Translate

Sunday, November 11, 2012

ጎሽ! ከሥርጉተ ሥላሴ


ከሥርጉተ ሥላሴ – 10.11.2012                                                                                
ምርቃት እንዳልቸራቸው የደረሰ ከሆነ ይቆረቁርኛል። ስለምን? በነፍስ መቀለድ፤ መጫወት፤ በፍጥረት ማላገጥ ይሆናል እና። … እንደገናም እኔ እራሴ ሳስበው … ህሊናዬም እራሱ እኔኑAzeb Mesfin, the wife of Meles Zenawiበእግር ብረት ጥርፍ አድርጎ አስሮና ሰንጎ እያገላበጠ በጉማሬ እንደሚቀጣኝ፤ በመዶሻ እንደሚቀጠቅጠኝ አውቃለሁ እና። …. ስለዚህ በልሙጡ ልተወው።
ለማን ነው? አሉ ወ/ሮ አዜብ ቃለ ምልስስ ያደረጉት … ሰሞኑን … አዎን … ከዋልታ የመረጃ ማእከል ጋር … እ! እንዴት ያለ የወርቅ እንክብል ከኢትዮጵያ ሰፊ ህዝብ መዳፍ ሰተት ብሎ ገባ … ወሸኔ ነው። … ድርብ ትርፍ፤ እጥፍ ወቄት ያለው …. አጥቂ ጭብጥ!
ጠቅላይ ሚ/ር ሄሮድስ መለስ ዜናዊ ከመሞታቸው በፊት ትግራይን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማደረግ ያቀዱት ንድፍ ወይንም ሲናሪዮ ባለቤታቸው ወገባቸውን ጠበቅ አደርገው ለመተግበር እንደ ቆረጡ ተደመጡ … ማለፊያ ነው …

እሺ! በፈቃዳቸው ወገባቸውን ተይዘው እዬያቸውን ሲያጎረፉ የነበሩ ቅን ወገኖች መርዶቸውን ሲሰሙ ምን ይላቸው ይሆን ህሊናቸው …? ደግሞ ሊሠራ ሰለታሰበው የሄሮድስ መታሰቢያስ ይህ እንክብል ዕንቁዊ እውነት እንዴት ያፋጥጥ … ውውው ] ወደ እውነቱ ለመዝለቅ እውነቱም ለሚተናነቃቸውስ? ብዕርማ አይደለም ወያኔ ሥልጣን ይዞ ሳይይዝ ጫካ በነበረበት ወቅት ሁሉ ሃቁን ከእነእትብቱ ይፈታ ነበር።
እስኪ በእኔ በሥርጉተ ሞት  ዝም ብላችሁ ገጻቸውን ቢሞቱም እሰቡት …. የቀድሞ ጠቅላይ ሚ/ር ሄሮድስ መለስ ዜናዊን። በናፍቆት አይደለም። በትዝብት … ፈትሹት ማለቴ ነው። ገጻቸው ፈጽሞ ከቶውንም ኢትዮጵያዊ ጠረን አልነበረውም። ከዚህ ቀደምም መሞታቸውን አስመልክቶ „መጤ እንደ ራሴ“ በሚል አንድ ጹሑፍ ልኬላችሁ ነበር … እንኳንስ ለፓን አፍሪካኒስትነት ቀርቶ ለኢትዮጵያዊነትም መሰፈርቱን የማያሟሉ ግንጥል የሟሙ ፍጡር እንደ ነበሩ ነበር ሃተታው የሚያብራራው …
ተመስገን ነው። ገና የሚጎተት ሐረግ አለ። ጨላማ ውስጥ በደመ-ነፍሱ ለሚዳክረው ሆድ አደር ሁሉም ህሊናውን የሚገዘግዝ የሃቅ መጋዝ ቀኑን እዬጠበቀ እንዲህ ይወጣል። ስለምን? ገድለ – ታምራቱ የመዳህኒተዓለም ነውና …
