ነሃሴ ፮ ( ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተቃውሞ እየተናጡ ባሉት የአማራ እና የኦሮምያ ክልሎች ዙሪያ የኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ እና የክልል ስራ አስፈፃሚዎች እንዲሁም የፌደራል ባለስልጣናት የቪዲዩ ኮንፈረንስ እያደረጉ ነው፤ ስብሰባው መፍትሄ ማመንጨት አልቻለም።
Translate
Friday, August 12, 2016
“ሲመረው የማይነሳ ህዝብ የለም ባለም፣” አለ አቦይ ስብሐት ነጋ! (ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የኢትዮጵያውያን የጸደይ አብዮት በ2016 የክረምት ወቅት መጀመሩ ነውን?
አንድ ህዝብ ታምቆ ፣ ታምቆ ማለት ተጨቁኖ በዘመንታ አይቆይም ። ዩኒቨርሳል universal ማለት ነው ። አንድ ህዝብ እንደ ህዝብ መጠን በዓለም ታሪክ አንዳስቀመጡት አንደፈለጉት የሚቀመጥ አይደለም። ሲመረው ይፈነዳል። ይሄ ዓለም አቀፋዊ እውነታ /universal truth ነው። ሲመረው የማይነሳ ህዝብ የለም ባለም። በታሪክም /historically። አሁንም። ለወደፊትም ። (አዛውንቱ የእንጨት ሽበት ባለቤቱ አቦይ ስብሀት ነጋ፣ የዘ-ህወሀት ጭንቅላት፣ ንጉስ፣ የክርስትና አባት፣ ተጽእኖ ፈጣሪ እና የአለቆች ሁሉ አለቃ (ካቦ) እ.ኤ.አ በ2015 ከተናገረው የተወሰደ።) (ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ ።)
በዘ-ህወሀት ላይ የፍርዱ ቀን ደረሰ ማለት ነውን?

እ.ኤ.አ ታህሳስ 2015 “የኢትዮጵያውያን የጸደይ አብዮት በበጋው ወቅት መጀመሩ ነውን? በሚል ርዕስ በኢትዮጵያ በመምጣት ላይ ስላለው የጸደይ አብዮት ትችት አቅርቤ ነበር፡፡“
Breaking News: A Breakthrough agreement between ODF and Patriotic G7
Memorandum of Understanding (MoU)
Oromo Democratic Front (ODF) and Patriotic Ginbot 7 (PG7)
Oromo Democratic Front (ODF) and Patriotic Ginbot 7 (PG7)

August 11, 2016
Thursday, August 11, 2016
በኢትዮጵያ ሕዝባዊ ተቃውሞዎችን ተክትሎ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ደኅንነት ሁኔት አስጊ መሆኑን ሪፕሪቭ ገለጸ
በኢትዮጵያ ሕዝባዊ ተቃውሞዎችን ተክትሎ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ደኅንነት ሁኔት አስጊ መሆኑን ሪፕሪቭ ገለጸ
በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ህዝባዊ ተቃውሞ የተለያዩ አለማቀፍ ሚዲያዎች ሽፋን እየሰጡት ነው።
ነሃሴ ፭ ( አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ታላላቅ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃንና የሰብዓዊ መብት ተቋማት በኢትዮጵያ በተለይ በኦሮሚያና አማራ ክልል ውስጥ የተካሄደውን የጅምላ ግድያ በስፋት አትኩሮት ሰጥተው ዘግበውታል። በዋና ከተማዋ አዲስ አበባን ጨምሮ መላውን ኦሮሚያ ክልል በጎንደርና አካባቢው በባህርዳር የተካሄዱት ሰላማዊ ሰልፎች በጸጥታ አስከባሪዎች በግድያ ምላሽ መሰጠቱን ቢቢሲ ዘግቧል። ሁለቱ ታላላቅ የአገሪቱ ብሔረሰቦች አነስተኛ ቁጥር ባለው አንድ ብሄት በመሳሪያ ሃይል በግዳጅ መገዛታቸውንም ቢቢሲ የኢትዮጵያን ሕዝብ ቁጥር በመቶኛ ስሌት ቀመር ይዞ በመውጣት አሰነብቧል። 6.1% የሚሆኑት የትግራይ ብሔር ተወላጆች 34.4% የሚሆኑትን ኦሮሞችና 27% የሚሆኑት አማራዎች ያገለለ አስተዳደር መመስረታቸውን፣ የስልጣን፣ የሃብት፣ ወታደራዊና ደኅንነቱ በህወሃት ቁጥጥር ስር መውደቁን ቢቢሲ በመረጃ አስደግፎ ዘግቧል። የኦሮሚያ ክልልን የመሬት ቅርምትና የወልቃይት ሕዝብን የማንነት ጥያቄዎችም ሰፊ ሽፋን አግኝተዋል።
ወልቃይት የማን ነው? የማይረባ ጥያቄ | ከፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
ነሐሴ 2008
አንድ
በነገረ አስተሳሰብ ወይም በአስተሳሰብ ሕግ (ሎጂክ) ትምህርት ላይ አንድ የማስታውሰው ምሳሌ አለ፤ ‹‹ሚስትህን መደብደብ ትተሃል ወይ?›› የሚል ጥያቄ ነው፤ ጥያቄው የሚነሣው ጠያቂው አውቃለሁ ብሎ ከያዘው እውቀት ወይም እምነት ነው፤ ስለዚህም ጠያቂው የሚፈልገው ጥያቄ ለማስተላለፍና መልስ ለማግኘት አይደለም፤ ጠያቂው የሚፈልገው በጥያቄ መልክ የራሱን ‹‹እውቀት›› ወይም እምነት ለተጠያቂው ለማስተላለፍና ተጠያቂውን የጠያቂው ደቀ መዝሙር ለማድረግ ነው፡፡

