(እርእሱ ቁርጥ የኢቲቪ ዜና ብለው ያሽሟጡኝና ወደ ቁምነገሩ ይግቡ!)
ያለፈው አርብ እትም “ለሀገር ደህንነት ስጋት የሆነ ወንጀል ነክ ዘገባ ይዛለች” በሚል እንዳትሰራጭ በፍትህ ሚኒስቴር የታገደችው ፍትህ ጋዜጣ ለሚቀጥለው አርብ እትም እየተዘጋጀች እንደሆነ ዋና አዘጋጁ ተመስገን ደሳለኝ ለሸገር ሬድዮ ገለፀ።
መታገዷን አስመልክቶ ሸገር ሬድዮ ያነጋገራቸው የፍትህ ሚኒስቴር ተወካይ (ስማቸውን ረሳሁት) ጋዜጣዋ መታገዷ አግባብ መሆኑን ጠቅሰው፤ “ጋዜጣዋ ወንጀል የሆነ ዘገባ ማካተቷን መረጃ ስለደረሰን በፕሬስ ህጉ አንቀፅ አስራ አምስት (መሰለኝ አንቀፅ እና ገንዘብ አይያዝልኝም) ብቻ በአንዱ አንቀፅ መሰረት እንደታገደች ተናግረዋል።
የፍትህ ሚኒስትሩ ሰው እንዳሉት ከሆነ አቃቢ ህግ ይህንን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ማመልከቱን እና እገዳው አግባብ መሆን አለመሆኑን ፍርድ ቤቱ በ 48 ሰዓት ውስጥ ሲያሳውቀን፤ ተቀባይነት ካገኘን በአስራ አምስት ቀን ውስጥ አቃቤ ህግ በጋዜጣዋ ላይ ክስ ይመሰርታል” ሲሉ ተናግረዋል።
የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ በበኩሉ “ምንም በወንጀል የሚያስጠቅ ዘገባ ጋዜጣዋ እንዳልሰራች ገልፆ ፍትህ ሚኒስቴር ባደረገብን ድንገተኛ እገዳ ለከፍተኛ ኪሳራ ተዳርገናል” በማለት ለሸገር ሲናገር ሰምቼዋለሁ።
ፍትህ ጋዜጣ የመከሰሰ አደጋ ተጋርጦባትም ለሚቀጥለው አርብ እትም እየተዘጋጀች መሆኑን ተመስገን አያይዞ ተናግሯል!
ዜናው በዚህ አበቃ ቸር ያሰማን!
No comments:
Post a Comment