ሃብቱን በሚመለከት ሥርጉተ የቁጥር ተማሪ ስላለሆነች በዚህ ዙሪያ ደካማም ስለሆነች የትርፋማነቱን ስሌት ዘላ ግን ኤፈርት አፈራ ስለሚባለው ጥቅል ንብረት ትንሽ አንድ ሁለት ማለት ትሻላች … በመጀመሪያ ነገር እኔ የወያኔን እንቅስቃሴ ከጫካ ጀምሮ በፍጹም ሁኔታ የምከታተል አነስተኛ ፍጡር ነኝ። ራዲዮ ፕሮግራማቸውን፤ ድራማዎቻቸውን ሁሉ በትእግስት ዕታደምበት ነበር ለዛውም በአፍላ ዕድሜ። … ማለት ወጣትነትና ትእግስት … ይከብዳሉና። በዕድሜ የማይቀሩ ተፈጥሯዊ ሁነቶች ሰለሚኖሩ። ስለምን ይመስላችኋል ያን ጊዜ የወያኔ ሃርነት ትግራይን የማሌሊትን ድምጽ በተደሞ አደምጥ የነበረው? የሚያሰፈልግኝ ቁልጭ ያለ መንፈስ ስለነበር። እሱ ደግሞ ኢትዮጵያዊነት እና ወያኔ ጦር ግንባር ላይ ስለነበሩ። ዬወያኔነት መፍቻ ቁልፍ እናም ትርጉምም … ኢትዮጵያዊነት በጠላትንት ፈርጆ መፋለም ነበር። እራሱ የራዲዮ ጣቢያው ከሃቅ ጋር ዬነበረው አቅርቦተ -እርቀት ሆነ፤ በሠራዊቱ ላይ ድል አስመዘግብኩ ብሎ ሲፏልል የድምጹ ቃና የሚያመሳጥረው ብረቱ ሚስጢራዊ ቅኔ ነበረው። 21 ዓመት ሙሉም የታዬው ይኽው ነው። በሁሉም ዘርፍ የተለወጠው ነገር ከጫካ ከተማ መከተም ብቻ እንጂ ጥሩ ዕውነትማ እንዳለ ነው።
ኢትዮጵያዊነት ረቂቅ … ቅዱስ … ማንነት ያለው ከፈጣሪዬ በታች የማምነው ቤተ- መቅደሴ ነው -  ለእኔ። ኢትዮጵያዊነት ንጹህ ነው። ኢትዮጵያዊነት ቅዱስ ነው። ወያኔ ደግሞ የዚህ ንጹህ ማህሌተ – መቅደስ ተጻራሪ ነው። ስለሆነም ከወጣትነቴ እስከ ጉልምስናዬ ድረስ የምከታተለው፤ አትኩሮት የምሰጠው ጉዳይ ነው …. የወያኔ ዓላማ፤ ተግባር፤ እንዲሁም ፓሊሲ …
  • ዓላማው አንድ ነው፤ … ታላቋ ትግራይን በመጠንም በዓይነትም ለይቶ መፍጠር።
  • ተግባሩ፤ …  ኢትዮጵያዊነትን እያከሰሙ ታላቋ ትግራይን መገንባት።
  • ፖሊሲው፤ … ኢትዮጵያዊነት የፈጠራቸው ማናቸውንም ነገሮች፤ ዕሴቶች ምድማዳቸውን አጥፍቶ አቧራ በማልበስ የልዕለ ትግራይን ማንነት ማንጠር …
ለመሆኑ ወያኔ ከመጣ በኋላ የወጡ የጎብኝ ቱሪስቶች የጉዞ መመሪያ (ጋይዳንስ ቡክስ) መጸሐፍቶችን በእንግሊዘኛም ሆነ በጀርመንኛ የተጻፉትን እስኪ ጊዜ ሰጥታችሁ አንብቡት። …. የሁለመናችን ሃብትነት እኮ የኢትዮጵያ የጋራ ሃብት መሆኑ ቀርቶ የትግራይ ብቻ ነው የሆነው። … ግርም ነው የሚላችሁ ስታነቡት። .. እርእሱን እረሳሁት አንድ በጀርመንኛ ቋንቋ የተጻፈ፤ ታሪካችን አጋድሞ  የዘገበ ትልቅ መጸሐፍ በአንድ ወቅት አነበብኩ። የዛሬ አራት ዓመት ገደማ ነበር። … ከዛ ላይ ልዑል አስፋው ወሰን አስራተ ካሳም አሉበት። የሚገርማችሁ የአራስ ቤት ወግ ሳይቀር የተዘገበው የትግራይ ነው። ሟቹ አባ ጳውሎስም ተኮፍሰው ጉብ ብለው አገኘኋቸው።
