Translate

Thursday, April 30, 2015

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ 25ኛ በዓለ ሢመታቸው መታሰቢያነቱ በሊቢያ ለተሰውት እንዲሆን አሳሰቡ

“…ይሁን እንጅ ይህ ጊዜ ልጆቻችን በስደት ሀገር በሃይማኖታቸው ምክንያት በሰይፍ እየታረዱ ያሉበት ጊዜ በመሆኑ የተዘጋጀው የ25ኛ ዓመት በዓለ ሲመት መታሰቢያ፣ የመርሐ ግብር ማሻሻያ ተደርጎበት፣ በሊቢያ ሚያዝያ ፲፩ ቀን ፪ሺ፯ ዓ.ም ለተሰየፉትና በጥይት ተደብድበው ለሞቱት ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች የመታሰቢያ በዓል እንዲሆን ይደረግ ዘንድ በአክብሮት አሳስባለው።” [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]
አባ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
Message from His Holiness Abune Merkorios

ኢትዮጵያ በታሠሩ ጋዜጠኞች ብዛት በአፍሪካ አንደኛ ነች!!!

Netsanet Yibeltal's photo.Netsanet Yibeltal's photo.Netsanet Yibeltal's photo.Netsanet Yibeltal's photo.
Netsanet Yibeltal's photo.
ኢትዮጵያ እሥር ላይ የምትገኘውን ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙን፤ ቪየትናም ደግሞ የኢንተርኔት ፀሐፊዋን ወይም ብሎገሯን ታ ፎንግ ታንን እንዲለቅቁ ዩናይትድ ስቴትስ ጠየቀች፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቃል አቀባይ ጄፍ ራትካ ናቸው ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ይህንን የመንግሥታቸውን ማሳሰቢያ ያስተላለፉት፡፡

“መንግሥት የሌለው እዚህ ብቻ ነው!”

"ህወሃት የአገር ውስጥ አይሲስ" የአኢጋን አስተያየት ሰጪዎች

Slide3
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ስሞኑን በአሸባሪው አይሲስ የተወሰደውን አሰቃቂ ተግባር በማውገዝ በአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ላይ ያወጣው መግለጫ እንዲህ ይነበባል:-

“ሞት የዘመኑ ዕለት እንጅ የመነኑ ዕለት አይደለም” (መነገር ያለበት ቁጥር 8)

ቤልጅግ አሊ – ከፍራንክፈርት

“ከመሸ ተነሳሁ ከተፈታ በሬ፣
እደርስ አይመስለኝም ከእንግዲህ ሃገሬ።”

አገኘሁ እንግዳ
ጀርመን ፍራንክፈርት በሚገኘው የመድኃኒዓለም ቤተክርስትያን ውስጥ በሊቢያ ለተሰው ዜጎቻችን ጸሎተ-ፍትሃትና ከዛም ሰላማዊ ሰልፍ ሲደረግ ተገኝቼ ነበር። በደቡብ አፍሪካም ይሁን በሊቢያ በደረሰው ችግር ሁላችንም ሃዘን ገብቶናል። በዚህ ግፍ እንባ ያነባንም አለን። ከልባችንም ያዘንን ብዙ ነን። ቄሱ ትምህርት ሲሰጡ እነዚህ ለሃይማኖታቸው ሲሉ በወጣትነት የሞትን ጽዋ የተቀበሉ ሰማዕታት ትልቅ በረከት አግኝተውበታል ነው ያሉት። አዎ ለእምነት መሞት ትልቅ በረከት ነው። ጥንትም ለአመኑበት መሞት ታሪክ መስራት ነው፤ ሕይወትን በሌላ ፈርጅ መቀጠል ነው፤ ዳግም ትንሳዔ፣ ዳግም ልደት ነው። አሁንም ቢሆን የተቀየረ ነገር የለም።
ቤተክርስትያን ውስጥ ሆኜ ጸሎተ-ፍትሃቱን በመከታተል ላይ እያለሁ ለማነው የምናለቀሰው? ለምንስ ነው የምንላቀሰው? የሚለው ጥያቄ አዕምሮዬን አጣበበው። በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ችግሩ ባለ ብዙ ፈርጅ ነውና እያንዳንዳችን የችግሩን ምንጭ ማሰባችን አይቀርም። የስደቱ ምንጭ ሃገራችን ውስጥ ያለው ቅጥ ያጣ የዘረኝነት ሥርዓት መሆኑ ግልጽ ነው። ምንም እንኳን የምናለቅስው አሁን በወገኖቻቸን ላይ በደረሰው ችግር ቢሆንም የችግሩ መንስዔ ግን ሃገራችን ውስጥ ያለው አገዛዝ መሆኑን ልንዘነጋው አይገባም። ለዚህ አስከፊ ሥርዓት መቀጠል የእኛም አስተዋፅዖ ትንሽ አይደለም። እንዲውም ከፍተኛው ቦታ ሊይዝ ይችላል።

Wednesday, April 29, 2015

ልብሴን እንዳወልቅ ከታዘዝኩ በኋላ ራቁቴን በወንድ መርማሪዎች ፊት ስፖርት እንድሰራ እገደድ ነበር›› ትላለች የዞን ዘጠኟ ማህሌት ፋንታሁን፡፡

ጋሻው መርሻ .
ፈቃዱ የተባለ በአሁኑ ሰዓት ቂሊንጦ ታስሮ የሚገኝ የሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ አስተባባሪ የነበረ ወጣት ማዕከላዊ በተባለ ማጎሪያ ቤት ታስሮ በነበረበት ወቅት ራቁቱን እንዲቆም ይደረግ እንደነበር ተናግሯል፡፡ ‹‹ወንድ መርማሪዎች ፊት ለፊት ራቁቴን ስቆም ሀፍረት እንደሚሰማኝ የተረዱት መርማሪዎች ይድነቅህ ብለው ሴት መርማሪዎች ፊት ከ3 ሰዓት ላላነሰ ጊዜ እርቃኔን እንድቆም እገደድ ነበር›› ይላል ፈቃዱ በወቅቱ ስለነበረው ነገር ሲያስረዳ፡፡ እንደ ፈቃዱ ምስክርነት ከሆነ ሴት መርማርዎቹ ፈቃዱን ፊት ለፊታቸው አስቁመው ጌም ይጫዎታሉ፡፡ ይሳሳቃሉ፡፡ ‹‹እኔን ራቁቴን ከሶስት ሰዓት በላይ እስቁመው ደብድበው ይሸኙኛል›› ይላል የሕሊና እስረኛው ፈቃዱ፡፡

በአማራ ክልል የሚገኙ የብ.አ.ዴ.ን/ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ስጋት የወለደው ስብሰባ አካሄዱ

በአማራ ክልል የሚገኙ የብ.አ.ዴ.ን/ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ስጋት የወለደው ስብሰባ ሲያካሂዱ መሰንበታቸውን የደረሰን መረጃ አመለከተ፣እንደምንጮቻችን መረጃ።- የብ.አ.ዴ.ን. /ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ከፍተኛ አመራሮች ሚያዝያ 6 እና 7 2007 ዓ/ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት በተካሄደ ስብሰባ የአካባቢያችን ደህንንትና ሰላም ምን ይመስላል? የዚህ ክልል አለመረጋጋት ምክንያቱ ምንድን ነው? በሚሉና በሌሎችም ጉዳዮች ሲከራከሩ መቆየታቸውን የገለፀው መረጃው። በተለይ የትጥቅ ትግል የሚያካሂደው የአርበኞች ግንቦት 7 ድርጅት በመንግስታችን ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ሊያደርግ ሰራዊቱን በሁመራና አካባቢው ላይ አስጠግቷል በሚል ፍርሃት የወለደው ስብሰባ ማካሄዳቸውን ለማወቅ ተችሏል፣
እኒህ ከፍተኛ ባለስልጣኖች በስብሰባው። መንግስት በአርበኞች ግንቦት 7 ላይ ተመጣጣኝ እርምጃ ሊወስድ ስለሆነ በክልላችን ስለድርጅቱ የሆነ መረጃ ያመጣ ሰው ለማበረታቻ የሚሆን ሽልማት ይሰጠዋል በማለት ህብረተሰቡን በማታለል ስራ ላይ ተጠምደው እንደሰነበቱ ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ፣

