Translate

Monday, July 9, 2012

ቃሉ ነው ? ድርጊቱ አሸባሪ


   ከተስፋዬ ዘነበ    ኖርዌይ በርገን                                                                          10.06.2012                                            
ሃያ አንድ የመከራና የሰቀቀን አመታት ለኛ ለንጹሃን ዜጎች እንዲሁም ለገዢዎቻችን እኛ የነሱ የግፍ
ቀንበር ተሸካሚ ሆነን በሃገራችን በነጻነት የመኖር መብት አጥተን ሲያሻቸው ሲገሉን፣ ሲያስሩን፣
ሲያሳድዱን እንዲሁም ሲያስርቡን ፣በድህነት ሲያማቅቁን ሃብት ንብረታችንን ስንነጠቅ የበይ ተመልካች
ስንሆን እንሆ ሃያ አንድ አመት ሆነን ፡፡ገዢዎቻችንም እንደ ሰለጠነ ሰው ማሰብ ተስኗቸው ቀን ከሌት
ለክፋትና አገር ለማፍረስ አላማ ሲታትሩ ፣ንጹሃን ዜጎችን ለመወንጀል የክስ ሰነድ ሲያዘጋጁ ፣ በዘርና
በሃይማኖት ሊበታትኑን እቅድ ሲያወጡ ፣የሶስት ሺ ዘመን ታሪክ ያላትን ታላቅ አገር ለማፍረስ ሌት
ከቀን ሲደክሙ ድፍን ሃያ አንድ አመት ሆነን፡፡
ከሁለት አስርተ አመታት በፊት ዘረኛው የወያኔ ቡድን ስልጣን ሲይዝ በአፍሪካ ዴሞክራሲያዊት ሃገር
ቦትስዋና ብቻ ነበረች፡፡ አሁን ከግማሽ በላይ የአፍሪካ አገሮች ከኛ በተሻለ የዴሞክራሲያዊ ስርዓትን
ጭራውን ይዘውታል ፡ በተለይ የሰሜን አፍሪካው አብዮት ለብዙ የአፍሪካ መሪዎች ትምህርት የሰጠ
ይመስል ቱኒዝያ ፣ ግብጽ፣ ሊቢያ የሆነውን አይተው የተለያዩ መንግስታት በፍቃደኝነት ተሃድሶ
ጀምረዋል ፡ በሚገርም መልኩ ይህ የለውጥ ማህበል ያልነካቸው የአፍሪካ ቀንድ አምባገነን መንግስታት
ናቸው፡፡

ከላይ እንደተጠቀሰው አፍሪካ ውስጥ የዴሞክራሲ ስርዓት እያራመዱ ያሉት ሃገራት በጠቅላላ ማለት
ይቻላል በምንም መለኪያ ከኢትዮጵያ የተሻሉ አይደሉም ፡፡ በስልጣኔም ቢሆን ቀደምት ታሪክ ያላት
ሃገር ናት ፡ እንዲያውም ኢትዮጵያ ብዙዎቹን የአፍሪካ አገራት ለነፃነት ያበቃች    ናት፡፡ በጋና እና
በታንዛኒያ በሌሎችም የአፍሪካ ሃገራት ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት ከተቻለ እኛ ጋር የማይሆንበት
ምክኒያት  ምንድነው  ማን ጋር ነው ችግሩ  እኛ እራሳችንን የምናወዳድረው ከማን ጋር ነው፡ አሁን
በህይወት ኖረው በስኬት ካሉት ወይስ ሞተው ከተቀበሩ.....