ምን ለማለት ነው ታሪካችን፣ ባህላችን፤ ወጋችን፤ ልማዳችን በጣም በብዙ ሁኔታ እዬተዘረፈ ለአንድ ክልል ብቻ ካለተቀናቃኝ ተሸልሟል። ይህን ስል ትግራይ የኢትዮጵያ አካል አይደለችም ለማለት አይደለም። … አልወጣኝም። እያንዳንዱ ክፍለ ሀገር የራሱ ማንነት ሲኖረው ማንነቱን ተከትለው የሚመጡ ሆነ የሚኖሩ አብነቶችና ትውፊቶች አሉት። ነገር  ግን በወያኔ ይህ ሁሉ ተሰርዟል። አንጡራ የምንላቸው ቀደመት የሀገራችንና የህዝቦቿ የመንፈስ ቅርሶቻችን ሁሉ የትግራይ ናቸው … „ዘመን የሰጠው ቅል …. ድንጋይ ይሰብራል።“
እኛ ላይ ላዩን ነው የምንጋለበው … እነሱ ደግሞ ውስጥ ውስጡን ነው የሚሄዱት። … እኔ ይሄንን በተጨባጭ በእራሴ ህይወት የማዬው ነው። እኛ እጅግ ሲበዛ ግልጾችና ቅኖች፤ እነሱ ደግሞ ምስጦችና  ነቀዞች … የግድ መውጣት ካለበት እንኳን ከጨረሱ በኋላ ነው አደባባይ የሚያውሉት። እንዲህ በዋዛ የሚታዩ ሊሆኑ አይገባም።
አሁን የእኛ የተቃዋሚ ዬፖለቲካ መሪዎቻችን የፌድራል ወታደሮችን ሆነ አጋዚን ጨምሮ የእኛ የእራሳችን ለማደረግ ይሰብኩናል። እንደ እኛ እንድናያቸው። እንዲዋህዱን – በቅንነት።  እውነቱና ተጨባጩ የሚነግረን ግን ሌላ ነው። አነጣጥረው ሲገድሉ እንኳን አናትን ነው። ከእነሱ የተጠጋው ባሩዱ እራሱ የቋሳ አርበኛ ነው። ዬዕውነት በዚህ ዙሪያ ያለን ግንዛቤ ዓይን እያለን ግን የዓይንን ሚና የቀማነው ይመስለኛል። ህሊና እያለንም የህሊናን ድርሻ ያጨለምንበት ወይንም የጋረድንበት ይመስለኛል። ጥላቻ እንጠስስ ማለቴ አይደለም። በማስተዋል ሆነን የህዝብንና የሀገርን ጉዳት በጣም በጥልቀትና በትእግስት እንመርምረው … እንፈትሸው … ለማለት ነው … ታሪካችንም ነው።
ዖዬ! የተነሳሁበትን እንዳልረሳ ልመለስ … የኤፈርት ዲታነት እኮ ምንጩ የኢትዮጵያ ሃብት ነው። ወያኔንን እኮ ጫካ እያለ እናውቀዋለን። ለከፈን እንኳን ያልበቃ ነበር። በመኸር ወቅት ዘመቻ ነበረው። – ለስርቆት … የጎንደርንና የወሎን ገበሬዎች ምርትና ንብርት እንዲሁም ባንክ የሚዘርፍበት … ወያኔ እኮ  በጣም ድሃ ድርጅት ስለነበር ሰራዊቱን እንኳን የሚቀልብበት አቅም አልነበረውም። … „ ለማያውቅሽ ታጠኝ“ ይላል ጎንደሬ። ደረግን ከመርገም መመረቅ ያለበት ድርጅት ቢኖር ወያኔ መሆን አለበት። ስንቅም ትጥቅም እዬሆነ ኮለል አድርጎ በትረ መንግሥቱን ያስጨበጠው ….
