግንኙነት እንዳለው ይገልጻሉ ። አቶ ሙስጠፋ ሁሴን ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ለረጅም አመታት ሲኖሩ ቀዋሚ የሆነ የገቢ ምንጭ እንዳልነበራቸው የሚጠቅሱት ታዛቢዎች ከቅርብ ግዜ ውዲህ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሪያሎችን ማገላበጥ መጀመራቸው ጉዳዩ የሳውዲን የደህንነት ህይሎች ባቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ መንግስትንም የሚያሳስብ ጉዳይ ነው ብለዋል ።

ድሆችን ያፈናቀለው “ኢንቨስትመንት” ዕዳ ዋጠው

"እኛን የሚያሳስበን በሊዝ ያልሸጥነው መሬት ነው" መለስ

DSCN0291
“መሬታችንን ለምን እንነጠቃለን?” በማለት የጠየቁ ተገድለዋል። ተገርፈዋል። ታስረዋል። አሁን ድረስ እስር ላይ የሚገኙ አሉ። ባዕድ እንኳን ባልሞከረው የከፋ ጭካኔ በከባድ መሳሪያ በተደገፈ የጦር ሃይል የተወለዱበትን መሬት እንዲለቁ የተገደዱ አዛውንቶች ላይ የተፈጸመው ግፍ እስከ ወዲያኛው የሚያሽር አይደለም። በሌሊት እርቃናቸውን ከሚያርፉበት ታዛ ስር ነፍጠኛ ሰራዊት እንዲከባቸው እየተደረገ የተፈጸመው አስነዋሪ ግፍ ጊዜ የሚጠብቅ እንደሆነ በየጊዜው የሚገለጽ ነው።

ተስፋዬ ገብረአብ እጅ ሰጠ

ተስፋዬ ገብረአብ እጅ ሰጠ
ተስፋዬ ገብረአብ እጅ ሰጠ
ተስፋዬ ገብረ አብን ላጋለጠው ጀግናና ለዳኛ ወልደ ሚካኤል ያለን አድናቆታችን እጅግ ታላቅ ነው። ጎልጉል !!
ተስፋዬ ገብረአብ ከኤርትራዊያን ቤተሰቦች ቢሾፍቱ ተወልዶ ያደገ በውብ የስነጽሁፍ ችሎታው ብዙዎች የሚያደንቁት ጋዜጠኛና ደራሲ እንዲሁም የ‹‹ብዙ ማንነቶች›› ባለቤት ነው፡፡ አዎ! ከሁለት ወር በላይ ባልዘለቀ የብሄራዊ ውትድርና ግዳጅ መማረኩ በፈጠረለት ምቹ አጋጣሚ ከከፍተኛ የኢህአዴግ ሹማምንቶች ጋር ለመተዋወቅ ብሎም በ20ዎቹ የዕድሜ ክልል መጀመሪያ ላይ ሆኖ ለከፍተኛ የመንግስት ኃላፊነት የታጨ፤ በለጋ እድሜው ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ የሆነለት የኢህአዴግ ሹመኛም ነበር፡፡ ያ ግን ትናንትና ነው፡፡ ዛሬ ደግሞ በማራኪ የስነጽሁፍ ችሎታው በልዩነታችን ውስጥ ስላለው ውበት ሳይሆን በልዩነታችን ልክ እንዴት መጥፋት እንዳለብን የሚሰብክ መሰሪ ባህታዊ ነው የሚሉ ቁጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡ በዚህ ባህሪው ብዙዎች ግራ ተጋብተዋል፡፡ በተለይ የኤርትራ ገዢዎችን ስውር ዓላማ የሆነውን በኢትዮጵያ ላይ የዘር ጥላቻ የመንዛት ሰይጣናዊ ተልእኮ በየአጋጣሚው በስነ ጽሁፎቹ ላይ የማንጸባረቅ አመሉን የተረዱ ‹‹ተስፋዬ ገብረእባብ›› የሚል ስያሜ እስከመስጠት ደርሰዋል፡፡ እሱም ለኢትዮጵያ ያለውን ‹‹ተቆርቋሪነት›› ያለመታከት ይደሰኩራል፡፡
ዛሬ ግን ይህ ሰው እጅ ሰጥቷል፡፡ ለበርካታ ዘመናት የዘለቀው የተስፋዬ ብልጣብልጥነት በአንድ ቆራጥ ኢትዮጵያዊ ተጋልጧል፡፡ ለሁለት አመት ያህል ተስፋዬን በቤቱ አስጠግቶ ይህንን አስደናቂ የቤት ስራ የሰራው ወጣት አክቲቪስት አለማየሁ መሰለ ይባላል፡፡

