Translate

Thursday, August 23, 2012

ኢትዮጵያ-ፖለቲካዊ ግምቶች


ከአቢቹ ነጋ[1]
ነሃሴ 10, 2004
የመለስ መታመም ወይም መሞት የሃገራችንና የዓለም የመነጋገሪያ ርእስ ሆኗል:: ተቃዋሚው እንደገጸበረከት ቆጥሮ የሚአኝከው ዜና ሆኗል:: እራይና እቅድ ነድፎ ተጨባጭ ስራ ETHIOPIAN FLAGበመስራት ፋንታ በወደቀ ግንድ ላይ መጥረቢያ መጣልን መርጧል:: ይህ የነጻነት ተስፋችንን በመጠኑም ቢሆን አጨልሞብናል::
ባለፈው “የማይተባበሩ አያደንቁሩ” በሚል ርእስ ባስተላለፍሁት መጣጥፍ መደረግ ያለባቸውን ዓበይት ጉዳዮች መጠቆሜ ይታወሳል::  በጠቃሚወች ላይ መንቀሳቀስ ይገባል::በዘገየን ቁጥር ለወያኔ ጊዜ እየሰጠን የቤትስራውን እንዲአጠናቅቅ እየረዳነው መሆኑ ከወዲሁ ልብ ይሏል::

በአንጻሩ ወያኔ የመለስን ዜና አቅልሎ አይቶታል:: ንብረቱንና ጉልበቱን አቀነባበሮ መለስን የሚተካ ታማኝ ሰው ለመምረጥ በዝግጅት ላይ ይገኛል::ምክንያቱ ቀላል ይመስለኛል:: ከልምድ እንደተማርነው ድርጅቱ ግለሰቦችን ተጠቅሞ እንድሎሚ ልጣጭ የመወርወር ባህሪ አለው::  በጫካ ተለማምዶ በቤተመንግስት ያጎለበተው ባህሪው ነው:: ሕውሃት እንደ ድርጅት መለስን በሚገባ ተጠቅሞበታል:: አሁን ያረጀ ያፈጀ ሆኗል:: ተመጦም አልቋል:: ከዚህ በኋላ ቆሻሻ ድሪቶ ሆኗል:: የርሱ መኖር አለመኖር አያስጨንቀውም:: ለዚህ ነው ስብሃት ነጋ መለስ ኖረም አልኖረም የሚለውጥ ነገር የለም ያለው:: ወያኔን አስጨንቆ እንቅልፍ የሚአሳጣው ስልጣን የሚጠበቁበትን ሁኔታ ማመቻቸት ነው::
ባሁኑ ስዓት ወያኔ በዝግ ችሎት መለስን የሚተካ ሰው ለመምረጥ በልህ አስጨራሽ ውይይት ተጠምዶ እንደሚሆነ ከወዲሁ መተንበይ አያዳግትም:: መሪ ለመምረጥ የሚደረገው ግብግብ ቀላል አይሆንም:: ይህን ውስብስብ የሚአደርጉት ምክንያቶች ብዙ ቢሆኑም አንኳር አንኳሮቹን ከዚህ እንደሚከተለው እንፈትሻለን::
ወያኔወች እንደ ድርጅት 37 ኣመታት አበሮ ተጉዟዋል:: በዚህ ጉዞ ከፍተኛ ውጣ ውረድ ገጥሞታል:: ለምሳሌ ጫካ በነበሩ ጊዜ የነበራቸው የዓላማ የእርዮተ ዓለምና የመርህ አንድነት ባለፉት 21 ዓመታት በብዙ መልኩ ተበርዟል::  በመካከላቸው በአውራጃ በዘር ግንድና በደም ሃረግ ተሰነጣጥቀው በእርስበርስ ቅራኔ ውስጥ ተወዥቀዋል::  ብዙ አባሎቹ  ለዓመታት ታስረው ተለቀዋል ወይም ተገድለዋል::  በዚህም ከዘመዶቻቸውና ከጓዶቻቸው ጋር ደም ተቃብተዋል:: ከፊሎቹ ከድርጅቱ ተባረው ተራ ቦዘኔ ሆነዋል:: ብዙወቹ ከሃገር ወጠው ተሰደዋል:: ይህ ከባድ ቁርሾንና አለመተማመንን በመካከላቸው ፈጥሯዋል::
