Translate

Thursday, August 23, 2012

ተወዳጁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቃሊቲ እስር ቤት ተወሰደ!



የፍትህ ጋዜጣ አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ ባለፈው ሳምንት ውስጥ ፍርድ ቤት ቀርቦ እንደነበር ይታወቃል። በቀረበበትም እለት በርካታ አድናቂዎቹ እና የፍትህ ጋዜጣ አንባቢ ወዳጆች ፍርድ ቤቱን አጨናነቀውት የነበረ ቢሆንም ዳኛ አልተሟላም በሚል ሰበብ ለዛሬ ነሐሴ 16/2004 ዓ.ም  ተቀጥሮ ነበር።

በዛሬው እለት የተመስገንን ክስ የተመለከተው ፍርድ ቤቱ ጋዜጠኛው የተከሰሰበት ወንጀል ዋስትና አያሰጥም በሚል ወደ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት እንዲወሰድ እና በቀጣይ ነሀሴ 28/ 2004 ዓ.ም እንዲቀርብ ቀጠሮ ሰጥቷል።
አቃቤ ህግ “ፍትህ ጋዜጣ ትታገድልኝ” ሲል ኮሚክ የሆነ ጥያቄ ፍርድ ቤቱን የጠየቀ ሲሆን፤ ጋዜጣዋ ከአንድ ወር በፊት የጠቅላይ ሚኒስትሩን በጠና መታመም ብሎም “ሞተዋል” የሚለውን ጭምጭምታ ከተለያዩ ምንጮች ጠቅሳ ልታትም ስትል ተገኝታለች በሚል መታገዷ ከዛ በኋላም  ታትማ እንደማታውቅ አቃቤ ህግም ተመስገንም ዳኛውም እኛም እናውቃለን!
በመጨረሻም
አስተያየት
ተመስገን ደሳለኝ በፍትህ ጋዜጣ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መታመማቸውን እና ሞቱ የሚባል ጭምጭምታም እንዳለ ሲዘግብ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ተወሰደ። ጋዜጣውም ታገደ። ታድያ፤ ከትላንት ወዲያ በጠዋቱ የጠቅላይ ሚኒስትሩን መሞት መርዶ ነግሮን እስከ አሁንም ድረስ በዋሽንት እንጉርጉሮ እንባ የሚያራጨን ኢቲቪስ ማነው የሚያስረው!?
ኧረ የፍትህ ያለ!  ብንል የሚሰማን ይኖር ይሆን!?

No comments:

Post a Comment