መቼም ነገርን ነገር ያንሳዋል ነው የሚባለው.......ይገርመኛል ዘረኛው የወያኔ ቡድን (ወያኔን እንደ ሃገር
እንደሚመራ የመንግስት    ቡድን አስቤው አላውቅም    አይዋጥልኝም)  እራሱን የሚያነፃፅረው
ከሚፈልገው ጉዳይ ጋር በመንተራስ ነው ለምሳሌ ህግ እና ደንብን በተመለከተ ኮረጅኩ የሚለው
በአብዛኛው ከአሜሪካ ፣እንግሊዝ ፣ህንድ ወ.ዘ.ተ...ነው ፡፡ የሚገርመው የሃገር እድገትንና ሌሎችን
ተዛማች ጉዳዮችን  የሚያወዳድረው ደግሞ ሞቶ ከተቀበረው ካለፈው ስርዓት(ከደርግ) ጋር ነው  በምን
መመዘኛ ሃያ አንድ አመት በፊት ከአገልግሎት ውጪ የሆነ ስርዓት አሁን በዚህ ዘመን ካለ ስርዓት ጋር
እንደሚነፃጸ
i
ር ይገርማል ፡፡
ለነገሩ ህዝብ እንደ ህዝብ ያ ከዚህ ይሻላል ሊል ይችላል ያውም ለአጭር ግዜ ዘመን ከረዘመ ሁሉም
ያልፋል ይለወጣል እስኪ የኔን እይታ ላካፍላችሁ፡፡ለምሳሌ የደርግ ስርዓት እጅግ ገዳይ እና ምህረት
የለሽ አምባገነን ቢሆንም በአገር አንድነት ላይ ያለው አቋም ፍፁም ኢትዮጵያዊ ነው ህዝቡም ለዛች
አገር ያለው ብሔራዊ ስሜት እንዳሁኑ ሳይራረፍ ተጠብቆ እንዲኖር አድርጎአል፡፡ በጨፍጫፊነቱ ወደር
ባይኖረውም የአገራችንን ለም መሬት ለህንድና እና ለፓኪስታን አልቸበቸበም በአንድ ሰንደቅ ዓላም ስር
አንድ አገር በሚል ስሜት አቆይቶናል ፡፡በሌላ በኩል ደርግ ድህነታችንን አምኖ እንደ ድህነታችን
የምንኖርበትን መሰረታዊ ፍጆታ በተመጣጣኝ ዋጋ የምናገኝበት የህብረት ሱቅ በመክፈት ደሃው
እንደድህነቱ ሳይራብና ሳይቸገር የሚያገኝበትን አቅም በፈቀደ አዘጋጅቷል ፡፡በተጨማሪ በከተማ
ለሚኖሩ የመንግስት ሰራተኞች በግል የመኖሪያ ቤት መገንባት ለማይችሉ ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ገቢ
ያላቸውን እንደ አቅማቸው በማህበር በማደራጀት የቁጠባ ሂሳብ በማስከፈት የቤት ባለቤት አርጓቸዋል
ለምሳሌ በአዲስ አበባ ሳሪስ አዲሱ ሰፈር ፣ገርጂ ፣አየር ጤና አለም ባንክ ፣ላፍቶ የመሳሰሉት ሰፈሮች
የተሰሩት በግሉ መኖሪያ ቤት መገንባት ለማይችል የህብረተሰብ ክፍል ነው ፡፡ በአጠቃላይ ደርግድህነታችንን አምኖ ሲቀበል በአንጻሩ ዘረኛው የወያኔ ቡድን ግን አገር ለማፍረስ የሰላ በመሆኑ ገና
በእድሜው መጀመሪያ ለዘመናት በአባቶቻችን ደምና አጥንት ተከብራ የኖረች አገርን ማስገንጠሉ ሳያንስ
በፍቃዱ የባህር በር አሳጣት አንድ በሉ፡ በመቀጠልም ለሱዳን መንግስት እጅ መንሻ ዳር ድንበሯን
ቆርሶ ለም መሬታችንን አሳልፎ ሰጠ ሁለት አትሉም፣ ብዙዎች መሬት ላራሹ ብለው ውድ
