Translate

Wednesday, August 1, 2012

የውጭ ጉዳይ ዜናዎች

በሙሉነህ ዮሃንስና የውጭ ጉዳይ ምንጮች የተጠናከረ (ጁላይ 31 2012)
  • አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ መለስን ሲያስታምም ከርሞ ከብራስልስ ወደ አዲስ አበባ እየተመለሰ ነው!
  • አምባሳደር ሙሉጌታ አለምሰገድ ባጣዳፊ ቤተሰቡን ወደ ጣሊያን አሸሸ!
  • አሜሪካን ሃገር በአምባሳደርነት ማእረግ ያሉ አራት ዲፕሎማቶች ከአበበ ገላው ጋር በተያያዘ ጠቅልለው እንዲመለሱ ታዘዙ!
  • መጠኑ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብና የባለስልጣናት ቤተሰቦች ወደ ኬንያ እየተሸጋገሩ ነው!
አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ መለስን ሲያስታምም ከርሞ ከብራስልስ ወደ አዲስ አበባ እየተመለሰ ነው!
ህወሃት በጫካ እያለ ጀምሮ የድርጅቱን ገንዘብ ውጭ ሃገር በማንቀሳቀስ የሚታወቀውና በአሁኑ ወቅት በምክትል ሚኒስትርንት ስም ውጭ ጉዳይን የሚያዘው ብርሃነ ገብረክርስቶስ
Ethiopian pm Meles Zenawi
Meles Zenawi
መለስ ዜናዊ ከታመመ ጀምሮ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር (ሄድ ኦፊስ) አካባቢ ጠፍቶ መክረሙን በቦታው ያሉ ሰራተኞች አረጋግጠዋል። ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰራተኞች እንዳረጋገጡት ብርሃነ የከረመው ብራስልስ ውስጥ መለስ ዜናዊን በቅርብ ሲያስታምም ነው። የመለስ ዜናዊ የመሞት ዜና በውጭ ጉዳይ አካባቢ የመረበሽ ድባብ እንደፈጠረ የገለጹት የዜናው ምንጮች ብዙ ዲፕሎማቶች ለማምለጥ አጋጣሚ እያመቻቹ መሆኑን ጠቁመዋል። ብርሃነ ገብረክርስቶስ መጠኑ ያልተገለጸ ከፍተኛ ገንዘብ ከውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ወደብራስልስ ይዞ መሄዱም ተያይዞ ተገልጿል። መለስ ዜናዊ በጸና መታመሙ ከተረጋገጠበት የዋሽንገተን ቆይታ አንስቶ በቅርብ ሲያስታምም የከረመው አምባሳደር ብርሃነ በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ አዲስ አበባ እንደሚገባ ማወቅ ተችሏል። ይህም በራሱ የማስታመሙ ስራ በሰውየው ሞት ምክንያት ማለቁን ይጠቁማል ይላሉ የውጭ ጉዳይ ሰራተኞች። የሚመለሰው አስከሬን ይዞ ወይም ቀብሩን ለማመቻቸት ይሆናል የሚል ግምት አለ።
አምባሳደር ሙሉጌታ አለምሰገድ ባጣዳፊ ቤተሰቡን ወደ ጣሊያን አሸሸ!
የመለስ ዜናዊ ቅርብ የደህንነት ሹም ሆኖ ለረጅም አመታት ያገለገለውና በአሁኑ ወቅት በጣሊያን አምባሳደር ተደርጎ የተሾመው ሙሉጌታ አለምሰገድ ቤተሰቦቹ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥ ቢቆዩም በአሁኑ ወቅት ግን በአስቸኳይ ወደ ጣሊያን እንዲሄዱ አስደርጓል። በጉዳዩ ጥድፊያ የተገረሙት የውጭ ጉዳይ ሰራተኞች የወያኔ ባለስልጣናት ሽሽት መጀመራቸውን በይፋ ያሳያል ብለዋል። ሙሉጌታ አለምሰገድ ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ገብታ የነበረችውን ልጁን ጭምር ትምህርቷን አቋርጦ ማሸሸቱ የወያኔ ባለስልጣናት ሽሽቱን እያጧጧፉት መሆኑን ይመሰክራል። ይህችው ልጅም በጣም ሃብታም የሆኑ ቤተሰቦች የሚማሩበት ጣሊያን ሃገር ከሚገኝ የአሜሪካን ዩንቭርሲቲ እንድትማር አስገብቷታል። የአምባሳደሩ ደሞዝ ይህንን ወጭ በፍጹም እንደማይሸፍን ስለሚታወቅ በርሃብ ከሚንገላታው የኢትዮጵያ ህዝብ ተዘርፎ መሆኑ ግልጽ ነው። በሌላም አለማት ያሉ እጅግ ብዙ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ወደ ሃገር ቤት ተጠርተው ከሄዱ ቤተስቦቻቸውን በሙሉ በምእራብ ሃገራት በተለይም በአሜሪካን ሃገር ጥለው መመለስ በስፋት እየታየ ነው። ብዙዎቹም ባለቤቶቻቸው የፓለቲካ ጥገኝነት እንዲያገኙ አመቻችተው መሄዳቸው ገሃድ ወጥቷል። ይህም ዲፕሎማቶቹ ተመልሰው ለመኮብለል በቋፍ እንዳሉ ያሳያል ተብሏል።
