Translate

Thursday, April 18, 2013

የኢሕአግ ሰራዊት በዋልድባ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀመ


የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር (ዜና)

Ethiopian People Patriotic Frontየኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በዋልድባ አካባቢ ልዩ ስሙ ሰቋር እና አምቦ ጠበል በተባለ ቦታ በተከታታይ ሁለት ቀናት ከወያኔው የፈጥኖ ደራሽ ጋር ባደረገው የፊት ለፊት ውጊያ በጠላት ላይ ወታደራዊ የበላይነትን በመቀዳጀት አኩሪ የአርበኝነት ጀብድ ፈፅሟል።
የግንባሩ ሰራዊት በዋልድባ ልዩ ስሙ ሰቋር በተባለ ቦታ በሚያዚያ 8-2005 ዓ.ም የወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ መመኪያ በሆነው የፈጥኖ ደራሽ ላይ በከፈተው የማጥቃት እርምጃ 21 የጠላት ወታደሮችን በመግደል 25 ያቆሰለ ሲሆን፣ በተመሳሳይ በሚያዚያ 9-2005 ዓ.ም በዋልድባ ልዩ ስሙ አምቦ ጠበል በተባለው ቦታ ውጊያው የተካሄደ ሲሆን በዚሁ እለትም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት 25 የጠላት ወታደሮችን ገድሎ 39 በማቁሰል ከፍተኛ ድል የተቀዳጀ ሲሆን፣ በዚሁ አውደ-ውጊያ ላይም የተለያዩ የቡድንና የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያዎችንም ከመሰል ጥይቶቻቸው ጋር ማርኳል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በሁለት ተከታታይ ቀናት ባደረጋቸው አውደ-ውጊያዎች ላይ በድምሩ 46 የፈጥኖ ደራሾችን ከጥቅም ውጭ በማድረግና 64 በማቁሰል የግንባሩ ሰራዊት የተሰለፈበትን ሐገራዊ ተልዕኮውን በመፈፀም በጠላት ላይ ከፍተኛ የሕይወትና የንብረት ኪሳራ በማድረስ አኩሪ የአርበኝነት ጀብድ ፈፅሟል።
የግንባሩ ሰራዊት ጥቃቱን በፈፀመበት አካባቢ የሚኖሩ የሕብረተሰብ ክፍሎችም ስርዓቱ በሚያራምደው የግፍ አገዛዝ ከፍተኛ ምሬትና ተቃውሞ እያሰሙ ሲሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊትም የጀመረውን ወታደራዊ የማጥቃት እርምጃ አጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላቸውን አስተዋፅዖ በማበርከት ሐገራዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ወደ ግንባሩ ሰራዊት እየተቀላቀሉ እንደሚገኙም ታውቋል።

No comments:

Post a Comment