Translate

Friday, April 19, 2013

የከሸፈው ዝርፊያ... ስውር ደባ...የቤንሻንጉል ጉምዝ ለም መሬቶች ለማን ሲሳይ ሊሆኑ ነበር??


የከሸፈው ዝርፊያ... ስውር ደባ...የቤንሻንጉል ጉምዝ ለም መሬቶች ለማን ሲሳይ ሊሆኑ ነበር??


 Minilik Salsawi
ባሳለፍነው ሰሞን እንዲሁም አሁንም ድረስ የመነጋገሪያችን ርእስ የሆነው በምእራብ የሃገራችን ክፍል የሚገኘው የቤንሻንጉል ጉምዝ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የተወሰደው የዘር ማጥራት እርምጃ በአለማቀፍ ደረጃ አነጋጋሪ ከመሆኑም በላይ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ታላቅ ቁጣን የቀሰቀስ ሆኖ ተገኝቷል::በገዛ ሃገራቸው ሰርተው ለመኖር ራሳቸውን ለመምራት ህብረተሰብን እና ሃገርን ለመርዳት ብለው አስበው ህገመንግስቱ በሰጣቸው በሃገራቸው በየትኛውም አከባቢ የመኖር እና የመዘዋወር መብት ተጠቅመው ሃገር አልምተው እነሱም ኑሮን ለማሸነፍ ሲፍጨረጨሩ በነበሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ከባድ የሆነ የማፈናቀል ወንጀል ተፈጽሟል::እየተፈጸመም ነው ::ይህ ወንጀል ከተጠያቂነት ያማያድናቸው ባለስጣናት የማይሆን ታሪክ በመዘላበድ ላይ ሲሆኑ ከዚህ መፈናቀል ጀርባ ሕወሓት ከበረሃ ይዞት የመጣው የጸረ አማራ ማኒፌስቶ ማስፈጸሚያ የሆኑ ባለጽልጣናት እና የህ ወንጀል እንዲፈጸም ትእዛዝ የሰጡ የሕወሓት የበላይ ሰው በውስጥ አዋቂ ምንጮች ተጋልጠዋል:: እነሆ ዝርዝሩን ያንበቡ:-

1-የዝርፊያ ምክር በአቡዳቢ
የቤንሻንጉል ጉምዝ የተፈጥሮ ዉበት ያጓጓቸው አንድ ባለስልጣን አከባቢውን ላውጭ ኢንቨስተሮች ምቹ እና አስፈላጊ በመሆኑ ለራሳቸው ጥቅም እንደሚያገኙበት በማሰብ የአረብ ሰዎች በዚህ ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሰማሩ አስፈላጊውን በማድረግ መሬቱን በመስጠት እንዲያለሙት አስፈላጊውን እንደሚደረግ አውጥተው እና አቅደው ከጨረሱ በኋላ በኢምሬት የሚገኙትን ከፍተኛ ዲፕሎማት ወደ አገርበት አስጠርተው ይህንን ጉዳይ በመንገር በዚህ ጉዳይ ዙሪያ እንዲሰሩ እና አስፈላጊውን የጥቅም ተካፋይ እንደሚሆኑና በስራው ላይ ለመሰማራት የሚፈልጉ ኢንቨስተሮችን አፈላልገው እንዳገኙ እንዲጠሯቸው እና....በመንገር  ለዚሁ የዘረፋ እቅድ የኤምባሲያቸውን ጄኔራል ኮንሱለር አቶ ምስጋኑ አረጋን መልምለው ላኳቸው::አቶ ምስጋኑም በኢምሬት የሚገኙ ደላሎችን እና ታማኝ ብለው ያሰቧቸውን ዲፕሎማቶች መልምለው አሰማሩ::
የቀድሞ የወያኔ ሊቀመንበር እና የጸረ አማራ ማኒፌስቶ አቀነባባሪ የሆኑት የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ አባይ ጸሃዬ ወደ ዱባይ እና አቡዳቢ ያቀኑት ይህንን መክረው እና ዘክረው የኢምሬትስ የፍራፍሬ እና የአትክልት አስመጪ የዐረብ ካምፓኒዎችን እንዲያግባባ ስራዬ ብሎ የያዘው ዲፕሎማት ምስጋኑ አረጋ ተብየው የዛሬው የቤንሻንጉል ጉምዝ ምክትል ፕሬዚዳንት ባደረገላቸው የስልክ ጥሪ ነበር::በኢምሬት በኢትዮጵያውያን ሴቶች ላይ የሚደርሰውን ግፍ እና ሰቆቃ ወደጎን በመተው በቢዝነሱ አለም ላይ በመሰማራት ደላላዊ ስኬቱ አጠናቀቀ::
አቶ አባይ ጸሃዬም በተጠሩት መሰረት የተዘጋጁትን የአቡዳቢ እና የዱባይ የፍራፍሬ እና የአትክልት አስመጪዎች እና ላኪዎችን ለማነጋገር በቦታው በመገኘት አስፈላጊውን ገለጻ እና የሚገኘውን ጥቅም የኢትዮጵያ መንግስት ለ3 አመታት ቀረጥ እንደማያስከፍላቸው እና አስፈላጊውን ትብብር ሁሉ እንደሚያደርግላቸው በመግለጽ ጥናቱን አድርገው ፕሮፖዛል እንዲያቀርቡ በክልሉ የመስክ ጉብኝት እንዲያደርጉ በመስማማት በፌሽታ ወደ አገር ቤት ተመለሱ::

