Translate

Tuesday, August 28, 2012

Dagem Ahunem

የአቶ መለስ አስከሬን ለአንድ ወር ሙሉ ከተቀመጠበት ማቀዝቀዣ ፍሪጅ ውስጥ አውጥተው አዲስ አበባ በገባበት ምሽትና ወ/ሮ አዜብ የባለቤታቸውን አስከሬን በተረከቡበት ወቅት፣ ……. ወይኔ ተቀጣሁ፣ እንኳን ደህና መጣችሁ፣ …… መለስ ግን የለም፣ ….. ቤታችን ቀዝቅዟል፣ …… አልጋው ባዶ ነው፣ ሲሉ የተሰሙት ትራሱን በእጃቸው አቅፈው ይዘው ነበር። በመሪር ሀዘን ውስጥ ለምትገኙት ለአቶ መለስ ዜናዊ ቤተሰቦች፣ ዘመዶች፣ ጓደኞችና ወዳጆች የማቀርበው አንድ መሠረታዊ ጥያቄ አለኝ፤- በአቶ መለስ፣ በሕወሓት ከፍተኛ ባለሥልጣናትና በእርሳቸው እውቅና (ወ/ሮ አዜብ መስፍን) የወልቃይ ጠገዴ እና ጠለምት ጀግና ሕዝብን የእኩይ ተግባራቸው ተባባሪ ባለመሆኑ ወንዶች እየተመረጡ፣ የአልጋ ቁራኛ (በሽተኛ) ሳይቀር የወያኔ ስቆቃ መፈፀሚያ ባዶ-6 በተባለ እስር ቤት በማጎር በተፈፀመባቸው ስቃይ ብዛት ሰውነታቸው እስኪተላ ተገርፈው ዘር ማጥፋት በሚባል መልኩ የተጨፈጨፉ፣ በ21 ዓመታት ብልሹ አስተዳደር ሳቢያ በወለጋ፣ በአርሲ፣ በጋምቤላ፣ በሶማሊያ፣ በቤንሻንጉል፣ በሐረር፣ በሞያሌ፣ ወዘተ… በብሔርና ጎሳ ግጭት ምክንያት በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የአንድ ቤተሰብ አባላት የተጨፈጨፉ፣ ዋጋቢስ ለሆነ ኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በአገር ሉዓላዊነት ስም ተግዘው ደመ- ከልብ የሆኑ፣ በቀናነት አገራቸውንና ወገናቸውን ሲያገለግሉ በአቶ መለስ ዜናዊ ፀጥታ አስከባሪ ተብየዎች በጠራራ ፀሐይ በጥይት የተገደሉት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አመራር የነበሩት የአቶ አሰፋ ማሩ፣ በወያኔ እሥር ቤት ማቀውና በሽተኛ ተደርገው የሞቱት የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን አለኝታ የነበሩት የፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስና የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት አባላትን በማናለብኝና እብ
ሪት የተገረፉ፣ የተሳደዱ፣ በአደባባይ ላይ የተረሸኑና እስካሁንም ያሉበት ያልታወቁ፣ እንደነ ሸብሬ ደሳለኝ ዓይነት ለጋ ወጣቶች፣ ሕፃናት ልጆች፣ ሽማግሌዎችና አሮጊቶች፣ በአቶ መለስ ዜናዊ ቀጥተኛ
