Translate

Sunday, November 25, 2012

ለመሆኑ አባ ገብርኤል ስንት ምላስ አላቸው?


ዘመነ ካሳ ፍራንክፈርት ጀርመን

በቀደመ ስማቸው ኢያሱ ተፈሪ ተብለው ይጠሩ የነበሩት አባ ገብርኤል በቀድሞው ፓትርያርክ በብጹእ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ፈቃድ አባ ገብርኤል በመባል የዽዽስና ማእረግHis Grace Abune Gebriel ተቀበሉ ከዚያም በተለያዩ የኢትዮዽያ አሕጉረ ስብከቶች በሊቀ ጳጳስነት አገልግለዋል በተለይም የቀደመችው የኢትዮጵያ አካል የነበረችው የኤርትራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ጊዜ ከተዋሕዶ ትምህርት የወጣ የምስጢረ ሥላሴን ትምሕርት የሚያፋለስ  መጽሐፍ በመጻፋቸው ምክንያት ተወግዘውና ተሽረው በቀደመው አለማዊ ሥማቸው አቶ ኢያሱ ተፈሪ ተብለው በቅዱስ ሲኖዶስ ተለይተው እንደነበር ታሪክ መዝግቦት የተቀመጠ መሆኑ የታወቀ ጉዳይ ነው

አባ ገብርኤል በአቋማቸው ወላዋይነት በተናገሩበት የማይጸኑእንደ ገበታ ውኃ የሚዋልሉ ይህን ብየ ነበር ብለው ይሉታና ትዝብት የሌላቸው እና ጠንካራ ነው ብሎ ያመኑበትን ክፍል በመጠጋት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሚታወቁት እኚህ ግለሰብ ከአባ ጳውሎስም ጋር በፈጠሩት ጠብ አስመልክተው በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ተናግረው ነበር ”አባ ጳውሎስ እንዲመረጡ ለዚህ ፕትርክና እንዲበቁ ባደረግሁት አስተዋጽኦ እጅግ ይጸጽተኛል”በማለት ከሀገር ወጥተው መንግሥትንና ፐትረያርኩን ሲቃወሙ የነበሩ በመንግሥትም የሰላ ሂስ ሲሰነዝሩ የታወቁ ግለሰብ መሆናቸው የአደባባይ ምሥጢር ነው
በምድረ አሜሪካ በነበሩበት ጊዜም ትክክለኛውና ሕጋዊው ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ናቸው እያሉ ሲናገሩ የነበሩት እኒህ አባት
የሰላማዊ ሰልፍ መሪ በየቲቪው መስኮትና በየሬዴዎው ጣቢያው የኢትዮጵያን ችግር ተንታኝ የነበሩ ግለሰብ ባልታወቀ ምክንያት እንደ አክሮባቲስት ተገልብጠው አዲስ አበባ በመግባት የሆነውን ያልሆነውን በመዘላበድ  እነደገና ተቀይረውና ሌላ ሰው ሆነው ትናትና ደግሞ በአሜሪካ ሬዲዮ ጣቢያ የሰጡትን አስተያየት የሰማ ሰው እጅግ የሚያሳዝን ሆኖ እናገኘዋለን
ታዲያ እነዚህን ከመሰሉ አባቶች የቤተ ክርስቲያን አንድነት ይመጣል ብሎ መጠበቅ ከዝንብ ማር እንደመጠበቅ ያህል ነው አኒህ አባት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ተጣቂ እንደሆኑና ይታጠቁት የነበረው የጦር መሳሪያ እንደጠፋባቸው  በዚህ ጦስ ምክንያት አንድ ግለሰብ ተጠርጥሮ ሥራውን እንዲያጣ ምክንያት አንደተደረገ በአንድ ኢንተርኔት ድህረገጽ  እንዲህ ይነበባል