2-ከዲፕሎማትነት ወደ ክልል ባለስልጣንነት
በስምምነቱ መሰረት አስፈላጊውን ቀጣይ ሂደቶችን እንደጀመሩ እንዲጨርሱ ተልእኮ የተሰጣቸው አቶ ምስጋና በቀደዱት የቢዝነስ መስመር በመሄድ የአረብ የፍራፍሬ እና የአትክልት አስመጪ እና ላኪዎችን ከህንድ ባለስልጣኖቻቸው ጋር በመምራት በቤንሻንጉል ጉምስ ይፋዊ ያልሆነ ቱሪስታዊ ጉብኝት የክልሉ ፕሬዚዳንት ሳያውቁ አደረጉ::
ከጉብኝቱ በኋላ ከአባይ ጸሃዬ ጋር በመነጋገር ለቀጣዩ ዝግጅት እንዲደረግ እና አቶ ምስጋኑ አረጋም ወደ ክልሉ መተው ምክትል ርእሰመስተዳደር እንዲሆኑ ታቀደ ይህም ተፈጸመ::ቢፈጸምም ሁኔታዎች አመቺ ስላልነበሩ አዘግይተውት የነበረ ቢሆንም አቶ ምስጋኑ ይህንኑ የቢዝነስ መስመር ለማቃናት ደፋቀና እያሉ በሕወሓት ሰው በተሰጣቸው ትእዛዝ መሰረት ከአከባቢው የሰፈሩ የአማራ ቤሄር ተወላጆችን ህገወጥ ናቸው ብሎ ለማፈናቀል በታቀደው መሰረት በአንድ ባላ ሁለት ወፍ ለመምታት የሚቻልበትን ስራ እንዲሰሩ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ የተነከሩበትን ለማስፈጸም በትጋት ሲሰሩ ይህን ጉዳይ በተመለከት ምንም አይነት ደብዳቤዎች እንዳይጻጻፉ ማስጠንቀቂያ ተሰቷቸዋል::
ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ ቀጣይ መስራት የለባቸው መሬቱ ለሚፈለግባቸው አከባቢ ላሉ የክልሉ የወረዳ የዞን እና የቀበሌ ባለስልጣናት ለተመረጡ ሰዎች የዘረኝነት ኦረንቴሽን መስጠት እንደሆነ በስልጡኑ ዘረኛ አቶ አባይ ጸሃዬ በተነገራቸው መሰረት ሰብስበዋቸው በህዋስ በማዋቀር አማራ አከባቢውን ለቆ እንዲወጣ የውስጥ ለውስጥ ቅስቀሳ ጀመሩ::በዚህም መሰረት በክልሉ ከ8 አመት እስከ 30 አመት የኖሩ ኢትዮጵያውያን በአማራው ህዝብ ላይ የተጀመረው የወያኔ ስውር ደባ እና የግል ጥቅም በመተሳሰር ጎጃሜዎች ተብለው ተጭነው ወደ መጡበት እንዲመለሱ አቶ ምስጋኑ ባዋቀሩት ህዋስ አማካኝነት ትእዛዝ አወረዱ::በጥቂት ቀን ማስጠንቀቂያ አማሮቹ / ጎጃሜዎች የተባሉትም ያላቸውን ንብረት በስርኣት ፈር ሳያሲዙ አቤቱታ ላይ እንዳሉ ድንገት አነሷቸው::