ኢ-ፍትሀዊነትን በመቃወም፤ በኢትዮጵያዊነት ላይ የሚቃጣን አደጋ በመፋለም የሚታወቀውና፤ በእስር ብዛት አገሩን ለቆ እስኪሰደድ ድረስ ከሸዋ ሮቢት እስከ ቃሊቲ ድረስ ለአመታት በኢትዮጵያን እስር ቤቶች ያሳለፈው ይህ ደፋር ወጣት ከዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ ጋር በመሆን የመጀመሪያውን ክፍል መረጃውን ይፋ አድርጓል፡፡ አለማየሁ ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለጸው ከሆነ ተስፋዬ ከኤርትራው የደህንነት መስርያቤት ጋር በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች አማካኝነት የተለዋወጣቸው ምስጢራዊ ሰነዶችና ኦዲዮቪዧል መረጃዎች በአለማየሁ አስደማሚ ጥበብ ኮፒ ተደርገው ተዘጋጅተዋል፡፡ በተለያዩ ክፍሎችም ለህዝብ ይቀርባሉ፡፡ በአለማየሁ መረጃ አቅራቢነት በዳኛ ወልደሚካኤል ተከሽኖ የቀረበው የመጀመሪያው የጽሁፉ ክፍል ከተለያዩ መረጃዎች ጋር ሊንኩን ይክፈቱ
http://www.awrambatimes.com/wp-content/uploads/Tesfaye-Gebreab.pdf
ከአውራምባ ታይምስ ዝግጅት ክፍል የተወሰደ
ተስፋዬ ገብረ አብን ላጋለጠው ጀግናና ለዳኛ ወልደ ሚካኤል ያለን አድናቆታችን እጅግ ታላቅ ነው። ጎልጉል !!
ተስፋዬ ገብረአብ ከኤርትራዊያን ቤተሰቦች ቢሾፍቱ ተወልዶ ያደገ በውብ የስነጽሁፍ ችሎታው ብዙዎች የሚያደንቁት ጋዜጠኛና ደራሲ እንዲሁም የ‹‹ብዙ ማንነቶች›› ባለቤት ነው፡፡ አዎ! ከሁለት ወር በላይ ባልዘለቀ የብሄራዊ ውትድርና ግዳጅ መማረኩ በፈጠረለት ምቹ አጋጣሚ ከከፍተኛ የኢህአዴግ ሹማምንቶች ጋር ለመተዋወቅ ብሎም በ20ዎቹ የዕድሜ ክልል መጀመሪያ ላይ ሆኖ ለከፍተኛ የመንግስት ኃላፊነት የታጨ፤ በለጋ እድሜው ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ የሆነለት የኢህአዴግ ሹመኛም ነበር፡፡ ያ ግን ትናንትና ነው፡፡ ዛሬ ደግሞ በማራኪ የስነጽሁፍ ችሎታው በልዩነታችን ውስጥ ስላለው ውበት ሳይሆን በልዩነታችን ልክ እንዴት መጥፋት እንዳለብን የሚሰብክ መሰሪ ባህታዊ ነው የሚሉ ቁጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡

Wednesday, October 2, 2013

የአዜብ መስፍን የመያዝ እድል እየሰፋ ነዉ የሙስና ንሰሃ አባቷ እና ባልደረባዋ ተይዟል

ምንሊክ ሳልሳዊ
የአዜብ መስፍን የመያዝ እድል እየሰፋ መቷል። የሙስና ንሰሃ አባቷ እና ባልደረባዋ ተይዟል። በከፍተኛ ደረጃ በሙስና በመዘፈቅ ያለአከራይ ከባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር ለቁጥር የማይገመት ሃብት አፍርተዋል የተባሉት ሃያሁለት አካባቢ የሚገኘው የኮሜት ሕንጻ ባለቤት አቶ ገብረስላሴ ሃይለማርያም (አለቃ ገብረስላሴ) በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ በባለስልጣናት ዙሪያ ከፍተኛ መደናገጥ ተፈጥሯል።

Tuesday, October 1, 2013

የአንዱዓለም አራጌ መልክት ከቃሊቲ (በሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተነበበ) የአንዱዓለም አራጌ መልክት ከቃሊቲ (በሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተነበበ)

580fa-andualem-arage
ከሁሉ አስቀድሜ በዚህ ታላቅ ህዝባዊ ሠላማዊ ሠልፍ ለተገኛችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼለእያንዳንዳችሁ በተናጠል ልባዊ የአክብሮትና የናፍቆት ሠላምታዬ በግፍ ከታሰርኩባት ጠባቧ ክፍል ይድረሳችሁ
Andualem Aragie (3)ኢትዮጵያውያን ለዘመናት እውን ያላደረግነውን የህዝባዊ ልዕልና ጥያቄና ሌሎች ከነፃነት እጦት ጋር የተቆራኙ በአገዛዙ የሚፈፀሙ አያሌ የአፈና ተግባሮችን ለመቃወም በተጠራው በዚህ ሠላማዊ ሠልፍ ላይ ከጎናችሁ መሠለፍ ባለመቻሌ ባዝንም፣ ከተሰለፋችሁላቸው ዓላማዎች አንዱ የእኔና የጓደኞቼን ከእስር መቀቀቅ የሚመለከትና የታሰርኩለትም ዓላማ አካል በመሆኑ በመንፈስ ከጎናችሁ እንዳለሁ አምናለሁ፡፡ በዚህም ታላቅ ደስታ ይሰማኛል፡፡