Translate

Sunday, November 11, 2012

“ተናነቀኝ እንባ” ኢህአዴግ ቁስለኛ ሆነ አሉ!



አንድ ወቅት አንድ ተበዳይ ሰውዬ የበደላቸውን ልክ በአንድ እውቅ ፀሐፊ አስፅፈው ለሚመለከተው አካል አቤት ለማለት አሰቡ። እውቅ የተባለው ፀሐፊም መጣ በደላቸውን ዘክዝከው ነገሩት “ን…ሽ እቴ! በል ደህና አድርገህ ፃፍልኝ” አሉት።
ፀሐፊውም በደንብ አጣፍጦ እና አስተዛዝኖ “ኩችም” አድርጎ ፃፈላቸው። “ኩችም” ሰሜን ሸዋ አካባቢ አንድን ነገር “ደህና አድርጎ” ሲሉ የሚጠቀሙባት ሰሜን ሸዊኛ ቋንቋ ናት!

ታድያ የፃፈው ነገር ላይ የቀረ ካለ እንዲጨምሩ የማይሆን ነገር ገብቶም እንደሁ እንዲቀንሱ ብሎ ሊያነብላቸው ጀመረ። ይሄኔ ሰውዬው… ስቅስቅ ብለው ማልቀስ ጀመሩ። ፀሐፊው ደነገጠ። ግራ ገባው። “ምን ሆኑ አባቴ!?” ብሎ ቢጠይቃቸው፤ “በጣም መበደሌ ገና አሁን ነው የገባኝ!” አሉት።
ሀና መታሰቢያ አቶ መለስ ከሞቱ በኋላ በኢህአዴግ ውስጥ የተከሰቱ ጉልህ ክስተቶችን አስነብባን ነበር። ልክ ይሄንን ሳነብ ኢህአዴግ በቃ ቁስለኛ ሆነ ማለት ነው!? ብዬ አብዝቼ ተጨነቅሁ! እስቲ እርስዎም  ያንብቧት እንደኔ በእውነት የኢህአዴግ የልብ ወዳጅ ከሆኑ እንባ እንባ ይልዎታል!
ከአቶ መለስ ሞት በኋላ የተከሰቱ አበይት ጉዳዮች፦
=>ለ34 ወታደራዊ መኮንኖች ከፍተኛ የማእረግ እድገት ተሰጣቸው ከነዚህ ውስጥ 29ኙ የትግራይ ተወላጅ ናቸው
=> የአቶ ጁነዲን ሳዶ ባለቤት ታሰሩ
=> አቶ ጁነዲን ሳዶ በኢትዮቻናል ጋዜጣ ለመንግስት አቤቱታ አቀረቡ ። ሳምሶን ማሞ ከነባለቤቱ ለ2 ቀናት ታስሮ ከተፈታ በኋላ ኢትዮቻናል ተዘጋ
=> የህወሀት ምንደኞች የሆኑት የነ ብርሀኔ ኢትዮፒካ ሊንክ ታገደ 
=> የህወሀት ማእከላዊ ኮሚቴ አባልና የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው በላይ ወደ አሜሪካ ተሰደዱ
=> የቀድሞው የአ/አ ምክትል ከንቲባ አቶ ከፍያለው ከሀገር ተሰደዱ
=> አቶ ጁነዲን ሳዶ ከስልጣን ተወገዱ
=> ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የኦህዴድ ለቪኦኤ ደውለው የኦህዴድን መከፋፈል ይፋ አደረጉ
=> አቶ አማረ አረጋዊ ህወሀት/ኢህአዴግ እራሱን እንዲያፀዳ ተማፀኑ ካለዚያ መከፋፈል እጣፈንታው እንደሆነ አሳወቁ
=> ወ/ሮ አዜብ ከቤተ መንግስት አልወጣም አሉ
=> በጄ/ል ሳሞራ ትዕዛዝ የአየር ሓይል አዛዥ የነበሩት ጄ/ል ሞላ ሃ/ማሪያም ከሃላፊነት ተነሱ
=> ፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እና የህወሐት አባል አቶ አታክልቲ ሐጎስ ከነቤተሰባቸው ከሃገር ተሰደዱ።
ይህ የበሰበሰ አገዛዝ ይዞን ገደል ሳይገባ በህብረት እናውርደው!
29/02/05 ሀና መታሰቢያ
ሃና መታሰቢያ ይሄንን ሁሉ ከየት አስታወሺው…!? ማስታወስሽ ይባረክ

No comments:

Post a Comment