መንግስት በመላ ሃገሪቱ የሚከተለውን የፖለቲካ የዘር ማጥፋት የሃይማኖት ማዋረድ የትምህርት የጤና የግብርናና የጠቅላላ የልማት ፕሮግራም ፖሊሲ የሚቃወሙ በምሃላቸው በዝተዋል:: ያሁኑ አሰራር ለ17 ዓመታት ያህል ሕይወታቸውን ከሰውለት ዓላማና መርህ ውጭ በመሆኑ የሚቃወሙና የሚአወግዙ አባሎች አሏቸው::  ጫካ እያሉ አህያና ሰው በላ እያሉ ይሳለቁበት በነበረው የመሃል የደቡብና የምስራቁ  የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚፈጸመውን ኢ-ሰብአዊና ልክ ያልሆነ ድርጊት የተረዱ ብዙ ናቸው::
ኤርትራ ከእናት ሃገሯ ከኢትዮጵያ መገንጠሏና፣  ሃገሪቱ ወደብ አልባ መሆኗ፣  መሬቶቿ እየተቆረሱ ለባእዳን ሃገሮች መሰጠቱ፣  በምግብ ራስን ለመቻል በሚል ነዋሪወች እየተፈናቀሉ መሬታቸው ለውጭ ኩባንያወችና ባለሃብቶች ከነጻ በማይተናነስ ዋጋ መሰጠቱ፣  የስልጣን መባለግና የህግ የበላይነት መጥፋት እንደሌላው ኢትዮጵያዊ የሚከነክናቸውና የሚአንገበግባቸው አባላት ቁጥር በትቂቱ የሚገመት አይደለም::
የትግራይ ሕዝብ በኦርቶዶክስ ሃይማኖት እምነት ጽናታቸው የታወቁና ምስክርነት ሊሰጥላቸው የሚችሉ ናቸው:: በዋልድባ ገዳምና የትግራይ ሕዝብ የማንነቱና የባህሉ መሰረት የሆነችውን ቤትክርስትያንን ለማዳከምና ለማጥፋት በመንግስት የሚደረገውን  መርህ በጅጉ ይቃወማሉ::  የትግራይን ሕዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብና ሕብረተሰብ ጋር ለማቃቃር መጠነ ሰፊ በሆነ መልኩ በፖለቲካ ደረጃ ተደግፎ የሚደረገውን እርኩስ ተግባር የሚቃወሙ አያሌ ናቸው:: የፖለቲካና የመከላከያ ኅይላቸው መሰረት ከሆነው የትግራይ ሕዝብ ጋር ቅራኔ ውስጥ ገብተዋል:: ሕዝባቸውም በስማችን እየነገዳችሁ፣  ተጋብተን ተዋልደንና፣  ክርስትና ተናስተን ከኖርነው ከድጉ የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ደም አቃባችሁን ሃይማኖታችንን አረከሳችሁብን፣  ለልጅ ልጅ የሚተርፍ ቁስልና ደም መቃባት ደርጃ አደረሳችሁን እያለ የሚአጉረመርመው ሕዝብና ካድሬ ቁጥር ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም::
የስልጣን ሽግግሩ በማንኛውም መመዘኛ ሲታይ አልጋባልጋ አይሆንም :: አገሪቱ የምትጓዝበት አቅጣጫ አስቸጋሪ ስለሆነ ተባበረን ከክሳራ እናድናት እያለ ተቃዋሚው የሚአቀርበው ጥያቄና ግፊት ወያኔን አያስጨንቀውም ብሎ መገመትም አይቻልም:: የምእራቡ ዓለም በተለይም ዩኤስ አሜሪካ የኢትዮጵያ መንግስት የሚከተለው የፖለቲካ መስመር አገሪቱን ለርስበርስ እልቂት ሊዳርጋትና የአልሸባብ መፈንጫ ልትሆን ትችላለች ብሎ ያምናል:: በመሆኑም መንግስትንና ተቃዋሚውን የሚአስማማ ሰፊ የፖለቲካ ምህዳር እንዲፈጠር በውያኔ ላይ ጫና ማሳደሩ አይቀሬ ነው:: ቻይናና ሩስያ የበኩላቸውን ግፊትና ጫና ስለሚአደርጉ ወያኔ በብዙ መልኩ የሚጨነቅበት ሁኔታ ግልጽ ሆኖ ይታየኛል:: በውሳኔው ጀርባ ያለው እውነታ በአብዛኛው ከላይ የተጠቀሱት ናቸው:: እነዚህም ሁኔታወች በሚወሰደው ውሳኔ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ስለሚኖረው ወያኔን እርስበርስ የሚአነታርከው ይሆናል:: ይህን ከግንዛቤ ውስጥ አስገብተን ሊሆኑ የሚችሉ አምስት መላምቶችን እንደሚከተለው መተንበይ ወይም መገመት እንችላለን::
ግምት 1የወያኔ ሃርነት ግንባር በዝግ ችሎት ተጨቃጭቆ፣ ተፋጭቶና በቴስታ ተፋልጦ አንድነቱን አጠናክሮ ለግንባሩ መሪ መርጦ ጠቅላይ ሚንስትር ሊአደርግ ይችላል::ይህን በፍጥነት ማድረግ ካልቻል በምክትል  ጠቅላይ ምኒስትርነት ያሉትን ለፖለቲካ ፍጆታ ሲል ጠቅላይ ምንስትር አድርጎ በመሾም የውስጥ ውጥረቱን አስተንፍሶ ጊዜ ይገዛል::
ይህን ማድረግ ከቻለ አሁን ያለውን የአፈና ስርዓት እስከሚቀጥለው ምርጫ ድረስ ያሸጋግራል:: ይህም ቢሆን በሰላም መግዛት ይችላል ብሎ መገመት ግን አይቻልም:: የሙስሊሙ ሕብረተሰብ ጥያቄና የተቃውሞ ሰልፍ፣ የተቃዋሚወች ጫጫታ፣ የኢኮኖሚው ድቀት፣ የስራአጥነት ብዛት፣ የፖለቲካ ምሕዳሩን እንዲአሰፋና የዜጎችን መብት እንዲጠብቅ  በምእራቡ ዓለም የሚደረግበት ግፊትና ተጽእኖ ወዘት ከአቢዮታዊ ዴሞካራሲ ጋር በቀጥታ የሚላተምበት ስለሆነ ብዙ ቅራኔ ውስጥ መግባቱ አያጠራጠርም:: በሰላም ሊአስገዛው የሚችል አይሆንም:: ተቃውሞው በዓይነት በመጠንና በስፋት እየጨመረበት ይሄዳል:: የህዝብ ተቃውሞ እየጨመረ በሄደ ቁጥር የመንግስት አፈናም እይተባባሰ ይሄዳል::ይሕም ወደ ሕዝብ አመጽ ይሸጋገራል::
ግምት2- በቁጥር አንድ የተገመተው ካልሆን ወያኔ በማይታረቅ ቅራኔ ውስጥ ገብቶእርስበርሱ ሊበላላ ይችላል:: ክፍፍሉ ሊሆን የሚችልበት ብዙ ምክንያቶች ይኖራሉ:: ዋና ዋናወቹ ግን የሚከቱሉት ይሆናሉ ብየ አምናለሁ::
አንዱ ቡድን ” ሃ” የመለስ ደጋፊ ሆኖ ሊወጣ ይችላል:: በመለስ የተጀመረውን የአጥፍተህ ጥፍ ፖለቲካ መርህ  መቀጠል  ይሆናል::  በዚህ ቡድን ይጠቃለላሉ ተብለው የሚገመቱት ከአድዋ አውራጃ የፈለቁ የግንባሩ ታጋዮችና በአብዛኛው የኤርትራ ዘርና ደም የሚበዛባቸው ይሆናሉ ተብሎ ይገመታል:: የዚህ ቡድን ስብስብ በአብዛኛው በስልጣን ላይ ያሉ ባለስልጣኖችን ያጠቃልላ:: የሃገሪቱን የአስተዳደር መዋቅር የያዘ ቡድን ሲሆን ዋናው ጉልበቱ የመከላከያ ሃይልን የመገናኛ ብዙሃንና የኤርትራ መንግስት ናቸው::  በተራው የግንባሩ አባላትና ካድሬወችም ሆነ በትግራይ ሕዝብ ግን የሚደገፉ አይሆኑም::
