ሰበር ዜና፣ የቦስተን ማራቶን ፍንዳታ ተጠርጣሪ ተገደለ። ፖሊስ ሁለተኛውን ለመያዝ ዘመቻ ላይ ነው።
UPDATE:
10:21 am EST: ነዋሪዎቿ ከቤት እንዳይወጡ የታዘዙባት፣ ፀጥ እረጭ ያለችው የቦስተን ከተማ
10:10 am EST: የኮኔክትከት ጠቅላይ ግዛት ፖሊስ ተጠርጣሪው በአሁኑ ሰዓት የታርጋ ቁጥሩ 316 ES9 የሆነ ጥቁር ሆንዳ መኪና እየተጠቀመ ነው ብሏል።
9:25 am EST: በመታደን ላይ ያለው የቦስተን ማራቶን ፍንዳታ ተጠርጣሪ አጥፍቶ ለመጥፋት የሚያስችለው ቦምብ በራሱ ላይ አጥምዷል ተባለ።
SWAT Scanner Again “EXTREME CAUTION’ Suspect confirmed in wearing a suicide jacket”
9፡10 am EST: ቀደም ሲል “በመታደን ላይ ያለው ተጠርጣሪ የእጅ ስልክና ኢንተርኔት ኮኔክሽን ካለው በቀላሉ የፖሊሶቹን እንቅስቃሴ ሊያውቅ ይችላል።” ብለን መዘገባችን ይታወቃል። አሁን ከፖሊሶች እየተነገረ እንዳለው ከሆነ በመታደን ላይ ያለው ተጠርጣሪ የእጅ ስልክ እና ኢንተርኔት ኮኔክሽን አለው። ከደቂቃዎች በፊት ፖሊሶችን ሁሉ እንደሚገድል ዛቻ በኢንተርኔት አስተላልፏል። “ወንድሜን እንደገደላችሁ እኔም እገድላችሁላው” የሚል መልክት ነው እያስተላለፈ ያለው።
8:16 am EST: ከቤት እንዳይወጡ የተነገራቸው የቦስተን ነዋሪዎች አንዳንዶቹ ከቤታቸው ሆነው በመስኮት አጮልቀው ያነሱትን የፖሊስ እንቅስቃሴ ፎቶዎች፣ በፌስቡክና ትዊተር እየለቀቁት ነው። ሁኔታው ብዙዎችን አሳስብዋል… በመታደን ላይ ያለው ተጠርጣሪ የእጅ ስልክና ኢንተርኔት ኮኔክሽን ካለው በቀላሉ የፖሊሶቹን እንቅስቃሴ ሊያውቅ ይችላል።
ይህ ቪዲዮ የቦስተን ነዋሪ የቀረጸው የተኩስ ልውውጥ ነው
7፡55 am EST: ተጠርጣሪዎቹ ከቺቺንያ እንደሆኑና ከእስልምና አክራሪ ቡድን ጋር ግንኙነት ሳይኖራቸው እንደማይቀር እየተነገረ ነው።
ይህ የተጠርጣሪ ቁጥር አንድ የፌስ ቡክ ፔጅ ምስል ነው። (screenshot)
————————————–
እስካሁን ተጠርጣሪዎቹ አንድ ፖሊስ ገድለዋል። ከነሱም ሚድያዎች ተጠርጣሪ 1 እያሉ የሚጠሩት ተገድሏል።
ተጠርጣሪ ሁለትን ለመያዝ ነው ቦስተን እየታመሰ ያለው። ባለስልጣኖች አሁን በቴሌቪዥን ብቅ ብለው ባጠቃላይ የህዝብ ትራንስፖርት ተዘግቷል፣ ማንኛውም የከተማዋ ነዋሪ ከቤት እንዳይወጣ ብለዋል።
ምናልባት ይህን ሲሰሙ ላያምኑ ይችላሉ…
ተጠርጣሪ ሁለትን ለመያዝ ፖሊስ የሚያደርገው እንቅስቃሴ (የራድዮ ግንኙነት) በቀጥታ በኢንተርኔት እየተላለፈ ነው።
አንዳንዶች መተላለፉን አምርረው እየተቃወሙ ነው።
ጃክ ሙር በትዊተር ገጹ ላይ እንዳለው፣
“It’s so weird the cops are broadcasting plan on unencrypted line. What if the suspect has a Smartphone?”
ተጠርጣሪ ሁለትን ለመያዝ ፖሊስ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በቀጥታ ለማዳመጥእዚህ ይጫኑ።
No comments:
Post a Comment