የአቡነ ገብርኤል ማካሮፍ ሽጉጥ ጠፋ

  • ሰርቀሀል ተብሎ የተጠረጠረው ዲ/ን ፍጹም እንዳለ የተባለ አገልጋያቸው እንዲባረር ተደርጓል፡፡
በአቋማቸው ወላዋይነት እና ጠንካራ ነው ብሎ ያመኑበትን ክፍል በመጠጋት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሚታወቁት አቡነ ገብርኤል በቤታቸው ደብቀውት የነበረው ማካሮፍ ሽጉጥ ጠፋ፡፡ አጣሪ ኮሚቴ አቋቁመው ነገሩን እንዲጣራ እያደረጉ ነው፡፡ የአጣሪ ኮሚቴው ሊቀመንበር ከሀገረ ስብከተ ስራ አስኪያጅነት ከተባረረ በኃላ አሁን አቡነ ጳውሎስ ካረፉ በኃላ በአባ ገብርኤል ወደ ቦታው የተመለሰው አለም እሸት ነው፡፡ አለም እሸት ከስልጣኑ የተነሳው ከ12 መኪና በላይ የሚሆን ህዝብ ከአዋሳ መጥቶ አቤቱታ ስላቀረበበት እንደሆነ አይዘነጋም፡፡ ከቅዱስነታቸው ዕረፍት በኃላ ግን አለምእሸትን አባ ገብርኤል በማን አለብኝነት መልሰውታል፡፡የሽጉጡን መጥፋት በተመለከተም ምንም እንኳ አለም እሸት ማኅበረ ቅዱሳናዊ የምርመራ ዘዴውን ተጠቅሞ ለማውጣጣት ቢሞክርም ልጁ ግን ባልወሰደድኩት ንብረት እንዴት እጠየቃለሁ በማለቱ አባረውታል፡፡ እውነተኛውን ሌባ ፈልጎ አንደማውጣት ድሀን በመግፋት መፍትሔ ሰጠን የሚል አሰራር የእነ አባ ገብርኤልን እና አለምሸትን አምባገነንነት ያሳያል፡፡
ሽጉጥ በጓዳ አስቀምጠው የሀይማኖት አባት ነኝ ለማለት መሞከር በእጅግ አሳፋሪ ነገር ነው፡፡ ነገሩ አሳፋሪ ስለሆነም ለፖሊስ ለማመልከት አልደፈሩም፡፡ እስራኤልን የሚጠብቅ አያንቀላፋም የሚለውን ቃል ያላነበበቡት አባቶቻችን ራሳቸውን ለመጠበቅ የማያንቀላፋውን ጌታ ትተው ሽጉጥን ተስፋ ማድረጋቸው ይገርማል፡፡ እውነትን ጽድቅን እየሰሩ እግዚአብሔርን ተስፋ ከማድረግ ይልቅ ሁሉን እያደፈረሱ በሽጉጥ መታመን የማይጠቅም ነገር መሆኑን መዘንጋታቸው ገርሞናል፡፡
ብጹዕነታቸው በደርግ ጊዜ አድርገውት በነበረው ንግግር “ሰው ራሱን በሚያስፈልጉ ነገሮች መጠበቅ አለበት፡፡ እግዚአብሔርም እኮ የሚጠብቁት ጠባቂ መላዕክት አሉት” በማለት እግዚአብሔርን በማያውቅ ባህሪያቸው ስለ እግዚአብሔር የስህተት ትምህርትን አስተምረው እንደነበረ ይታወቃል፡፡ በቅዳሴያችን “መላዕክትን የምትጠብቃቸው አንተ ነህ” የተባለውን ጌታ፤ አቡነ ገብርኤል ግን ብቻውን ምንም እንደማያደርግ አስበው መላዕክቱ ይጠብቁት ነበር ማለታቸው በወቅቱ ትዝብት ላይ ጥሎዋቸው እንደ ነበረ ይታወሳል፡፡ እኚሁ ጳጳስ ታድያ እግዚአብሔርም ይጠበቃል ብለው የሚያምኑ በመሆናቸው ለራሳቸው መጠበቂያ ሽጉጥ ቢይዙ የሚደንቅ አይሆንም፡፡ ብቻውን ሀያል እና አሸናፊ የሆነውን ጌታ በማንነቱ አለማወቅ እና ልጆቹን አክብሮ እንደሚዝ እና አንደሚጠብቅም አለማወቅ ከማካሮፍ ሽጉጥ ጋር ተቃቅፎ ለመተኛት እንደሚዳርግ እሙን ነው፡፡ የሀይማኖት አባቶች የሚጠበቁት በመንፈስ ቅዱሰ እንጂ በሽጉጥ አለመሆኑን ለአባቶቻችን እግረ መንገዳችንን ለማስታወስ እንወዳለን፡፡
ታዲያ ወገኖቼ ይህን በመሰለና እጅግ ለመስማት በሚዘገንን ድርጊት በሥነምግባርና በሞራል ዝቅጠት በወደቁ አባቶች የቤተ ክርስቲያን አንድነት የምዕመናን ሕብረት እንዴት ይምጣ የሀገር ሰላም የወገን ሰቆቃስ እንዴት ይወገድ ??
እባካችሁ ሁላችንም ለቤተ ክርስቲያን ሰላምንና አንድነቷን የምንናፍቅ ወገኖች በሕብረት የምንነሳበት ጊዜው አሁን ነው
ዘመነ ካሳ ፍራንክፈርት ጀርመን

No comments:

Post a Comment