ህይወታቸውን የሰዉለትን የአርሶ አደሩን መሬት በሶስት ትውልድ ለሚለካ ዘመን ደሃውን ገበሬ
እያፈናቀለ ለባህዳን ቸበቸበው፡፡ በአንድነትና በመተሳሰብ ተከባብሮ በአንዲት ኢትዮጵያ ጥላ ስር ይኖር
የነበረውን ህዝብ በዘርና በጎጥ ከፋፍለው ሰንደቁን አብዝተው ብሔራዊ ስሜቱን ነጠቁት፡፡ ለዚህ ነው
የበደላችን ፅዋ ከአፍ እስከ ገደፉ ሞልቶ እያየን በቃን ብለን በአንድነት ለለውጥና ለትግል መነሳት
ያልቻልነው፡፡ በተጨማሪ በመልካም አስተዳደር እጦት ፣በሙስናና በተለያዩ የስርዓቱ ችግሮች
ጫንቃችን ላይ ያረፈውን  ድህነታችንን እንኳን ቀምተውናል ፡፡ለዚህም ነው  ጉርሻ በሚሸጥበትና ዜጎች
በቆሻሻ ገንዳ ላይ እየተመገቡ፣ በየአቅጣጫው የከተማይቱ ጎዳናዎች ላይ ድንጋይ ተንተርሰው ላስቲክ
ለብሰው የቀን ሀሩር የለሊት ቁር እየተፈራረቀባቸው ባሉበት ሁኔታ ይህ ዘረኛ ቡድን ግን ድህነታችንን
ቀምቶን ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ በሁለት አሃዝ አደግን ተመነደግን  ምናምን ምናምን የሚለን ፡፡
ብዙ አልኩ መሰለኝ ዛሬ ወደተነሳሁበት ርእሰ ጉዳይ ልመለስ ከላይ እንደጠቀስኩት በአፍሪካ ውስጥ
የነፃነትን ጎሕ የቀደድን ዜጎች አሁን ከኋላ ሆነን ዴሞክራሲይ ፣መልካም አስተዳደር ፣ፍትሕ ፣እኩልነት
፣የሰው ልጅ ሰው በመሆኑ ሊያገኝ   የሚገባው ሰዋዊ ነፃነት እንደሰማይ እርቆብን ይህው በባርነት
ስንማቅቅ ሃያ አንድ አመት ሆነን ፡፡
ታዲያ እኛ የፍትህ ርሃብትኞች ገዢዎቻችን በምድረ ኢትዮጵያ ያለውን ሰማንያ ሚሊዮን ሕዝብን
አፍነው እነሱ ከሚሉትና ከሚደሰኩሩት ውጭ እንዳይሰማ አማራጭ ሚዲያዎችን ዘግተው የመናገርና
የመቃወም መብቱን ነፍገው ሲያሻቸው ሲሰድቡት፣ ሲሳለቁበት ኖረዋል፡፡የዘረኛው ቡድን ፊትአውራሪ
መለስ ዜናዊ በዛ አምስት መቶ ምናምን ካድሬዎች በተሰበሰቡበት ፓርላማ ተብዬ ያሻውን ተሳድቦ፣
የፈለገውን ዘልፎና አስፈራርቶ በመጨረሻም በባንዶች ጭብጨባ ታጅቦ እራሱ ጀምሮ እራሱ
ይጨርሳል፡አንድም እውነት ስለማያወራ አንድ ሰዓት ቢደስኩር የአምስት ደቂቃ ጭብጥ የለውም ፡፡
የሚገርመው በአገር ቤት የተለመደው ድንፋታ አግድሞሽ እያዩ መዛለፍ ያሁሉ ጉራና ማቅራራት
በምድረ አሜሪካን በተዘጋጀው    የG8 ስብሰባ ላይ መና ሲሆን ሳየው የተሰማኝን ስሜት በቃላት
መግለጽ ይቸግረኛል፡፡
በፕሬዝዳንት ኦባማ ጋባዥነት የወያኔው ፊትአውራሪ መለስ በአገራቸው የዴሞክራሲ ስርዓት ካሰፈኑና
መልካም አስተዳደር ከመሰረቱ ከ3 የአፍሪካ አገራት መሪዎች ጋር በምግብ ዋስትና ላይ በሚያተኩረው