ሁለተኛው ቡድን “ለ”  የመለስን አጠቃላይ አሰራርና የፖለቲካ አቅጣጫ የሚቃወም ሊሆን ይችላል:: እነዚህ በቁጥር በዛ ያሉ ነገር ግን በሃገሪቱ መስተዳድርና አገዛዝ ከፍተኛ ስልጣን የሌላቸው ናቸው:: በቁጥር ግን በዛ ያሉና በአብዛኛው የግንባሩ የቀድሞና አዳዲስ አባልት ይደገፋል::  በትግራይ ሕዝብ ውስጥ ብዙ ተደማጭነት ያለው ሃይል ነው:: ይህ ቡድን የኢትዮጵያን ጥቅም በአንጻራዊ ደረጃ በተሻለ የሚአስጠብቅ  ቢሆንም ከሁሉም በላይ ግን የትግራይን ጥቅም ወደ ማስጠበቁ ያዘነብላል::
ቡድኖቹቢሸና  ምንሁኔታሊከሰትይችላል::
ቡድን “ሃ”ካሸነፈ ሃይሉን አጠናክሮ የበላይነትን ለማግኘት በቡድን “ለ” ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ያደርሳል:: ይህንም ቅጣት ለሌሎች ተቃዋሚወች ማስተማሪያ በትር አድርጎ ሊቆጥረው ይችላል:: መለስን እያወደሰና እያሞካሸ፣ የሰራውንና ያቀደውን እያገዘፈ አገዛዙን መስመር ለማስያዝ ብሎም ሕዝብንና አገርን ለማረጋጋት ይጥራል:: መለስ የጀመረውን ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የማፈራረስ ተግባር በሰፊው ያካሂዳል:: ከኢትዮጵያና ትግራይ ህዝብና  ከተቃዋሚወች ከፍተኛ ተቃውሞ እምቢ አልገዛም እምቢ ለሃገሬና ለነጻነቴ የሚለው ግፊት በተጠናከረ መልኩ ይስፋፋል::
ይህ ቡድን የሚጠቃና የሚሸነፍ ከመሰለው የድረሱልኝ ጥሪ ለኤርትራ መንግስት ማቅረቡ አይቀርም ::  ኤርትራም ጥሪውን በደስታ ተቀብላ ታስተናግደዋለች:: ኤርትራም አፋኝ ቡድን ባስቸኳይ ልካ የቡድኑን የአገዛዝ መዋቅር በጇ ታስገባለች::  ከባድሜ ጦርነት በኋላ ያጡትን የምኒልክ ቤተመንግስት በህጋዊነት ይረከባሉ:: በጦርነትና በዲፕሎማሲ ያላገኟትን ባድሜንም በጅመንሻነት ከነበረከት ቡድን ያገኛሉ:: የጸጥታ የኢኮኖሚ የማህበራዊና የወታደራዊ መዋቅሩን በቁጥጥር ስር ታደርጋለች:: የኤርትራ ቀጥተኛ የቅኝ አገዛዝ በኢትዮጵያ ላይ ይነግሳል:: ኢትዮጵያንና ሕዝቧን እንዲሁም ኢኮኖሚዋን በቁጥጥር ስር በማድረግ ኢትዮጵያን እያለበ ያደርቃታል:: በብሄር ብሄረሰብ እየከፋፈለ ኢትዮጵያን የማፈራርሱን ተግባር ዳር ያደርሳል:: የመቶ ዓምት ቤት ስራ እሰጣለሁ ብሎ የፎከረውን ተግባራዊ ለማድረግ አዲስ እድል ያገኛል:: እነበረከት ስሞኦንም በደስታ የሚተባበሩት ይሆናል::
ይህ ከሆነ በአገሪቱ ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ ቁጣ ተነስቶ ብጥብጥ ሊፈጠርና ወደ እርስበርስ መተላለቅ  ልታመራ ትችላለች:: በተጨማሪም የኤርትራ መንግስት ይህን እድል ካገኘ በራሱ አገር የሚንቀሳቀሱትን የኢትዮጵያ መንግስት ተቃዋሚወችንና የነጻንት ግንባሮችን ከሃገር በማስወጣት ለኢትዮጵያ መንግስት ያስረክባል:: ይህን እንኳን ማድረግ ቢሳነው እንዳይንሰራሩ አድርጎ ሊበትናቸው ይችላል::