ሚስትህን መደብደብ ትተሃል ወይ? መልስ የሌለው ጥያቄ ነው፤ ‹‹አዎ›› የሚል መልስ ሰውዬው ሚስቱን ሲደበድብ እንደነበረ አመነ ማለት ነው፤ ‹‹አልተውሁም›› ከአለ በራሱ ላይ መሰከረ፤ ሁለቱም መልሶች ተጠያቂውን የሚያስወነጅሉ ስለሆኑ መልስ አይደሉም፤ ከዚያም በላይ ጥያቄው ትክክል አይደለም፤ የማይረባ መጥፎ ጥያቄ ነው፡፡
‹‹ወልቃይት የማን ነው?›› የሚለው ጥያቄ ትክክል አይደለም፤ የማይረባና መጥፎ ጥያቄ ነው፤ ጠያቂው የሚፈልገው መልስ የአማራ ነው፤ የጎንደር ነው፤ የትግሬ አይደለም፤ የሚል ነው፤ ነገር የሚገባው ተጠያቂ ጥያቄውን ጠያቂው በፈልገው መልክ አይመልስለትም፤ ሊመልስለትም አይገባም፤ ወልቃይት የኢትዮጵያ ነው የሚል መልስ አይፈለግም፤ የማይፈለግበትም ምክንያት ‹‹ወልቃይት የኢትዮጵያ ነው፤›› ማለት ወልቃይትን ከጎሠኛነት አጥር ስለሚያወጣ ነው፤ የትግራይ አይደለም፤ የአማራ አይደለም፤ የኢትዮጵያ ነው፤ አሁን ትግራይና አማራ የኢትዮጵያ ናቸው፤ ይህ ከተባለ በኋላ ወልቃይት የትግራይ ነው? ወይስ የአማራ? የሚለውን ጥያቄ ማንሣት የጎሠኛነት ጥያቄ ነው፤ የኢትዮጵያዊነት ጥያቄ አይደለም፤ ጥያቄው የማይረባ የሚሆንበት አንዱ ምክንያት ይህ ነው፤ ሁለተኛው ምክንያት የጎሠኛ ጥያቄ በመሆኑ የወያኔን የጎሠኛ መመሪያ የሚያከብር መሆኑ ነው፡፡
Wednesday, August 10, 2016
እነ አባይ ጸሃዬ አሜሪካ ነበሩ፤ “ኦሮሞና አማራ ተባበሩብን፤ ሰግተናል”
አሜሪካ ህወሃትን ለማዳን ጥገናዊ ለውጥ እንዲደረግ ፈልጋለች

የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ከፍተኛ አመራር አባይ ጸሃዬ፤ ሳሞራ የኑስን ጨምረው ሌሎች ከፍተኛ የህወሃት ባልደረቦቻቸውንና በመያዝ አሜሪካ አገር አጭር ቆይታ አድርገው መመለሳቸውን ጎልጉል አረጋግጧል። አሜሪካ በግል የተቃዋሚ ፓርቲዎችን በማነጋገር ውሉ ባግባቡ የማይታወቅ የሽግግር ሃሳብ ለመተግበር ማሰቧ ተሰምቷል። የሽግግር ሃሳቡ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) የያዘውን ስልጣን በተወሰነ መልኩ የሚያስቀጥል በመሆኑ ለአሜሪካ ፖሊሲ አውጪዎች ሃሳብ የሚያቀርቡ ተጽእኖ ፈጣሪዎች አሜሪካ ይህንን መሰሉን አቋም እንድትቀይር እየወተወቱ ነው። ለኦባማ አስተዳደር ፖሊሲ አውጪዎች ዕቅድ ለማቅረብ እነዚሁ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ዝግጅት አላቸው።
Subscribe to:
Posts (Atom)