የG8ቱ ሲምፖዚየም ላይ ተገኝ ነበር፡፡
እንግዲህ አምባገነኑ መለስ በምን መስፈርት ለዚህ ሲምፖዚየም እንደታጨ ባይታወቅም ብቻ አለቆቹ
ጋብዘውት ተሰይሟል፡፡ ይህ ስብሰባ በአለም ላይ ከፍተኛ ግምት ስለሚሰጠው የበለጸጉ አገራትን
ወክለው የተገኙ ባለስልጣናትና የአገር መሪዎች ታድመውበታል እንዲሁም ታላላቅ የሚዲያ ተቋማት
በስፍራው ተገኝተዋል፡፡
ሲንፖዝየሙ በተያዘለት ፕሮግራም መሰረት ሊጀመር የአገር መሪዎችና  ተጋባዥ እንግዶች ወደ ሬገን
አዳራሽ ሲያመሩ ወትሮም በዚህ አይነቱ ዝግጅት ላይ የኛው ገዳይና አምባገነኑ መለስ መጋበዝ
ያልተዋጠላቸውና ግብዣው እንዲሰረዝ በጽናት ሲታገሉ የነበሩ ውድ ወገኖች ሀይላቸውን
አስተባብረው ዘርና ሃይማኖት ሳይለያቸው በተቃውሞ ሰልፍ ድምፅ ለተነፈገው ምስኪን የኢትዮጵያ
ህዝብ ድምፅ ሊሆኑ መንገን ሞልተውት ነበር፡፡እንግዲህ ደንባራው መለስ የውጪውን ትእይንተ ህዝብ
አልፎ ነው እየተወገዘና ማንነቱ ለአለም ህዝብ እየተገለጸ ወደ አዳራሹ የገባው  መግባት አይበለው፡፡
በፕሬዘዳንት ኦባማ ሲንፖዝየሙ በይፋ ከተከፈተ በኋላ በስፍራው የተገኙ የተለያዩ አገር ባለስልጣናት
በቅደም ተከተል በእለቱ እርእሰ ጉዳዩ ማለትም በአለማችን የምግብ ዋስትና ላይ የየበኩላቸውን ንግግር
አድርገው ጨረሱ፡፡ ማነህ ባለ ሳምንት እንዲሉ አፍሪካን ወክለው የተገኙት ንግግር ለማድረግ
ቦታቸውን ያዙ የኛው ጉድ መለስም በእሱ የግብርና ፖሊሲ ህዝቡ በኑሮው ውድነት እንደሚሰቃይ፣
ትርፍራፊ ጉርሻ የሚሸጥባት፣ከኢትዮጵያዊ ስነብግባር ውጪ አይን አውጥቶ መለመን ስራ የሆነበት
ህዝብ በቀን 3 ግዜ አይደለም ለአንድ ጊዜ እንኳን መመገብ እንደከበደው ሳይሆን ኢትዮጵያ የምትባልምድር በሰብል ምርት እንደተጥለቀለቀች ገበሬው ጠግቦ በቁንጣን እንደሚሰቃይ ሌላም ሌላም
የተለመደና አሰልቺ ዲስኩሩን ለመጀመር መነጋገሪያውን ይዞ የመጀመርሪያውን አረፍተ ነገረ እንደ
ጀመረ ጢም ካለው አዳራሽ አንድ ፍፁም የማይጠበቅ ሀያል ድምፅ ተሰማ
             
“መለስ ዜናዊ አምባገነን ነው” የሚለው የጀግናው ጋዜጠኛ አበበ ገላው ድምፅ አስተጋባ በዛች ቅፅበት
የሚደፍረኝ የለም ብሎ ሃያ አንድ አመት ሙሉ በጸያፍ ቃላት የታጀቡ ዲስኩሮችን ያነበንብ የነበረው
ገዳዩ መለስ የደነገጠው ድንጋጤና የሆነውን መቼም በታሪኩ አጋጥሞት የሚያውቅ አይመስለኝም ፡፡ሃያ
አንድ አመት ሙሉ የንፁሃን ዜጎችን ደም ያፈሰሰ በማን አለብኝነት የአገር ሀብትና ንብረትን
