Translate

Thursday, July 26, 2012

ወይ ጣጣ፤ ፍትህ ጋዜጣ ነገም ለንባብ አትበቃም!

የጋዜጣዋ አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ በፌስ ቡክ ገፁ ላይ እንደገለፀው ፍትህ ጋዜጣ ዛሬ ስራዋን አጠናቃ ማተሚያ ቤት ብትገባም የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ሃላፊዎች “ፍትህን እንዳናትም ከፍትህ ሚኒስቴር በቃል ታዘናል” በሚል ለማተም እንደሚቸገሩ ገልፀውላቸዋል።
ተሜ እንደነገረን ከሆነ ፍትህ ሚኒስቴር ሄደው ነገሩን ለማጣራት ባደረጉት ሙከራ ሃላፊው ያለፈው ሳምንት እገዳ በእርሰቸው ቢሮ መታገዱን ገልፀው ለዚህኛው ሳምነት ግን ምንም አይነት እገዳ እንዳላዘዙ እና የሚያውቁት ነገር እንደሌለ “ዘና” ብለው ነግረዋቸዋል።
ዘና ለማለት ያልታደሉት የፍትህ ጋዜጣ ባልደረቦችም ይህንኑ ምላሽ ይዘው ወደ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ቢሮጡም የማተሚያ ቤቱ ሃላፊዎች የስራ ሰዓታቸውን ጨርሰው ከቢሮ ወጥተዋል።
ዋና አዘጋጁ ተመስገን በዚህ የተነሳ ጋዜጣዋ ዛሬን ሳትታተም እንዳደረች ነገ ደግሞ የአቅማቸውን በሙሉ ጥረት እንደሚያደርጉ ነግሮናል።
እኔ የምለው ይሄ አዲስ እየመጣ ያለው መንግስት “ፍትህ” የሚባል ነገር እንዳይኖር ቆርጦ ተነስቷል ማለት ነው!? እስቲ ነገ ደግሞ የሚሆነውን አብረን እናያለን!
ABE TOKCHAW

No comments:

Post a Comment