Translate

Tuesday, March 26, 2013

የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል አብረን እንታገል የሚል የትግል ጥሪ አደረገ


የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል አብረን እንታገል የሚል የትግል ጥሪ አደረገ

የኢትዮጵያ ህዝብ ሃያ አንድ አመት ሙሉ ከቀለደበት  የወያኔ ኢህአዴግ አገዛዝ እጅግ በጣም የተሻለ አማራጭ ኃይል እንዳለዉና ይህንን ለኢትዮጵያ አንድት፤ ለህዝቦቿ እኩልነትና ነፃነት በቆራጥነት የቆመዉን አማራጭ ኃይል የኢትዮጵያ ህዝብ በፍጥነት እንዲቀላቀልና የትግሉን የመጨረሻ ምዕራፍ እንዲጀምር የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል አገራዊ ጥሪ አደረገ። የወያኔ ንቀት፤ጥላቻና ህዝብን ማሸበር ማብቃት አለበት ብለዉ አምርረዉ በተነሱ ወጣቶች፤ምሁራንና ወታደሮች በቅርቡ የተቋቋመዉ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል በላፈዉ ሳምንት እንዳሳወቀዉ በወያኔ ተራ ካድሬዎች መረገጥና እየተገፋ እስር ቤት መወርወር የሰለቸዉ ኢትዮጵያዊና በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ዉስጥ በህዝብ ነጻ ፍላጎት ተመስርቶ ህዝብን በታማኝነት የሚያገለግል ስርአት ለመመስረት ምትፈልጉ ኢትዮጵዉያን ሁሉ ወያኔ እስካለ ድረስ ይህንን ህዝባዊ ስርአት ካለመስዋዕትነት ማምጣት አይቻልምና ለድል ሊያበቃን የሚቸለዉን መስዋዕትነት ለመክፈል እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በተጠንቀቅ እንዲቆም አገራዊ የአደራ ጥሪዉን አስተላልፏል። የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል ይህንን ጥሪ ያደረገዉ የወያኔ ህወሀት ተሸካሚ ፈረስ የሆነዉ ኢህአዴግ ካለፈዉ ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን እስከዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 17 ቀን ድረስ ባህርዳር ላይ ጌታዉን ተሸክሞ ያካሄደዉን ትርጉም የለሽ የወሬ ጉባኤ አስመልክቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ ባስተላለፈዉ መልዕክት ነዉ።

“አሁን በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ባመዛኙ ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ የባንዳ ልጆች ነበሩ”


ፍኖተ ነጻነት መጋቢት 15 ቀን 2005 ዓ.ም.

የዛሬው እንግዳችን አቶ ታዲዎስ ታንቱ ይባላሉ፡፡ አቶ ታዲዎስ የታሪክ ምሁርና በኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ነፃ ፕሬስ ውስጥ ትልቅ ሚና ያላቸው ሲሆን በአሁን ወቅት “ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ኮሚቴ” ዋና ሰብሳቢ ናቸው ፡፡ በተለይ ለፋሺስቱ ግራዚያኒ ከተሰራው ሐውልት ጋር በተያያዘ አጭር ቆይታ አድርገናል ተከታተሉን፡፡
በጣሊያን የሩዶልፍ ግራዚያኒንን የሐውልት ለመቃወም የሐሳቡ ጠንሳሽ ማን ነው?
አቶ ታዲዎስ፡- የፋሽቱ ጣሊያን የኢትዮጵያውያን ዋና ጨፍጫፊ የነበረውን ሩዶልፍ ግራዚያኒ ሐውልት መሰራት ለመጀመሪያ ጊዜ ተቃውሞው የተጀመረው በውጭ ሀገር ባሉ
Interview with Ato Tadiwos Tantu
አቶ ታዲዎስ ታንቱ
ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት
ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ
ኢትዮጵያውያን ነው፡፡ በሀገር ውስጥ ግን የሐሳቡ ጠንሳሽ “ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ኮሚቴ” ነው፡፡ ከዛ በኋላ የባለዕራዕይ ወጣቶች ማኀበር ሰልፉን ለማስተባበር ፈቃደኛ መሆኑን ገለፀልን፤ በዚህም ላይ ሰማያዊ ፓርቲ እንደሚተባበረን ከገለፀ በኋላ መጋቢት 8 ቀን 2005 ዓ.ም. ሰልፉን ለማካሄድmወሰንን፡፡

