(Aug. 27) የአቶ መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ በኢትዮጵያ ውስጥ ህዝቡ ሀዘኑን እንዲገልጽ የተለያዩ ጫናዎች እየተደረጉበት እንደሆነ ከኢትዮጵያ የሚመጡት መረጃዎች አስረዱ።
ለጎንደር ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ የተጻፈ ደብዳቤ እንደሚያሳየው የጎንደር ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ በመስቀል አደባባይ ተገኝቶ ሀዘኑን እንዲገልጽ ታዞ እንደነበር ታውቋል።
በዚህም መሰረት፤ ባለፈው አርብ በጎንደር መስቀል አደባባይ በተዘጋጀው የሀዘን መድረክ ላይ፤ የመንግስት ሰራተኞች በሙሉ ከስራ መግቢያ ሰዓት ቀደም ብለው ከጠዋቱ 1 ሰዓት ከ40 ጀምሮ በስራ ገበታቸው በመገኘት፤ ወደ ሀዘን ስፍራው እንዲሄዱ ተነግሯቸዋል።
በደብዳቤው ላይም፤ በእለቱ ምንም አይነት ስራና ትምህርት እንደማይኖር የተጠቀሰ ሲሆን፤ ሰራተኞችና የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ፤ የሀዘን መግለጫ ልብስ ለብሰው እንዲመጡም ማሳሰቢያ እንደተሰጣቸው ደብዳቤው ያሳያል።
በተመሳሳይ ዜና፤ ከወላይታ ሶዶ የደረሰን ተመሳሳይ ደብዳቤ እንደሚያሳየው፤ ለአቶ መለስ ዜናዊ ሞት ሀዘን መግለጫ እንዲሆን፤ ከዞን መስተዳድር በተጻፈ ደብዳቤ፤ ለአቶ መለስ በወላይታ ባህል ንጉስ ደረጃ ልቅሶ እንዲዘጋጅላቸው መታዘዙ ታውቋል።
የዞኑ መስተዳድር ደብዳቤ “የኢትዮጵያ ብርሀን የሆኑት” ያላቸው ክቡር ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው፤ ህዝቡና የመንግስት ሰራተኞች፤ በሶዶ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ፊት ለፊት ከተዘጋጀው የሀዘን መግለጫ ስነ-ስርአት በተጨማሪ፤ ቅዳሜና እሁድ፤ በሶዶ ስታዲየም በመገኘት፤ በወላይታ ባህል ለንጉስ በሚደረግ ልቅሶ ስርአት፤ እንዲሳተፉ፤ በተለይም ለዞኑ ሰራተኞች ትእዛዝ መተላለፉን ያሳያል።
ባለፈው ሳምንት እንደዘገብነው፤ በኢትዮጵያ በተለያዩ ከተሞች፤ በተለይም በአዲስ አበባ የሚገኙ የመንገስት ሰራተኞች፤ ጥቁር ልበስ በመልበስና የአቶ መለስ ዜናዊን ፎቶ በመያዝ፤ ስራ ትተው በቤተመንግስት በመሄድ በአቶ መለስ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን እንዲገልጹ እየተደረገ እንደሆነ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን፤ አቶ በረከት ስምኦንም ባለፈው ሳምንት በሰጡት መግለጫ፤ ህዝቡ ሀዘኑን እንዲገልጽ ከፍተኛ የማደራጀት ስራ እየሰሩ እንደሆነ መናገራቸው ይታወሳል።
በዚህም መሰረት፤ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በአቶ መለስ ዜናዊ ሞት የደረሰባቸውን መሪር ሀዘን እየገለጹ ሲሆን፤ ባለፈው ቅዳሜ አዲስ አበባ የሚገኙ የጎዳና ተዳዳሪዎች በቤተመንግስት በመገኘት በአቶ መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።
ኢቲቪ እንደዘገበው፤ የጎዳና ተዳዳሪዎች “አቶ መለስን ተማምነው ጎዳና እንደመወጡና” በሳቸው መሞት መሪር ሀዘን እንደተሰማቸው እንዲሁም ለአደጋ እንደተጋለጡ ገልጸዋል።
በተመሳሳይ መልኩም፤ በአዲስ አበባ ሆስፒታሎች ውስጥ የሚገኙ ህመምተኞችና አካለስንኩላንም፤ በክራንችና ከነሆስፒታል ልብሳቸው ወደቤተመንግስት በመጓዝ ሀዛናቸውን እንደገለጹ ኢቲቪ ጨምሮ ዘግቧል።
በአዲስ አበባ በተለያዩ ስፍራዎች የሀዘን ድንኳኖች የተተከሉ ሲሆን፤ በአዲስ አበባ የኑቨርስቲ ስድስት ኪሎ አቅራቢያ በተለምዶ አሴ ባር ተብሎ በሚታወቀው ስፍራ ድንኳን መጣሉንና፤ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ነገ ነሀሴ 22፤ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋክልቲ ልዩ የመታሰቢያ መረሀግብር እንደተዘጋጀላቸው የሚያሳስብ ትልቅ ማስታወቂያም እንደተለጠፈ ምንጮቻችን ጠቅሰዋል።

No comments:
Post a Comment