Translate

Sunday, August 19, 2012

ወቅታዊ ዜና:-በኢድ አል ፈጥር በአል ላይ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከፍተኛ ተቃውሞ አሰማ


በኢድ አል ፈጥር በአል ላይ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከፍተኛ ተቃውሞ አሰማ
የተወሰኑ ሰዎች ታሰሩ
በአዲስ አበባ ስታዲየም የኢድ አል ፈጥርን በአል ለማክበር የተሰባሰቡ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ተቃውሞ አሰምተዋል። የክብር እንግዳው የነበሩት የአዲስ አበባ ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ እና የእስልምና ምክር ቤት ሃላፊዎች ንግግር እንዳይደመጥ እና እንዲቋረጥ ተደርጓል።
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተቃውሞው እንደተጀመረ የቀጥታ ስርጭቱን አቋርጧል። በተመሳሳይም በደሴ ፣ አዳማ ( ናዝሬት) , ጅማ እና ሻሸመኔ  የባለስልጣናቱ ንግግሮች  በተመሳሳይ መንገድ በተክቢራ እና በተለያዩ መፈክሮች እንዲቋረጡ ተደረጓል። የኦሮሚያ ቴሌቪዥን የአዳማውን ስገደት በቀጥታ ሲያሰራጭ የነበረ ቢሆንም ፣ የክብር እንግዳው የመንግስት ባለስልጣኑ ንግግር ሊያደርጉ ሲሉ በድንገት ተቃውሞው ሲበረታ የተወሰነ ክፍሉን ለእይታ አቅርቦ የቀጥታ ስርጭቱን አቋርጧል።

በአዲስ አበባ የፌደራል ፖሊሶች በስታዲያም አቅራቢያ ፣ ራቅ ብለው በኮመርስ ኮሌጅ ውስጥ እና በሜጋ አምፊ ቲያትር ግቢ ውስጥ ተደብቀው በተጠንቀቅ ይጠባበቁ ነበር።
የአዲስ አበባ የስግደት ፕሮግራም ህዝቡ ከማለዳው 12 ሰአት ጀምሮ በመጉረፍ በከፍተኛ ፍተሻ ወደ ስታዲየሙ ቢገባም በርካታ መፈክሮችንና የታሳሪ የሙስሊም መሪዎችን ፎቶ ግራፎች በመያዝ ተቃውሞን አሰምቷል።
ሙስሊሞቹ ነጭ ሪባን ይዘው እጃቸውን በማቆላለፍ፣ አፋቸውን በሜአዝ እጃቸውን በካቴና እንዲታሰር በማድረግ ፣ በመንበርከክ ተቃውመዋል።
በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በር ላይ የተሰባሰቡ ሙስሊሞች “ውሽት እስከመቼ፣ ለሙያውና ለግል ስእብናችሁ ስትሉ እውነት ዘግቡ፣ ውሸት ሰለቸን፣ ውሸታም ጣቢያ ” በማለት ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል።
ዘግይቶ በደረሰን ዜና ሲቪል የለበሱ የደህንነት ሀይሎች አንቀሳቃሽ ያሉዋቸውን ሙስሊሞችን በቁጥጥር ስር አውለዋል።

No comments:

Post a Comment