ወጣቱ ፖለቲከኛ አቶ ሀብታሙ አያሌው ለከፍተኛ ህክምና ወደ ውጭ ሀገር እንዲጓዝና ፍርድቤት የጣለበትን ከሀገር ውጭ የመጓዝ እገዳ ያነሳል ተብሎ የተጠበቀው ችሎት “ዳኛው ቀርተዋል” በሚል ምክንያት ጉዳዩ ለሌላ ጊዜ በቀጠሮ መተላለፉን ያደመጠችው የአቶ ሀብታሙ ባለቤት እራሷን ስታ ወድቃለች።
አቶ ሀብታሙ አያሌው በሕወሃት የታገደው የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ በፖለቲካ አመለካከቱ ምክንያት ለረጅም ጊዜ ታስሮ በቅርቡ በዋስ የተፈታ ቢሆንም በእስር ላይ በቆየባቸው ጊዚያት ጤናው በመታወኩ በአስጊ ሁኔታ ላይ ሆስፒታል ተኝቶ ይገኛል።
አቶ ሀብታሙ አያሌውን እያከሙት ያሉት ዶክተሮች “ከአቅማችን በላይ ነው ህመምተኛው በውጭ ሀገር ከፍተኛ ህክምና ሊያደርግ ይገባል” በማለት የጻፉትን ደብዳቤ ይዘው ነበር የአቶ ሀብታሙ ባለቤት እና ወዳጅ ዘመዶች ፍርድቤት የተገኙት። ይሁንና ፍርድቤቱ “ጉዳዩን የያዙት ዳኛ አልተገኙም” በሚል ተልካሻ ምክንያት ውሳኔ ሳይሰጥ ቀርቷል።
No comments:
Post a Comment