ቡድን”ለ”በአሸናፊነት ከወጣ  የኢትዮጵያ  የፖለቲካ  መልካ ምድር በዓይነት በስፋትና በመጠን ሊቀየር ይችላል:: የጠቅላይ  ምኒስትርነቱን ቦታ ከወሰደ ከዚህ የሚከተሉት ዓበይት ከስተቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ:: ለ21ዓመታት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በተቃቃረባቸው ዓበይት ሳንካወች ላይ እርምጃ ወስዶ ከህዝብ ጋር የሚቀራረብበትንና ሊደመጥ በሚችልበት ጉዳዮች ተግባሮችን ይፈጽማል:
በመለስ ፈላጭ ቆራጭ ትእዛዝ ኢትዮጵያንና በኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት በመንግስት የወጡትን የፖለቲካ ፖሊሲወችና ሕጎች በይፋ በማውገዝ መሰረታዊ ያሰራርና ያመለካከት ለውጥ ያደርጋል :: ይህ ቡድን በቀጥታም ሆነ በተዛዋሪ የመለስ የጥፋት ተለእኮ ተባባሪ የነበረ በመሆኑ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ለተደረጉ ጥፋቶችና ስህተቶች ህዝብን ይቅርታ ጠይቆ ሕዝብን ለማረጋጋት ይሞክራል::
አገሪቱን ባህር አልባ ያደረገውን የመለስ ዜናዊ ፖሊሲ ቀልብሶ በአስችኳይ አሰብን ወስዶ አገሪቱ ከቀይባህር እንደገና ውሃ እንድትጠጣ ማድረግ ይሞክር ይሆናል:: ይህን ለማድረግ አስፈላጊውን የዲፕሎማሲ ስራ ከተባበሩት መንግስታት ከሃያላን መእራባዊያን ሃገሮች ከአፍርካ ማህበር ከቻይናና ከራሽያ ጋር በድርድርና በሰላም አሰብን ማስመለስ ይሞክር ይሆናል:: የሰላሙ መንገድ ካላዋጣ ወይም ብዙ ካላስሄደው በኅይል አሰብንና ሌሎች አወዛጋቢ የድንበር ይገባኛል ጥያቄወችን መፍትሄ ሊሻ ይችላል:: ይህን ካደረገ የኢትዮጵያን ህዝብ ከጎኑ ለአጭር ጊዜም ቢሆን ሊአሰልፍ ይችላል::
ከዚህ በኋላ የአንድ ፓርቲና የአንድሰው ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ያረጀ ያፈጀ መሆኑን ለኢትዮጵያ ህዝብ አስታውቆ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት የሚገነባበትን መንገድ ሊአመቻች ይችል ይሆናል:: ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ አድርጎ በስደት ላይ ያሉ የተቃዋሚ ድርጅቶችም ሆኑ ፖለቲከኞች ወደ ሃገራቸው ተመልሰው አገራቸውን እንዲታደጉና እንዲገነቡ ጥሪ ሊአደርግ ይችላል:: የሕግ የበላይነትን በአዋጅና በተግባር መተግበር ለተፈጻሚነቱንም ቅድመሁኔታወችን ሊአመቻች ይችላል:: የመከላከያ ሃይሉና ሰራዊቱ በፖለቲካ እንዳይሳተፍ በህግ ይደነግጋል::
