ከጁላይ 25 እስከ ጁላይ 28 ቀን በጣሊያን ሮም ከተማ ላይ በሚካሄደው የአውሮፓ የባህልና ስፖርት ፌስቲቫል ላይ በመገኘት ውድድሩን ለመዘገብና እንዲሁም የተለያዩ የገቢ ማስገኛ ዝግጅቶችን ለማድረግ በቦታው ላይ የተገኘው የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) የጋዜጠኞችና ድጋፍ አስተባባሪ ቡድን ውድድሩ በሚካሄድበት አካባቢ ድንኳን እንደማይሰጠው በውድድሩ አዘጋጆች ተገልጾላቸዋል::
የውድድሩ አዘጋጆች አስቀድመው ለኢሳት ማኔጅመንት ኢሳት በቦታው በመገኘት የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶችን እንዲያደርግ ፈቃደኝነታቸውን ከገለጹ በዃላ ነበር የኢሳት ቡድን ወደቦታው የተጓዘው:: ዝግጅቱ በሚከፈትበት ዕለት ግን ቃላቸውን በማጠፍ የኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በአስር ሺዎች ወጪ የተደረገበትን የአስቴር አወቀ የዘፈን ዝግጅት ይሻማብናል የሚል ምክንያት አቅርበዋል :: አስቀድመው ፈቃደኝነታቸውን የገለፁበትና በተለያዩ ሚዲያዎች ሲተዋወቅ ተቃውሟቸውን ያላሰሙት አዘጋጅኮሚቴዎች የኢትዮጵያ ህዝብ አይንና ጆሮ የሆነውንና በኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን የቆመውን ኢሳትን ለመጉዳት ባደረጉትን አሳዛኝና አሳፋሪ ተግባር ያዘን በሆናችንን መላው ኢትዮጵያዊ በተለይም በውድድሩ ቦታ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዲያውቁልን እንፈልጋለን::
በመጨረሻም በሮም የሚገኙት የኢሳት ብድን አባላት ባደረጉት ጥረት በአሁኑ ሰኣት ወድድሩ በሚካሄድበት ቦታ አቅራቢያ የራሳቸውን ድንኳን በመትከል የተለያዪ ቁሳቁሶችን በመሸጥ ላይ ይገኛሉ :: እንዲሁም የፊታችን ቅዳሜ የተዘጋጀው ልዩ የኢሳት መዝናኛ ፕሮግራም አስቀድሞ በተወሰነው ጊዜና ቦታ እንደሚካሄድ እየገለፅን ፤ በዝግጅቱ ላይ ተሳታፊ የሆናችሁ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ኢሳት ባለበት ቦታ በመገኘት ድጋፋችሁን እንድትገልፁ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ሙሉ በሙሉ በወያኔ ቁጥጥር ስር የዋለው የውድድር አዘጋጁ ክፍል በመውደቅ ላይ ያለው የመለስ ዜናዊ መንግስት ዋነኛ ደጋፊ እና ባለሟል ከሆኑት አስቴር አወቀ እና ሼህ አላሙዲን ጋር ቅዳሜ ጁላይ 28 ቀን ባዘጋጁት የዘፈን ዝግጅት ላይ ባለመገኘት ተቃውሟችሁን እንድታሳዪም እንጠይቃለን ::
የአውሮፓ ኢሳት ደጋፊዎች ግብረ ሃይል
http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/3648
No comments:
Post a Comment