ኢህአዴግ ሰማያዊን ለማውገዝ በየ አካባቢው የአደባባይ ስብሰባ መጥራቱ ተሰማ

ኢህአዴግ ሰማያዊ ፓርቲን ለማውገዝ ለነገ ሀሙስ አዲስ አበባ ውስጥ በየ ወረዳው በሚገኙ ሜዳዎች የአደባባይ ስብሰባዎችን መጥራቱን ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ህዝባዊ ንቅናቄ›› የተባሉት የአደባባይ ስብሰባዎች ባለፈው ሰልፍ ላይ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ›› ፈጥረዋል በሚል በገዥው ፓርቲ እየተከሰሱ ያሉትን በተለይም ሰማያዊ ፓርቲን ለማውገዝ የተጠሩ ናቸው ተብሏል፡፡ በህዝባዊ ስብሰባዎቹ ከካድሬዎች ውጭ ተቃውሞ የሚያሰሙ ኢትዮጵያውያን እንዳይገኙ የኢህአዴግ አባላት ብቻ እንዲገኙ በደብዳቤ እንደተጠሩ ታውቋል፡፡

መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስ በኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ እርምጃ ለማውገዝ በጠራው ሰልፍ ላይ ለጉዳዩ ትኩረት አልሰጠም በሚል ተቃውሞ ከገጠመው በኋላ ሰማያዊ ፓርቲ ከተቃውሞው በስተጀርባ እንዳለበት ከመክሰሱም ባሻገር በተለያዩ አካባቢዎች በጠራቸው ሰልፎች ሰማያዊን ሲያወግዝ ተስተውሏል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ በበኩሉ ኢህአዴግና የመግንስት ተቋማት ስሙን ከማጥፋት ካልተቆጠቡ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት እንደሚወስደውና ከዚህም ባሻገር ሌሎች ተከታታይ እርምጃዎችን እንደሚወስድ በመግለጽ ህዝብ ከጎኑ እንዲቆም ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

Tuesday, April 28, 2015

አልሸባብ አይሲስን ሊቀላቀል ነው

ተጨማሪ የሽብር ስጋት በኢትዮጵያ

ial

በሶማሊያ የሽብር ተግባራትን በመፈጸም የሚታወቀው አልሸባብ ደመኛና አረመኔውን አይሲስን ሊቀላለቀል መሆኑ ተሰማ፡፡ አገራችንን በተጨማሪ የሽብር ስጋት ውስጥ እነደሚጥላት ተገምቷል፡፡
የሶማሊያን ስፊ ግዛት የሚቆጣጠረው አልሸባብ የማእከላዊ ስልጣኑን ካጣ ወዲህ በደረሰበት ወታደራዊ ኪሳራ የአለም አቀፍ አሸባሪው አልቃይዳ ክንፍ በመሆን እያካሄደ ባለው የደፈጣ ውጊያ ሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት ርቋት በንጹሃን ደም የታጠበች መንግስት አልባ ጦር ሜዳ ከሆነች ከሁለት ዓስርት አመታት በላይ አስቆጥራለች።

Monday, April 27, 2015

ሰማያዊ ፓርቲ መንግስት የከፈተበትን የጥላቻ ዘመቻ በአስቸኳይ እንዲያቆም አሳሰበ

መንግስት ሊቢያ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ላይ አሰቃቂ እርምጃ የወሰደውን አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም ራሱ በጠራው ሰልፍ ላይ ከህዝብ የገጠመውን ተቃውሞ ተከትሎ ሰማያዊ ላይ የጥላቻ ዘመቻ እንደከፈተበትና ይህንን የጥላቻ ዘመቻውን እንዲያቆም ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳስቧል፡፡Semayawi Parties latest press conference
መንግስት የጠራውን ሰልፍ ከማንም ተቃዋሚ ፓርቲ ቀድሞ የደገፈው ሰማያዊ እንደሆነ የገለጸው መግለጫው ‹‹የዜጎችን ስቃይ ለፖለቲካ ፍጆታ ማዋል የፈለገው ህወሓት/ኢህአዴግ ሰማያዊ ፓርቲ በወገኖቻችን ላይ ለሚደርሰው በደል መፍትሄ እንዲሰጥ መወትወቱ፣ የፖለቲካ ልዩነታችንን ወደ ጎን አድርገን በሰልፉ ላይ መገኘታችን እንዳላስደሰተው ከሰልፉ ቀን ጀምሮ በፓርቲያችን ላይ የተከፈተው ዘመቻ ትልቅ ማሳያ ነው፡፡›› ብሏል፡፡
ከሰልፉ ማብቃት ጀምሮም ጉዳዩን ገና ፖሊስ ሳይመረምረው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ሚኒስትር ሬድዋን ሁሴን ሰማያዊ ፓርቲ ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት እየጣረ ነው በሚል መወንጀላቸውን፣ የመንግስት ሚዲያዎች ሰማያዊ ፓርቲ ሁከትና ብጥብጥ ሊያስነሳ ነው ብለው ሚዛናዊ ያልሆነ መረጃ ማሰራጨታቸውንና አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም ተብለው በተጠሩ ሰልፎችም ሁሉ መንግስት ሰማያዊ ፓርቲ ለመቃወም እየተጠቀመባቸው መሆኑን መግለጫው አትቷል፡፡

Sunday, April 26, 2015

የወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ለኢትዮጲያና ለሕዝቧ ክብር ስለማይመጥን ይወገድ!!!!

ተስፋዬ ዘነበ(ኖርዌይ ስታቫንገር)
tplf and isis
የረጅም ጊዜ የነፃነት ታሪካችን በመቻቻልና በመከባበር አብሮ የኖረው ህብረታችን፣ ለሃገራችን  ነፃነት ያደረግነው ተጋድሎ፣ ኢትዮጲያን እንደ ታላቅ  ሉአላዊት ሃገር በጠንካራ መሰረት ላይ ያቆማት ምህተ አመታትን ያስቆጥረ ጠንካራ ማንነታችን ነው፡፡ በዚህ ባለንበት ሃያ አንደኛው ክ/ዘመን የኛን አባቶች የነፃነት ተጋድሎ የነፃነት ታሪክ ተምሳሌት አርገው በኛ ፈር ቀዳጅነት እንደ ሃገር ሉአላዊነታቸውን የተቀዳጁ ሃገራት የተቀዳጁትን ሃገራዊ ክብር በተግባር ሲመሰክሩ፣ እኛ  ለነፃነት የመጀመሪያዎቹ፣ እኛ ቀደምት የነፃነት ፋና ወጊዎቹ፣ እኛ ስለ ሌሎች በባእዳን ተፅእኖ ስር ለወደቁ የአፍሪካ ሃገራት ተሟጋቾች፣ እኛ ስለ ነፃነት ትግል አስተማሪዎችና ለጋሾች፣ መከታዎች፡ ክብራችንን የሚያስጠብቅ የቀደመ ማንነታችንን የሚያስጠብቅ፣ ለሃገራችን ሉአላዊነት የሚታገል፣ ታፍሮና ተከብሮ ለኖረ ኢትዮጲያዊ ማንነታችን ቀናኢ ሆኖ የሚሟግርትልና በአንድ ኢትዮጲያ ጥላ ስር የሚሰበስበን የኛ የሃገራችን የሕዝባችን የምንለው ለዚች ታላቅ ሃገር የሚመጥን፣ ለሃገርና ለሕዝብ ታማኝ የሆነ እንዲውም ሃገሩና ሕዝብን የሚወድ አስተዳደር(ስርዓት) አጥተን ለመስማትም ሆነ ለማየት የሚዘገንን ግፍና ሰቆቃ በውስጥም በውጪም ስንቀበል እንሆ ዘመናት ተቆጠሩ፡፡

ሽብርን በማሸበር!!