ግምት 3- የወያኔ ድርጅት የሃገሪቱን የፖለቲካ ሁኔታ አስተውሎ በአረብ ሃገራትየተካሄደውን አብዮት ተመልክቶ ለራሱና ለሃገሪቱ ህልውና ሲል ከተቃዋሚ የፖለቲካድርጅቶች ጋር ተቀራርቦ መስራትን ቢመርጥ ብሎ ማሰብ ይቻላል::
ይህን መንገድ ተጠቅሞ ከሰራ የሚከተሉት ሊከሰቱ ይችላሉ:: ከሁሉም የተውጣጣ ጊዚያዊ የሽግግር መንግስት ሊቋቋም ይችላል:: አወዛጋቢ የሆነውን ህገ መንግስት እነደገና ተጠንቶ ለሕዝብ ውይይት ማቅረብ:: ከትቃዋሚወች ጋር ተቀራርቦ በመስራት ድርጅቱ 37 ዓመታት በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ለፈጸማቸው የፖለቲካ የኢኮኖሚና የማሕበራዊ ስህተቶችና ወንጀሎች ተቀብሎ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ መጠየቅ:: በተቃዋሚ ጎራ የተሰለፉትም እንደዚሁ ላደርጉት ጥፋት  ሕዝቡን ይቅርታ መጠየቅና ለሃገሪቱ አዲስ የፖለቲካ የኢኮኖሚና ማህበራዊ አቅጣጫ መትለም:: በአጠቃላይ በኢትዮጵያ አገራዊ እርቀሰላም የሚፈጠርበት ሁኔታ ሊከሰት ይችላል::
ግምት 4- ዓለማቀፉ ሕብረተሰብ የኢትዮጵያን መንግስትና ተቃዋሚውን አደራድሮየሃገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታ የሚረጋጋበትን መንገድ መቀየስ::
የወያኔ መንግስት በራሱ አነሳሽነት ከተቃዋሚው ጋር አብሮ መስራትን ከፈለገ በሚለው መላምት ዓይነት የሽግግር መንግስት ሊቋቋም ይችላል:: የዓለም አቀፉ ሕብረተሰብ የፖለቲካ ምህዳሩ ሰፍቶ ሁሉም ተጫዋቾች በእኩልነት የሚወዳደሩበት የፖለቲካ መስመር ሊቀየስ ይችላል:: የዓልም አቀፉ ሕብረትሰብ ለሽግግር መንግስቱ ሙሉ እውቅና በመስጠት የፋይናንስ የመዋለ ነዋይ የቁሳቁስና የዲፕሎማሲ ድጋፍ በሰፊው በመስጠት አገሪቱ ሰላማዊ የሆነ የፖለቲካ ሽግግር ልታደርግ ትችላለች:: በዚህም ዲፕሎማሲያዊ ድርድር አገሪቱ ወደብ እንዲኖራት ለማድረግ የሚቻልበት ሁኔታ ይፈጠራል:: ጉልበት ተጠቅሞ ሕይወት አጥፍቶ ገንዝብ ከስክሶ ልማትንና ኢኮኖሚን አድቅቆ አሰብን ከማስመለስ በሰላማዊ መንገድ በዓለም አቀፉ ሕብረተሰብ እርዳት ትብብርና እውቅና  ሊፈጸም ይችላል:: አለማቀፉ ሕብረተሰብ አዲስ ሕገመንግስት የሚረቀቅበትን ሁኔታም ሊአመቻች ይችላል::
ግምት 5ከላይ የተጠቀሱት ሁሉ ሳይሆኑ ሕዝቡ መብቱን ለማስከበር በአንድነትሆብሎ በአመጽ ወያኔን ከስልጣን ሊአስወግድ ይችላል:: ይህ ከሆነ መሰረታዊ የሆኑከስተቶች ይፈጠራሉ:: ከነዚህም ከፊሎቹን እንመልከት::
