Translate

Saturday, August 25, 2012

የመለስን እረፍት ተከትሎ ኢትዮጵያ የነጻነት አየር ትተነፍሳለች ብየ አምናለሁ ሲሉ ክብርት አና ጎሜዝ ተናገሩ


ነሀሴ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የአውሮፓ ፓርላማ አባልና በ1997 ዓም በኢትዮጵያ የተካሄደውን ምርጫ የታዘቡት ክብርት አና ጎሜዝ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ፣ በማንም ሰው ሞት  መደሰት ተገቢ ባይሆንም፣ የመለስን ሞት ተከትሎ ኢትዮጵያ የነጻነት አየር ትተነፍሳለች ብየ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል።
መለስ ዜናዊ አምባገነን፣ የገዛ ህዝቡን ጨፍልቆ የገዛ ነው ያሉት ክብርት አና ጎሜዝ፣ አለማቀፉ ማህበረሰብ የመለስን ስራዎች እያየ እንዳለየ በመሆን ሲያልፍ መቆየቱንም ወቅሰዋል።
አቶ መለስ ስልጣኑን በእርሳቸው ዙሪያ በማሰባሰባቸው ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ይኖር ይሆን በማለት እንደሚሰጉ የተናገሩት ክብርት አና ጎሜዝ፣ የአለማቀፉ ማህበረሰብ በተለይም የአውሮፓ ህብረት እስካሁን የተከተለውን የተሳሳተ ፖሊሲ በመተው ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሚሳተፉበት ነጻና ፍትሀዊ ምርጫ ተካሂዶ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር መኖር እንዳለበት ገልጠዋል።
አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ሙሉ በሙሉ ስልጣን ኖሮአቸው የሚመሩ ባለመሆናቸው፣ አለማቀፉ ማህበረሰብ ትክክለኛ ዲሞክራሲ እንዲሰፍን መስራት እንዳለበት ክብርት አና ገልጠዋል።

No comments:

Post a Comment