Translate
Sunday, July 10, 2016
የትምህርት ሚኒስትሩ የፈተና ወረቀት አልተሰረቀም አሉ
ከሰኞ ሐምሌ 4 ቀን የሚጀመረው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተሰረቀ በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ድረ-ገፆች የተሰራጨው ወሬ ሃሰተኛ መሆኑን የት/ት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አስታወቁ፡፡ 26 የፈተና ወረቀቶች ተሰርቀው መውጣታቸውን አንዳንድ ድረ ገፆች ያስታወቁ ሲሆን በማህበራዊ ሚዲያዎችም የእንግሊዝኛ ፈተና መሰረቁን የሚያመላክት መረጃዎች ተሰራጭተዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ አዲስ አድማስ ያነጋገራቸው የትምህርት ሚኒስትር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ ፈተናው ተሰርቋል የተባለው “ውሸት ነው፤ የራሳቸውን የውሸት የፈተና ወረቀት አዘጋጅተው ነው ወሬውን ያሰራጩት” ብለዋል፡፡
ቀደም ሲል ፈተናው ግንቦት 22 ቀን እንዲካሄድ ታስቦ በነበረበት ወቅት የፈተና ወረቀቶች ስለመሰረቃቸው በተለያዩ ድረ ገፆችና ማህበራዊ ሚዲያዎች ሲገለፅ እንደነበረ የሚታወስ ነው፡፡ መንግት መረጃውን እያስተባበለ ቆይቶ፣ በፈተናው መስጫ እለት ነው በድንገተኛ መግለጫ ፈተናው እንዲቋረጥ የወሰነው፡፡
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment