እረፍት ላይ ናቸው በያቅጣጫው ይነገራል ሁለቱም ቡችሎቻቸው ካገር ዉስጠም ሆነ ከውጭ ሃገር ሲያብራሩልን የሀኪም እነደሆን ረገጥ እያደረጉት ነው ሆኖም ወደ ስራ መመለሻቸውን ጊዜ ደግሞ በውል አያዉቁትም ያሉበትንም ቦታም ለደህንነታቸው ሲባል መግለጽ አስፈላጊ አይደለም ብለው ይዘጉታል
ይህ አገላለጽ ሁለት ነገሮችን እንዳሰላስል ያደርገኛል በመሆኑም አንድም አቶ ለገሰ ራሳቸውን የተሸሸጉ የጦር ወንጀለኛ አሊያም ያሉበት አካባቢ ኢትዮጵያዊያን ቢሄዱበት በባሀል
መቸም ያደቆን ሰይጣን ሳያቀስ አይቀርም ይባላልና ከውጭ ሃገር እንደተመለሱ ሁለት ጋዜጦች ዘግበው ወሬ ሆኖ ቀርቶዋል ምናልባት ባለቤታቸውን ጭምር ደጅ ያስጠኑት ጠንቓይ ከቃሊቲ ወደ ቤተ መንግስት ተዛውረው ይሆን ወይስ ሌላኛው እረፍት አሳቸውም ላይ ደረሶ ይሆን ለማናቸውም እርፉ ከተባሉ መቆየቱን ለማሳየት ትንሽ የምለውን አንብቡ
ባሁኑ ወቅት ያለበትን እስር ቤት በውል ባላውቀም አንድ ወቅት መንግስት ጋዜጠኞችን ጋብዞ በአማራ ክልል ያለውን የልማት ሁኔታ ሲጎበኙ ውብሸት ታዬ ያነጋገራቸው ገበሬ ያሉትን በ1997 ምርጫ ወቅት ኢህአዴግ ደክሞታልና እረፍት ስለሚያሰፈልገው አውቀን እንዲያርፍ በካርዳችን ብንነግረው አማራ ባፉ ከናንተ ጋር ነን እያለ በካርዱ አደባየን አለን ማለታቸውን ዘግቦልን ነበር ታዲያ ይህ አባባል ጥርስ ውስጥ አስገብቶት በበቀል የተካነው ያቶ ለገሰ መንግስት ለእስር ዳርጎት ፍዳውን እያየ ይገኛል ርእዮትም አነሳችው የተባለው መፈክር በቃ ማለት ድካም አለና እረፍት ይደረግ መልእከት ውጪ ሌላ ነገር ያዘለው የለም እስክንድርም ደጋግሞ የጻፈው አቶ ለገሰ ራስዎ ደክመው በጻፉትና ባጻፉት ህግ መሰረት ሲጸድቅም እስክሰታ መሳይ ተሊት የወረዱበትን ህግጋት ደረማመሰው ራሰዎ ህግ ሆነዋልና ወደ ህሊናዎ ይመለሱ (ህሊና ካለዎ) የባሰ ሁኔታ ተከስቶ ከቤናሊ እስከ ጋዳፊ እይነት ሁኔታ ከሚከሰት እረፍት ያስፈልጎታል መልእከት ነው
ለመድከማቸውም ማረጋገጫ 11.7 ቢሊዮን ዶላር ካገር መሸሹ 10 ሽህ ቶን ቡና አየር ላይ በኖ መቅረቱ ባሊስትራ ብረት ወርቅ ተብሎ ብሄራዊ ባንክ መገኘቱ ከሚጠቀሱት የጎሉት ሲሆኑ ራሳቸው የመንግሰት ሌቦች መኖራቸውን ማመንናቸው አፍንጫቸው ስር ያሉት ድልብ ቡችሎቻቸው በሃያ አመት ውስጥ በሚሊዮን የሚያወጡ ህንጻዎች መገንባታቸው አንዳንዶችንም እባካችሁ ለፓርቲህ ስጥ ብለው ለመደበቅ መሞከራቸው የቅርብ ጊዜ እውነታዎች ናቸው
ከእነዚህ ያገጠጡ እውነታዎች ባሻገር እረፍት እንዲያደርጉ የሚያሰገድዳቸው አንኩዋር ሁኔታዎች ግን በተለያዩ ጊዚያት በሲዳማ አኝዋክ አማራ ኦሮሞ ሶማሌና አዲሰ አበባ የፈጸሙዋቸው ጅምላ ጭፍጨፋዎችና የሀገሪቱን እስር ቤቶች በባነኑ ቁጥር ቅልብ ውሾችዎትን በመላክ የህዝብ ጉረኖ ማድረጋቸው ነው
እነዚህ ሁኔታዎች የምቀኛና ሙዋርተኛ አመለካከቶች እንጂ እኔን አይመለከቱም ብለው ሲመጻደቁ አበበ የሚባል ትንታግ ለሰላሳ ሴኮንድ እርቃናቸውን አሰቀርቶ ላለም ካጋለጠ ወር ባለሞላው ጊዜ ደብዛቸው ጠፍቶ ሰንበተው አሁን እረፍት ላይ እንደሆኑ አንዴ ካዲሳባ አንዴ ከዋሽንግተን መግለጫዎች እየተሰራጩ ነው
የህይወት ሩህያ ወሳኙ የማያመኑበት አምላክ ፈቃድ ስለሆነ ከሱም ጋር ሙግት አሰፈላጊም ስላለሆነ ያሉበትን ለሱ ትቼ መልካም እረፍት እያልኩ እንደባለቤታቸው እኛ ሰፈር መጥተው እንዳይፈወሱ እኛ ሁሉን አድናለሁ የሚሉትን እያንጉዋለለን ቃሊቲ ልከዋቸል ምናልባት እሳቸው ጋር ተደብቀው እየታከሙ ይሆን ወይስ ኦፕራሲዮን ማድረጋቸውም ሹክታ ስላለ ለመሆኑ አጃቢዎቻቸው ሁሉ ደህና ናቸው ወይስ ባምላክ የተገደበውን ለማራዘም ከመሃላቸው ጭዳ የሆነ እንዳለ ለማረጋገጥ ፈልጌ ነው ምክንያቱም አንባ ገነኖች የማይበጥሱት ቅጠል
የማይሞክሩት የለምና ነው
የአንባገነኖች እድሜ የሳሙና አርፋ ነው
No comments:
Post a Comment