ድርጅቱ ያለ የሌለ ሃይሉን ተጠቅሞ የሕዝብን ዓመጽ በኅይል ለማጥፋት ይሞክራል:: ያስቸኳይ ጊዜ አዋጅም ሊታወጅ ይችላል:: በሚደረገው ግብግብ ብዙ ሕዝብ ያልቃል ንብረት ይወድማል:: የሃገሪቱ ደካም ኢኮኖሚ ይንኮታኮታል:: ቁጥሩ ሰፊ የሆነ ሕዝብ ወደጎረቤት አገሮች ይሰደዳል:: በተቃዋሚው በኩል የጎበዝ አለቃ ተፈጥሮ የህዝቡን አምጽ አስተባብሮ የሚመራ ሊፈጠር ይችላል:: ሁኔታውን  በመመልከት ባለስልጣናት ንብረትና ቤተሰብ ወደውጭ ማሸሽ ይጀመራሉ:: የውጭ ዲፕሎማቶችም የቢሮ ኅይ ላቸውን ይቀንሳሉ ወይም ዘግተው ከሃገር ይወጣሉ :: በዚህ ጊዜ ከፍተኛ የሆነ ስራዓት አልበኝነት ሊከሰት ይችላል::ኢትዮጵያም እንደሶማሊያ የውድቀት ሃገር (failed state) ትሆናለች::
ሁኔታው እይጠጠረ ከመጣ በየጓዳው ተደብቆ የነጻነት ትግል የሚአካሂደው ቡድን ሁሉ ብቅ እያለ ነጻነቱን ሊአውጅ ይችላል:: ወያኔ በሕዝብ አመጽ የሚወድቅ መስሎ ከታየውና መውደቁን ማስቀረት የማይቻለው ከሆነ ለተለያዩ ነጻ አውጭ  ግንባሮች አንቀጽ 39ኝን ተጠቅሞ ነጻነታቸውን ሊአውጅ ይችላል:: ድርጅቱ ሰራዊቱን ይዞ ወደ ትግራይ ይሸምቅና ነጻነቱን ያውጃል::
ከዓለም አቀፍ አኳያ በአፍሪቃ ቀንድ ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ የኢኮኖሚና የማሕበራዊ ቀውስ ይፈጠራል:: አገሪቱ በአክራሪ እስላሞች የተከበበች እንደመሆኗ መጠን አልካይዳና አልሸባብ ከፍተኛ የሆነ ገዥ መሬት አግኝተው የጥፋት ውሃዋቸውን መዝራት ይጀምራሉ:: ዩኤስ አሜሪካና ሌላው መእራብ ዓለም አክራሪ እስልምናን ለመዋጋት በሚል ሽፋን ቀጥተኛ የሆነ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ይጀምራሉ:: ባለሰማያዊ ኮፊያ ያላቸው የተባበሩት መንግስታት ወታደሮችም ሰላምንና ሰባዊ መብትን ለማስጠበቅ በሚል ሽፋን የሰላም ጠባቂ ሆኖ ኢትዮጵያን ሊይዝ ይችላል:: ሁኔታው እጅግ የሚበላሽ ከሆነ የኤርትራ መንግስት በተባበሩት መንግስታት ድርድር ያጣትን ባድሜን በቁጥጥሩ ስር ያደርጋል:: ከተቻለውም ትግራይን ተቆጣጥሮ የሱ ደጋፊ የሆነ የትግራይ መንግስት አቋቁም ሊገዛ ይችላል::
በሳውዲ አረቢያ ገንዝብ የሚደገፈው ወሃቢ የተባለው አክራሪ የስላም ቡድን አገሪቱን የጦር አውድማ አደርጎ የስልምና አገዛዝና የሻሪያ አገዛዝን ሊአሰፍን የሚችልበት አጋጣሚ ያገኛል:: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ክርስቲአኖች ሃይማኖታቸውን ለመከላከልና ለመጠበቅ ሊንቀሳቀሱ ይችላሉ:: ነገር ግን ይህች ቤተክርስትያን የውስጥም የውጭም ጠላቷ ብዙ በመሆኑ አቅሟ የደከም እንድሚሆን ይገመታል:: ለምሳሌ በምእራቡ ዓለም የሚገኘው ክርስትያን ኦርቶዶክስን ለማዳከምና ለማጥፋት ሁልጊዜም የሚጥር ስለሆነ ብዙ የፋይናንስና የቁሳቁስ እርዳታ አይለግሳትም:: እርሷን ለመከላልከልና ለመጠበቅ በቂሃብትና ንብረት የላትም:: የፔትሮ ዶልላር እርዳት ከሚአገኘው የስልምናው ሃይማኖት ጋር የሚመጣጠን ድጋፍ ማግኘት አትችልም:: እነአላሙዲንና የሳውዲ ነገስታት የእስልምና ሃይማኖት ተለኳቸውን  ያሟላሉ ብሎ ማሰብ ይቻላል:: ሁለተኛው ግራኝ መሃመድም ሊነግስ ይችላል::
