Translate

Monday, November 19, 2012

በኬኒያ- ናይሮቢ ኢስሊ፤ ሳንትሬዛ ሰፈር ቦንብ ፈንድቶ 7 ሰዎች ሞቱ


ትላንት ነው አሉ በዕለተ ሰንበት በኬኒያ ናይሮቢ ከተማ በምስራቁ የከተማዋ ክፍል ሳንትሬዛ የካቶሊክ ቤተከርስቲያን አካባቢ ኬኒያውያን ዛሬም ቦንብ “ተጥሎባቸው” 7 ሰዎች ለሞት እንዲሁም ወደ ሰላሳ የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ ለጉዳት ተዳርገዋል።
ይህ አካባቢ በርካታ ሀበሻ ኤርትራዊያን እና ሱማሊያውያን የሚኖሩበት ቦታ ነው። በአካባቢው ያሉ ወዳጆቼ እንደነገሩኝ ፍንዳታውን ተከትሎም በአካባቢው የሚኖሩ ኬኒያውያን ከሱማ ያውያኑ ጋር ተጋጭተዋል። በዚህም ሳንትሬዛ እና አካባቢዋ ኢስሊ የተኩስ ልውውጥ እየተሰማ ነው።
ኬኒያ በሱማሊያ ጉዳይ ጣልቃ ከገባች ወዲህ ይሄ የቦንብ ፍንዳታ ስንተኛው እንደሆነ እንጃ! ግን በተደጋጋሚ የቦንብ ጥቃት ሰለባ ሆናለች። ብታምኑም ባታምኑም ከእያንዳንዱ ቦንብ ጀርባ ገንዘብ የወሰደ ኬኒያዊም አለ!
ኢትዮጵያዊ መሆን ጥቅሙ ይሄ ነው። እንደ ሀገሪቷ ባለስልጣናት ስራ ቢሆን ኖሮ አልቀን ነበር። ነገር ግን እንደ ህዝቡ ጨዋነት እና እንደ ፈጣሪ ቸርነት እስካሁን አለን!
ጉዳት ለደረሰባቸው ጎረቤቶቼ እግዜር ብርታቱን ይስጣችሁ እላቸዋለሁ!

No comments:

Post a Comment