Translate

Sunday, November 25, 2012

ኢሳትን አያችሁ የተባሉ ወታደሮች ታሰሩ፤ ሠራዊቱ ዉስጥ የተፈጠረዉ መከፋፋል አሁንም እንደቀጠለ ነዉ



ሰሜን ኢትዮጵያ ዉስጥ በባድሜ ግንባር ወታደራዊ ክበባቸዉ ዉስጥ ቁጭ ብለዉ በናይልሳት የሚተላለፈዉን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንን ሲከታተሉ የተገኙ በርካታ ወታደሮች ለሁለት ሳምንታት ታስረዉ በከባድ ማስጠንቀቂያ መለቀቃቸዉን ትግራይ ዉስጥ የሚገኙ ወታደራዊ ምንጮቹን በመጥቀስ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት ዘገበ። አንድ ስማቸዉና ማዕረጋቸዉ እንዳይጠቀስ የጠየቁ ከፍተኛ መኮንን በስልክ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት ወታደሮቹ የታሰሩት በክበባቸው ውስጥ ቁጭ ብለዉ የኢሳትን ዝግጅት ሲከታተሉ ሲሆን ከ 14 ቀናት እስርና እንግልት በኋላ የተፈቱት የዲሻቸውን አቅጣጫ ወደ ናይል ሳይት ያዞሩት ሳያዉቁ በስህተት መሆኑን ለበላይ አለቆቻቸው ተናግረዉ ዳግመኛ ኢሳትን እንደማይመለከቱ ቃል ከገቡ በኋላ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዚያዉ ከባድሜ ግንባር አንድ ሌላ ከፍተኛ የጦር መኮንን ለኢሳት በሰጡት መረጃ መሠረት በመከላከያ ሠራዊቱ ዉስጥ ከፍተኛ የሞራል ዉድቀት የሚታይ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ በሠራዊቱ ዉስጥ ይህ ነዉ የማይባል የኤኮኖሚ ችግር፤ ሰር የሰደደ የዘር ልዩነትና ከፍተኛ የአስተዳደር በደል በየቦታዉ ተንሰራፍቶ ይታያል ብለዋል። መኮንኑ ንግግራቸዉን በመቀጠል አብዛኛው የኢትዮጵያ ወታደር የመከላከያ ሠራዊቱን የሚቀላቀለዉ በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ቢሆንም የሰራዊቱ አባላት በአገሪቱ ከሚታየዉ የኤኮኖሚ ችግር ማምለጥ አልቻሉም ብለዋል። እንደ መኮንኑ አበባል ከኮሎኔልነት በታች ማዕረግ ያላቸው መኮንኖች ገቢያቸዉ ከተራው ወታደር ብዙም እንደማይለይና ተደማጭነትም እንደሌላቸው ለማወቅ ተችሏል።
በወያኔ ሠራዊት ዉስጥ ኮሎኔልና ከኮሎኔል በላይ ሹመት ካላቸዉ መኮንኖች ዉስጥ ከ95 በመቶ በላይ የሚሆኑት የህወሀት አባል የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ የእነዚህ መኮንኖች ኑሮ ከበታቾቻቸው ጋር ሲነጻጻር ሰማይና ምድር መሆኑን ተራው ወታደር ጭምር የሚያዉቀዉ ጉዳይ ነዉ።በኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞች ዉስጥ ህንፃና ዘመናዊ ቤቶችን ሰርተው የሚያከራዩት አነዚሁ የህወሀት መኮንኖች ናቸዉ።ለምሳሌ አዲስ አበባ ዉስጥ በወረዳ 17፣ በቦሌ መድሀኒአለም አካባቢ ጄኔራል ወዲ አሸብር የ55 ሚሊዮን ብር ህንፃ ያሰራ ሲሆን  ኮሎኔል ታደሰና ጄነራል ዮሀንስ የሚባሉ የህወሀት መኮንኖቸች ደግሞ የ12 ሚሊዮንና የ45 ሚሊዮን ብር ህንፃ አሰርተዉ በማከራየት ላይ ናቸዉ።

No comments:

Post a Comment