እንጂ ወያኔማ በፍጥረተ ነገሩ በጣም አመዳም ቡላ ድርጅት ነበር። ከዬት የመጣ ሚሊዮነርነት ነው] … ከኢትዮጵያ ህዝብ አንጡራ ሃብት እየተዘረፈ ነው። በሌላ በኩል ወያኔ እንደ አንድ የፖለቲካ ድርጀት ሊታይ የማይገባው ማፍያም ነው። ሌባ ነዋ! … በስውር ከሚዘርፈው በላይ የሀገሪቱን ህግ ተላልፎ ካለቀረጥ፤ ካለ ግብር ታክሲ በጠራራ ፀሐይ ነው የሚሞልጨው። … የዚህ ሁሉ ዝርፊያ ማሰረጊያ ዓላማ ደግሞ ይኽው እንደ ሰማችሁት የታላቋ ትግራይ አውሮፓዊነት ራዕይ ነበር …
እሺ አሁንስ የኢትዮጵያ ህዝብ ማለት በእንጥልጥል ላይ የነበረው „ታላቁ ባለ ራዕይ“  የሚለውን ድንብስ መፈክር ከጫንቃው አሽቀንጥሮ ይጥለው ይሆን? መቼም ዓይኑን ያፈጠጠ የተከደነና የታመቀ ጉድን ነው ወ/ሮ አዜብ መስፍን የዘለዘሉት …. ጎሽ! ማለፊያ ምስክርነት ነው።
እንዲህ አንጀት ጉበቱን አውጥቶ ገመናውን ቁልጭ አድርጎ የሚገልጥ ወቅታዊ የፋመ መረጃ ሲያቀበሉ፤ ለጸረ ወያኔ ትግሉ የቤት መገንቢያ መሰናዶ እንዳሟሉ ነው እኔ በግሌ እምቆጥረው። አንዳንድ ጊዜ አንዳንድ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ተከላለከልን ብለው በራሳቸው መረብ  ላይ ኳሷን ይለቁና ለተቀናቃኛቸው ነጥብ ያስቆጥራሉ። እራሳቸው በተቀናቃኛቸው ላይ ባስመዘገቡት ነጥብ ተሸንፈውም ይወጣሉ። አሁንም እንዲህ ነው የሆነው …. ለሥምና ለዝና። ለርካሽ ተቀባይነትም ብለው የዘረገፉት ጉድ ለእኛ ዕንቁችን ነው። የትግራይ ህዝብ ሄሮድስን ቢያጣም  ልጃችን አልሞተም። እሷ አካሉ እያለች እንዲባሉ እና … መቼም ልብ አይሞትም በቀጣዩ ምርጫ ደግሞ … ለመ …. ሪ … ነ … ት፤ …. እን ዲ ታጩ ….
እኔ እስከሚገባኝ ድረስ የሄሮድስ መለስ ዜናዊ መሪነት ለኢትዮጵያ ፈጽሞ አልነበር።  ዬእሳቸው የፍጥረት ድርሻ ኢትዮጵያዊነትን ማክሰምና ማምከን ነበር። እትብታቸው ለተቀበረበት ትግራይ ግን መድህንነት ነው። ለዚህም ነው ደግሜ ደጋግሜ አጋጣሚ ሳገኝ የምናገረው ጥቅሙን የሚጻረር ተጠቃሚ የለም የምለውም። ስለምን … መስጥረው ሄሮድስ መለስ ዜናዊን እጅግ ይወዷቸዋል አብዛኞቹ  ወዲ ትግራይ  …. ሥልጣን ቀረብን ከሚሉት በስተቀር። እነሱም ቢሆን ይህቺን መሰል የተዛባ የሐብት ስርጭት ይሁን የተዛነፍ አትከሮታዊ ፖሊስን ይመርቋታል – በልባቸው።
ሌላው ግን ለወ/ሮዋ መንገዱን ጨርቅ ያድርግላቸው ብዬ ሳልመርቅ ዳገትና ረግረግ እንዲሆንላቸው ግን ቅን አምላኬን እማጸናለሁ። ምን አልባትም መጥፊያቸውም ሊሆን ይችላል። በተለጠፈ ማንነት ተሞሸረው፤ በቀን የጨለማ ካሊብ ተኮፍሰው ለሚንደፋደፉት … ሌት ተቀን ለመባተል ለሚደናበሩት … ካህዲ …. ዳጥና ገደል … ብያለሁ … ። እናንተስ? ….
የጎንደር ህዝብማ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ በበቀለ እዬተጨቀጨቀ እዬተገፋ – እዬተገፈተረ መሬቱን ሲያስፈልግ ለታላቋ ትግራይ፤ ሲያሻ ደግሞ ለሱዳን፤ … አቤት! እንዴት ያለ የዘር ምክነት ነው። …. አዜብን ያፈራች ቃብቲያ …  አብልታ፤ አጠጥታ፤ ተንከባክባ ያሳደገች ቀዬ እርግማኗ እስከ ልጅ ልጅ ነው …. በእውነት … ደብረ ዳሞ ምን ደረሰበት] ምንም። ዋልድብስ? … ቀራንዮ።
ይህም ብቻ አይደለም ጎንደር ከማህል ሀገር ጋር እንኳ ሲነጻጸር በዋጋ ግሽበት የመጀመሪያ ረድፈኛ ነው። ስለ ምን? የተያዘ የተረዘዘው ሁሉ ከጎንደር ነው የሚጫነው ☞ ወደ ትግራይ። … እንጃ የቀረው ነገር አፈር መጫን ብቻ ነው። ይህንም አድርገውት ይሆናል … ጉደኞች እኮ ናቸው ….