ሰማያዊ ፓርቲ “ሊታረድ ነው”

tplf and isis


* ሕዝብ ዋስትናና መተማመን አጥቷል
ረቡዕ ዕለት ኢህአዴግ በጠራው ሰልፍ ዜጎች ስሜታቸውን ሲያንጸባርቁ የተሰጣቸው ምላሽ ሽብርን በአሸባሪነት አመጣጥኖ የመመለስ አይነት እንደሆነ ተጠቆመ፡፡ የሰላማዊ ሰልፉ አጠቃላይ ገጽታና የሕዝብ ስሜት በአገሪቱ የዋስትና ማጣት ስሜት እየገዘፈ መሄዱን የሚያሳይ ሆኗል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ሊታረድ ነው፤ በሰሜን አሜሪካ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ባሉት ይልቃል ላይ እዚያው እንዲቀሩ ተጽዕኖ ይደረጋል ተብሏል፡፡

Saturday, April 25, 2015

“የችግሩ መሰረታዊ ምንጭና መፍትሔው ፓለቲካዊ ነው’!! – ኤርምያስ ለገሰ

“የችግሩ መሰረታዊ ምንጭና መፍትሔው ፓለቲካዊ ነው’!! –  ኤርምያስ ለገሰ
ሰሞኑን በኢትዬጲያውያን ላይ የመከራ ዶፍ እየዘነበ ነው። ይህ የድቅድቅ ጨለማ ናዳ ባስከተለው አደጋ የተፈጠረው ቁጭትና መብከንከን ከቃላት በላይ ሆኗል። በኢትዬጲያውያን ዘንድ ከዚህ ውጭ የመተከዣ አጀንዳ ያለ አይመስልም። እንባ እንደ ጐርፍ እየወረደ ነው። የእናቶቻችን ደረት በእሳት የተለበለበ እስኪመስል ድረስ እየተደለቀ ነው። ወጣቶቻችን ከአረመኔዎች ጋር ግብግብ እየገጠሙ ነው። በመንገድ፣ በትራንስፓርት፣ በምግብ ቤት፣ በስራና በተለያየ አጋጣሚ የምናገኛቸው የባእድ አገር ሰዎች ሳይቀር የሀዘናችን ተካፋዬች መሆናቸውን እየነገሩን ነው። ነግረውን ብቻ አያቆሙም ። 

Friday, April 24, 2015

እየተስተዋለ – ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

እነዚህ ወገኖቻችን ሰማዕታት ናቸው፡፡ ሃይማኖታቸውን አንለውጥም ብለው የተሠዉ፡፡ ‹ስደተኛ ኢትዮጵያውያን› የሚለውን አገላለጽ ነፍሴ ትጸየፈዋለች፡፡ ከአኩሪው የሰማዕትነት ተግባራቸው በላይ ስደተኛነታቸው ለማጉላት ስለሚያኮበኩብ፡፡ ሰው በሀገሩ ቢኖር፣ ቢሠራና ቢከብር የመጀመሪያ ምርጫው ነው፡፡

ኢትዮጵያውያኑ እና ኤርትራውያኑ በአይ ኤስ በግፍ ሲቀሉ በግድ እንዲያይ የተደረገው ታዳጊ ይናገራል (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ16 ዓመቱ ኤርትራዊ ስደተኛ ናኤል ጎይቶም የኤይ ኤስ ታጣቂዎች ኢትዮጵያውያኑን እና ኤርትራውያኑን በግፍ ሲቀሉ እና ሲረሸኑ እንዲመለከት መደረጉን ይናገራል።

Eritrean teen migrant forced to witness Libya massacre
A 16-year-old Eritrean migrant who escaped captivity under the Islamic State (Isis) in Libya has exclusively told IBTimes UK that the jihadists forced him to watch the beheading and shooting of Ethiopians and Eritreans | ኢትዮጵያውያኑ እና ኤርትራውያኑ በአይ ኤስ በግፍ ሲቀሉ በግድ እንዲያይ የተደረገው ታዳጊ ይናገራል
(ኤፍ.ቢ.ሲ) የ16 ዓመቱ ኤርትራዊ ስደተኛ ናኤል ጎይቶም የኤይ ኤስ ታጣቂዎች ኢትዮጵያውያኑን እና ኤርትራውያኑን በግፍ ሲቀሉ እና ሲረሸኑ እንዲመለከት መደረጉን ይናገራል።

የሃዘኑ ድባብ በዱላ ታጅቦ…

ክንፉ አሰፋ
Ethiopia police brutality at Meskel Squareየሃዘኑ ድባብ ከመብራቱ መቆራረጥ ጋር ተዳምሮ ጨለማውን አብሶታል። የአሁኑ መብራት መቋረጥ ግን ከወትሮ ፈረቃ ለየት ያለ ነው። ሆን ተብሎ የተደረገ ይመስላል። ከጥቂት ስፍራ በስተቀር ሁሉም ቦታ በአንዴ እንዲጠፋ ነው የተደረገው። ከሬድዋን ሁሴን እና ከሃይለማርያም የቴሌቭሽን ዲስኩር በኋላ ሃገሩ ሁሉ ጨለማ እንዲሆን አደረጉ። ይህንን ለማድረግም በቂ ምክንያት ነበራቸው። ሃዘን ያልወጣለት ህዝብ አደባባይ ወጥቶ በአረመኔ ወታደሮች ሲቀጠቀት በማህበራዊ ድረ-ገጽ እንዲታይ አልተፈለገም። ህዝቡ እርስበርስ መረጃ እንዲለዋወጥ መፍቀዱም አደጋ አለው። ስልኩም ጠፋ!
ለጥቂት ጉልበተኞች ግን ይህ መብራት ከቶውንም አይጠፋም። ግዜው እስኪደርስ፣ የሚመኩበት ጉልበታቸው እስኪፈታ ድረስ ይበራል። እስከዚያው ብዙሃኑ በጨለማ ይኖራሉ።
የአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ንግግር ግን ከቴድሮስ አድሃኖም ጋር ትንሽ የሚጣረዝ ይመስላል። ድህነታችን ለስደት እንደዳረገን ነበር ሃይለማርያም በአደባባይ ይናገሩ የነበረው። ተሳስተው ነው? ወይንስ በጥድፍያው ምክንያት አልተናበቡ ይሆን? ልማታዊ መንግስት ድህነት የምትለዋን አይጠቀምም።

ብሄራዊ ሃዘንን ወደ ብሄራዊ እምቢተኝነት

በያዝነው ሰሞን የሚሰሙ ዜናዎች፣የሚታዩ ምስሎች፣የሚደመጡ የሲቃ ድምጾች አጥንት ድረስ የሚዘልቁ ብሄራዊ ቁስል ሆነውብናል። ፳፬ ዓመት በኢትዮጵያውያን ጀርባ የተሰበቀውን ፍላጻን በመሸሽ ስደትን እንደ አማራጭ የወሰዱ ወጣቶች የዓሳ ነባሪ የዕለት ከዕለት ቀለብ ሆነዋል፣ የደቡብ አፍሪካን ጫካዎች ሲያቋርጡ በአውሬ ተቆርጥመዋል፣ከሰባራ ጀልባና ከመንገድ ቀማኛ የተረፉት ባካባቢ አገራት ለመድረስ የቻሉትም በጎማና በቤንዚን ከነህይወታቸው ተቃጥለዋል በማጅራታቸውም ታርደዋል።addis ababa protest18
የዋሽንግተን እና አካባቢው የጋራ ግብረሃይል ባጠቃላይ ኢትዮጵያ ሆይ ፈጣሪ ያጽናሽ፤ ኢትዮጵያ ሆይ የልጆችሽ ደም ለአገር ተንሳዔ ያድርግልሽ ከማለት ሌላ ቋንቋ የለንም። ሐዘናችንን ስንገልጽ ግን ነገ የሚወጣውን የነጻነት ብርሀን ከቅርብ ርቀት በተስፋ እያየነው ነው። የኢትዮጵያ ወጣት ሆይ …
ዘረኝነትን ሸሽተህ ወደ ተሳለው ካራ ወደ እሚንቀለቀለው እሳት፣ እሚሰምጠው ጀልባ ላይ ከመሳፈር ነጻነት ያሳጣህን አረመኔ ዘረኛ ስርዓት እዛው በአገርህ ሜዳ ተናንቀህ ጥለህና ወድቀህ ነጻነትህን ብታውጅ የስደት እና የውርደት ምንጭ የሆነውን ከምንጩ ታደርቀዋለህ። መደራጀትም ምትሐት አይደለም ከየአካባቢህ የጎበዝ አለቃ መምረጥና መናበብ እንደሚቻል ጠንቅቀህ እወቅ። የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ …

Thursday, April 23, 2015

የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያቀረቡት አስቸኳይ ጥሪ

def-thumbየተከበራችሁ ወገኖቼ፤ ከሰላሳ በላይ የሆኑ ወገኖቻችን አይ ሲስ በተሰኘ ህሊና ቢስ፣ ፀረ-ሰው እና ፀረ-ስልጣኔ ቡድን በሊቢያ በአሰቃቂ ሁኔታ የመገደላቸው መርዶ ከትናንት ወዲያ ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓም ደርሶን ኢትዮጵያዊያን በያለንበት በመሪር ሀዘን ውስጥ ነን። ዛሬ “እግዜር ያጥናህ” ወይም “እግዜር ያጥናሽ” የሚባል ሰው የለም። ሁላችንም ሀዘንተኞች ነን። ካጣናቸው ቁጥራቸው በብዙ እጥፍ የሚበልጥ ወገኖቻችን አሁንም በአራዶች መዳፍ ውስጥ መሆናቸው ሀዘናችን እጅግ የበረታ ያደረገዋል። ቁጥራቸው በትክክል የማይታወቅ ሆኖም በሺህ የሚገመቱ ኢትዮጵያዊያን ዛሬም ሊቢያ ውስጥ ናቸው። በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን አሁንም ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ናቸው። ሌሎች በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ደግሞ በየመን ከሰማይም ከምድርም በቦንብና በጥይት እየተማገዱ ነው።
ለምንድነው ኢትዮጵያዊያን እንዲህ እሳት ውስጥ ለመማገድ የምንደፍረው? መልሱ ግልጽ ነው። አገር ውስጥ ተስፋ የለም፤ ወያኔዎች ተስፋችንን አጨለሙት። ከሳዉዲ በመከራ የተመለሱ ወንድሞቻችን ናቸው በሊቢያ በኩል ለመሰደድ ሲሞክሩ በአይ ሲስ ተይዘው የታረዱት። ወያኔዎች አገራችንና ክብራችን ዘረፉን። ወያኔዎች ስብዕናችንን ገፈፉን።

Wednesday, April 22, 2015

የምትሞትለት ሰው ከሌለህ አንተ ሞተሃል ( ሄኖክ የሺጥላ )

የምትሞትለት ሰው ከሌለህ አንተ ሞተሃል ( ሄኖክ የሺጥላ )
የምትሞትለት ሰው ከሌለ ለምን ትኖራለህ ። ለሰው እና ለነጻነት ሲሉ መሞት ሁሌም ክብር ነው ። ይህንን ሶቅራጥስ አድርጎታል ፣ ክርስቶስ አድርጎታል ፣ ይስሐቅ ለጥቂት የተረፈው ከሰማይ በወረደለት በግ እንጂ እሱም አባቱን ለመሰማት ሲል ለጥቂት አድርጎት ነበር ። ቴዎድሮስ አድርጎታል ፣ አሰፋ ማሩ አድርጎታል ፣ አስራት ወልደየስ አድርጎታል ። አሳፋሪው ነገር
ለሰው ሲሉ መሞት ሳይሆን ፣ ለመኖር ሲሉ ሰው መግደል ነው ። ለሆድ ሲሉ መግደል ብርቅ አይደለም ፣ ሰው ይበላ ዘንድ መሞት ግን ተአምር ነው ! ሞትን አስፈሪ ያደረገው ፣ ነብስን የተሸከማት ኗሪው ነው ። ለጀግና ሰው ፣ የሌሎች መኖር ከሱ መኖር ለሚበልጥበት ሰው ፣ ሞት ገለባ ነው ።
በባህላችንም ሆነ በማንኛውም የሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የሚታወሰው አንዲት ስንጥር ሳይነካው ፣ የግንብ ውስጥ ስዳሃርታ ( የግቢ ውስጥ ቡድሃ ) ሆኖ የኖረና የሞተ ሰው አይደለም ፣ ታሪክ ለሆዳቸው ሲሉ ህዝባቸውን የጨቆኑ ፣ ህሊናቸውን የሸጡ ፣ ሀገራቸውን ያዋረዱ ፣ ሆድ አደሮች መዘክር አይደለም ። ይልቁንም ታሪክ ከነዚህ ሆድ አደሮች ጋ ታግለው ፣ ወጥተው ፣ ወርደው ፣ ከስተው ፣ ጠቁረው ፣ አይሆኑ ሆነው ፣ ከሰውነት ጎዳና ወጥተው ፣ ለራሳቸው አንዳችም ( ቅንጣት ) ታህል ቅሪት ሳያካብቱ ይወታቸውን ለሰው ልጅ ነጻነት ፣ ለሀገራቸው አንድነት ፣ ለህዝባቸው ክብር አሣልፈው የሰጡ ባለታሪኮች አምድ ነው ።
እንደ ጥያቄ የምትሞትለት ከሌለ ለምን ትኖራለህ ? የምታየው በሙሉ የሚያስፈራህ ፣ የምያንቀጠቅጥህ ፣ አንገትህን የምያስደፍው ከሆነ ፣ እወቀው መኖር ካቆምክ ቆይተሃል ። ሰውነት የሚለካው በቁሳዊ በረከትህ ፣ ወይም በሥጋ ክብደትህ፣ ወይም በዓለማዊ እውቀትህ አይደለም ። ሆኖም አያውቅም ። እንኳንስ በዓለማዊ በመንፈሳዊው እውቀትህ ሰውነት አይለካም ። የሰውነት መለኪያው ፣ ሰው ነኝ ባልከው ማንነትህ ላይ ያካበትከው እውነትህ ነው ፣ የተሸከምከው ኃላፊነት እና የተገበርከው መልካም ግብር ነው የሰውነት መለኪያው ። የጀግንነት መለኪያው 17 ዓመት ጫካ መቆየት ፣ ደርግን መደምሰስ አይደለም ። የጀግንነት መለኪያው ፣ ሕይወት ለመልካም ነገር አጋጣሚ በሰጠቻት ሕይወትህ ውስጥ ምን ያህል ቁም ነገር ሰራህባት የሚለው ነው ። 

Tuesday, April 21, 2015

“ሕገወጦቹ!”

“ሕገወጦቹ!”

balcha-and-eyasu


አይሲስ አሰቃቂ ግድያ የፈጸመባቸው ወገኖቻችን ቤተሰቦች መርዶ ሰምተው ሃዘን ተቀምጠው ባሉበት ወቅት ኢህአዴግና “የፌስቡክ የልማት አርበኛ ሚኒስትሮቹ” “ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን እያጣራን፤ እስካሁን አላረጋገጥንም” እያሉ ያላግጡ ነበር፡፡

በአዲስ አበባ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፣ ሰልፈኛው በሊቢያ የኢትዮጵያውያንን መገደልና መንግስት ያሳየውን ቸልተኛነት በመቃወም ላይ ነው

