(Aug. 17) በአዲስ አበባ የሙስሊሞች ተቃውሞ በዛሬው እለትም የቀጥለ ሲሆን፤ አንዋር መስጊድ በተቃውሞ ጭር ብሎ እንደዋለ ከአዲስ አበባ ለለማወቅ ችለናል።
የአዲስ አበባ ምንጮቻች እንደገለጹልን፤ በዚህ አርብ ደህንነቶች ቀንደኛ ያሉዋቸውን የሙስሊሙን አስተባባሪዎች ለመያዝ ዝግጅት ላይ እንደሆኑ መረጃ በመውጣቱ የተነሳ፤ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ወደአንዋር መስጅድ ሳይሄድ እንደዋለና አንዋር በተቃውሞ ጭር ብሎ እንደዋለ ምንጮቻችን ጠቅሰዋል።
በደሴም በትናንትናው እለት ከተደረገው በመንግስት የተቀነባበረ ሰልፍ በሁዋላ ውጥረቱ ቀትሎ እንደዋለ ምንጮቻችን ገልጸዋል።
በትናንትናውና በዛሬው እለት ያነጋገርናቸው የደሴ ነዋሪዎች፤ ህዝቡ ሱቁንና ስራውን እየዘጋ ሰልፍ እንዲወጣ እንደተገደደ እንዲሁም ገበሬዎች መሬታችሁን ትቀማላችሁ በሚል ምክንያት ሰልፍ እንዲወጡ እንደተገደዱ ተናግረዋል።
በተያያዘ ዜና፤ በእስር ላይ የሚገኙት የሙስሊሙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትና የሀይማኖት አባቶች በትናንትናው እለት ወደፍ/ቤት የቀረቡ ሲሆን፤ ስቱዲዮ እስክንገባንበት ሰዓት ድረስ የፍ/ቤቱ ውጤት ምን እንደነበር ለማወቅ አልቻልንም።
ባለፈው ወር አጋማሽ የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትና የሄኢማኖት አባቶች መታሰራቸው ይታወቃል።
በመንግስት የሚደገፈውን የአህባሽ አስተምህሮትና ከመጅሊስ ምርጫ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የተነሳው የሙስሊሞቹ እንቅስቃሴ ባለፈው ታህሳስ ተጀምሮ ላለፉት 9 ወራት በተይ አርብ አርብ በሚደረጉ ተቃውሞዎች ታጅቦ እስካሁን መዝለቁ ይታወቃል።
No comments:
Post a Comment