ሌላው በፕሮቴስታንቱ በኩል የሚመጣው ተጽእኖና ግፊት ነው:: ይህ ሃይማኖት በሚቻለው ሁሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስን ጨርሶ ለማጥፋት ሃብቱንና ስንቁ ቋጥሮ ተነስቷል:: ይህ ግፊት ደግሞ የሚመጣው ዩኤስ አሜሪካ ካለው ሃይለኛው ፕሮቴስታንት ቡድን ስለሆነ ኦርቶዶክስን ለማውደም ማንኛውንም የገንዘብ የቁሳቁና የጉልበት መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም:: ፕሮቴስታንቱ ከኦርቶዶክሱ ጋር ከመወገን ይልቅ ከአክራሪ እስላም ጋር መወገንን የሚመርጥ ነው:: በዚህም አነ በዚያ ኦርቶዶክሱ ማህበረሰብ በጣም ስለሚዳከም የስልምና ሃይማኖትና አክራሪነት አሽናፊ ሆኖ ሊወጣ ይችላል:: አክራሪው ቡድን በሃብቱ ብቻ ሳይሆን ሕይወቱን በአጥፍተህ ጥፋ እየሰዋ ዓላማውን ከዳር የማድረስ ኅይሉ ግምት ውስጥ መግባት አለበት::
ከአንዳንድ ሰወች ጋር ይህን አንስቸ ስነጋገር ብዙወቹ ይስቁብኛል አንዳንዶቹ ደግማ ይህ በኢትዮጵያ ምድር ሊሆን የማይችል ነው በልው ይደመድማሉ::አይሆንምን ጥለሽ ይሆናልን አስቢ ይላል ያገራችን ተረት::  አዲሳ አበባ በሩዋንዳ ኢምባሲ አካባቢ ያሉትን የሶማሌ ጥገኞች በመርካቶና በተክለሃይማኖት እንዲሁም በሃረር አካባቢም ያሉትን ያየ አክራሪ እስልምና ኢትዮጵያን አያሰጋም የሚል ካለ የሃገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታና የአካባቢውን የፖለቲካ መልካአ ምድር ያላስተዋለና ያላገናዘበ ሰው መሆን አለበት::  ለማንኛውም የንጹሃን እስላም ኢትይጵያኖችና የክርስቲአይኖች አምላክ ኢትዮጵያን ይጠብቅ:: ኢትዮጵያም እጆቿን ወደ እግዚብሔር እንደዘረጋች ትቀጥል::
ከላይ ከተጠቀሱት መላምቶች ውስጥ ሊሆኑ የሚችሉትን አንባቢ የራሱን ግምትናምርጫ ማድረግ ይችላል:: በእኔ አመለካከት በከፍተኛ ደረጃ ሊሆን ይችላል ብየየምገምተው በቁጥር ሁልተ የተጠቀሰውን ነው:: የታለመው ከሽፎ ሁኔታው ሲጠጥርጠጣሩ እንዲላላ የላላውን ወጥር በሚለው የገሞራው ግጥም ነግግር መሰረት ከሁለቱ ብድኖች መካከል ቡድን “” ባሸናፊነት ይወጣል በሚለው ላይ አንድ ሳንቲሜንአስቀምጥና ባንኮ የሚለውን ካርታ ጨዋት እጫወታለሁ::
ቸር ይግጠመን
ሁላችንም ለኢትዮጵያችን በአንድነት ዘብ እንቁም

No comments:

Post a Comment