Translate

Monday, July 23, 2012

መድረክ ወደ ግንባር የተሸጋገረው ከአቶ መለስ ህመም ጋር ተያይዞ አለመሆኑን ዋና ጸሀፊው ገለጡ

ሐምሌ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፣ የኦሮሞ ህዝቦች ኮንግረስ /ኦህኮ / ፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ኦፌዴን / ፣ አረና ትግራይ ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት ፣ የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ /ኢሶዴፓ/ ናቸው ባለፈው ቅዳሜ በጋራ ግንባር የመሰረቱት።
አቶ ጥላሁን እንዳሻው ሊቀመንበርነት ፥ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳን ምክትል ሊቀመንበርና የፋይናንስ ጉዳይ ሀላፊ ፣ ዶክተር መረራ ጉዲናን ምክትል ሊቀመንበርና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ፣ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፣ አቶ ገብሩ አስራትን ምክትል ሊቀመንበርና የውጭ ጉዳይ ኃላፊ እንዲሁም ዶክተር ሞጋ ፍሪሳን ዋና ፀኃፊ አድርጎ ግንባሩ የመረጠ ሲሆን፣ የስልጣን ሽግግሩም በየስድስት ወሩ በተራ የሚደረግ ነው።
ዶ/ር ሞጋ ፍሪሳ ለኢሳት እንደተናገሩት መድረክ በዚህ ሰአት ወደ ግንባር ለመሸጋገር የፈለገበት ምክንያት ከአቶ መለስ ዜናዊ ጤና ጋር የተያያዘ ሳይሆን፣ ወቅቱ ያመጣው ነው::

No comments:

Post a Comment