ተዚህ ላይ አንድ ነገር ትዝ አለኝ። በጣሊያን ወቅት በተከፈለው መስዋዕትነት ለካሳነት የተሰጠው በጎንደር ከተማ ወቶባርኮ ላይ የነበረው  የኤሌክትሪክ ጄኔሬት ስንት የጎንደር የገጠር ከተሞች በጨለማ ውስጥ ሆነው …. የተጫነው ትግራይ ነበር። … ይህንንም ካህዲዋ እያዩ እዬሰሙ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው የግፉን ቁና ወሸኔ እርምጃ እያሉ ሲያቆላምጡት ኑረዋል። … ከእራሱ ከመሰረቱ የተነሳውን የኤሌክትሪክ መስመር ወደ ትግራይ ሲዘረጋም በሚያልፍባቸው ከተሞች እንኳን ብርሃኑን ማዕቀብ ጥሎ በመቁንን ነበር ትግራይ ላይ ጉሮ ወሸባዬ እንዲል የተደረገው … እህህህ …
ጆሮ የተለጠፈላቸው ግን አላውቅህም የሚሉት፤ አንገት ተስርቶላቸው የእኔ አይደለህም የሚሉት  ወ/ሮ አዜብ በተለጠፈ ማንነት ተደናብረው መልካም እርምጃ በማለት አድናቆታቸውንም ችረውታል። … ለዚህም በአንድ ወቅት „የመለስ ጭንቅላት ቢሸጥ ስንት ዋጋ ባወጣ ነበር“ በማለት የታበዩት ….
እኮ! …. ሄሮድስ አለፉ ሄሮዳዳይ ተተኩ … ለምርጥ ዘር ጥብቅና ቆሙ …  ክክክክ! ለነገሩ የዶር. አረጋይ በርሄም የጎሳ ድርጅታቸው አስተምህሮም እኮ ይኽው ነው። ትግራይ በወያኔ የሚገባትን ያህል አልተጠቀመች ነው። ከአንድ ዘር የሚፈጠረው ተመሳሳይ ፍሬ ነውና … አቶ ገብረመድህን አርያን እና እጅግ ጥቂት ከጎሰኝነት የጸዱ የእውነት አርበኞችን ንጹኃንን ሳይመለከት …. አንዳንድ ጊዜ ተፈጥሮ ፈንገጥ ይላል አይደል?! … ከንፍሮ ጥሬ ስለሚያወጣ … የማውቃቸው ስላሉኝ። ከልብም የማከብራቸው።
በተረፈ መልካም አጋጣሚ ነው ታምራትን ገድላትን ማንበብ መተርጎም ይገባናል። ይህ የሰሞኑ የወ/ሮ አዜብ መረጃም ከቀደሙት ሰማያዊ ገድላት ረድፍ መመደብ አለበት። …. እንዲሁም በዚህ ዙሪያ ሀገር ቤት የሚደርሱ ራዲዮኖች በርካታ ተግባራትን ሊከውኑበት ይገባል። ወቅታቂና ተጨባጭ የመረጃ ምንጭ ነውና …
ወ/ሮ አዜብ  ፍሬዎች አሏቸው። …. እነኝህ ፍሬዎች ነገ እንዴትና እንዴት ባለ መስመር ይሆን ከሌላው ፍሬ  ጋር የሚገናኙት] ነገ ቅዱስ ነው። ነገ ያልባለቀ ድንግል ነው። ይህ የወ/ሮዋ አሰር …. የዛቀጠ ታሪክ ቅድስናና ድንግልና ካለው ነገ ጋር ግብግብ እንደሚገጥም እርግጠኛ ነኝ። ቅዱሱ ነገ፤ ድንግሉ ነገ፤ ሳይወድ ተገዶ ጦር ሜዳ መዋሉ ግድ ይላል። ነገር ግን ቅድስናውንና ድንግልናው ድል አድርጎ ታሪክን ይሞሽራል። ወ/ሮ አዘቤን ደግሞ ከካህዲዎች፤ ከአይሁዶች፤ ከቀያፋዋች ተርታ ከነጉዲት ይመድባቸዋል ….  ወህ! ለዛሬ ጨረስኩ።
ኢትዮጵያ ሀገራችን ማንነቷ እንደ ዕንቁ ለዝንቷዓለም የሚያበራ ዕውነት ነው።
አራት ዓይናማው መንገዳችን ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው!
ሀገራችን ኢትዮጵያን አምላካችን ከነክብሯ ይጠብቅልን።
አሜን!
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

No comments:

Post a Comment