ሄኖክ የሺጥላ
ይሄ ሃይሌ ለ ካ ሆደ ቡቡ ነው:: ያን ጊዜ በኦሎምፒክ ፖል ቴርጋትን አሸንፎ ሲያለቅስ እኮ እኔ ለባንዲራው መስሎኝ አብሬው አነባሁ:: ወይ ጊዜ… ለካ እንዲህ ገር ሰው ኖረሃል…::መቼም ሰው ለምን አለቀስክ አይባልም ግን ጠቅላይ ሚንስትሩ ሃውልት እንድይሰራላቸው ያደረገው ንግግር በጣም ሊተኮርበት የሚገባ ነው:: ሃይሌ ይሄ አሁን ካንተ ይጠበቃል?… እሳቸው የሚወዱትን “አስመራ መንገድ” ባንተ ስም ሲተኩት እኮ እንዲህ ውለታ ትበላለህ ብለው አልነበረም….እኔ እንደውም ጠቅላይ ሚንስትሩ የጀግኖች ጀግና ስለሆኖ….ያንን ለማሳየት ሳሞራ የኑስ እንኮኮ ብሎዋቸው የሚያሳይ ሃውልት ይሰራላቸው ትላለህ ብዬ ስጠብቅ እንዲህ በቀላሉ ሃውልት አያስፈልጋቸውም ብለህ ታስደነግጠናለህ?
አንተ ህውሃት እኮ እንኩዋን ለመሌ ለትግል አጋራቸው አህዪት እንኩዋ ሃውልት ያቆመ ጽኑ ድርጅት ነው:: ደሞ ድንጋይ በበዛበት ሃገር ተወልደን የምንን ሥስት? ደሞ ስራቸውን ለምን ታሳንስብናለህ… እሳቸው ለመሆኑ በቃላት ብቻ የሚገለጹ ናቸው? ኢንዲሁ ዝም ብሎ ‘የጀግኖች ጀግና” ተብለው የሚታለፉ ናቸው….? ሰው ስላሳቸው ስንት እንደሚል በሰማህ…”" አኢትቭኢ እንክዋ ኢትዮጵያ አርቆ አሳቢ መሪዋን ተነጠቀች ብል ሆድ በሚበላ አገላለጥ አስቀምጦታል:: ባለቤታቸው…ሲያለቅሱ ብትሰማ የቅርብ ሰዎች ስለሳቸው እንዴት ኢነሚናገሩ ይገባህ ነበር…. ይኸውልኽ ወይዘሮ አዜብ ምን አሉ መሰለኽ…”ቤታችን ቀዘቀዘ…አልጋው ባዶ ነው”…. “ይሄ የኛ ቤት ነው ኢንክዋን ደህና መጣችሁ መለስ ግን የለም” ይህ የቀዳማይ እመበቲቱ ለቅሶ ስንት ነገር አስታወሰኝ መሰለህ…ያዲሳባ አልቤርጎ አከራዮች ለቅሶ ትዝ አለኝ…ቀጥሎም…ይህ የኛ ቤት ነው እንኩዋን ደህና መጣችሁ ሲሉ… “አይ ሴትየቱ መለስ ከሞቱ መሁዋላ መጽሃፍ ቅዱስ ማንበብ ጀምረዋል…ለዚህም ምስክሩ ገና ኦሪት ዘፍጥረት ጋ ናቸው.. የአብርሃምን ታሪክ አንብበው ሳይጨርሱ ነው ሬሳው ቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት የደረሰው”….. ሌላኛዋ ቀጠል አርገው ” አንበሳ ሃወይ” ሲሉ በቃ ምርር ብዬ አለቀስኩ…. “ከሞተ አንበሳ እንደ ሃይሌ ያረጀ አንበሳ ይሻላል አልኩ በልቤ” የልቤን በልቤ ተናግሬ ሳልጨርስ “አንበሳ ሲያረጅ የዝንብ መጫወቻ ይሆናል የሚለው ትዝ አለኝና…” “ታዲያ ምነው ሃይሌ የወሬ መጫወቻ ሆነ አልኩ?”እዩት ንጉሱ ግርማ ሞገሱ” ተብሎ የተዘፈነለትም ሰው አንተ መሆንህን ሳስብ…”ቴዲን ማንም ሸውዶት ባያውቅም ሃይሌ ግን ሩጦ ሸወደው” አልኩኝ:: ለነገሩ ዘፈኑ ሪሚክስ ተደርጎ…
“እዩት ንጉሱ ግርማ ሞገሱ
አለቃው ሲሞት ያለቅሳል እሱ
ይቺ ባንዲራ ናት እድለኛ
እግዜር አኮራት….
እግዜአብሄር ኬኛ”…ነው አሉ ነገሩ::
አለቃው ሲሞት ያለቅሳል እሱ
ይቺ ባንዲራ ናት እድለኛ
እግዜር አኮራት….
እግዜአብሄር ኬኛ”…ነው አሉ ነገሩ::
እንደውም ለአንድ ወዳጄ ሃይሌ እንዴት እንዴት እንዳረገው ስነግረው… “እንዴት ነው ቀዳማዊ እመቤት በእንባ ለክተው ሊያጩነው እንዴ ሲለኝ”… ባንድ ወቅት ናሽናል ጆግራፊ መጽሄት ላይ ሰለ አቦ ሸማኔ ይሁን ሰለ ቡፋሎ ያነበብኩት ትዝ አለኝ:: ቡፋሎዎች እንበለው… አዎ ሴት ቡፋሎዎች ወንድ ቡፋሎዎችን ለድሪ የሚመርጡት ከፍተኛ ድምጽ ማውጣት የቻለውን ሲሆን ይሄም ባለ ረጅም የአየር ቡዋንቡዋ (the one with longer wind pipe) ከሌሎቹ የተሻለ አቅም እንዳለው ሲለሚያሳይ ይመረጣል.. ይላል.. ይህ በአናብስቶችም ህይወት ውስጥ ያለ ነው… (teritorial integrity) እና ወዘተንም ጨምሮ… እና ሃይሌንና መሰሎቹን ሲያለቅሱ ስመለከት ሰው የመጣው ከጦጣ ነው የሚለውን ላምን ጥቂት ቀርቶኝ…. ግን እግዚአብሄር ሰሞኑን እያደረገ ያከውን ተአምራት ተመልክቼ ሃሳቤን ቀየርኩት:: እናላችሁ ሃይሌ አለቀሰ… ግን ያለቀሰው ለአለም ሲኒማው ይሁን… ለፎቁ ይሁን…. ለልተመነዘረው ዶላሩ ይሁን… በስሙ ስለተሰየመው አውራ ጎዳና ሲል ይሁን… ወይስ ህዝብ ጠልቶት ከሱ ኢርዳታ አንፈልግም እንዲሉ ፈልጎ ይሁን…. እንደ ተቅላይ ሚንስትራችን ሞት ይዘገያል ኢንጂ እውነቱ መታወቁ አይቀርም… ለማንኛው… ሰርቆ ከማሰብ እጅን መሰብሰብ ነው የሚሉት… እኔም አልቅሶ ከማስለቀስ ተደብቆ ማልቀስ ብያለሁ::
ቸር እንሰብት
ሄኖክ የሺጥላ
ሄኖክ የሺጥላ
No comments:
Post a Comment