በህወሓት የጉባኤ ኣጀንዳ ዙርያ ስብሰባ ሊጠራ ነው …!
አብራሃ ደስታ
ከኢህኣዴግ ጉባኤ በኋላ መሪዎቻችን (ከበፊቱብሶባቸው) መግባባት ኣቅቷቸዋል። በፌደራል ደረጃየሚደረጉ ስብሰባዎች ያለ ዉጤት ይጠናቀቃሉ።ለምን ኣይግባቡም? (‘ቀሽም ጥያቄ’)። የሚያግባባነጥብ የላቸውማ። ድሮ (ከ‘ባለራእዩ መሪ’ ዕረፍትበፊት) ሁሉም ነገር እሳቸው ይሰሩት ስለነበር)በመሪያቸው ነበር ‘የሚግባቡት’ (አብረው የሚጓዙ)።በሰው ‘ይግባባሉ’ (ሌላ ሊያግባባቸው የሚችል ሓሳብወይ መርህ አልነበራቸውም፣ የላቸውም)። አሁንታድያ እንዴት ይግባቡ?
‘ባለራእዩ’ ሰውዬ መመርያ ይሰጣል፣ ‘ፖሊሲ ነው ተግብሩት’ ይላቸዋል፣ እነሱም እሱ የተናገረውን‘ቃል’ እየደገሙ (ከላይ እስከ ታች) ይዘምራሉ።ስሕተት መሆኑ (ሊተገበር የማይችል መሆኑ) ሲረዱ‘ስሕተቱ ያለው አፈፃፀም ላይ ነው’ ብለው ራሳቸው ያፅናናሉ። ህዝቡ በማይፈፀሙ ፖሊሲዎች ተስፋ እንዳይቆርጥ መሪዎቻችን ሁሌ ስለ አዲስ ፖሊሲ ወይ አሰራር ይሰብካሉ። ሁሌ ስለ‘አዲስ ኣሰራር’ ወይ ዕቅድ ሲወራልን ለውጥ የመጣ ያህል እንዲሰማን ለማድረግ ያህል ነው።
አሁን ሰውየው ‘አርፈዋል’። ለተከታዮቻቸው የተውት መርህ መሰረት ያደረገ የፖለቲካ አቅጣጫየለም። የኢህኣዴግ ካድሬዎች ታድያ አሁን የሚግባቡበት ቋንቋ የላቸውም። የኣምስት አመቱ‘የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን አቅድ’ ይዘት ወይ መሰረታዊ ፅንሰ ሓሳብ ምን እንደሆነየሚያውቀው የለም። በዚህ ጉዳይ ተደጋጋሚ ውይይት ተደርጎ ያለ ዉጤት ተበትነዋል። (ዕቅዱግን ድሮውም ቢሆን ምንም የሚጨበጥ ሓሳብ አልነበረውም ….. የሚሰማን አጣን እንጂ)።ዕቅዱ ‘Ambitious’ ብለን በተደጋጋሚ አሳስበን ነበር (‘ሊተገበር የሚችል ዕቅድ አሳዩን’ ብለንተማፅነን ነበር)። አሁን ግን ካድሬዎቹ ራሳቸው (በተለያዩ ስብሰባዎች) ‘የተለጠጠው(ዝተለጠጠ)’ ዕቅድ ማለት ጀምረዋል።
በኢህኣዴግ ደረጃ ያለው ችግር የስልጣን ሽኩቻ ነው (የባለስልጣናቱ ዓላማ ስልጣን ነው)።ህወሓቶች በኢህኣዴግ የነበራቸው ሚና ማጣት አይፈልጉም። ግን ይህንን ሚና ሊጫወትየሚችል ደህና ሰው የላቸውም። (ዓቅም የነበራቸው የፓርቲው ሰዎች በተለያየ ምክንያትእንዲጠፉ ተደርገዋል ) ። ራሳቸው በራሳቸው ችግር ፈጥረው (በሁለት ተከፍለው፣ ጓደኞቻቸውኣባረው) ተዳክመዋል (አሁን ትግራይ እንኳ መቆጣጠር በሚችሉበት ሁኔታ ኣይገኙም)።
በኣሁኑ ግዜ በኢህኣዴግ ዉስጥ የተሻለ የስልጣን ተፎካካሪ ብአዴን ነው። ግን ብአዴን ከሌሎችሦስቴ የኢህኣዴግ አባል ድርጅቶች ተቀባይነት የለውም። የህዝብ ድጋፍም በሰፊው የለውም።የሚጠበቀው ያህል (ኢህኣዴግ ለመቆጣጠር የሚያስችል) ጠንካራ አባላትም የሉትም። ግንበኢህኣዴግ ስርወ መንግስት የህወሓት አልጋ ወራሽ ብአዴን ይመስላል። በህወሓትና ብኣዴንከፍተኛ ውዝግብ አለ።
ኦህዴድ በኢህኣዴግ ዉስጥ በጣም ያኮረፈ ቡድን ነው። የተለያዩ ምክንያቶች እየደረደረ ስልጣንለኦህዴድ መሰጠት እንዳለበት ይወተውታል። ግን ኦህዴድ ሁለት ችግሮች ተደቅነውታል።(አንድ) በኦህዴድ ውስጥ መግባባት ብሎ ነገር የለም። (ሁለት) በሌሎቹ የኢህኣዴግ አባልድርጅቶች እምነት ባለፈው የኦህዴድ ጉባኤ ወደ ሓላፊነት የወጡ ሰዎች ከኦነግ ጋር ግንኙነትአላቸው። በነሱ እምነት ኦነግ የኦህዴድ መዋቅር ተቆጣጥሮታል። ስለዚ ለኦህዴድ ስልጣንመስጠት እጅግ ያስፈራቸዋል።