3-የወረደው ትእዛዝ እና መንግስታዊ ትኩሳት
ለክልሉ ፕሬዚዳንት ሪፖርት ሳይደረግ ለአማራ ክልላዊ መስተዳደር የተቀበሉቸው ጥሪ ሳይደረግ እንደሚነሱ ቢነገራቸውም ድንገት የተፈናቀሉት ዜጎች በመንግስት ባለስልጣናት ዘንድ በተለይ ባአቶ አያሌው ጎበዜ በኩል ከፍተኛን ድንጋቴ በመፍጠሩ አስቸኳይ ድርድር እንዲካሄድ ወደ ቤንሻንጉል ባለስልጣኖቻቸውን ቢልኩም ከፌደራል ጉዳዮች ሳታሳውቅ እንዴት ይህን ታደርጋለህ የሚል ቁጣ ከህወሃቱ አቶ አባይ ጸሃዬ ቢመጣም ድሮም በአቋማቸው ጠንካራ እንደሆኑ የሚነገርላቸው አቶ አያሌው አቶ አባይን ከቁብ ባለመቁጠር በዙሪያቸው የብኣዴን የባህዳር ባለስልጣናትን ድጋፍ በማግኘታቸው ድርድሩን ወደ ውይይት ጀምረው ተሳክቶላቸዋል ::
በሁኔታው እንዳዘኑ ይታወቅባቸው ነበር ተብለው በአማራ ክልል ባለስልጣናት የተነበቡት አቶ አህመድ ናስር ይህ ጉዳይ እንዴት እና ለምን እንደተደረገ ግልጽ ሪፖርት ብጠይቅም እንዳላገኘሁ በዉነት ልነግራቹህ እወዳለሁ እንዳሏቸው ባለስልጣናቱ ተናግረዋል :; በወቅቱ ደረቅ ፊት ይታይባቸው የነበሩት አቶ ምስጋኑ ብዙ እንዳልተናገሩ እና አንዳንድ ጉዳዮች ያልተስታካከሉ ካሉ ለማስተካከል እንደሚጥሩ ሲነገሩ በቀዘቀዘ አንደበት ተደምጧል::

አለም አቀፍ የዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን እና የመንግስታት እንዲሁም የህገርቤት ዲፕሎማቶች ጫና ትኩሳት ውስጥ የከተቱት የወያኔው መንግስት አስቸኳይ እርምጃ መወሰድ እንዳለበት ባስተላለፈው መሰረት የተፈናቀሉት ዜጎች ወደ ቦታቸው እንዲመለሱ እና አስፈላጊው ነገር ሁሉ እንዲደረግላቸው ብሏል::
ይህን ተከትሎ ህዋሱን ማፍረስ የነበረበት አቶ ምስጋኑ በወሰዱት እርምጃ የህዋሱ መሪዎች ራሳቸውን ነገር እስኪረጋጋ እንዲደበቁ የነገሯቸው ሲሆን ቀሪዎቹም እንደሸፈቱ ተደርጎ እንዲወራ አድርገዋል::አቶ አባይ ጸሃዬ  ያቀዱት ዝርፊያ እና የዘር ማጥራት ሃሳብ የከሸፈባቸው ሲሆን ህወሃት በዚህ ጉዳይ ከተጠያቂነት እንደማይተርፍ ይህን መረጃ የሰጡን በጉዳዩ ላይ ከኢምሬትስ ጀምሮ የተሳተፉ የውስጥ አዋቂ ምንጮች ተናግረዋል::

No comments:

Post a Comment