**** ሰበር ዜና፣ ሰልፈኛው የኢቲቪ/ ኢብኮ ጋዜጠኞችን ደበደበ ****

(ነገረ-ኢትዮጵያ) ከደቂቃዎች በፊት የኢቲቪ/ ኢብኮ ጋዜጠኞች በለቀስተኞች መደብደባቸው ተሰምቷል፡፡ የኢትቪ /ኢብኮ ጋዜጠኞች ለቅሶ ቤት ውስጥ ቀረጻ አድርገው ሲመለሱ ‹‹ሌቦች እናንተ ልታስተላልፉት አይደለም፡፡ ስለ እኛ ምን አገባችሁ?›› ተብለው እንደተደበደቡ ለማወቅ ተችሏል፡፡
—————————
Addis Ababa protest against Ethiopian government
በሊብያ አሸባሪዎች በኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸሙትን አሰቃቂ ግድያ ለማውገዝና መንግስት ነኝ ባዩ ወያኔ ያሳየውን ቸልተኛነት ለመቃወም በአዲስ አበባ ህዝቡ ነቅሎ አደባባይ ወጥቷል።

Tuesday, April 14, 2015

8 የፖለቲካ ፓርቲዎች ራሳቸውን ከምርጫው ሊያገሉ እንደሚችሉ አስጠነቀቁ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

በወላይታ ዞን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ምክር ቤት ዕጩዎችን ያቀረቡ 8 የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዞኑ እየደረሰባቸው የሚገኘው አፈና እና በደል መፍትሄ ካልተሰጠው ራሳቸውን ከመጭው ግንቦት 2007 ዓ.ም ምርጫ ራሳቸውን ሊያገሉ እንደሚችሉ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለዞኑ ምርጫ ማስተባበሪያ፣ ለምርጫ ቦርድና ሌሎች የመንግስት ተቋማት ባስገቡት ደብዳቤ አስጠንቅቀዋል፡፡

ከመጭው ምርጫ ራሳቸውን ሊያገልሉ እንደሚችሉ ያስጠነቀቁት የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰማያዊ፣ የኢትዮጵያ ፍትሕና ዴሞክራሲ ሃይሎች ግንባር (ኢፍዴሃግ)፣ የወላይታ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ወሕዴግ)፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ (አትፓ)፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)፣ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) እና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ (አንድነት) ናቸው፡፡
ማስጠንቀቂያውን ያቀረቡት ፓርቲዎች ለምርጫ ምቹ የሆነ አጋጣሚ እንዳለ በሚዲያ የሚገለፀው ትክክል እንዳልሆነ፣ ያለ ገደብ መብት የሰጠው ገዥው ፓርቲ ሰሆን በእነሱ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጫና እና በደል እየተፈፀመባቸው እንደሚገኝ በደብዳቤያቸው ገልጸዋል፡፡ ፓርቲዎቹ አክለውም ምህዳሩ እጅግ የጠበበ መሆኑን በየጊዜው አቤቱታቸውን ለምርጫ ክልሎችና ለጋራ ምክርቤት ቢያቀርቡም ምንም አይነት ምላሽ እንዳላገኙና በአባላቶቻቸው ላይ የሚፈፀመው በደል ከአቅማቸው በላይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

Monday, April 13, 2015

የአክራሪዎች፣ የተስፈንጣሪዎችና የአሸባሪዎች ዘመን

ይሄይስ አእምሮ (አዲስ አበባ)
ወቅቱ ለክርስቲያኖች የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል ሰሞን እንደመሆኑ በዓሉ የሚመለከታቸውን አንባቢ ወገኖቼን “እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው [በሰላም] አደረሳችሁ” ማለትን እወዳለሁ፡፡ የደርግ ጊዜ አንድ ትዝታ አለኝ፡፡ በአብዛኛው በሀገር ወዳድ ደናቁርት የታጨቀው የደርግ መንግሥት ሠለጠንኩ ብሎ ሃይማኖተቢሱንና ሃይማኖተኝነትን ከልካዩን የሶሻሊዝም ሥርዓት ካወጀባት ጠማማ ዕለት ጀምሮ በዓል በመጣ ቁጥር በተለይም የአብዮቱ በዓል በሚከበርበት ወቅት “እንኳን ደረሳችሁ” ይል ነበር – ያ ለአገራችን ባዕድ የነበረ የአገዛዝ ሥርዓት አንዲት ፊደል ላይ እንዲያ ይጨነቅ የነበረው፣ ሰው ለበዓሉ የደረሰው በራሱ እንጂ በፈጣሪ እንዳልሆነ ለማጠየቅ ነበር፤ የሥርዓቱ አቀንቃኞች በአብዛኛውና በግልጽ ይዞታቸው ሶሻሊስትና ኮሚኒስት እንጂ የሃይማኖት ሰዎች አልነበሩም – አንዳንዶች አምልኮታቸውን በኅቡዕ ያከናውኑ እንደነበርና ልጆቻቸውን ሣይቀር በድብቅ ክርስትና ያስነሱ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ በመሠረቱ አንድ ሰው ምንም ዓይነት እምነት ላይከተል ይችላል፡፡ መብቱም ይመስለኛል፡፡ ነገር ግን ሃይማኖት አልባነትን በግድ መንግሥታዊ ሥርዓት ውስጥ በማጫፈር በእምነትና በሃይማኖት ጸንቶ የኖረን ሕዝብ በአንዴ እግዜርን ወይም አላህን ወይም የምታመልከውን ሌላ መንፈሣዊ አካልን ክደህ ኮሚኒስት ሁን ማለት የደርግን ብልህነት ሣይሆን ጅልነት የሚያሣይ ነበር – ሠለጠነች ቢሏት ጊዜ የባሏን መጽሐፍ ያጠበችውን ሴት ዓይነት ጅልነት፡፡ መጨረሻው ባለማማሩ ይከተለው የነበረውንም የአካሄድ ሥርዓት አይረቤነት በእግረ መንገድ መረዳት አይከብድም፡፡ እንዲያው ትዝ ብሎኝ ነው፡፡
ርዕሴን በእንግሊዝኛ ብጽፈው ኖሮ “The Age of Terrorists, Extremists and Deviants” በሚል እንዲነበብ አደርገው ነበር፡፡ ያለንበትን ዘመን ከየአቅጣጫው ስንቃኘው ጥቂት የማይባሉ አክራሪዎች፣ ተስፈንጣሪዎችና አሸባሪዎች ዓለማችንን እያተረማመሱ እንደሚገኙ መገንዘብ አያስቸግርም፡፡ ሌላውን ዓለም ለአሁኑ እንተወውና ወዳገራችን ተስፈንጣሪዎችና ምናምንቴዎች እንመለስ፡፡ በነሱ ነውና መቅኖ አጥተን የቀረነው – “ትንቢትሰ ይቀድሞ ለነገር” የምትለዋን ሐረግ እንድታስታውሱልኝ ግን ልማጠን፡፡

Friday, April 10, 2015

የመን ለሚገኙ ወገኖቻችን እንድረስላቸው!


pg7-logoየመን የሚገኙ በመቶ ሺዎች የሚገመቱ ኢትዮጵያዊያን አደጋ ላይ ናቸው። ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው የመብት አፈና፣ ሥራ አጥነት፣ ችጋርና ተስፋ ማጣት ለመሸሽ የራሳቸውንና የዘመዶቻቸውን ጥሪት አሟጠው ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ለሚሰደዱ ወገኖቻችን የመን መሸጋገሪያቸው ናት። ዛሬ የህወሓት ወዳጅ የሆኑም ያልሆኑም የየመን አምባገነን ገዢዎች እርስ በርሳቸው እየተላለቁ፤ ከምድር እሳት እየነደባት መሆኑ ሳያንስ ከሰማይም እሳት እየዘነበባት ነው።
እንኳን አሁንና በሰላሙም ጊዜ የመን ለኢትዮጵያዊያን ምቹ አልነበረችም። በበረሀ ጉዞ የዛሉ እግሮች፤ ከአቅማቸው በላይ በጫኑ ታንኳዎች ባህር በመሻገር የታወኩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች የመን ጠረፍ ላይ የሚጠብቃቸው ተጨማሪ እንግልት፣ ስቃይና መደፈር ነበር። የመን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ሕይወት እኛ ኢትዮጵያዊያን እንደ አገር የደረስበት አሳፋሪ ደረጃ መገለጫ ሆኖ ቆይቷል። በየመን፣ ወገኖቻችን ተደብድበዋል፤ አካላቸው በስለት ተዘልዝሏል፤ ሴቶች ብቻ ሳይሆን ወንዶችም ተደፍረዋል፤ ጓዳችን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ታፍኖ ለህወሓት ተላልፎ ተሰጥቶብናል። አሁን የመን እየነደደች ነው።