የመዘበረውና ለሰው ልጅ ቅንጣት ክብር የሌለው የወያኔው መሪ በአለም ፊት ሲዋሽና እንደ ንጹህ
ለመታየት ሲሞክር አይቶ ማለፍ ያልቻለው ጋዜጠኛ አበበ ገላው የተከናነበውን የማስመሰል ቡሉኮ ቀዶ
በአለቆቹ ፊት እርቃኑን አስቀረው ፡፡አምባገነንነቱን በመግለፅ ብቻ አላበቃም የፖለቲካ እስረኞች
ጓደኞቹንም በማስታወስ እንጂ “Free Esiknder Nega and political prisoners! You are dictator!
Your policy is crime ability against humanity! You are talking about food with out
freedom we need freedom more than food !  We need freedom ! freedom freedom !
Meles  Zenawi is a dictator !  Meles  Zenawi is a dictator ! free Esiknder  Nega and
political prisoners !  ያለፍትህ በወህኒ ለሚማቅቁት ለሞያ አጋሮቹና ታጋዮች ሁሉ ጮኸ ጀግናው
ጋዜጠኛ አበበ ገላው፡፡
ከወራት በፊት በመለስ ባሸባሪነት የተከሰሰው ጋዜጠኛ አበበ ገላው ባገኘው አጋጣሚ ተጠቅሞ የሰማኒያ
ሚሊዮን ህዝብን ብሶት ተንፍሶለታል የአንባገነኑንም አንገት አስደፍቷል ቃሉ ነው ድርጊቱ አሽባሪነት ፡፡
ይህ    ወገንን ከዳር እስከ ዳር ያስደሰተና ያኮራ ተውኔት በማግስቱ በካምፕ ዴቪድ ለተጠራው
የተቃውሞ ሰልፍ ቤንዚን ሆኖት የወያኔውን መሪ መከራ አበዛበት ፡፡የተቀናጀና በኢትዮጵያዊነት ላይ
የተመሰረተ ግፍ በቃን ፣እስር በቃን ፣እንግልት በቃን ፣መፈናቀልና መጋዝ በቃን፣ መሬታችንን
አትቸብችቡ በእምነታችን ጣልቃ አትግቡ በቃን በቃችሁን የሚለው ሰፊ አገራዊ ፋይዳ ያለው
የተቃውሞ ሰልፍ የወያኔ መሪዎችንና ጭፍሮቻቸውን አንገት ያስደፋ ነበር፡፡
በአጠቃላይ አቤ ያሳየው ታላቅ ገድል በህዝቡ ዘንድ የፈጠረው መነቃቃት ደቡብ አፍሪካ ተሻግሮ
ወያኔን መግቢያ እንዳሳጣ አይተናል ፡፡ይህ የትግል መንፈስ ውጤት እንዲያመጣ በመላው አለም
የምንገኝ ኢትዮጵያውያን በዘርና በሃይማኖት ሳንከፋፈል አገራችንንና ሕዝባችንን እንታደግ ፡፡አቤ
በፈጠረው መነቃቃት ተጠቅመን ይህን ስሩና መዋቅሩ የበሰበሰን ስርዓት ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ
ከላያችን እናስወግድ፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ ! ሞት ለወያኔ !
ለአስተያየቶ  ftih_lewegen@yahoo.com

No comments:

Post a Comment