ሌላው ደኢህዴን ነው። ደኢህዴን ጠንካራ ኣይደለም። በሁለት ቡድኖች ተከፍሎ ትርምስ ላይነው። ከቡድኖቹ አንዱ ከህወሓት ጎን መሰለፍ ይፈልጋል። ብቻውን (ህወሓት ከዚህ በፊትእንዳደረገው) የኢህኣዴግ ስልጣን መቆጣጠር የሚችልበት ዕድል የለውም። ህወሓትም ቢሆንደካማ ሁነዋል። ዶር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በኢህኣዴግ ጉባኤ ሲናገር “በቃ ወድቀናል” ብሎነበር። ይሄ ከህወሓት ጋር መጠጋት ለሚፈልግ ቡድን ራስ ምታት ነው።
ህወሓቶች ጉዳዩ ኣስጨንቋቸዋል። የነ አባይ ወልዱ ቡድን የነ አርከበ ዕቁባይ ቡድን ካባረሩወዲህ የባሰ ንትርክ ዉስጥ ገብተዋል። እርስበርሳቸው አይግባቡም፣ ይናናቃሉ። የኣሁኑ መሪዎችማንም አያከብራቸውም። በህወሓት ጉባኤ የተሳተፉ አባላት በነ ኣባይ ወልዱ የተመለመሉቢሆኑም በጉባኤው ወቅት በነኣርከበ የተወሰደው እርምጃ ግራ አጋብታቸዋል። ጉባኤተኞቹ ‘እነኣርከበ ከውጡ ህወሓት ከማን ጋ ትቀራለች?’ የሚል ጥያቄ ነበራቸው።
የፓርቲው ሊቀመንበር የሚመረጠው (በፓርቲው ደንብ መሰረት) በጠቅላላ ጉባኤ ነው (በቀጥታግን አይደለም)። እንዲህ ነው። ጉባኤተኞቹ አርባ አምስት የፓርቲው የማእከላዊ ኮሚቴ አባላትይመርጣሉ። በውጤቱ (ባገኙት ድምፅ) መሰረት በቅደም ተከተል (የተመረጡት ሰዎች)ስማቸው ይገለፃል። የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት የፓርቲው ስራ ኣስፈፃሚ (ፖሊት ቢሮ)ይመርጣል። ፖሊት ቢሮ አባላት ደግሞ የፓርቲው ሊቀመንበርና ምክትል ይመርጣሉ።
በምርጫው ከፍተኛ ስልጣን ያለው (በመርህ ደረጃ) ጉባኤተኛው ስለሆነ ከፍተኛ ድምፅ ያለው(By Default) የፓርቲው ሊቀመንበር ይሆናል። የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ይሄንን አውቀውባገኙት ድምፅ መሰረት ዘጠኙ (Top Nine) ለፖሊት ቢሮ ይመርጣሉ። ፖሊት ቢሮ አባላትምበተሰጠው ድምፅ መሰረት ከፍተኛውን ያገኘ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርገው ይመርጣሉ።
በጉባኤው የተሳተፉ አባላት ሊቀመንበር (ከተሰጣቸው አማራጭ) አድርገው የመረጡት ዶርደብረፅዮን ነበር። ዶር ደብረትፅዮን የኣንደኛነት ድምፅ ሲያገኝ አባይ ወልዱ ሁለተኛ ነበር።(ደብረፅዮን ለኣባይ በ23 ድምፅ ይበልጠዋል)። ውጤቱ ግን ጉባኤተኞቹ እንደጠበቁትኣልሆነም። የፖሊት ቢሮ አባላት ሁነው የተመረጡት (top nine) ዘጠኙ ኣልነበሩም።በውጤቱ መሰረት የህወሓት ሊቀመንበር መሆን የነበረት ዶር ደብረፅዮን ሲሆን ዉጤቱተገልብጦ አቶ ኣባይ ተመረጠ። ይሄ የሆነው የኣቶ አባይ ቡድን አብዛኛው የማእከላዊ ኮሚቴወንበር መያዝ በመቻሉ ነበር። (ጉባኤተኞቹ የነኣባይ ቡድን ደጋፊዎች ሲሆኑ አባይ ፓርቲውይመረዋል ብለው ግን አያምኑም። ስለዚህ ጉባኤተኞቹ ደብረፅዮን ሊቀመንበር አድረገውመርጠው እንደሄዱ ነው የሚያውቁ)።
ይሄን ዉሳኔያቸው ታድያ በጉባኤተኞቹ ጥሩ ስሜት አልፈጠረም። የኣሁኑ መሪዎች የህዝብአመኔታም የላቸውም። ይሄን ችግር ለመፍታት ሲሉ ከነገ እሮብ (ሚያዝያ 16, 2005 ዓም)ጀምሮ ጉባኤው በተመለከተ በመላው ትግራይ (በየደረጃው ከከፍተኛ የክልል ቢሮዎች ጀምሮእስከ ቀበሌ አስተዳደር ድረስ) ስብሰባ እንደሚደረግ ታውቋል። ለስብሰባው ማስኬጃ ብዙሚልዮን ብር ተመድበዋል (ከመንግስት ካዝና መሆኑ ነው)።
ኣየ ህወሓት! በቃ ስብሰባ ነው። እኔ ደግሞ ስብሰባ ስጠላ! (እንኳን የህወሓት አባል አልሆንኩ)።
It is so!!!

No comments:
Post a Comment