መነበብ ያለበት-የወቅቱ የኢትዮጵያ ወጣት እና ህወሓትን የማስወገድ ትግል (ታደሰ ብሩ)

አገራችን ኢትዮጵያ በሕዝብ ብዛት ከአፍሪቃ ሁለተኛ ስትሆን በተባበሩት መንግሥታት መመዘኛ “ወጣት” ተብሎ በሚጠራው የኅብረተሰብ ክፍል ብዛት ግን አንደኛ ነች። እርግጥ ነው ወጣነት በእድሜ ብቻ የሚገለጽ የኅብረተሰብ ክፍል አይደለም።  የሚከተለው የወጣት ትርጉም ሰፋ ያለ  ተቀባይነት ያለው ይመስለኛል።
ወጣት፣ በማኅበረሰቡ አንኳር ጉዳዮች ላይ እየወሰነ ባለው “አዋቂ” ተብሎ  በሚጠራው የኅብረሰተሰብ ክፍል እና ማኅበራዊ ፋይዳ ያላቸውን ውሳኔዎች ለመስጠት ገና ባልተዘጋጀው ሕፃን መካከል ያለ የኅበረተሰብ ክፍል ነው።
በዚህ ትርጓሜ መሠረት ወጣትነት የማኅበራዊ ግኑኝነት መገለጫ ጽንሰ ሀሳብ ነው። ይህ ማኅበራዊ ግኑኝነት ወደ እድሜ እንመዝረው ስንል ችግር ውስጥ እንገባለን፤ ምክንያቱም ወጣቱ ወደ አዋቂነት የሚሸጋገርበት ጊዜ እንደየአገሩ ባህሉና እንደ እድገቱ ይለያያል። በዚህም ምክንያት ነው የወጣትነት የህግ ትርጓሜዎች በየአገሩና ባህል የተለያዩ የሆኑት። ለምሳሌ፣ የተባበሩት መንግሥታት ወጣት ማለት “እድሜው 15 እስከ 24 ዓመታት ድረስ ያለው ሰው ነው” ሲል ይተረጉማል፤ ይሁን እንጂ የራሱ አካል የሆነው  UN Habitat “ወጣት ማለት እድሜው 15-32 ዓመት ያለው ሰው ነው” ይላል።  በአገሮች ትርጓሜ መካከል ያለው ልዩነት ደግሞ በጣም የተዘበራረቀ ነው። ዩጋንዳ ውስጥ እድሜው 12-30 የሆነ ዜጋ ወጣት ሲሰኝ ጎረቤትዋ ኬንያ ውስጥ 18-35 ነው። ስለዚህም አንድ የ16 ዓመት ወጣት ዩጋንዳዊ  ድንበር ተሻግሮ ኬኒያ ሲገባ ሕፃን ይሆናል፤ አንድ የ 32 ዓመት ኬንያዊ ወጣት ዩጋንዳ ሲሻገር ጎልማሳ ይሆናል።  ከአፍሪቃ ዝብርቅርቅ የወጣት ትርጓሜዎች ለአብነት ጥቂቶቹን ላንሳ: ሞውሪሸስ 14-29፣ ደቡብ አፍሪቃ 14-29፣ ናይጄሪያ 18-35፣ ጂቡቲ 16-30፣ ኬኒያ 18-35።
በ2004 ዓም የወጣው የኢትዮጵያ መንግሥት የወጣቶች ፓሊሲ ከ15 -29 ዓመታት ውስጥ የሚገኝን ኢትዮጵያዊን ዜጋን ወጣት ብሎ ይተረጉመዋል። በወጉ የሚያስተናግደው አላገኘም እንጂ ይህ ፓሊሲ በወጣበት ወቅት የኢትዮጵያ የወጣት ትርጓሜ እንደ ኬኒያና ናይጄሪያ 18- 35 መሆን ይገባዋል የሚል ሀሳብ ቀርቦ ነበር። የወጣቱ ከፓለቲካና ማኅበራዊ ውሳኔዎች መገለል መብዛትን በማጤን የላይኛው ጣራ እስከ 39 ከፍ ማለት አለበት የሚል ክርክርም ነበር። በበኩሌ ሥራአጥነትና ዘረኛ የህወሓት ፓሊሲ ያስፋፋው መድልዎና መገለል የወጣት የእድሜ ማዕቀፍ እንዲሰፋ አድርጓል ብዬ አምናለሁ። አርባ ዓመት አልፏቸው ከወላጆቻቸው ጥገኝነት ያልወጡ “ወጣቶች” ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ነው። እኔ በዚህ አጭር ጽሁፍ ውስጥ ስለወጣት ስናገር እድሜው በ 18 እና 39 ዓመታት መካከል ያለውን ዜጋ እያሰብኩ ነው።

Thursday, April 9, 2015

በሳምንታዊዋ ‹‹ፍቱን›› መጽሔት ላይ፣ ከሰርካለም ፋሲል ጋር ያደረግነው አጭር ቃለ-ምልልስ (ኤልያስ ገብሩ )

‹‹የማምነው ነገር፣ የሀገሪቷ ችግር ሲፈታ፤ እስክንድርም አብሮ እንደሚፈታ ነው››
‹‹የስደት ህይወት ሁሉንም ነገር ከዜሮ ያስጀምርሃል››
‹‹የእስክንድር ፅናት እና ብርታት ከፈጣሪ የተሰጠው ፀጋ አድርጌ እመለከተዋለሁ››
Serkalem Fasil ‹‹በሀገራችን ጉዳይ ላይ ለመሳተፍ የግድ ፖለቲከኛ መሆን አይጠበቅብንም›› ሰርካለም ፋሲል (ጋዜጠኛ)
በአንባቢያን ዘንድ ታዋቂ የነበሩት ‹‹አስኳል››፣ ‹‹ሚኒሊክ‹‹ና ‹‹ሳተናው›› ጋዜጦች አንዷ አሳታሚ ነበረች፡፡ የ97 ምርጫን ተከትሎ በተፈጠረ ግርግር ለእስር ከተዳረጉት ጋዜጠኞች እና አሳታሚዎች መካከልም አንዷ ነች – ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል፡፡ በሀገራችን የግል ፕሬስን በመጀመር ፈር ቀዳጅ የሆነው የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባለቤት ሰርካለም ልጃቸው ናፍቆትን የወለደችው በቃሊቲ እስር ቤት መሆኑ ይታወቃል፡፡
ከእስር ከተለቀቁም በኋላ እስክንድር የጋዜጣ ፍቃድ ቢከለከልም ሀገሬን ጥዬ አልመሄድም በሚል አቋሙ በመጽናቱ ጽሑፎቹን በተለያዩ በውጭ ሀገር ባሉ ድረ-ገጾች ላይ ማቅረብ ቀጠለ፡፡ በሀገር ውስጥ የግል ጋዜጦች ላይም ቃለ-ምልልስ በማድረግ የግል ሀሳቡን በድፍረት በማቅረብ ላይ ሳለ ነበር በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥሮ መስከረም 03 ቀን 2004 ዓ.ም ለእስር የተዳረገው፡፡ በፍርድ ሂደትም 18 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈረደበት፡፡ በዚህ ሁሉ ውጣ ውረድ ውስጥ ባለቤቱ ሰርካለም ከጎኑ ነበረች፡፡

“ምስክር ፈላጊው ችሎት” – 27ተኛ የፍርድ ቤት ውሎ (ዞን 9)

በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ ከጎንዬሽ ጉዳዬች ውጪ ለ25ተኛ ጊዜ (በአጠቃላይ ለ27ተኛ ጊዜ) የተሰየመው ችሎት ዛሬም የደረጃ ምስክሮችን ሲያሰማ ውሏል፡። ከሳምነትት በፌት የተሰየመው ችሎት አቃቤ ህግ 41 ምስክሮች አሉኝ ነገር ግን ላገኛቸው ስላልቻልኩ ተከሳሾቹ በማረሚያ ቤት ቆይተው ተጨማሪ ማፈላለጊያ ጊዜ ይሰጠኝ በማለት ጠይቆ ለዛሬ የተቀጠረ ቢሆንም ዛሬም “የሽብር ተግባሩ “ ዋና ምስክሮች ባለመገኘታቸው ፍተሻ ላይ ተገኝተናል ያሉ አምስት ምስክሮች ተሰምተዋል፡። የምስክሮቸን ቁጥርም 35 ነው በማለት ቀይሮታል፡፡Ethiopian arrested zone 9 bloggers
ባለፈው የተሰሙት 13 ምስክሮች ሲሆኑ በዛሬው ችሎት ባልተካደ ነገር ላይ ሲመሰክሩ የዋሉት የደረጃ ምስክሮች
14ተኛ ምስክር ተወዳጅ ኃ/ማርያም ይባላሉ፡፡ እድሜያቸው 34 ሲሆን የመንግስት ሰራተኛ ናቸው፡፡ የምስክርነት ቃላቸውም ‹‹የመጣሁበት ኬዝ ግንቦት 7/2006 ዓ.ም በምኖርበት ልደታ 5ኛ አካባቢ የፌደራል ፖሊስ ታዛቢ ሁነኝ ብሎ ጠይቆኝ በታዛቢነት ያየሁትን ለመመስከር ነው፡፡ ማህሌት ጤና ጥበቃ ሚ/ር ትሰራለች መሰለኝ፣ እዚያ መስሪያ ቤት ፖሊስ ማህሌት ኮምፒውተርና ጠረጴዛ ላይ ያለውን ሲበረብር አይቻለሁ፡፡ መንግስት መስሪያ ቤት የምትጠቀምበት ኮምፒውተር ላይ የተገኙ ሰነዶች ላይ ማህሌት ስትፈርም እኛ ታዛቢዎችም ፈርመናል፡፡

Wednesday, April 8, 2015

በየመን ጦርነት ማጥ ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አበሳ ! – ነቢዩ ሲራክ

People gather at the site of an air strike at a residential area near Sanaa Airport
* ኢትዮጵያውያን ማን ይታደጋቸው ?
*
ከቀሩት የውጭ ዜጎች ምን እንማር ይሆን ?
*
ለነፍስ አድኑ ጥሪ የእኛ አማረጭ ምን ይሆን ?

Monday, April 6, 2015

“በማላውቀው ምክንያት ፓስፖርቴን ተነጥቄ ጉዞዬ ተስተጓጉሏል” ይልቃል ጌትነት፣ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር

yilikal


በአሜሪካ ከሚገኙ የሰማያዊና የአንድነት ለፍሕትና ለዴሞክራሲ (አንድነት) ፓርቲ አባላት ጋር በተለያዩ ስቴቶች ለመወያየት ወደዚያ ለማቅናት ወደ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ያመሩት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፣ ባላወቁት ምክንያት ፓስፖርታቸውን ተነጥቀው ጉዟአቸው እንደስተጓጎለ ገለጹ፡፡
መጋቢት 23 ቀን 2007 ዓ.ም. ከምሽቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ወደ አሜሪካ ለመብረር ሁሉን ነገር አሟልተው ከምሽቱ አንድ ሰዓት አካባቢ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መድረሳቸውን የተናገሩት ሊቀመንበሩ፣ የአውሮፕላን መሳፈሪያ ሰዓት እስከሚደርስ ሊሸኟቸው አብረዋቸው ከነበሩ ጓደኞቻችው ጋር ሲጨዋወቱ አምሽተው ወደ ውስጥ መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡

Sunday, April 5, 2015

የት ሂዱ ነው? (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

መስፍን ወልደ ማርያም (አዲስ አበባ)
Prof. Mesfin Woldemariam : is an Ethiopian Human Rights activist and philosopherዓለም ሁሉ ጠላን፤ በየትም አገር እየሄድን ‹‹የሙጢኝ!›› ከራሳችን መሬት በጉልበት እየተነቀልን፣ ከራሳችን ቤት እየተባረርን፤ ከተወለድንበትና ከአደግንበት አካባቢ እየተፈናቀልን፣ ጭራውን ቆልምሞ እንደሚሮጥ ባለቤቱ እንዳባረረው ውሻ በአገኘነው አቅጣጫ እየሮጥን፣ እጃችንን እያርገበገብን ‹‹የሙጢኝ!›› እንላለን፤ የፈራነውን ሞት በየመንገዱ እናገኘዋለን፤ ሞትን ሸሽተን ሞት ያጋጥመናል፤ የሞቱ ልዩነት አይታየንም፤ በየመንገዱ የሚያጋጥመው ሞት የውርደት ሞት ነው፤ የብቸኛነት ሞት ነው፤ ዘመድ-ወዳጅ ለቀብር የማይገኝበት ሞት ነው፤ ሠለስት፣ አርባ፣ ሙታመት የማይወጣበት ሞት ነው፤ ባዕድ ምስጥ ያላሳደገውን አካል የሚበላበት ነው፤ የሞት ሞት ነው፡፡
ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ከአገር አስወጥቶ ባዶ መሬት ብቻ ይፈልግ ይመስል የወያኔ ሎሌዎች በማስፈራራት ሁሉም አገሩን እየተወላቸው እንዲሄድ ያቀዱ ይመስላል፤ ጥንት ኢሰመጉ በምሠራበት ጊዜ በየጊዜው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ሰዎችን በማስፈራራት ሰላማቸውን ለመረበሽ ወደስደት ወይም ወደወንጀል ተግባር የሚመሩ የወያኔ አባለች ነበሩ፤ አሁን እንደገና ብቅ ማለት ጀምረዋል፤ ሕጋዊ ሥርዓት እየላላ ጉልበተኞች በግላቸው ለዘረፋና ለቅሚያ እየተሰማሩ ይመስላል፡፡

Thursday, April 2, 2015

ወቅቱ የተግባራዊ ትግል ነው!

pg7-logoለገዛ ራሱ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እና ለኢትዮጵያ ቅን የሚመኝ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ህወሓትን ለማስወገድ ተግባራዊ ትግል ውስጥ መሳተፍ የሚኖርበት ወቅት ላይ እንገኛለን። በዚህ ወሳኝ ወቅት ከዳር ሆኖ መታዘብ ዘረኛውን፣ አምባገነኑን፣ ፋሽስቱን ህወሓት እንደመደገፍ ይቆጠራል።
ዛሬ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ህሊናውና አቅሙ በሚፈቅድለት የትግል ዘርፍ የመሰማራት ሰፊ እድል ተፈጥሮለታል። በዚህም መሠረት የህወሓትን አፈና በጠነከረ ክንድ ለመመከት የቆረጡ ኢትዮጵያዊያን ወደ በረሃዎችና ተራራዎች አቅንተዋል። ብዙዎች በመንገዱ ላይ ያሉ ጋሬጣዎችን ተቋቁመው እየተቀላቀሏቸው ነው። በደል የመረራቸው ሌሎች በርካታ ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች በቡድን ለነፃነታቸው ዘብ ቆመው በህወሓትና አገልጋዮቹ ላይ እርምጃ መውሰድ ጀምረዋል። ይህ የሚበረታታ እና ተቀናጅቶ ሊጠናከር የሚገባው ጉዳይ ነው።
አሁን ያለንበት ጊዜ ልዩ የትግል ወቅት ነው። ትናንት በከተሞች ይካሄድ የነበረው ፀረ ወያኔ ትግል ዓይነተኛ መታወቂያው ሕዝባዊ ተቃውሞ ነበር። ዛሬ ግን ይህ ሁኔታ ተቀይሯል። በተለይ በአገዛዙ ፈቃድ የሚደረጉ ተቃውሞዎች ፋይዳ ቢስ ሆነዋል። በአገዛዙ ፈቃድ በሚደረጉ ተቃውሞዎች ለውጥ እንደማይመጣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በማያሻማ ሁኔታ ተረድቷል። ስለሆነም ትግሉ ወደ ሕዝባዊ እምቢተኝነት አድጓል።
ዛሬ ከዚህ በፊት ያልተሞከሩ የትግል ስልቶች ተግባራዊ እየሆኑ ነው። በዚህ ረገድ የሙስሊም ኢትዮጵያዊያን የተቀናጁ ርምጃዎች በአርዓያነት የሚጠቀሱና የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ የሚሹ ናቸው። እነዚህ የሕዝባዊ እምቢተኝነት ተግባራት የእምነት አጥር ሳይለያየን ፍትህ የተጠማን ዜጎች ሁሉ ልንተገብራቸው የሚገቡ ናቸው።

