ላለፉት ሃያ አንድ አመታት የወያኔ ቁንጮ የነበረው መለስ ዜናዊ ሞት በመንግስት ደረጃ ይፋ ከተደረገ እነሆ ቀናት ተቆጥረዋል።ይሁንና በአንድ ሰው አምባገነንነት ላይ የተመሰረተው
የወያኔ መንግስት ከወዲሁ ግራ መጋባቱን የሚያሳብቁ ሁኔታዎች ከመከሰታቸውም ባሻገር ይህንን የዕውር ድንብር ግራ መጋባት ለመሸፈንና ብሎም በቀጣይ በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት /Legitimacy/ ለማግኘት ወያኔ እየወሰደ ያለውንና ሊወስድ እየተዘጋጀባቸው ስላሉ እርምጃዎች እና የእርምጃዎቹን የአጭር እና የረጅም ጊዜ አንድምታ መፈተሽ የዚህ ፅሑፍ ዋና አላማ ይሆናል።
ሀ. መለስን የህዝብ ልጅ ለማስመሰል የተደረገው ሩጫ
ወያኔ/ኢህአዴግ የመለስ አስከሬን አዲስ አበባ ከገባ ጀምሮ ያለመታከት እየታተረበት የሚገኘው አንዱ ክስተት መለስ ዜናዊን የህዝብ ልጅ ለማስመሰል የሚያደርገው ከንቱ ሩጫ ነው።ለዚህም፦
1. ቅጥረኛ ካድሬዎች እና የሥርዐቱ ተጠቃሚዎች በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ወጥተው እንዲያለቅሱ በማድረግ እና የለቅሶ ፕሮግራሙን በቀጥታ የቴሌቪዥን ሽፋን በመስጠት መለስ በህዝብ የሚወደድ ማስመሰል፤እንዲሁም እነዚህን ቅጥረኞችንና ጥቅመኞችን በቴሌቪዥን ቃለ ምልልስ እንዲያደርጉ በማድረግ “መለስ ቢለየንም ግቡን ወደፊት እናስቀጥላለን” በማለት የህወሃትን የግፍ አገዛዝ ቀጣይነት በዘወርዋራው ለቀሪው ህዝብ መልዕክት ማስተላለፍ፤
2. ባልተለመደ ሁኔታ ቤተ መንግስቱን ለተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ክፍት በማድረግ በኢትዮጵያውያን ወግ መሠረት በሟች ቤት እርም እንዲያወጡ በማድረግ ነገር ግን በመለስ ጓዳ መንግስት እና ህዝብን ያቀራርባል ብለው ያሰቡትን የህዝብ ግንኙነት ሥራ መስራት፤
3. በቀጣይነትም ወያኔ ያቋቋማቸው ሊጎች፧ፎረሞች እንዲሁም ማህበራት እያደረጓቸው ያሉ እና ያደርጓቸዋል ተብለው የሚጠበቁ “ጫጫታዎችን” /Noises/ በተለመደው የወያኔ የፕሮፖጋንዳ ማሽን ህዝባዊ መሰረት ያለው አስመስሎ ማቅረብን ያካትታል። ይቀጥላል…
No comments:
Post a Comment