Translate

Friday, July 8, 2016

ፈተናው… ከፈተና በፊት እንደገና ተሰራጨ (መረጃውን ይዘናል)

(ኢ.ኤም.ኤፍ) የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በድጋሚ ከፈተናው በፊት መሰራጨት ጀምሯል። ከአንድ ወር በፊት ፈተናው በተመሳሳይ ሁኔታ ወጥቶ በመባዛቱ፤ ተማሪዎች በድጋሚ እንዲፈተኑ በዚህ ሳምንት ቀነ ቀጠሮ ተይዞ ነበር። ከዚህ በፊት ፈተናው ወጥቶ እንዲሰራጭ ምክንያት የሆነው የኦሮሚያ ተማሪዎች ጉዳይ መሆኑ ይታወሳል። በወቅቱ ለፈተናው መሰራጨት ምክንያት የሆነው፤ “ከወራት በፊት በኦሮሚያ በተነሳው ረብሻ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ነበር። በዚህ ምክንያት የኦሮሚያ ተማሪዎች በደንብ አልተዘጋጁም፤ ስለሆነም የፈተናው ግዜ ይራዘምልን።” የሚል ሲሆን፤ መንግስት ጥያቄያቸውን ባለመቀበሉ…. ፈተናው ከመሰጠቱ በፊት፤ እንዲሰራጭ መደረጉ ይታወሳል።
2በወቅቱ የትምህርት ሚንስትሩ ሽፈራው ሽጉጤ፤ “ፈተናው አልተሰረቀም” ሲሉ ቆይትተው፤ ማምሻውን ግን ፈተናው መሰረቁን አምነው፤ ትምህርት ሚንንስቴር ፈተናውን ሙሉ ለሙሉ መሰረዙን ይፋ አድርጎ ነበር። ከዚያ በአፋጣኝ ፈተናውን ለመስጠት ሲጣደፉ፤ “በረመዳን ጾም ወቅት ፈተናውን ብትሰጡ ዋ!” የሚል ማስጠንቀቂያ ከሙስሊም መምህራን አካባቢ በመምጣቱ፤ ፈተናው ከረመዳን ጾም በኋላ እንዲሰጥ ተወሰነ። እንግዲህ ይህ ሁሉ አልፎ ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ በዝግጅት ላይ እያሉ፤ ፈተናው ለሁለተኛ ግዜ ተሰርቆ መውጣቱ በሰፊው እየተነገረ ነው።
በአሁኑ ዙር ፈተናው ወጥቶ እንዲሰራጭ ምክንያት የሆነው ደግሞ የገዢው መደብ፤ ኢፍትሃዊ አሠራር መሆኑን አንዳንድ መምህራን እየገለጹ ናቸው። ምክንያቱን ሲዘረዝሩ… “በየአመቱ ፈተናው ሲሰጥ መምህራን በልዩ የአውሎ አበል ክፍያ ይመደባሉ። ይህን የክፍያ ጥቅማጥቅም መምህራኑ አይጠሉትም። ሆኖም በአሁኑ ዙር ፈተናውን እንዲከታተሉ የተደረጉት የኢህአዴግ ደጋፊ ወይም አባል የሆኑ መምህራንን መሆናቸው ቁጣ ቀስቅሷል።” ይላሉ።

ኬዚህ ጋር በማያያዝም፤ “እንዲህ ያለ የፖለቲካ ስራ በትምህርት ሚንስቴር መስሪያ ቤት በኩል በመደረጉ ለአሁኑ ፈተና መውጣት እና መሰራጨት ተጠያቂው ራሱ ኢህአዴግ ነው።” እያሉ ነው መምህራኑ።
እንደ ድረ ገጻችን EMF እምነት ከሆነ፤ ተማሪዎች አመቱን ሙሉ ተዘጋጅተው ሲያበቁ፤ በአዋቂዎች እልህና ፉክክር ምክንያት መጎዳት እንደሌለባቸው እናምናለን። በዚህ ምክንያት በአሁኑ ወቅት እየተሰራጨ ያለውን የፈተና ወረቀት ይፋ ላለማድረግ አስበን ነበር። ሆኖም ለዚህ ውሳኔ ዘግይተናል። በርግጥ እኛ ባናሰራጨው ሌሎች ማሰራጨታቸው አልቀርም። ስለዚህ ቢያንስ ፈተናው 2ግዜ እንዲሰራጭ ምክንያት የሆነው የትምህርት ሚንስቴር ተመሳሳይ ስህተት እንዳይሰራ፤ ከፖለቲካ ነጻ ሆኖ ፍትሃዊ አሰራር እንዲከተል በማሳሠብ ጭምር፤ ከዚህ በታች የእንግሊዘኛውን ጥያቄ ያህል ለህትመት አብቅተነዋል።
7110

No comments:

Post a Comment