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በደህንነቶች የአሜሪካ ጉዟቸው ታገደ፣ ሻንጣቸው ግን ወደ አሜሪካ ተጉዟል

ይድነቃቸው ከበደ (አዲስ አበባ)
Eng. Yilkal Getnet, Chairman of the Blue Partyህጋዊ የጉዞ ሠንድ በአግብቡ እንደተሟላ አየር መንገዱ አረጋጧል፡፡ ይሁን እንጂ የወያኔ እንባ ጠበቃ ነጭ ለባሾች አማካኝነት ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ከአገር እንዳይወጣ ተከልክሏል፡፡ የሰጡትም ምንም ዓይነት ሕጋዊ ምክንያት የለም፤ ያሉት ነገር ቢኖር “እርሶዎ ከአገር እንዳይወጡ ትእዛዝ ተሰጥቶናል፣ ነገ ጠዋት 2፡30 ኢሚግሬሽን ይምጡ!” ከማለት በስተቀር፡፡ በኢ/ር ይልቃል ላይ እንዲህ አይነቱ የውንብድና ተግባር ሲፈፀምባቸው ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡
ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት
ኢ/ር ይልቃል ለጉዞ ያዘጋጁት ሻንጣ አስፈላጊው ፍተሻ ከተደረገ በኋላ አውሮፕላን ላይ የተጫነ ሲሆን፣ የሻንጣው ባለቤት የሆኑት ኢ/ር ይልቃል ወደ አሜሪካ መጓዝ ተከልክለው ሻንጣቸው ብቻ ከአገር እንዲወጣ ተደርጓል፡፡

ገዥው መንግስት ከቦታ ወደ ቦታ የመዘዋወር አለም አቀፍ እንዲሁም ህገመንግስታዊ መብት ፣ ያለምንም ሕጋዊ መክንያት መገደቡ የወያኔ መንግሰትን አምባገነንነት ፍንትው አድርጎ የሚያሣይ ነው፡፡ እንዲህ አይነቱ መንግስታዊ ውንብድና የያዝነውን ትግል የበለጠ አጠንክረን እንድንቀጥል ተጨማሪ ሃይል እንደመሆኑ መጠን በትግላችን የምናመጣውን ውጤት ያፋጥናል፡፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !

ስልጣን ላይ አድሮ ለመገኘት ሃገርን መሽጥ፤ ህዝብን መሸፈጥ ለምን? እስከመቼ?

እስከ ነጻነት
1. ስልጣን ላይ አድሮ ለመገኘት ሃገርን መሽጥ፤ ህዝብን መሸፈጥ ለምን? እስከመቼ?
የህወሃቱ መሪ መለስ ዜናዊ ሰሜን አፍሪቃ የተነሳሳው ህዝባዊ አመጽ በኢትዮጵያኖች ዘንድ መወያያ ርዕስ እንዳይሆንና አመጹም እንዳይዛመት “ዛሬን ስልጣን ላይ አድሮ መገኘት፤ ቀኑን እንዳመጣጡ ለማለፍ ስልት መቀየስ” በሚል እምነቱና ስልጣንን ከህዝብም ከሃገርም በላይ አምላኪነቱ የተነሳ: ለነገ ምን ችግር ያመጣል? ጉዳቱስ መጠኑና ስፋቱ ምን ያህል ይሆናል? ሃገር ሉዓላዊነትና ዘላቂ ብሄራዊ ጥቅም ላይ የሚኖረው አዎነታም ሆነ አሉታ ተጽዕኖ ሳያሳስበው: ብልጭ ባለለት ማምለጫ መንገድ ብቻ የሚንቀሳቀሰው መለስ “አባይን እገድባለሁ” የሚል ቅዥት ይዞ ብቅ እንዳለ ሁላችንም እናስታውሳለን። ይህን ያልታሰበበት፤ ያልተጠና፤ ህዝብ ያላወቀውና መክሮ ያልተስማማበትን ቅዥት በየሙያው ዘርፉ አንቱ የተባሉና የሃገራቸው ጉዳይ የሚያሳስባቸው ተናገረውበታል፤ ጽፈውበታል አስጠንቅቀዋል፡ ህወሃት ግን የዕለት ስልጣንና ከስልጣን የሚገኝ ጥቅም እንጂ የህዝብ ስሜትና ፍላጎት ስለማያስጨንቀው ሊሰማ አልቻለም፡ በምጣኔ ዘርፍ፤ በአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ፤ በህግ ዘርፍ፤ በርካታ ባለሙያዎች አስተያየታቸውን ስለሰጡበት እኔ እሱ ላይ አልመለስም።
እኔ ማንሳት የምፈልገው: ከሙያው ቅርበት ካላቸው በስተቀር የኢትዮጵያ ህዝብ አያውቀውም ብዬ የምገምተውን: ማወቅ አለበት፤ አውቆም ለጥፋቱና ለሃገራዊ ሉዓላዊነት መደፈር ከህወሃት እኩል ተጠያቂ መሆኑን ሊያስገነዝብ ይችላል የምለውን አባይ ወንዝ ዙሪያ የተደረጉ ጥናቶችን፤ የቀረቡ ሃሳቦችንና እቅዶችን; ህወሃት የሄደበትን የተቃርኖ መንገድ በተመለከተ ይሆናል።
1.1 በአባይ ወንዝ ዙሪያ የተደረጉ አብይ ጥናቶች
በአባይ ዙሪያ የተደረገው የመጀመሪያ ጥናት በአሜሪካ ጂኦሎጂ ቅየሳ (United States Geological Surfay(USGS)) እ አ አ በ1960ዎቹ የነበረ ሲሆን በዚያን ጊዜ የተመረጡት አራት የግድብ ቦታውች ነበሩ፤ እነዚህም ከጎሃጽዮን-ደጀን አባይ ድልድይ ወደ ሱዳን አቅጣጫ ተከትለን ሲንሄድ በቀደም ተከተል (ካራዶቢ፤ ማቢል፤ መንዳያ እና የግርጌ (Karadobi, Mabil, Mandaia and Border) ናቸው።
ከታች ያለውን ንድፍ ይመልከቱ፡
Proposed dams on Blue Nile
ሁለተኛው ጥናት የተደረገው በ1980ቹ ሲሆን ቼዘን (CESEN) የተባለ የጣያን አማካሪ መሃንዲስ ቡድን ሲሆን የሃገሪቱን ጠቅላላ የሃይል ፍላጎትና አቅርቦት አጥንቶ ነበር፤ ይህም ጥናት እነዚህን አራት የአባይ ግድቦች በጥናቱ አካቶ ነበር።

በቤተ-መንግስቱ፣ ሰማይ ጠቀስ መንታ ህንፃዎች ሊሰሩ ነው

ዳዊት ከበደ ወየሳ – ዘና ዜና
ዘና ዜና ማለት፣ አዲስ የተፈጠረ… አንባቢዎች ዘና የሚሉበት፤ ነገሮችን ትኩረት ሰጥተው የማይጨናነቁበት፤ የደራሲው ፈጠራ የታከለበት በአጭሩ እራስዎን ፈታ ዘና የሚያደርግ የአራዳ ልጆች ወግ ወይም ወሬ አልያም ጨዋታ ማለት ነው። [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]
Ethiopian News April 1 2015