“ዘጠኝ ቦላሌ…” ከይኸነው አንተሁነኝ


ከይኸነው አንተሁነኝ

መጋቢት 26 2013
የክህደት ቁልቁለት አሉ ታላቁ ምሁር!!! የክህደት ውርስ የበቀል ዛር እያስጎራ፣ የሚሆነውንም የማይሆነውንም እያስቀባጠረ ሃያ አንድ ዓመት እያንደረደረ ወርውሮ እዚህ ያደረሰው ሕወሃት ስለመድረሱ እንጅ ወደ ፊት ስለሚሆነው ወይም ስለሚያደርገው ከግምት በላይ የሚያውቀው ነገር ያለ አይመስልም። አውቃለሁ ብሎ ያቀዳቸው ተማከርኩ ብሎ ያወራቸው ሁሉም እንዳይሆን እንዳይሆን እየሆኑበት መሆኑ ይሰማል። ብዙ የተነገረለት ስንት የተባለለት ”የሕወሃቱ የእድገት ትራንስፎርሜሽን”ም ብዙም እንዳልጨበጠ የሚወራው ሳይሆን እየሆነ ያለው የምድሩ ላይ እውነት እያሳበቀበት ነው። ወትሮም ያልነበረው የሁለት አሃዝ ተከታታይ የኢኮኖሚ እድገት ፉከራም ወደ ሗላ እየባረቀ ”ለነዚህ ያህል ዓመታት ሁለት አሃዝ ተከታታይ እድገት ለምን ድህነትንና ስደትን በመጠኑ እንኳ ሊቀርፍ አልቻለም?” የሚለውን የዓለም ማሕበረሰብ ጥያቄ ባልተሳከረ መልኩ ለመመለስ ለሕወሃት አስቸጋሪ ሆኖበታል። ምክንያቱም የኑሮ ውድነቱ፣ ርሃብ እና ችግር የሚያንገላታው የሕዝባችን ቁጥር፣ የተማረ የሰው ሃይል ስራ አጥነት እንደጉድ መጨመር፣ ሁሉን አቀፍ ስደት ለመናገር ከሚያስቸግር በላይ መሆን እንዲሁም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ከምንም ጊዜ በላይ ዋጋው  ረክሶ የታየባቸው ዘመናት በሙሉ በሕወሃት የአገዛዝ ዘመን በተለይም ሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ እድገት አመጣሁ እያለ በሚለፍባቸው በነዚሁ ዓመታት ነበርና ነው።

ዕውን ኢትዮጵያን የሚመሯት ኢትዮጵያውያን ናቸው?



ETHLየኢትዮጵያ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽ ኮሚቴና ባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር በመሆን ያዘጋጁት ሰላማዊ ሰልፍ አላማ ለፋሺስቱና ለጦር ወንጀለኛው ግራዚያኒ በጣሊያን ሀገር የተገነባውን መናፈሻ ስፍራና ሀውልት ለመቃወም ነው፡፡ ይህ ግለሰብ ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈፀመውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ ታሪክ አይዘነጋውም፡፡

እጅግ አስደንጋጭ ቭዲዮኢትዮጵያውያን በመደበኛነት ከቆሻሻ ገንዳ የተደፉ ምግቦችን በመሰብሰብ ይመገባሉ::