አሜሪካን ሃገር በአምባሳደርነት ማእረግ ያሉ አራት ዲፕሎማቶች ከአበበ ገላው ጋር በተያያዘ ጠቅልለው እንዲመለሱ ታዘዙ!
አሜሪካን ሃገር ዋሽንግተን ላለው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በአምባሳደርነት ማእረግ ሲያገለግሉ የቆዩት የዘርፍ ሃላፊዎች ተበጀ በርሄ፤ ተስፋየ ይልማ፤ ሙሌ ታረቀኝ እና አልማዝ አምሃ የስራ ጊዜያቸው ሳይጨርሱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ መታዘዛቸውን የኢምባሲ ምንጮች ገልጸዋል። ለመመለሳቸው ዋና ምክንያት የሆነውም የኢሳት ጋዜጠኛው አበበ ገላው እንደሆነ ታውቋል። ማብራሪያ የጠየቅናቸው የኢምባሲ ምንጮች እንደሚሉት እነዚሁ ዲፕሎማቶች ስራችሁን በአግባቡ ስላልተወጣችሁ ነው አበበ ገላው ያንን አጋጣሚ ተጠቅሞ የመንግስትን ገጽታ ያበላሸው ተብለዋል። ሊደርስባቸው ስለሚችለው ቅጣት የጠየቅናቸው የኢምባሲ ምንጮች ግምት ቢያንስ ከእርከን ዝቅ ሊያደርጓቸው፤ ሊባረሩ ወይም ከጠላት ጋር ተባባሪዎች ተብለው ሊወነጀሉ እንደሚችሉ አመላክተዋል። ይሁንና እነዚሁ ዲፕሎማቶች ቤተሰቦቻቸውን ይዘው እንደማይመለሱ ምልክቶች እየታዩ ነው። እስካሁን ወደ ኢትዮጵያ በብቸኛ እንደሄደች የታወቀችው አልማዝ አምሃ ልጆቿን ከድሮ ባሏ (ስመ ጥሩ ጀግና የኢትዮጵያ አየር ሃይል ጀኔራል) ጥላ እንደሄደች ተረጋግጧል።
መጠኑ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብና የባለስልጣናት ቤተሰቦች ወደ ኬንያ እየተሸጋገሩ ነው!
ከወደኬንያ ያሉ የኢምባሲ ምንጮቻችን እንዳረጋገጡት ደግሞ መጠኑ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ በሞያሌ ድንበር አቋርጦ ወደኬንያ እየገባ መሆኑን ገልጸዋል። በየብስ ማጓጓዙ ለምን እንዳስፈለገ የጠየቅናቸው እነዚህ ምንጮች እንደሚሉት ይህን ያህል ግዙፍ የገንዘብ መጥን በአውሮፕላን ማጓጓዝ ትኩረት ከመሳቡም በላይ አመችነት የለውም። በመኪና ግን ሸቀጥ እያስመሰሉ በታጠቁ የወያኔ የደህንነት ሃይሎች እንዲሻገር ይደረጋል። በኢትዮጵያ ብርም ሆነ በዶላር እየተሻገረ ያለው ገንዘብ ወደ የትኛው ባንክ ወይም ሃገር እንደሚላክ ለጊዜው አልታወቀም። በተያያዘም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ቤተሰቦች ወደ ናይሮቢ በብዛት እንዲሸሹ እየተደረገ ነው። በኢትዮጵያ ኢምባሲ አማካኝነትና በገንዝብ ሃይል ሁሉንም ማድረግ በሚቻልበት የኬንያ ሃገር እነዚሁ የባለስልጣናት ቤተሰቦች ወደ ሶስተኛ ሃገራት ሽሽት እየተመቻቸላቸው ይገኛል። እነዚህ ሰዎች በቦሌ ኤርፖርት እንዳይወጡ መደረጉ ሆን ተብሎ የህዝብ ትኩረት እንዳይስብ ነው። ይሁንና በመፍረክረክ ላይ ያለው የወያኔ መንግስት ገሃድ እየወጣ ያለውን የመጨረሻ ውድቀታቸውን ከለውጥ ፈላጊው ህዝብ ሊሸሽጉት አይችሉም።
በመጨረሻም ግርምቴን አጋርቸ ልጨርስ፦ዋልድባ ገዳምን እያተራመሱ የሚገኙ የምንግስት ፓሊሶች ለመለስ ዜናዊ መታመም ተጠያቂዎቹ የዋልድባ መነኮሳት ናቹህ በማለት እነዚሁን መናንያን ለድብደባና ለእስር እየዳረጓቸው መሆኑን ደጀ-ሰላም የሚባል ድህር-ገጽ ገልጿል ቪ.ኦ.ኤም ስለችግሩ ቀጣይ ዘገባ አቅርቧል። እኔም ዘግይቶ ከአካባቢው በደረሰኝ መረጃ መሰረት ማንነታቸው በውል ያልታወቁ ሃይሎች በትናንትናው እለት አስራ አራት የመንግስት ወታደሮችን በገዳሙ አካባቢ በመግደላቸው ውጥረቱን እንዳከረረው ተገልጿል።
http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/3719

No comments:

Post a Comment