ትዕዛዝ ርህራሄና ስብዕና እንደሌለው በሚነገርለት በአረመኔ አጋዚ የትግርኛ ተናጋሪ ቅልብ ወታደር በጎዳና፣ በበር፣ በመጫዎቻ ሜዳ ላይ ጭንቅላት ጭንቅላታቸው እየተመታ የተገደሉ፣ አካላቸው የጎደለ፣ የተገረፉ፣ የተሰደዱና የአዕምሮ በሽተኞች የሆኑበት የ1997 ብሔራዊ ምርጫ ተጎጂዎች፣ በሚደርሰው ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ቀውስ ሳቢያ ወደ አረብ አገራት በመሰደድ የሚሰቃዩ፣ ህይወታቸውን የሚያጠፉና በአሠሪዎቻቸው የሚገደሉ ለጋ ሴት እህቶቻችን፣ በአቶ መለስ ዜናዊ አምባገነን አስተዳደር ስቃይ፣ ግርፋት፣እስርና ግድያ ሲሸሹ ውሀ ያስቀራቸውና በሰውነት የውስጥ አካል ነጋዴዎች እየተገደሉ በሰሃራ በረሃ ያለ ቀባሪ አሸዋ ውስጥ ተቀብረው የቀሩ፣ የወያኔው ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለቅፅበት እንኳን ያላያቸው እንዲሁም የትኛውም የዜና አውታር ያልዳሰሳቸው ነገር ግን
ቤት የሚቆጥራቸው፣ በተረሪስት ስም በውሸት ድራማ ተቀናብሮ በቃሊቲ፣ ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ በሚገኘው ቀሌንጦና የተለያዩ እስር ቤቶች ታስረው የሚማቅቁና በእስር ቤቶች በስቃይ ብዛት ህይወታቸው ያለፈ፣ ወዘተ…… ቤተሰቦች፣ አፍቃሪዎች፣ ወላጆች፣ ዘመዶች፣ጓደኞችና ወዳጆችስ ስቃይ፣ መሪር ሀዘን፣ እሮሮ፣ ደም እንባ ማንባት፣ የመሳሰሉት ለአንዲት ሰኮንድ ትዝ ብሏችሁ ያውቅ ነበርን???
እንግዲያውስ እንደናንተው ወይም ከእናንተ እጅግ በላቀ መጠን ተንሰቅስቀዋል፣ ሀዘናቸውን በቀል ለሚመልስ አምላክ ተንበርክከው በዓይናቸው ያሳያቸው ዘንድ አንብተዋል፣ እስካሁንም እያነቡ ይገኛሉ። እነዚህ ከላይ የተጠቀሱትን ተጎጂ ቤተሰቦች ሐዘን ከአቶ መለስ ቤተሰብ የከፋ የሚያደርገው ወ/ሮ አዜብ መስፍን ሙሾ እንዳወረዱት ዓይነት ብቻ ሳይሆን ልጆች ያለ አሳዳጊ መቅረት፣ የእለት ጉርሳቸውን በማጣት ወንዶች ልጆች የጎዳና ተዳዳሪ መሆንና ሴቶች ልጆቻቸው በመንገድ ዳር በመቆም ክብረ-ሥጋቸውን ለመሸጥ መገደዱ፣ በድህነት ተቆራምደው ያሳደጓቸው ልጆቻቸው በመገደላቸውና ከአረመኔው
ሥርዓት ሲሸሹ ከታሰበበት ቦታ ሳይደርሱ በመንገድ ላይ የቀሩ የስደተኛ እናቶች ጧሪ አልባ መሆን ወዘተ፣ ወዘተ፣ ወዘተ፣….ነው።
ስለዚህ እናንተ የዚህ ሀዘን ተጠቂዎች የሆናችሁና በዚህ ሥርዓት ስም ሕዝብን ያሳዘናችሁና የበደላችሁ ሆይ የኑሮ አጋር ያደረጉት፣ ያፈቀሩት፣ የወደዱት፣ የወለዱትና ያሳደጉት ሲገደል ወይም ሲሞት እንደዚህ ከማሳዘን፣ መሪር እንባ ከማስነባቱም በላይ ብቸኝነትን፣ ጎደሎነትን፣ ረዳት አልባነትን፣ አለመረጋጋትን፣ በሽተኝነትንና እብደትንም ስለሚያስከትል ነገም በእኔ በማለት ካለፈው ስህተት ተምራችሁ በመተሳሰብና በመተዛዘን ለመኖር ፍርድን የማያጓድል እግዚያብሔር ማስተዋልን ይሰጣችሁ ዘንድ ምኞቴ ነው።ኢትዮጵያንና ሕዝቧን እግዚያብሔር ይባርክ!!!!
August 26, 2012,
ፀሐፊውን በ belete_z@yahoo.co.uk ሊደርሱት ይችላሉ፤፤

No comments:

Post a Comment