ከዘመናት በፊት ለስብህናው ዋጋ የሚሰጠው፣ በየትኛውም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ቢያልፍ የሰው እጅ አይቶና ለምኖ ማደርን የማይፈቅደው የሃገሬ ሰው፣ ለእምነቱና ለክብሩ ሟች የነበረው ወገኔ ይኸው በዚህ ዘመን በሃገሩ በልቶ የመኖር ዋስትና አጥቶ፣ ድርሻውን በጥቂት ዘረኞች ተነጥቆ ኑሮው የምድር ሲኦል ሆኖበት ክብሩን አዋርዶና ነውር ትቶ ነብሱን ለማቆየት ይህንን የመሰለ ዘግናኝ የለት ከለት ኑሮ ይገፋል በመሃል አዲስ አበባ፡፡ ስለልማት፣ ስለተሰራው መንገድ፣ ባለጊዜዎች ስለገነቡት ህንፃ የምናወራ ጉደኞች፣ እድገት ምናምን እያልን የምናዜም አንድ ትውልድ ያመከንን  ከንቱዎች፣ ወገኖቻችን በእንደዚህ አይነት የሰቀቀን ህይወት ውስጥ እያይን ከራሳችን ባለፈ ማሰብ ተስኖን እንደቀትር እባብ ከደሃው ቀምተን ባገኘነው ሃብት የምንንፈላሰስ ከንቱዎች ጥሩም ሆነ መጥፎ መንግሰታት ያልፋሉ ሃገርና ሕዝብ ግን ህያው ናችው፡፡ ያኔ ምን ይውጣችሁ ይሆን . . . . . . . .

ከ100.000 በላይ ኢትዮጵያውያን በመደበኛነት ከቆሻሻ ገንዳ የተደፉ ምግቦችን በመሰብሰብ ይመገባሉ::ይህ የሚያሳየው ሃገራችንን የሚያስተዳድረው የወያኔ ጁንታ 11% እድገት አለ እያለ ቢሆንም ዉሸት መሆኑን ነው ::ወያኔ እየደረሰበት እያለው ኪሳራ መውድቂያው በመሆኑ ህዝቡን ለከፋ ችግር ዳርጎታል::

ነጋሶ ሞገቱ ወይስ ተሞገቱ?


“ኢህአዴግ በህዝብ (ያልተመረጠ) ስለሆነ እውቅና አንሰጠውም”

N G
“ … አንተም ሆንክ ማንም ኢትዮጵያዊ ውጪ ያሉትን ጨምሮ ቢደግፉን ደስ ይለናል። በዚህ መንገድ ሂዱ ብለው እንዲጠመዝዙን ግን አንፈልግም። … ሰላማዊ ትግል የምትሉት ለውጥ አያመጣም ይሉናል። እንደዚህ የምትሉ ከሆነ ከፈለጋችሁ ገንዘብ አትርዱን እንላቸዋለን … ኢህአዴግን እንደ መንግስት እውቅና አንሰጠውም” ከዶ/ር ነጋሶ የተመረጡ መልሶች መካከል የተጠቀሱ ናቸው። በዚህና በሌሎች ምክንያቶች ዶ/ር ነጋሶ ሊሞገቱ ሄደው ሞገቱ የሚል ርዕስ ለጽሁፌ መረጥኩ።

ከእሁድ እስከ እሁድ


ከእሁድ እስከ እሁድ

(የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች)
bottle


አንድ ላስቲክ ውሃ 10 ብር!!
በአፋር የቡሬ ነዋሪዎች ለከፍተኛ የውሃ ችግር መዳረጋቸውን ውሃ የሚሸጥበትን ላስቲክ በፎቶ በማያያዝ የጎልጉል የአይን ምስክር ከስፍራው አስታውቋል። በክልሉ የጎልጉል ተከታታይ የሆኑ እንደገለጹት በመጠጥ ውሃ ችግር እየደረሰ ያለው ችግር ከፍተኛና ህይወትን የሚፈታተን ነው። አካባቢው የጦር ቀጠና ከመሆኑ አንጻርና የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር አሳሳቢ እንደሆነ ያስታወቀው የአይን ምስክር “እባካችሁ የሚሰማ ካለ ንገሩልን” ሲል ጥሪ አስተላልፏል።